Skip to content
  Wednesday 10 June 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የትግራይ ህዝብ የሰላም፣የህልውናው እና ደህንነቱ ዘብ እራሱ ህዝቡ ነው -ዶ/ር አብርሃም በላይ

    May 29, 20210

    በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው አሸባሪ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እርምጃ ተወሰደበት

    September 4, 20210

    Ethiopian Envoy Briefs Sudan Based Media On GERD

    July 4, 20210

    በአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በመሞከርና በምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት የተከሰሱ ተቀጡ

    June 21, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1875
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ልጆቻቸው መቀለ ዩኒቨርስቲ የቀሩባቸው ወላጆች የተመድ ፊት እያነቡ ነው “ልጆቻችንን አስለቅቁልን”

    July 23, 20210

    መከላከያ በኦሮሚያና አማራ ክልል የማጽዳት ስራ እንደቀረው አስታወቀ፤ አማራ ክልል መዋቅሩን እያጠራ ነው፤

    September 1, 20230

    “ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ ወቅታዊና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ችግሮች ለመፍታት አስቸጋሪ ነው”

    April 17, 20210

    “በተለመደው አሰራር ማስቀጠል የምንችለው ድህነትን ብቻ ነው” ሽመልስ አብዲሳ

    June 3, 20220

    “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች?”

    March 9, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1500
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  ENTERTAINMENT  ሲጥል – ያልተሰሰተ መጽሐፍ
(ቃልኪዳን ኃይሉ)
ENTERTAINMENT

ሲጥል – ያልተሰሰተ መጽሐፍ
(ቃልኪዳን ኃይሉ)

Ethioreview newsEthioreview news—September 2, 20240
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail



– ሲጥል ላይ ያለውን ሁሉ ጣለ

ሲጥልን አነበብኩት። ተገርሜም ተደንቄም አድንቄም አልበቃኝ። ደራሲው አልሰሰተም። ከጎረምሳነቴ ጀምሮ የማውቀው ደራሲ ነው። በግልም አውቀዋለሁ። እንደ ሰው። ንግግሩ ብዙ ፍሬ እንዲሁም ጨዋታና ቁምነገር አዘል ነው። ብዕሩን ከሞላ ጎደል ሁሉንም አንብቤያለሁ። ከምንም በላይ ‘በዐሉ ግርማ ሕይወቱና ስራዎቹ” ግርም ድንቅ ብልበትም ከ”ጥቁር ሰማይ ስር” ስስቴ ነው። ይህን ስል ከጣት ጣት ይበልጣል ለማለት ነው። ግን ሌላ የሚበልጥ ጣት አገኘሁ። ሲጥል!

በግል የማውቀውን እንዳለጌታን አየሁት። እንዳለጌታ ስስታም አይደለም። ለታናናሾቹ ትሁት ነው። ወዳጅ ነው። ሳይሰስት ይሰጣል። ያማክራል ይመክራል። እውነት ለመናገር በአንዳንድ የእሱ ዘመነኞች ቅሬታዎች አሉኝ። እሱ ከዘመነኞቹ ከሚለዩት አንዱ ይህ ነገሩ ነው። የ”ያ ትውልድ” ጥላ በደንብ ያረበባቸው ትምክህተኞች ይበዙበታል። በረኝነት። ማለፉ ላይቀር መተሻሸት። ማሸት። ደባሪ ሙድ! “አናስገባም ሰርገኛ እደጅ ይተኛ” ነገር። እንዳለጌታ ጋ ፒስ ነው። ግን እውቀቱን ማካፈሉ አይደለም ለጋስነቱ። ካለው ያለውን ሁሉ ይሰጣል።  መጽሐፍ ይለግሳል። ለተማሪዎች ገንዘብ፣ ቀለብ ይሰፍራል። ነድያንን ያበላል። የሰርጉእለትም ቢሆን።

ሲጥል ላይ ያለውን ሁሉ ሲጥል አየሁት። እንደ ደራሲ ለነገ የሚባል ሃሳብ አለ። የዛሬው ይበቃል። ደግሞ ለነገዬ ይባላል። ደንብ ነው። ደራሲ ሰው አይደለ? ለደራሲም ነገ አለው።

ሲጥል ላይ ለነገ አልነበረም። ለነገ ሳይል ሳይሰስት ነበር ያስነበበን። ልክ እንደ ባለጠገ ቤት ማዕድ። ዞረው ዞረው የማይጨርሱት የታሪክ ብፌ ያቋደሰን። ደራሲው ፈጣሪን ካልፈራ ሦስት ደንበኛ ልብወለድ ሊጽፍባቸው የሚችሉ ታሪኮችን ነው አንድ ያደረጋቸው። 
የቤርሳቤህ እና የምንተስኖት ታሪክ፣ የኢዮኤልና የመሪጌታ ሐብቴ ታሪክ እና የአቶ ስዩምና የተቀሩት ሰዎች ታሪክ ብቻ ብቻውን መጽሐፍ መሆን ይችላል።

እነዚህ ሶስት ትልልቅ ልብወለድ የሚወጣቸውን ግብብዳ ገጸ ባህሪያትና ታሪኮች  አንድ ሲያደርጋቸው ግን አንረበሽም። በምን ተገናኙ አንልም። ምን እግር ጣላቸው ብሎ መጠየቅ መብት ቢሆንም። እግር ይጥላል። ሲገናኙ ግን ግጥም ይላሉ። ጸባቸውም ፍቅራቸውም ምክንያታዊ ነው። ይህን ነው ቴክኒክ የሚሉት።

የስነ ጥበብ ሰዎች አንድን የሥነጥበብ ውጤት በሁለት አይን ያዩታል። ቅርጽና ይዘት (form and content)። ምንም የኪነጥበብ ስራ ከዚህ አያልፍም ይላሉ ሊቃውንቱ። ይዘቱና አቀራረቡ።

አንዳንዶች ቅርጽን እንደ ጆግ፤ ይዘትን እንደ ውሃ ያዩታል። እናም ውሃው እንጂ ጆጉ ምንድነው ይላሉ። አ አ….ግን ቅርጽ በጆግ አይመሰልም። ብዙ ቁምነገር፤ ብዙ ሃሳብ ቢታጨቅ ያለ ቅርጽ ያለ ማቅረቢያው ውሃውስ በምን ሊያዝ ሃሳብስ በምን ሊቀነበብ?



ሲጥል ውስጥ አንድ ነው የሚባል አጻጻፍ የለም። አጻጻፉም እንዲህ ነው የሚባል አይደለም። በአንድም በሦስተኛውም መደብም ይተረካል። ዛሬም፣ ነገም፣ ትናንትም አለ።

“…ትናንትናን ያየ ስለ ነገ ያውቃል
ታሪክ ያስተዋለ ከጠቢብ ይልቃል…” ትላለች በዛወርቅ አስፋው ።  ” if you want to hear deeply melacholic version of Tezeta listen to Bezawerke’s…”  የተባለላት ነች። ያውም ቢቢሲ ዶክመንተሪ ላይ። 

እና ሲጥል ላይ በእውን አለም ላይ የምናውቃቸው ሰዎች በገጸ ባህሪያት ይጠቀሳሉ። ራሱ ደራሲውም “የትምጌታ” በሚል ስም ተጠቅሷል (ይቺን ስታይል “ልጅ ማይክ፣ ሮፍናን ድሮፕ ኢት አጌይን፣ ቴዲ አፍሮ ማሚላ ኪችን ምናምን ምናምን…” ሲሉ ነው የማውቀው። ኦው ደራሲውም ፈታ እያለ ነው። እንዳለጌታም ስሙን ጠርቷል ደራሲ በሚለው ቦታ አላልኩህም ደግሞ። በፈጠራቸው ገጸባህሪያት ነው እንጂ። “የትም ጌታ” የሚሉት ጋሽ ኃይለመለኮት ናቸው። ሲባል ሰምቻለሁ።  አዳም ረታም ስሙ ተነስቷል። ዶክተር በድሉ፣ ዶክተር በላይ አበጋዝ እና ዶክተር ፈቃደ አግዋር (እኒህ የልብ ሐኪምች ናቸው። በእውኑ ዓለም ያሉ የምናውቃቸው፤ የመጀመሪው የስነ ጽሁፍ ሰው ናቸው።) 

ደራሲው የእነዚህን ሊቃውንት ስም በልብወለዱ ጠቅሷል። እና ይጠራአ ምን ይጠበስ? አይባልም። አባዬ ይጠራአ ምናምን ብለህ እንዳታቃልል። ምን ሆነሃል? ትላልቅ ዘፋኝና ደራሲ ስምህን በስራው ላይ ሲጠራህ በትንሹ ሰባና መቶ አመት ስምህ ከአየሩና ከሼልፉ ላይ አይጠፋም። ማነው ምንድነው ይልሃል? ትውልዱ። አትናቀው  የስምን ነገር። ጥቅሙን ዶክተር አብይን ጠይቃቸው። ቴዲ አፍሮ ለምሳሌ “ጎንደር ጎንደር ” ባለ አንደበቱ “አብይ አብይ አሻገርን ንጉስ የበላይ ነውና” ቢል… ቢል? አባዬ የጫካ ሲሶ የእሱ ነበር። ከጫካ ፕሮጀክት በላይ የልጁ ዘፈን ዘመን ይሻገራላ።

“ነይ እንሳፈር ነይ እንሳፈር
የምድር ኃላፊ ነው በሰማይ ባቡር
እድሜ ለተፈሪ አሳየን ታምር
ከተወለድን ቆየን ከቆየን ዘገየን
እድሜ ለተፈሪ አውሮፕላን አየን” አሁን ይሄ ስንኝ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ስም ቀድሞ ተፈሪ መሆኑ። አውሮፕላን ለኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ማመጣታቸው ከሚነግርህ በላይ አየር መንጉዱ ላይ በእግር በፈረስ ብትለፋ የቱጋ ነው የቀኃስ ታሪክ አይደለም ፎቶ የምታገኘው? እና ዘፈን ድንቅ ነው ነው ምልህ።

ከፈለክ ጠቢቡ ሰለሞንንም ስለ ስም ጠይቀው። በነገራችን ላይ ዶክተር አብይና ጠቢቡ ሰለሞን ሊዮ ናቸው። ነሐሴ ወር ነው የተወለዱት። እና ጠቢቡ ሰለሞን “መልካም ስም ከብዙ ባለጠግነት ይሻላል፤ መልካም ስምም ሞገስ ከብርና ከወርቅ ይበልጣል” ይላል። እስቲ ሂሳቡን ስራው አለ አማክሮ ኗሪው ሰውዬ።

ብቻ ምን አለፋህ ይህንን አጻጻፍ ነው ሊቃውንቱ ድህረ ዘመናዊነት (Postmodern literature) የአጻጻፍ ዘዬ ‘ሚሉት። የምናውቀውን የልምድ ነውን የእውኑን አለም ማፋለስ። ልብወለድ ነው ሲሉ እውን እውን ነው ሲሉ ልብወለድ (metafiction)።

ሀገር እንዲህ ነው ሚሰራው። ቴዲ አፍሮ እንዲህ ነው ትላልቅ አድባር እየሳበ ሀገሪቱን ባንድ ሊያስር ሁለት አስርት አመታትን ያሳለፈው። ጥበብ መከራ ነው። ቀንበር ያሸክማል። እዳ አለበት ዋጋ ታስከፍላል። እንዳለ ጌታ ይህንን ጠንቅቆ ያውቃል። የበአሉን የሕይወት ታሪክ መጻፍ ብቻውን ብዙ ያስተምራል።

የኪነጥበብ ሰው በግል ሳይሆን እኛ እያሉ ማሰብ የሚያስገድድ ሙያ ነው። የኪነጥበብ ሰው ይታመናል። ሕዝብ ያምነዋል። ተደራሲ ይከተለዋል። እምነት ካለ ጥንቃቄ ግድ ነው። የጋራ የሆነ ነገር ውስጥ መሳቀቅ አለ።  እንደ እኛ ያለ ሀገር።  ሁሉ ፖለቲካ ለሆነ ማኅበረሰብ። ሁሉ ጽንፍ። ሁሉ “አዋቂ” ለሆነበት ሀገር ረባሽ ነው። ጥበብ ትጨነቃለች። ጠቢብም ይሳቀቃል።

እንዳለ ጌታን ደብረ ሰምራን በዛጎል ጀምሮ በሲጥል ያቆያት፤ አሊይን በሲጥል ያመጣት። እንደ ልቡ ለመናገር ይሆን? ወይስ ስልት? 

ደራሲው ሲኒየር ነው። እንደልቡ መናገር ፈልጎ አይደለም። ልክ በሙያው እንደሸበተ ካፒቴን ያለመንገራገጭ ነው ታሪኩ ላይ ቁጭ የሚያደርግህ። የት ጀምረህ የት እንደምታርፍ በጥንቃቄ ካልተከታተልክ እየበረርክ ይሁን እንዳረፍክ ምታውቀው ካፒቴኑ በሰላም ደረሰን ካላላ በስተቀር። በማይክ።

ሲጀመር በጥበብ እንደልብ ምናምን ብሎ ነገር የለም። ጥበብ ጥበብ ነው። እና ደራሲው ሲጠበብ ነው አሊይ ደብረሰምራ ምናምን ‘ሚለን።  ድኅረ ዘመናዊነት። በቃ ተጠቦ ነው የጻፈው። ሳይሰስት ነው የለገሰን። ሲጥልን ሲጥልህ እጅህ ሲገባ እንደው እንደ አልፎ ሂያጅ አታነበውም። ቀልብ ገዝተህ ነው ሲጥልን ምታነበው። ሲጥል!

Vua – dire tube

entertainment
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

የሶማሊያ ጉዳይ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል ይፋ አደረገ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ራስ – በኢትዮጵያዊያን በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች IA መጠቀም የሚያስችለው መተግበሪያ

August 21, 20250
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
TOP NEWS

ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups

June 7, 20260
TOP NEWS

Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV

June 7, 20260
AFRICA

Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»

June 7, 20260
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
Load more
Recent Posts
  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science” June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ June 7, 2026
  • ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ» June 7, 2026
  • ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ” June 6, 2026
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ June 5, 2026
  • Agricultural Sovereignty, Economic Transformation, and the Defiance of Extremism Ahead of the 7th National Election June 5, 2026
  • የዘለንስኪ ጥሪ፦ “ጦርነቱን ለማቆም ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ዝግጁ ነኝ” June 5, 2026
  • የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አደነቀ June 5, 2026
  • The Inverted Frontlines: How Secret Alliances and the Western Tigray Fault Line Threaten to Reignite Ethiopia June 4, 2026
  • Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia June 4, 2026
  • ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው? June 3, 2026
  • International Partner Welcomes Ethiopia’s 7th General Election, Calls for Inclusive Voting in Remaining Constituencies June 3, 2026
  • ዓለም አቀፍ አጋሮች የኢትዮጵያን 7ኛ አጠቃላይ ምርጫ በበጎ ተቀበሉ፤ June 3, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news