Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Western Pressure on Ethiopia Intended to See Weak Gov’t, Nation – Scholars

    July 10, 20210

    Journalist demands UNWFP to tell truth about missing trucks

    October 3, 20210

    ብርሃኑ ባይህ እና አዲስ ተድላ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ

    December 19, 20200

    አብንና ባልደራስ ከተሸነፉ ” ውጤቱን አንቀበልም” ሊሉ የሚችሉ ፓርቲዎች እንደሚሆኑ ዲፕሎማቶች ገለጹ

    May 23, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሚስጥራዊ የቻይና ፖሊስ ጣቢያዎች በአሜሪካ ተገኙ

    December 19, 20240

    ሦስተኛው ዕድል እንዳይባክን … !

    May 21, 20220

    “Why I decided to extend my time at the club”

    May 24, 20230

    የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ዋና የጦሩ መሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ

    February 24, 20220

    “Ethiopia’s success reflects a new alternative for Africa’s development”

    January 29, 20240
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  “የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር ” ዐቢይ አህመድ ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገለጹ
News

“የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር ” ዐቢይ አህመድ ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገለጹ

Ethioreview newsEthioreview news—December 8, 20210
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዘመቻውን የመጀመሪያውን ምእራፍ አጠናቀው ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገለጹ። “የመጀመሪያውን ምእራፍ አጠናቅቄ ለተወሰኑ ጊዜያት ወደ ቢሮ መመለሴን እየገለጽኩ፣ ዛሬም ሆነ ወደፊት ጠላቶቻችን ጉልበታቸው ዝሎ፣ የጥላቻና የጠበኝነትን መንገድ ጥለው፣ የፍቅርና የሰላምን መንገድ እስኪመርጡ ትግላችን ይቀጥላል” ሲሉ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ወደ ትግል የገባነው ሐቅን ይዘን ነውና የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር። ድካማችንን አበርትቷል። ሕዝባችንን ከዳር እስከ ዳር አነቃንቋል። የሠራዊታችንን ቁጥርና ዐቅም ጨምሮልናል። ልባችንን አጀግኖ የኢትዮጵያን አሸናፊነት በዓይናችን አሳይቶናል” ብለዋል።

“ውድቀታችንን ሲመኙ የነበሩትን ሁሉ አሳፍሮ ዳግም የኢትዮጵያን ስም በወርቅ ቀለም እንድንጽፍ አስችሎናል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “የዚህ ታሪክ አካል ለመሆን ፈጣሪ ዕድሉን የሰጣችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ። የኢትዮጵያን ስም ከማድመቅ የበለጠ ዕድል የለምና” ብለዋል።

“ትግሉ ገና አልተጠናቀቀም። ነጻ ያልወጡ አካባቢዎች አሉን። አሁን የፈተነን ኃይል ዳግመኛ የኢትዮጵያ ፈተና ሆኖ እንዳይመጣ የሚያስችል ዘላቂ መፍትሔ ልንሰጠው ይገባል” ሲሉም አስታውቀዋል።

More stories

በመተከልና ሌሎች አካባቢዎች ተፈጥረው በነበሩ ግጭቶች የሱዳንና የግብፅ እጅ እንዳለበት ተገለጸ

March 5, 2021

የመከላከያን ጨምሮ የአሜሪካንን ሚስጢር “ለትውልድ አገሩ አቀብሏል” የተባለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ” ብሄራዊ ጀግና” እየተባለ ነው

October 1, 2023

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ወይም ሞት እያለ ነው

March 22, 2022

“የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር ” ዐቢይ አህመድ ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገለጹ

December 8, 2021

ለዚህኛው ችግር በምንሰጠው መፍትሔ ወደፊት ለክፉ ያሰቡን ሁሉ እጃቸውን እንዲሰበስቡ ማድረግ አለብን። ላለፈው የምናመሰግንበት እንጂ ጨርሰናል ብለን እፎይ የምንልበት ወቅት ላይ አይደለንም። የተበተነው ጠላት እንዲማረክ ማድረግ አለብን። አካባቢያችንን ከበፊቱ በበለጠ ነቅተን የመጠበቂያ ጊዜው አሁን ነው። ፍተሻና አሰሳዎችን አጠንክረን መቀጠል ይገባናል ሲሉም አሳስበዋል።

“በድል የታጀበው የመጀመሪያው ምእራፍ”

ውድ የሀገሬ ልጆች፣
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ትከበራለች፤ ትታፈራለች። ኢትዮጵያን መገዳደር ይሞከር ይሆናል። ተገዳድሮ ማሸነፍ ግን ትናንትም አልተቻለም፤ ዛሬም አይሆንም፤ ነገም አይቻልም። ኢትዮጵያ የሚለው ስም ሁሌም ከአሸናፊነት ጋር የተያያዘ ነው። ከጥቂት ጊዜያት በፊት ኢትዮጵያን ሊወጋ የተነሳውን ጠላት በጋራ ሆነን እንድንመክት ጦር ግንባር ላይ የያዝነው ቀጠሮ ጠላትን አንገት ሲያስደፋ ኢትዮጵያን ቀና አድርጓታል። ሀገራችን ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ለማድረግ በጦር ግንባር እየተከፈለ ያለው መስዕዋትነት የኢትዮጵያን የአሸናፊነት ስም የሚመልስ መሆኑን እያበሰርኩ፣ ያቀረብኩትን ጥሪ ተቀብላችሁ ሕይወታችሁን፣ ጉልበታችሁን፣ ሀብታችሁን፣ ዕውቀታችሁን፣ ጊዜያችሁንና ሞያችሁን ለሠጣችሁ ሁሉ በኢትዮጵያ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። በዚሁ አጋጣሚ፣ የመጀመሪያውን ምእራፍ አጠናቅቄ ለተወሰኑ ጊዜያት ወደ ቢሮ መመለሴን እየገለጽኩ፣ ዛሬም ሆነ ወደፊት ጠላቶቻችን ጉልበታቸው ዝሎ፣ የጥላቻና የጠበኝነትን መንገድ ጥለው፣ የፍቅርና የሰላምን መንገድ እስኪመርጡ ትግላችን ይቀጥላል።

የእኛ ፍላጎት ሁሌም ሰላምና ፍቅር ነው። ኢትዮጵያ ሕብረ ብሔራዊ አንድነቷ ተጠብቆ የብልጽግና ጉዞዋ የተቃና እንዲሆን ያለንን ፍላጎት ከጅምሩ አሳውቀን ለተግባራዊነቱ ስንተጋ ቆይተናል። ነገር ግን በተደጋጋሚ ያቀረብነውን የሰላም አማራጭ ባለመቀበል፤ አሳታፊና አካታች የሆነውን አዲሱን የፖለቲካ ባህላችንን ረግጦ በመውጣት፤ ጥፋትንና እልቂትን ለማስቀረት ሲባል የተደረገውን ትዕግሥት ከቁብ ባለመቁጠር፤ የአንዳንድ የውጭ ጠላቶችን አፍና ድጋፍ በመተማመን፤ አሸባሪው ሕወሓት ከግብር አምሳሎቹ ጋር ሆኖ በሀገራችን ላይ አደጋ ደቅኖ ነበር። ነገሮች ያለቁና የተጠናቀቁ እስኪመስሉ ድረስ ኢትዮጵያን የማያውቁ ሁሉ በሥጋትና በፍርሐት ተውጠው ነበር። ሠግተው ሊያሠጉን፤ ፈርተው ሊያስፈራሩን የሞከሩ የውስጥና የውጭ አካላትም ነበሩ። ልጣችን የተራሰ፣ ጉድጓዳችን የተማሰ መስሎ የተሰማቸው ነበሩ። የኢትዮጵያን የአሸናፊነት ምሥጢር የሚያውቁት ብቻ በጽናት እስከ መጨረሻው የቆሙበት አጋጣሚም ተፈጥሮ ነበር።

ወደ ትግል የገባነው ሐቅን ይዘን ነውና የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር። ድካማችንን አበርትቷል። ሕዝባችንን ከዳር እስከ ዳር አነቃንቋል። የሠራዊታችንን ቁጥርና ዐቅም ጨምሮልናል። ልባችንን አጀግኖ የኢትዮጵያን አሸናፊነት በዓይናችን አሳይቶናል። ውድቀታችንን ሲመኙ የነበሩትን ሁሉ አሳፍሮ ዳግም የኢትዮጵያን ስም በወርቅ ቀለም እንድንጽፍ አስችሎናል። የዚህ ታሪክ አካል ለመሆን ፈጣሪ ዕድሉን የሰጣችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ። የኢትዮጵያን ስም ከማድመቅ የበለጠ ዕድል የለምና!!

በዕቅዳችን መሠረት የመጀመሪያውን ምዕራፍ፣ “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነትን” በሁለት ሣምንት ውስጥ አሳክተናል። የመከላከያ ሠራዊት፣ የየክልሎቹ ልዩ ኃይሎች፣ የፌዴራል ፖሊስ አባላት እና የየአካባቢዎቹ ሚሊሻዎችና ታጣቂዎች በከፈላችሁት መሥዋዕትነት ለልጆቻችን የምንነግረው ድንቅ ታሪክ ሠርታችኋል። በሁሉም መስክ በደጀንነት የተሰለፋችሁ ሁሉ የኢትዮጵያ ውድ ሀብቶች መሆናችሁን በዓይናችሁ አይታችኋል።

ትግሉ ገና አልተጠናቀቀም። ነጻ ያልወጡ አካባቢዎች አሉን። አሁን የፈተነን ኃይል ዳግመኛ የኢትዮጵያ ፈተና ሆኖ እንዳይመጣ የሚያስችል ዘላቂ መፍትሔ ልንሰጠው ይገባል። ለዚህኛው ችግር በምንሰጠው መፍትሔ ወደፊት ለክፉ ያሰቡን ሁሉ እጃቸውን እንዲሰበስቡ ማድረግ አለብን። ላለፈው የምናመሰግንበት እንጂ ጨርሰናል ብለን እፎይ የምንልበት ወቅት ላይ አይደለንም። የተበተነው ጠላት እንዲማረክ ማድረግ አለብን። አካባቢያችንን ከበፊቱ በበለጠ ነቅተን የመጠበቂያ ጊዜው አሁን ነው። ፍተሻና አሰሳዎችን አጠንክረን መቀጠል ይገባናል።

ጠላት ያፈረሰውን መልሰን መገንባት፣ የተፈናቀሉትን መመለስ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎቻችንንም ከበፊቱ በበለጠና በፈጠነ መንገድ ማሳለጥ ይጠበቅብናል።
ለሠራዊታችን የምንሰጠውን ሁለንተናዊ ድጋፍ በዓይነትም በብዛትም አጠናክረን የምንቀጥልበት ወቅት ነው። ያልዘመቱ ወገኖች ግማሽ ያህል ጊዜና ጉልበታቸውን ለዘማች ቤተሰቦች መስጠት ይጠበቅባቸዋል፤ እነሱ ለእኛ ሕይወታቸውን ሲገብሩ እኛ ለእነሱ ገንዘብና ጉልበታችንን መስጠታችን ቢያንስ እንጂ አይበዛም። እናም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የዘማች ቤተሰቦችን መደገፍና ማበርታት አለብን።

ትግሉ በጦር ግንባር ብቻ አይደለም፤ በሁሉም መስክ መፋለም ይገባናል። የገበሬውን እህል አንዲት ፍሬ እንዳትባክን አድገን ወገባችን አሥረን መሰብሰብ አለብን። በዲፕሎማሲውና በፖለቲካው ዘርፍ የምንሠራቸውን ሥራዎች በአዳዲስ መንገዶች እያከናወንን መቀጠል ይገባል። ወጭ ቆጥበን፣ ጊዜና ጉልበት ጨምረን፣ ለሀገራችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መሥራት ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል።

በተለይ በተለይ በህልውና ዘመቻው ወቅት ያየነውን የኢትዮጵያውያንን አንድነት እስከ ዓለም ፍጻሜ ሀብታችን አድርገነው መቀጠል አለብን። በገጠርና በከተማ፣ በሀገር ቤትና በውጭ፣ በግንባርና በደጀን፣ ያለን ሁላችን ለአንድ ዓላማ ተሰልፈን አንድ ግብ እያሳካን ነው። ማንም ተነስቶ ኢትዮጵያን ማውረድ ከማይችልበት ማማ ላይ እየሰቀልናት ነው። ይህ አንድነታችን እንዲዘልቅ ከፋፋይ ሐሳቦችን እንመክት። የድል አጥቢያ አርበኞችን እንቃወም። በተጋድሏችን ያገኘነውን ነገር ለማቅለል የሚፈልጉትን ፊት እንንሣቸው። በጋራ ታግለን በጋራ ያስገኘነውን ድል፣ እንደ ቅርጫ ሥጋ ሊመድቡ የሚነሡትን አቃራጮች እናነውራቸው። ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ናት። ከዚህ የወረደ ነገር አንቀበልም።

የገጠመን ፈተና ብዙ መከራና ችግር ያስከተለብን ቢሆንም በምንም መንገድ የማናገኛቸውን ዕድሎችም ይዞልን መጥቷል። ከገጠመን ፈተና ይልቅ በዕድሎቻችን ላይ አተኩረን ከሠራን ኢትዮጵያን ኃያልና ራሷን በሁሉም መስክ የቻለች ሀገር እናደርጋታለን። ከፈጣሪ ቀጥሎ በፈተናችን ጊዜ አብረውን ለቆሙ እና በዓለም አደባባይ ለተማገቱልን ሁሉ ኢትዮጵያ ከፍ ያለ ምስጋና ታቀርባለች። የጀመርነው ህልውናችንን የማስከበርና ኢትዮጵያን በጽኑ መሠረት ላይ የመትከል ተጋድሏችንን በፍጥነት አጠናቅቀን ወደ ብልጽግና አጀንዳችን በሙሉ ጉልበት በቅርቡ እንደምንመለስ እምነቴ ነው።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሕዳር 29፣ 2014 ዓ.ም

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

Instagram is testing photo albums, because nothing is sacred anymore
“እኔ አሁን አቅም የለኝም። ልጆቼ ይሰሩታል!!”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news