ባለፈው አርብ የጸደቀው የውሳኔ ሀሳብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና አባል አገሮች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት የበለጠ እንዲተጉ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።
‘Countering disinformation and promotion and protection of human rights and fundamental freedoms’ የሚል ርዕስ ያለው ይህ የውሳኔ ሀሳብ የሀሠተኛ መረጃ ስርጭት በሰብዐዊ መብቶችና መሰረታዊ በሆኑ ነጻነቶች እንዲሁም ዘላቂ በሆኑ የልማት ግቦች (Sustainable Development Goals) ላይ እያስከተለ ያለውን አሉታዊ ሚና አጽኖት ሰጥቷል።
ሀሰተኛ መረጃ ለግጭት፣ ለመድሎ፣ ለሰብዐዊ ቀውሶች መከሰትና ለአለመረጋጋት ከፍተኛ ሚና እንዳለውም የውሳኔ ሀሳቡ እውቅና ሰጥቷል። በተጨማሪም የውሳኔ ሀሳቡ የማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በማናቸው የመገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ ጥላቻንና ግጭትን የሚቀሰቅሱ እንቅስቃሴዎችን አውግዟል።
የውሳኔ ሀሳቡ አገሮች ለሰላምና ለትብብር ጠንቅ የሆነውን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት አለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በማይጻረር መልኩ የመዋጋት ሀላፊነት እንዳለባቸውም ያሳሰበ ሲሆን የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት የፖሊሲ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።
የውሳኔ ሀሳቡ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የብዙ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ያሰመረ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ግልጽነትን በማስፈንና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን የሚያበረታቱ አሰራሮችን በመቀነስ የራሳቸውን በጎ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርቧል፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመዋጋት ረገድ ቀዳሚ ሚና እንዲጫዎቱም ሀላፊነት ሰጥቷል።
ይህ የውሳኔ ሀሳብ በፓኪስታን አርቃቂነትና በበርካታ አገሮች ድጋፍ የቀረበ ሲሆን ለወራት ውይይት ሲደረግበት ነበር።
EthiopiaCheck Updates
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
- የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?ቪኦኢ ዜና – በአዲስ መልክ እየተሳለ ያለው የዓለም የንግድ ካርታ ለግማሽ ክፍለ… Read more: የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?
- ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደርበኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ አነጋጋሪ ሰው ናቸው። በሁለት ጽንፍ ተፈርጀው… Read more: ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር
- Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises In a sudden change, Iran has reportedly once again closed off the… Read more: Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises
- Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump callTurkish President Recep Tayyip Erdogan welcomed the two-week truce with Iran, pledging… Read more: Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call


