ይህ ሳይሆን ቀርቶ የጽንፈኝነት አስተሳሰብ እየገነገነ ከሄደ ግን እንደ ሀገር የምንመኘውን ዘላቂ ሰላምም ሆነ ልማት ማረጋገጥ ከዚያም ከፍ ሲል እንደአገር በጋራ ለመኖር የሚኖረን ተስፋ የመነመነ ይሆናል …. ጽንፈኝነት ለሌላው አመለካከት ቦታ የማይሰጥ በመሆኑ አብሮ የመኖርን እና በመነጋገር ችግሮችን የመፍታት ባህልን የሚያጠፋ ነው። የእኔ ሃሳብ ብቻ ትክክል ነው ብለው የሚያስቡ አካላት የሚሰባሰቡበት እንደመሆኑ ለሌላው ሃሳብ ፈጽሞ ቦታ ባለመስጠት በመነጋገር እና በመደራደር ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ፍላጎትን በሃይል ለመጫን ተገቢነት የሌላቸው ኢፍትሃዊ እንቅስቃሴዎች እንዲደረጉ ምክንያት
አሁን አሁን ጽንፈኝነት በአገራችን ከሃሳብ አልፎ ጉዳቱ በተግባር እየታየ መምጣቱን ብዙዎች ይስማማሉ።ጽንፈኝነት በብሔር ወይም በሃይማኖት ዋሻ በመደበቅ የራሳቸውን ፖለቲካዊ ፍላጎት ለማሳካት የሚፈልጉ ኃይሎች መሰባሰቢያም ነው።
ጽንፈኝነት ለሌላው አመለካከት ቦታ የማይሰጥ በመሆኑ አብሮ የመኖርን እና በመነጋገር ችግሮችን የመፍታት ባህልን የሚያጠፋ ነው። የእኔ ሃሳብ ብቻ ትክክል ነው ብለው የሚያስቡ አካላት የሚሰባሰቡበት እንደመሆኑ ለሌላው ሃሳብ ፈጽሞ ቦታ ባለመስጠት በመነጋገር እና በመደራደር ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ፍላጎትን በሃይል ለመጫን ተገቢነት የሌላቸው ኢፍትሃዊ እንቅስቃሴዎች እንዲደረጉ ምክንያት እየሆነ መሆኑን ምሁራን ይገልጻሉ፡፡
ጽንፈኝነት እንደ አገር የእርስ በእርስ ግንኙነትን በማሻከር ወንድማማችነት እንዳይኖር በማድረግ ማህበራዊ ግንኙነትን የሚጎዳ፣ አገር እንዳይረጋጋ በማድረግ ኢኮኖሚው እንዳያድግ ማነቆ በመሆን እና ፖለቲካዊ ቀውስ የሚፈጥር በመሆኑ በጊዜ መገታት እንዳለበትም ያሳስባሉ፡፡
በጉዳዩ ላይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሃሳባቸውን የሰጡት የደቡብ ክልል ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ ፤ የጽንፈኝነት ምንጩ የራስ ጥቅም እና የግል ፍላጎት ማሳካት ሲሆን እኔ የበላይ ፣ፍጹም እና ትክክል ነኝ በሚል ሌላውን የሚጨፈልቅ አስተሳሰብ ነው ይላሉ፡፡
እንደ አቶ ጥላሁን ገለጻ፤ ጽንፈኝነት በአገራችን ብሔርን እና ሃይማኖትን መሸሸጊያ አድርጎ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች እያስከተለ ነው።እኛ ኢትዮጵያውያን የምንታወቀው በአቃፊነት እና አብሮ በመኖር ነው።በአንጻሩ ጽንፈኝነት በዓለም የምንታወቅበት የአብሮነታችን ማህበራዊ እሴት እንዲሸረሸር እያደረገ ይገኛል፡፡
በጽንፈኝነት አስተሳሰብ ምክንያት በአገራችን ብዙ ሰዎች መፈናቀላቸውን፤ ንብረት መውደሙን፤ የሰው ሕይወት ጭምር መጥፋቱን የሚናገሩት አቶ ጥላሁን፤ በኢኮኖሚውም የውጭ ኢንቨስተሮች ነጻ ሆነው እንዳይሰሩ መሰናክል በመሆን፣ በሰከነ ሁኔታ የሚሰሩ እጆች ሁሉ ባለመስራታቸው የጉልበት ምርታማነት እንዲቀንስ በማድረግ ለኑሮ ውድነት አንድ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
ጽንፈኝነት እርስ በእርስ ተናቦ መጓዝ እንዳይኖርና መጠራጠር እንዲኖር በማድረግ የፖለቲካ ቀውስ እንደሚፈጥር የተናገሩት አቶ ጥላሁን ፤ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የነበረው ጦርነትም እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን በሚል ወደ ትልቅ ቀውስ የተሸጋገረ የጽንፈኝነት ውጤት እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡
በጽንፈኝነት አካሄድ የትኛውም አገር አልሰለጠነም ያሉት ኃላፊው፤ የሃሳብ ልዩነቶች ካሉ በተለመደው መንገድ ቁጭ ብለን በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር እና በመወያየት መፍታት አለብን ብለዋል፡፡
ጽንፈኝነት የማህበራዊ ፣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ቀውስ በመፍጠር አገርን ስጋት ውስጥ የሚከት አደገኛ አስተሳሰብ በመሆኑ መገታት እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
አቶ ጥላሁን ጽንፈኝነትን እያበረታታ እና አቅም እንዲያገኝ እያደረገ ያለው የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች የሀሰት ፕሮፓጋንዳ መሆኑን ጠቁመው፤ ኢትዮጵያውያን ሆነው ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚሰሩ ሰዎች ከእኩይ ድርጊታቸው መታረም እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ጽንፈኝነት ላይ ሃሳባቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሰጡት በአማራ ክልል የተፎካካሪ ፓርቲዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ተስፋሁን አለምነህ በበኩላቸው እንደሚሉት፤ ፅንፈኝነት ካለ መነጋገር፣ መደራደር እና መስማማት የሚባል ነገር የለም።
ፅንፈኝነት በከፍተኛ ጥላቻ ላይ በመመስረት የራስን ፍላጎት ብቻ ማሳካትን መሠረት ያደረገ ነው። አንዳንዱ የራሱን ፍላጎት መሬት ለማስነካት የትኛውንም ዓይነት እርምጃ ይወስዳል። ፅንፈኝነት ደም በማፍሰስም ቢሆን አሸናፊ መሆን የሚፈልግ በመሆኑ ይህን ለማድረግ ግብረገብነት፣ መቻቻል እና መከባበር የመሳሰሉትን ጉዳዮች ረግጦ እንደሚሄድ የገለጹት አቶ ተስፋሁን፤ በዋናነት ከበደልና ከቂም በመነጨ ወሰን አልባ ጥላቻ የራስን ፍላጎት ማስፈፀም መፈለግ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

እንደ አቶ ተስፋሁን አገላለጽ፤ ከፅንፈኝነት የሚወለደው ሽብርተኝነት ነው። በጠረጴዛ ዙሪያ በመወያየት፣ በመነጋገርና በመቻቻል የማያምን አካል ወደሽብር ይሄዳል፤ በዚህ አይነት አካሄድ መንግሥታዊ ሥልጣንን ለመቆጣጠርም ሆነ ሰላማዊ አገርን ለመፍጠር ያለው ዕድል ግን አናሳ እንደሆነ ገልጸዋል።
ፅንፈኝነት ከጋራ አሸናፊነት ይልቅ ለብቻዬ አሸናፊ ልሁን የሚል በመሆኑ ጥፋት፣ ውድመት እንዲሁም አለመረጋጋት እንደሚያስከትል ጠቁመው፤ የሕዝብን አንድነት እና አብሮ የመኖር ባሕልንም እንደሚሸረሽር ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ፅንፈኝነት ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዳይገቡ እያደረገ እንደሆነ የተናገሩት አቶ ተስፋሁን፤ በዚህም ዜጎች በማንነታቸው ሲፈናቀሉ እየታየ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ የኔ ብቻ ነው የሚል እና ሌላውን አግላይ ሁኔታ እንዳለ ተናግረው፤ ከእኔ ውጪ ለምን ሌላ ሃሳብ ታራምዳለህ በሚል መገዳደሎችም እንደነበሩ አስታውሰዋል።
እንደ አቶ ተስፋሁን ገለጻ፤ ጽንፈኝነት አገር ሰላም እንዳይኖራት፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዳይኖር እና ማኅበራዊ እሴት እንዲበጠስ የሚያደርግ የአገር ጠንቅ ነው። ኢትዮጵያ የበለጸገው ዓለም የደረሰበት የእድገት ላይ እንድትደርስ እንጂ እኔ ብቻ የሚል ሃሳብ ይዞ መንቀሳቀስ ብዙ ርቀት እንደማያስኬድ ጠቁመው ፤የመፍትሔ ሃሳቦች የሚገኙት አብሮ ከመኖር እንጂ ከመነጣጠል አለመሆኑ መታወቅ አለበት ነው ያሉት።
ኢትዮጵያውያን ለራሳችንም ሆነ ለአገራችን የሚጠቅመን የነበረንን አብሮ የመኖር ባህል በማሳደግ አገራዊ አንድነትን ማስጠበቅ እንደሆነ የታመነ ነው።ብሔር እና ሃይማኖት ሳይለይ የሁላችንም ጠላት የሆነውን የጽንፈኝነት አስተሳሰብ በማስወገድ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን በማጎልበት በይቅርታና በፍቅር ማንኛውንም ችግሮች በውይይት መፍታት ብልህነት ነው።በሃሳብ የበላይነት በማመን እና በማሳመን ተባብሮ በመስራት የአገር አለመረጋጋት ስጋት የሆነውን ጽንፈኝነት ማስወገድ ለነገ የማይባል የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አቶ ጥላሁንና አቶ ተስፋሁን ይገልጻሉ።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ የጽንፈኝነት አስተሳሰብ እየገነገነ ከሄደ ግን እንደ ሀገር የምንመኘውን ዘላቂ ሰላምም ሆነ ልማት ማረጋገጥ ከዚያም ከፍ ሲል እንደአገር በጋራ ለመኖር የሚኖረን ተስፋ የመነመነ እንደሆነ የአዲስ ዘመን ሪፖርት ያስረዳል።
መዓዛ ማሞ
ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም ሆነ የተጠቀሱት አካላት ስለሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው መረጃዎች በአዎንታም ሆነ በአሉታ አልተነፈሱም። ነገሮችን በጥሞና የሚከታተሉ “ቴድሮስ ራሱ ወይም አግባብነት ያላቸው ሃቁን ለህዝብ ለምን አይናገሩም? ህዝብ ሲተራመስ ዝም የሚሉት ለምንድን…
ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማህበርን ዓመታዊ እራት ለመታደም ተሰብስበዋል። ከ2600 ባልይ እንግዶች ፊት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በክብር መድረኩ ላይ ተቀምጠዋል። ሴሽታው እየተጠበቀ ባለበት ሰዓት ድንገት አዳራሹን…
“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም ሳይቆዩ አሁን ወዳሉበት ደረጃ ደረሱ። የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምንት መፈረሙን ተከትሎ ያኮረፉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፣ ሰሞኑን አሜሪካ መልሳ ልትዋዳጃቸው ማቀዷ ተሰምቷል። ዜናው መልካም ቢሆንም ኢሳያስ ግን አይቀበሉትም የሚል አስተያየት እየተሰጠ ነው።…
አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ አደጋ ጊዜ እርስ በርስ የሚረዱበትን አዲስ የጋራ መከላከያ ስምምነት ረቂቅ ለማዘጋጀት መስማማታቸውን አስታወቁ። በቆጵሮስ አስተናጋጅነት በተካሄደው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተወሰነው ይህ ውሳኔ፣ አውሮፓ በራሷ የመከላከያ አቅም ላይ እንድትተማመን ለማድረግ የታለመ…
የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት” መሆኑን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። ምርመራው ቀጥሎ ማስተባበያው ሃሰት ከሆን የከፋ ቀጣት ይጠበቃቸዋል። ባለፉት ጥቂት ወራት የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ የኢልሀን ኦማር እና የባለቤታቸው ቲም ማይኔት ሀብት ከ51,000 ዶላር ወደ 30 ሚሊዮን ዶላር…
የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?
ቪኦኢ ዜና – በአዲስ መልክ እየተሳለ ያለው የዓለም የንግድ ካርታ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል የዓለም የኢኮኖሚ ሥርዓት በአንድ ያልተጻፈ ሕግ ላይ የቆመ ነበር፤ እርሱም “ነዳጅ በዶላር ብቻ ይሸጣል” የሚለው የፔትሮ-ዶላር (Petrodollar) መርህ ነው። ሆኖም እ.ኤ.አ. በ2026 ዓለም አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኳታር የጥቁር ወርቃቸውን በርሜሎች በቻይናው “ዩዋን” መሸጥ…


