Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Western Pressure on Ethiopia Intended to See Weak Gov’t, Nation – Scholars

    July 10, 20210

    Journalist demands UNWFP to tell truth about missing trucks

    October 3, 20210

    ብርሃኑ ባይህ እና አዲስ ተድላ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ

    December 19, 20200

    አብንና ባልደራስ ከተሸነፉ ” ውጤቱን አንቀበልም” ሊሉ የሚችሉ ፓርቲዎች እንደሚሆኑ ዲፕሎማቶች ገለጹ

    May 23, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሚስጥራዊ የቻይና ፖሊስ ጣቢያዎች በአሜሪካ ተገኙ

    December 19, 20240

    ሦስተኛው ዕድል እንዳይባክን … !

    May 21, 20220

    “Why I decided to extend my time at the club”

    May 24, 20230

    የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ዋና የጦሩ መሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ

    February 24, 20220

    “Ethiopia’s success reflects a new alternative for Africa’s development”

    January 29, 20240
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  law  የውጭ ሀገር ገንዘቦችን በማተምና ማዕድኖችን በመያዝ ወንጀል የተከሰሱት የፀሐይ ሪል ስቴት ጀነራልማናጀርን ጨምሮ 9 የውጭ ሀገር ዜጎች የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ
lawNews

የውጭ ሀገር ገንዘቦችን በማተምና ማዕድኖችን በመያዝ ወንጀል የተከሰሱት የፀሐይ ሪል ስቴት ጀነራልማናጀርን ጨምሮ 9 የውጭ ሀገር ዜጎች የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

Ethioreview newsEthioreview news—October 30, 20230
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የውጭ ሀገር ገንዘቦችን በማተም እና የተለያዩ ማዕድኖችን በመያዝ ወንጀል የተከሰሱት የፀሐይ ሪል ስቴት ጀነራል ማናጀርን ጨምሮ 9 የውጭ ሀገር ዜጎች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ።

ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን የዋስትና ጥያቄና የዐቃቤ ሕግ የመቃወሚያ ክርክሮችን መርምሮ የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ ያደረገው።

የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ ያደረገው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ልደታ ምድብ 8ኛ የገቢዎችና ጉሙሩክ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

በቀረበባቸው ተደራራቢ ክስ ላይ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ከተደረገባቸው ተከሳሾች መካከል የፀሐይ የሪል ስቴት መስራች፣ ባለድርሻ እና ስራ አስኪያጅ ቺያን ኩዊን ጨምሮ ዘጠኝ የውጭ ሀገር ዜጋ የሆኑ ተከሳሾች ናቸው።

More stories

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

May 10, 2021

[ቱጃሩ] ጃዋር መሀመድ በሌብነትና በዳግም የፖለቲካ ውንብድና ተከሰሰ

December 25, 2024

መንግስት በትግራይ የተቋረጠውን አገልግሎት ሊያስጀምርና ርዳታ ሊያቀርብ መሆኑን ይፋ አደረገ

October 18, 2022

የዶክተር ሙሉቀን ሃብቱ ያለመከሰስ መብት ተነሳ

July 17, 2022

የፍትህ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ የወንጀል ተሳትፎ ጠቅሶ ተደራራቢ ሰባት ክሶችን በየድርሻቸው አቅርቦባቸው ነበር።

በተለይም ባቀረበው በ1ኛ ክስ ላይ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ተከሳሾች ላይ ብቻ በቀረበው ክስ ላይ እንደተመላከተው የወንጀል ህግ አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 1/ሀ እና አንቀጽ 356 ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሾቹ ፀሀይ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ውስጥ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ቤት ውስጥ ከነሃሴ 24 ቀን 2015 ዓ. ም እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ሀሰተኛ ገንዘብ ለመስራት የሚያገለግሉ መሳሪያዎች፣ የተለያዩ ኬሚካሎች እና ወረቀቶች በመጠቀም ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር፣ ዩሮ፣ የእንግሊዝ ፓውንድ፣ የቻይና ይዋን እና የሌሎች የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችን አመሳስለው በማተም ላይ እያሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል የሚል ክስ ቀርቧል።

በሁለተኛው ክስ ደግሞ የወንጀል ህጉ አንቀፅ 32/ንዑስ ቁጥር 1/ሀ እናአንቀጽ 371 ንዑስ ቁጥር 2 ላይ የተደነገገውን በመተላለፍ፣ በሚኖሩበት ቤት ውስጥ ገንዘቦች ለመስራት የሚያገለግሉ፣ 2 የብር ማተሚያ ማሽን እና የተለያዩ ኬሚካሎች ማለትም በጀሪካን፣ በጠርሙስ፣ በብልቃጥ እና በበርሜል ባለ 500 ኖት ሀሰተኛ ዩሮ ለመስራት የተዘጋጀ 60 ሚሊየን 750 ሺህ ብር የሚገመት ነጭ ወረቀት ብዛት በነጠላ 121 ሺህ 500 ዩሮ እና 42 ሚሊየን 400 ሺህ ዶላር የሚገመት ሀሰተኛ ዶላር ለመስራት የተዘጋጀ ባለ 100 ኖት 424 ሺህ አረንጓዴ ወረቀት የተገኘባቸው መሆኑን ዐቃቤ ህግ ጠቅሷል።

በተጨማሪም 16 ሚሊየን 150 ሺህ የሚገመት ነጭ የዶላር ወረቀት፣ የተለያየ ነጭ ዱቄት፣ አንዱ እሽግ በውስጡ 500 ወረቀት የያዘ 32 እሽግ በብር ቅርፅ የተቆራረጡ ወረቀቶች፣ በአልሙንየም የተጠቀለለ በገንዘብ ቅርፅ የተቆረጠ ጥቁር ቀለም ያለው ወረቀት፣ 28 እሽግ አንዱ 500 የያዘ የገንዘብ መስሪያ ወረቀት፣ እንዲሁም ገንዘብ ለመስራት የሚያገለግሉ መስሪያና መሳርያዎች ይዘው በፀጥታ አካላት በተደረገ ክትትል ይዘውት የተገኙ መሆኑን ዐቃቤ ሕግ ጠቅሶ ሀሰተኛ ነገሮችን ለመስራት የሚያገለግሉ መስሪያ እና መሳሪያዎች መያዝ ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

3ኛ ክስ ደግሞ በ1ኛ ተከሳሸ ላይ ብቻ የቀረበ ሲሆን÷ በዚህም የወንጀል ህግ አንቀፅ 359 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ በጳጉሜን 1 ቀን 2015 ዓ.ም በተደረገው ፍተሻ ሀሰተኛ የሆኑ ባለ 100 የገንዘብ ብዛቱ 297 ሺህ 400 የአሜሪካ ዶላር፣ ባለ 50 የገንዘብ ብዛቱ 36 ሺህ 250 የእንግሊዝ ፓውንድ፣ ባለ 500 ዩሮ 62 ሺህ የሆነ፣ እና ባለ 200፣ 650 ሺህ 600 ዩሮ፣ እንዲሁም ባለ 1 ሺህ 567 የቻይና ዩዋን ይዞ የተገኘ መሆኑ ተጠቅሶ ተከሳሹ ላይ ሀሰተኛ ገንዘብ ይዞ መገኘት ወንጀል ክስ ቀርቧል።

በሌላ በኩል በአንደኛ ተከሳሽ ላይ በሌላኛው በቀረበበት 5ኛ ክስ ላይ ደግሞ ተከሳሹ ማዕድን የመያዝ ፍቃድ ሳይኖረው ክብደቱ 108 ነጥብ 43 እና 51 ነጥብ 88 ግራም የሚመዝን ኦፓል የተፈጥሮ ማዕድን እና 4 ነጥብ 99 ግራም የሚመዝን ኳርትዝ እንዲሁም 77 ነጥብ 71 ግራም የሚመዝን አጌት የተፈጠሮ ማዕድን እና 104 ነጥብ 59 ግራም የሚመዝን ማግኔታይት የተፈጥሮ ማዕድን ይዞ የተገኘ መሆኑ በክሱ ተጠቅሶ ፍቃድ ሳይኖረው የተፈጥሮ ማዕድን መያዝ እና የአዋጁን ድንጋጌዎች መተላለፍ ወንጀል ክስ መቅረቡ ይታወሳል።

በተለይም አንደኛ ተከሳሽ በኮንትሮባንድ ወንጀል ክስ የቀረበበት ሲሆን÷ ሌሎቹ ማለትም ከ2ኛ እስከ 9ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተከሳሾች ላይ ደግሞ የፀና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖር በሀገር ውስጥ መኖር ወንጀል ክስ ቀርቧል።፡

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ ላይ የቀረበባቸው ተደራራቢ የወንጀል ክስን በችሎት እንዲደርሳቸው ተደርጓል ማንነታቸውም ተረጋግጧል።

ከ1 እስከ 6 ኛተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሽ ጠበቆች የአንደኛ ተከሳሽ የልብ ህመምተኛ መሆናቸውንና ቋሚ አድራሻ እንዳላቸው ጠቅሰው የዋስትና መብት እንዲፈቀድ ጠይቀዋል ነበር።

በተጨማሪም ከ2 እስከ 6ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ደንበኞቻቸውን በሚመለከት የቀረበባቸው ክስ ከ7 ዓመት በላይ የማያስቀጣ የወንጀል ድንጋጌ መከሰሳቸውን ጠቅሰው የዋስትና መብት ጥያቄ አንስተዋል።

በዐቃቤ ሕግ በኩል ደግሞ ተከሳሾቹ ከተከሰሱበት ተደራራቢ ክስ የቀረበባቸው እና ቋሚ አድራሻ የሌላቸው ከመሆኑ አንጻር ቢወጡ የዋስትና ግዴታቸውን አክብረው ሊቀርቡ አይችሉም ሲል በመቃወም ተከራክሯል።

የሰበር ሰሚ ችሎት ተደራራቢ ክሶችን በሚመለከት በልዩነት ዋስትናን ሊያስከለክል ስለሚችል ድንጋጌዎች በማብራራት በመከራከር ተጠርጣሪዎቹ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ጠይቋል።

ሌሎቹ ከ7ኛ እስከ9ኛ ተራ ቁጥር የተከሰሱ በኤሌክትሪክ ባለሙያ እና ሁለት እግር ኳስ ተጫዋች ነን ያሉ የላይቤሪያና የጊኒ ዜግነት ያላቸው ተከሳሾችን በሚመለከት በችሎት የተገኙ ጠበቃ ድጋፍ ለማድረግ በማስፈቀድ ተከሳሹ በቱሪስት ቪዛ ሀገር ውስጥ በገቡ በሁለት ሳምንታቸው በፀሐይ ሪል ስቴት በሄዱበት መያዛቸውን ጠቅሶ ቪዛና ፓስፖርት ያላቸው መሆናቸውን በማመላከት ከሀገር እንዳይወጡ እግድ ተጥሎ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጥያቄ ቀርቦ ክርክር ተደርጎበት ነበር።

የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ችሎቱ ተከሳሾቹ ላይ የቀረበው ተደራራቢ ከባድ ወንጀል መሆኑን ተከትሎ ቢወጡ ተመሳሳይ ድርጊት ላይ ሊሳተፉና ቋሚ አድራሻ ስለሌላቸው የዋስትና ግዴታቸውን አክብረው ላይቀርቡ ይችላሉ የሚለውን ግምት በመያዝና እንዲሁም ዋስትና ሊገደብ የሚችሉባቸው የሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀመጣቸው የድንጋጌ ነጥቦች በምክንያትነት በመጥቀስ የተከሳሾቹን ዋስትና ጥያቄ አለመቀበሉን አብራርቷል።

የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው ተከሳሾች ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ በማለት ከቀጠሮ በፊት የሚቀርብ የክስ መቃወሚያ አስተያየትና የዐቃቤ ሕግ መልስን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለህዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ – FBC


  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም ሆነ የተጠቀሱት አካላት ስለሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው መረጃዎች በአዎንታም ሆነ በአሉታ አልተነፈሱም። ነገሮችን በጥሞና የሚከታተሉ “ቴድሮስ ራሱ ወይም አግባብነት ያላቸው ሃቁን ለህዝብ ለምን አይናገሩም? ህዝብ ሲተራመስ ዝም የሚሉት ለምንድን… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማህበርን ዓመታዊ እራት ለመታደም ተሰብስበዋል። ከ2600 ባልይ እንግዶች ፊት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በክብር መድረኩ ላይ ተቀምጠዋል። ሴሽታው እየተጠበቀ ባለበት ሰዓት ድንገት አዳራሹን… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም ሳይቆዩ አሁን ወዳሉበት ደረጃ ደረሱ። የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምንት መፈረሙን ተከትሎ ያኮረፉት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፣ ሰሞኑን አሜሪካ መልሳ ልትዋዳጃቸው ማቀዷ ተሰምቷል። ዜናው መልካም ቢሆንም ኢሳያስ ግን አይቀበሉትም የሚል አስተያየት እየተሰጠ ነው።… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ አደጋ ጊዜ እርስ በርስ የሚረዱበትን አዲስ የጋራ መከላከያ ስምምነት ረቂቅ ለማዘጋጀት መስማማታቸውን አስታወቁ። በቆጵሮስ አስተናጋጅነት በተካሄደው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተወሰነው ይህ ውሳኔ፣ አውሮፓ በራሷ የመከላከያ አቅም ላይ እንድትተማመን ለማድረግ የታለመ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
    ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት” መሆኑን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። ምርመራው ቀጥሎ ማስተባበያው ሃሰት ከሆን የከፋ ቀጣት ይጠበቃቸዋል። ባለፉት ጥቂት ወራት የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ የኢልሀን ኦማር እና የባለቤታቸው ቲም ማይኔት ሀብት ከ51,000 ዶላር ወደ 30 ሚሊዮን ዶላር… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
lawNEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

የኤርትራን መንግስት “እጥላለሁ” የሚል የወጣቶች እንቅስቃሴ በይፋ በትግራይ አዲግራት ተመሰረተ፤ ከመንግስት በኩል የተባለ ነገር የለም
“ከምክክር ውጪ ሌላ መፍትሔ እንደሌለ ሕዝቡ አምኗል… የታጠቁ ሃይሎችን ለማምጣት ጥረት እያደረግን ነው” ኮሚሽነር ሒሩት
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news