Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

Ethioreview newsEthioreview news—April 26, 2026
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም ሆነ የተጠቀሱት አካላት ስለሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው መረጃዎች በአዎንታም ሆነ በአሉታ አልተነፈሱም። ነገሮችን በጥሞና የሚከታተሉ “ቴድሮስ ራሱ ወይም አግባብነት ያላቸው ሃቁን ለህዝብ ለምን አይናገሩም? ህዝብ ሲተራመስ ዝም የሚሉት ለምንድን ነው?” የሚል ጥያቄ አሁን ድረስ ያነሳሉ። አመጣጥኖ መስራት የሚፈልጉ ሚዲያዎችም ከዚህ አንጻር ተቸግረው ታይተዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ጉዳዩን አስመልክቶ የወንጀል ምርመራ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ አብዲሳን በሰጡት ቃለ ምልልስ የተዎድሮስ ካሳሁን ሚስት የራሷ ሚዲያ እንዳላት ጠቅሰው ከመኖሪያ ቤቱ መግለጫ መስጠት እየቻለ ዝምታን የመረጠበትን ምክንያት “ህዝብ ያውቃል” ብለዋል። ኮሚሽነሩ ይህን ያነሱት “ቴዲ መግለጫ እንዳይሰጥ ተከለከል” ለተባለው የአመክንዮ ምላሽ ሲሰጡ ነው።

ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ  ሙሊሳ “የሳይበር ጦርነት” ያሉት ኦፊሳላዊ ምንጭ የሌላቸው ዜናዎች የተጀመሩት ገና ዘፈኑ ይፋ ከመደረጉ በፊት ነው። “ሚስቱ እኮ አለች ሚዲያ አላት፤ ቤቱ ሆኖ መግለጫ መስጠት አይችልም? በሞባይል ስልኩ መርጃ ማስተላለፍ አይችልም? ይችላል። መንግሥት ከለከለ የሚለው ከመነሻው መሰረተ ቢስ ነው፤ መንግስት ለምን ይከለከላል” ሲሉ ፍርድ ለሚሰጡ ሁሉ በኢክቫኽ በኩል አስታውቀዋል።

“ሰው የታገለው እንደዚህ አይነት መብቶች እንዲከበሩለት ነው። እንደ law enforcement የምንሰራው መብት እንዲከበር ነው ” በማለት ተናግረዋል።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

እሳቸው ይህን ከማለታቸው በፊት ግን መሰል አሳቦች ይንሸራሸሩ ነበር። ቴዲ አልበሙን በስምንተኛው ወር፣ በስምንተኛው ቀን፣ በስምንተኛው ሰዓት ለአድማጮች ይፋ እንደሚያደርግ ሲያስታውቅ፣ የተጠቀመው የግል ማህበራዊ ገጹን ነበር። ቴዲ ይህን ካስታወቀ በኋላ በየዕለቱ ፎቶና ቀስቃሽ ክሊፖች እየተዘጋጁ በስሙ ሲወጡ ለነበሩ አግደገኛ መረጃዎች ቢያንስ በፌስ ቡክ ገጹ ምንም አለማለቱ ወዳጆቹና አድናቆዎቹን ሳይቀር አስገርሟል። እንደውም “አትካሮውን ይፈልገዋል” በሚል ከድምዳሜ የደረሱ አሉ። ከዚያም አልፈው ጥያቄ ያነሱ ጥቂት አይደሉም።

ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ  ሙሊሳ ” በምንም መልኩ ከአርቲስቱ ጋር የሚገናኝ የወንጀል ምርመራ ስራ የለንም። አልሰራንም። እሱ ላይ የቀረበ ጥቆማም የለም። እሱ የኛ ተጠርጣሪ አይደለም” በማለት ሲያስታውቁ አንዳንዶቹን የፈጠራ ወሬዎች ከኤአይ ጋር በማገናኘት ጭምር ነው።

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ” ኢትዮሪካ ” አልበሙን ለአድማጭ አድናቂዎቹ ካቀረበበት ጊዜ አንስቶ በእሱና በእሱ ዙሪያ ባሉ ሰዎች ላይ ጫና እየደረሰ መሆኑ እየተነገረ ነው። “ምክትል ማናጀሩን ጨምሮ የረጅም ጊዜ የቅርብ ጓደኛው  ” መታሰራቸውም ተመላክቷል። ከዚህ ባለፈ ታጥቀው በመኪና የመጡ አካላት “ሲኤምሲ” አካባቢ የሚገኝ የሙዚቃ ስቱዲዮ እና ስራዎችን የሚያዘጋጅበት ቦታን በምሽት በኃይል በመስበር መዝረፋቸው ተነግሯል።

የጀርመን ድምጽ ሬድዮ ጣቢያም የቴዲ አፍሮን የቅርብ ሰዎች ዋቢ በማድረግ “ስቱዲዮው ተዘርፏል” ብሏል። ጠባቂዎችም መደብደባቸውን ገልጿል። ከተዘረፉት ውስጥ ያልወጡ የሙዚቃ ስራዎች ያሉባቸው ፋይሎች እንዳሉ አመልክቷል። ይህ ሁሉ ሲባል የጉዳዩ ባለቤት አልተነፈሰም። እስካሁን ድረስ እየደረሱ ነው ስለተባሉት ጫናዎች እና በስቱዲዮው ላይ በታጠቁ አካላት “ተፈጽሟል” ስለተባለው ዝርፊያ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁንም ሆነ በማነጀሩ በኩል የተሰጠ አንዳችም መረጃ የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምርያ የወንጀል ምርመራ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ አብዲሳን ስለተጠቀሱት ጉዳዮች ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። “የፌደራል ፖሊስ እንደዚህ አይነት ውንብድና አይሰራም። ስብእናውም አይደለም። የሚሰራው በህግና በህግ ብቻ ነው ” ብለዋል።

“ብዙ ኦፕሬሽኖችን እንሰራለን በነዚህ ኦፕሬሽኖች ውስጥ ከቴዲ አፍሮ ጋር የሚገናኝ አንድም ነገር የለም” ሲሉ ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ  ሙሊሳ ገልጸዋል።

ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የሚፈለግ ተጠርጣሪ እንዳልሆነ፣ በእሱ ላይ ምንም አይነት ምርመራ እንዳልተደረገ እና እንዳልተሰራ ፣ እንዲሁም ከእሱ ጋር የሚገናኝ ጥቆማ ለፖሊስ እንዳልደረሰውና ፌዴራል ፖሊስ እሱን በተመለከተ ያከናወነው አንዳችም ነገር እንደሌለ “ህዝብ ይወቅልን” በማለት ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ  ሙሊሳ ተናግረዋል። አርቲስቱ ሙዚቃውን አውጥቶ በሰላም እየኖረ መሆኑን አመልክተዋል።

እሱን አስመልክቶ “እኛም እንደማንኛውም ሰው ሚዲያ ላይ የሚወጣውን እናያለን ፤ በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የፈጠራ ወሬዎች ይሰራጫሉ። አርቲስቱን እንደማስያዣ ይዘው የፖለቲካ አጀንዳ ማራገብ የሚፈልጉትንም እያየናቸው ነው ” ሲሉ ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ  ሙሊሳ ተናግረዋል።

ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ መዝፈን ህገመንግስታዊ መብቱ እንደሆነና ይህንኑ መብቱን ተጠቅሞ ሙዚቃ መስራቱን እንደ አንድ መደበኛ ጉዳይ ገልጸዋል። አክለውም ደጋፊዎቹ ሲደግፉ የሚቃወሙትም ሊቃወሙ ይችላሉ፤ እንዲህ ያለው የስሜት መለያየት የፖሊስ ጉዳይ ሳይሆን ሌላ ሜዳ እንደሆነ አስታውቀዋል። ስለዚህ ከቴድሮስ ጋር የሚገናኝ ወይም ንክኪ ያለው ጉዳይ ላይ ፖሊስ ተሳትፎ አላደርግም። የሚያደርገበት እድልም የለም።

“ህግ ጥሶ ከተገኘ እንደማንኛውም ዜጋ በህግ ሊጠየቅ የሚችል ሰው ነው” ያሉት ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ ሙሊሳ፣ ለጊዜው ግን ከእሱ ጋር የሚገናኝ ምንም አይነት የምርመራ ስራ እየተሰራ እንዳልሆነ አመልክተዋል።

ዋናውና ትልቁ ነገር ህዝቡም በደምብ ሊገነዘብ የሚገባው በማለት ኮሚሽነሩ የተናገሩት እንደ ቀድሞ ዝም ብሎ ኮሽ ባለ ወይም “እንደዚህ ብልህ ዘፈንክ” ተብሎየሚታሰር የለም። “ፖሊስ እንደዚህ አይነቱን የቀድሞ አሰራር graduate አድርጎ አልፏል” ሲሉ ኮሚሽነሩ ስረድተዋል።

ፖፖሊስ የቆየውንና “እንደ ድሮው” የነበረውን የአፈና መንገድ ትቶ ወደ ተሻለና ወደ ሰለጠነ አሠራር መሸጋገሩን በመግለጽ ፖሊስ አሁን የሕግ የበላይነትን ለማክበር የሚያስችል ብስለት ላይ መድረሱን ያመለከቱት ኮሚሽነሩ፣ “ወንጀል ከሰራ ማንም ሰው ይጠየቃል ፤ የመንግሥት አካል ፣ አመራርም ቢሆን በህግ በማስረጃ ይጠየቃል። ወንጀል ያልሰራ ሰው ግን በፍጹም አይጠየቅም ” ብለዋል። የቴድሮስም ጉዳይ ከዚህ የተለየ እንዳልሆነ አመልክተዋል።

ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ አብዲሳ በተለያዩ መልኮች ቴዲ አፍሮ ላይ “ክልከላ ተደርጓል ተብሎ ሲሰራጩ የነበሩ መረጃዎች ሁሉ ውሸቶች ናቸው” ብለዋል። አክለውም “መረጃዎቹ ሁሉም መሰረተ ቢስ፣ ቴዲን ተጠቅመው ህዝብ ላይ ሽብር ለመፍጠር የሚደረግ የሳይበር ወሬዎች ናቸው። እውነቱ ግን ይህ ሁሉ የሃሰት መረጃ በስሙ የሚወጣበት ቴድሮስ ቤቱ ሆኖ በስላም እየኖረ ያለ ሰው መሆኑ ነው” ብለዋል።

“አርቲስት ሆኖ ሙዚቃ መስራትና የፈለገውን አመለካከት የመያዝ ህገመንግስታዊ መብት ነው። ማንም መበቱን መጠቀም ይችላል። ከዚህ ውጪ ያለ ማስረጃ ሰው የማይያዝበትን ሂደት ፈጥረናል። ለዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቅመን የትኛውም አይነት የምርመራ ስራዎችን እንሰራለን። የምንሰራቸውንም በግልጽ ለህዝብ እናሳውቃለን” ሲሉ ኮሚሽነሩ ድንቅብቅ ጉዳይ እንደሌለ ተናግረዋል።

ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ “ሰው ሊታወቅ ይችላል ፣ ወንድምህ ሊታሰር ይችላል አናውቅም ፣ ጓደኛህ ሊታሰር ይችላል አናውቅም ግን ይህ ሰው ከማን ጋር ይውላል ማነው ብለን አናስርም ፤ የምንሰራቸው ስራዎች legitimate ናቸው ፍ/ቤት አቅርበን በስርዓት ጊዜ ቀጠሮ ጠይቀን እንመረምራለን ይሄ የማስረጃ ጉዳይ ነው። የስራ ሂደታችንም ይኸው ነው። ከዚህ ውጭ ምንም ከአርቲስቱ ጋር የሚገናኝ ምርመራ አልሰራንም ” ሲሉ አስረድተዋል።

“ሌላ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች እሱን መጠቀሚያ ማድረግ ስለሚፈልጉ እሱ ስለማያዋጣቸው ቢተውት ጥሩ ነው” ሲሉ ኮሚሽነሩ መክረዋል።

“ከአርቲስቱ ጋር የተገናኘና እሱንም መሰረት የሚያደርግ ምንም ነገር ባልሰራንበት ፤ ሳይበር ተጠቅመው ብዙ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ህዝቡን በሌላ ነገር ማንቀሳቀስ ያልቻሉ እሱ እንደተነካ አድርገው የሚፈጽሙት ተግባር መሰረተ ቢስ ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። አክለውም ህዝብ በተለይም የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች የሚሰሙትን ሁሉ ከማመን እንዲጠነቀቁ፣ በተቻላቸው መጠን መረጃዎችን ለማጣራት እንዲሞክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

“የሰማነው ነገር ፣ የሚወራው ሁሉ እውነት አይደለም። ዛሬ ኤአይ AI አለ ፤ ለምሳሌ የሙዚቃው መሳሪያ ተወሰደ ‘ ተብሎ የተሰራው ሙሉ በሙሉ ውሸት ነው። በሳይበር፣ በሚዲያ የተወራው ሁሉ እውነት አይደለም። ህዝቡ ይሄን ማመዛዘን አለበት” በማለት ጥሪያቸውን ያቀረቡት ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ አብዲሳ የእነ ብርቱካንን ጉዳይ አስታውሰዋል። እነ ብርቱካን ተደራጅተውና ተታለው የተቀነባበረ ፊልም በኢቢኤስ ቲቪ ከሰሩ በኋላ በራሳቸው አንደበት “ሃሰት ነው” በማለት ይቅርታ መጠየቃቸው፣ የቴሌቪዥን ጣቢያውም “በድርጊቱ አዝናለሁ፤ ተጸጽቻለሁ” ማለቱ አይዘነጋም። ኮሚሽነሩ እንዳሉት  የእነ ብርቱካን ድራማ ህዝቡ ከተረጋጋ በኋላ እውነታው ወጣና ተገለጠ”

ም/ኮሚሽነር ሙሊሳ አብዲሳ “ዛሬ ላይ ሁሉም ሰው ሚዲያ በእጁ ነው”  ይሄንን መከልከል አይቻልም። የመረጃ ተጠቃሚው ህዝብ ግን በደምብ ቆሞ ማሰብ ያለበት የትኛው ነው የሚጠቅመው የሚለውን ነው ፤ መርምሮ እየለየ ሊጠቀም ይገባል ” ብለዋል።

ሰዋሰው ምልቲ ሚዲያ ቴዲ አፍሮ የተወሰኑ ፖለቲካ ይዘት ያላቸውን ዘፈኖቹን እንዲቀንስ፣ ቅድመ ሁኔታ በማቅረብ ቀደም ሲል የነበራቸውን ውል እንደሰረዘ ብስፋት መነገሩ ይታወሳል። ድርጅቱ ዝርዝር የውል ሂደቱን አስረድቶ በስላምና በውይይት ውላ ማፍረሳቸውን በመግለጫ ይፋ ሲያደርግ ቴድሮስ ምላሽ አለመስጥቱ ይታወሳል።


 ቴዎድሮስ ካሳሁን ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር የነበረውን ውል በስምምነት እንደፈረሰ ከሁሉም ወገን በተገኘ መረጃ ተረጋግጧል። ስምምነቱ የፈረሰው በአሳታሚውና በአርቲስቱ በኩል ውሉ ውስጥ የተካተቱት አዳዲስ ጉዳዮች ላይ ልዩነት በመፈጠሩ ነው።

ሊንኩን ተጭነው ሙሉውን ያንብቡ


ፖሊስ የሰጠውን መረጃ አስመልክቶ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ወይም ህጋዊ ወኪሎቹ ምላሽ ይሰጣሉ ወይም ፖሊስ የሰጠውን መግለጫ አጽንተው በዝምታቸው ይቀጥላሉ?

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
News

የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ

April 8, 2026
Load more
Read also
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2