Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Western Pressure on Ethiopia Intended to See Weak Gov’t, Nation – Scholars

    July 10, 20210

    Journalist demands UNWFP to tell truth about missing trucks

    October 3, 20210

    ብርሃኑ ባይህ እና አዲስ ተድላ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ

    December 19, 20200

    አብንና ባልደራስ ከተሸነፉ ” ውጤቱን አንቀበልም” ሊሉ የሚችሉ ፓርቲዎች እንደሚሆኑ ዲፕሎማቶች ገለጹ

    May 23, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሚስጥራዊ የቻይና ፖሊስ ጣቢያዎች በአሜሪካ ተገኙ

    December 19, 20240

    ሦስተኛው ዕድል እንዳይባክን … !

    May 21, 20220

    “Why I decided to extend my time at the club”

    May 24, 20230

    የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ዋና የጦሩ መሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ

    February 24, 20220

    “Ethiopia’s success reflects a new alternative for Africa’s development”

    January 29, 20240
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  TIPS 1  የግፍ ጎርፍ ራስን ይወስዳል! የግፍ እሳት ራስንም ያቃጥላል
TIPS 1

የግፍ ጎርፍ ራስን ይወስዳል! የግፍ እሳት ራስንም ያቃጥላል

Ethioreview newsEthioreview news—September 2, 20240
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ከአዘነ ጋር የሚያዝኑት፣ እናት የሌላቸውን ሕጻናት አጥብተው የሚያሳድጉት፣ የጎረቤት ልጅ እንደ ራስ ልጅ የሚቀጡት፣  ሕግና ሥርዓት የሚያስተምሩት፣  ከልጅ ልጅ ቢለዩ ዓመትም አይቆዩ እያሉ የሚናገሩት የት ገቡ?  ለሕጻናት የሚያዝኑ አንጀቶች፣ ለሕጻናት የሚንሰፈሰፉ ሆዶች፣ ለሕጻናት የሚራሩ ልቦች  ምን አስቆረጣቸው ? ምንስ አስጨከናቸው?

የት እየሄድን ነው?  በሕጻናት ላይ መጨከን እንደምን ያለ ጭካኔ ነው? ሕጻናትን መግደልስ እንደምን ያለ አገዳደል ነው?  እንባቸው አያሳዝንምን? ዋይታቸው አያንሰፈስፍምን? ለቅሷቸው አንጀት አይበላምን?  ኮልታፋ አንደበታቸው የጨካኝን ልብ አያራራምን? ፍቅራቸው ጥላቻን አያርቅምን? የልጅነት ወዛቸው ከክፋት አይመልስምን? ያልጠናው ገላቸው ልብ አይነካምን?  ስለ ምን ተጨከነባቸው? ስለ ምንስ ተቆረጠባቸው?

ዓይን እንዳይበዛቸው ሸፍኗቸው፣ በሰው ፊት አትግለጧቸው፣ በምሽት ከቤት አታውጧቸው እየተባሉ ጥንቃቄ የሚበዛላቸውን፣ አብዝቶ የሚሳሳላቸውን ሕጻናትን ለመግደል እንደምን ተቻላችሁ? እንደምንስ ኾነላችሁ?  ጭካኔውንስ ከየት አገኛችሁት?

ኢትዮጵያውያን እንደዚህ አስተምረዋልን? ኢትዮጵያን እንኳን ለሰው ልጅ ለአዕዋፋት ልጆች የሚያዝኑ፣  እናት  የሞተችባትን የፍየል ግልገል ወተት አጠጥተው የሚያሳድጉ አይደሉምን? ከየት መጣችሁ? ማንስ ይሄን የጭካኔ ሀሳብ በልባችሁ ጻፈላችሁ? የአጨካከንም ልክ አለው፤  የአገዳደልም ወግ አለው እኮ።

በማሕጸኗ የተሸከመች፣ አምጣ የወለደች፣ በጀርባዋ ያዘለች፣ እየተራበች ያጎረሰች፣ እየተጠማች ያጠጣች፣ እየታረዘች ያለበሰች፣ እንቅልፍ አጥታ ለልጇ የኖረች እናት አታሳዝንምን? ለልጆቹ ሲል በችግር የሚኖር፣ ሀዘኑን በልጆቹ ደስታ የሚረሳ፣ ለእነርሱ ሲል ዓለሙን የተወ አባትስ አያሳስብምን?  አምላክ ለዘር እንዲያበቃቸው የተማጸኑ ወላጆች አያሳዝኑምን?

እንደዚህ መክፋትስ ለማን ይበጃል?  የዘሩትን ማጨድ፣ በሰፈሩት ቁና መሠፈር አይመጣምን? በራስ እንዲኾን ያልፈለጉትን በሰዎች ላይ ማድረግስ የተገባ ነውን ?  ከሚደሰቱት ጋር ተደሰቱ፣ ከሚያዝኑትም ጋር እዘኑ እየተባለ በሚሰበክባት ሀገር፣ ደግነት እንደ ምንጭ ውኃ ሲፈስስባት በኖረች ምድር እንደዚህ ማድረግ ጤነኝነት ነውን ? የግፍ ጎርፍ እኮ ራስንም ይወስዳል። የግፍ እሳት እኮ ራስንም ያቃጥላል።  ለሰው የተቆፈረ መቃብር እኮ ለራስም ይኾናል። በግፍ የፈሰሰ ደም እኮ በምድርም በሰማይም ይጮሃል።  ለምሕረት የተጠበቀው ሰማይ እኮ ለማዕት የታዘዘ መከራ ያወርዳል።

የሕጻን ሄቨን ለቅሶ እና ሀዘን ሳይጠፋ፣ የፈሰሱ እንባዎች ሳይታበሱ፣  ያጠላው የድንጋጤ ድባብ ሳይገፈፍ  ሌላ አሳዛኝ ድርጊት ተፈጽሟል። ለወትሮው  ከሀዘን ማግስት ሀዘን የሚያስረሳ ተድላና ደስታ ይሰማ ነበር። ዛሬ ግን ሌላ መከራ፣ ሌላ ሀዘን፣ ሌላ እምባ፣ ሌላ አንጀት የሚቆርጥ መርዶ ተሰምቷል።

ኖላዊት ዘገዬ የተባለች ሕጻን በጎንደር በአጋቾቿ ተገድላ ኑ ሬሳችሁን አንሱ የሚል መርዶ መጥቷል። ከጡት ያልተለየች ሕጻን በአጋቾች ተወስዳ፣ በረሃብ እና በናፍቆት አልቅሳ በመጨረሻም በጨካኝ እጆች ላትመለስ አልፋለች። የወላጆቿን አንጀት ቆርጣ ያለ በደሏ  አሸልባለች። ከሀዘኑም የከፋው ሀዘን ደግሞ ሕጻን ኖላዊት ከእገታ እንድትላቀቅ ብር ተጠይቆባት ነበር። ወላጆችም  ልጃቸውን ለማስለቀቅ  ብሩን ከፍለው ነበር። ዳሩ ግን ልጃቸውን አላገኟትም። በሕይወት አልተመሰለችም። ሬሳቸው ተላከላቸው እንጂ።

ብሩን ተቀብለው ሕጻኗን ገደሏት።  ከበደልም የከፋው  በደል ተፈጽሟል። ሕጻን እያስለቀሳችሁ ከዚያም ጨክናችሁ ገድላችሁ በተቀበላችሁት ገንዘብ ልታጌጡበት ነውን?  ወይንስ ልጅ ልታሰድጉበት ነው? ግፍ አይደርሳበችሁምን?

የዚያች ታሪካዊት እና ቀደምት ከተማ ጎንደር  ነዋሪዎች፣ ደጋጎቹ  አዝነዋል። ከማንነታቸው፣ ባሕላቸው እና ከልካቸው የወጣ ክፉ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋልና አንብተዋል። እነርሱ የሚያውቁት ታላቅን ማክበር፣ ታናሽን እየወደዱ ማሳደግ እንጂ እንዲህ አይደለምና። በቀያቸው ተደርጎ የማይታወቅ ነገር ተደርጎባቸዋልና።  እነርሱ የሚያውቁት ያዘነን ማጽናናት ነውና እያዘኑ ነው።

እሺ ሕዝብ እትብቱ ከተቀበረበት፣  ተወልዶ ካደገበት፣ አግብቶ ወግ ማዕረግ ካየበት፣ ምድር ርቆ የት ይሂድላችሁ ? ምን ያድርግላችሁ ? ስለ ምን መከራውን ታበዙበታላችሁ ? ስለምንስ ስቃዩን ታጸኑበታላችሁ? ለምን በሰላም እንዲኖር አትተዉትም? ለምን በቆየው በባሕሉና እሴቱ እንዲኖር አትፈቅዱለትም? መከራው በዛ እኮ። ሰቃዩ በረታበት እኮ። መሳቀቅ ይበቃዋል። የጥይት ድምጽ ሰልችቶታል። እያነሱ መቅበር መርሮታል።

በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ግፍና በደል እንደቦይ ውኃ እየፈሰሰ ነው። በየቀኑ ንጹሐን ይታገታሉ፣ ለፍቶ አዳሪዎች ይታፈናሉ። በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ይጠየቃሉ። መክፈል የሚችሉ ጥሪታቸውን ሰጥተው ይለቀቃሉ። መክፈል የማይችሉ ደግሞ በአጋቾች አፈሙዝ ተበልተው የወገን ጸጸት ኾነው ይቀራሉ። ሕጻን ኖላዊትም የኾነችው እንዲሁ ነው።

ግፍና እንግልቱ ሊገልጹት፣ ሊናገሩት፣ ሊጽፉትና ሊተርኩት  ከሚችሉት በላይ ኾኗል። በሕጻን ሄቨን እንዲያቆም የታሰበው ግድያ በሕጻን ኖላዊት ቀጥሏል። እኒያ መልካም እሴቶች ካልተመለሱ፣ ነውር የሚፈጽሙት፣ ግፍን የሚያደርጉት ካልተወገዙ፣ ከሰው ካልተለዩ ነገም ላለመቀጠሉ ዋስትና የለም።

ግን የት እየሄድን ነው? መድረሻችንስ የት ነው? ግባችንስ ምንድን ነው? ስንት ሕጻናት ሲሞቱ ነው የሚቆጨን ? ስንት ንጹሐን ሲያልቁ ነው የሚያንገበግበን ? መቼ ነው በቃ የምንለው ? ዛሬ ከንፈር መጥጠው ቢያሳልፉት ነገ በየቤቱ ይደርሳል። ዛሬ እንደዋዛ ዝም ቢሉት አንዳንድ እያለ ሁሉንም ይወስዳል። ሁሉም ከመወሰዱ፣ ግፈኞች በንጹሐን ላይ ከመሠልጠናቸው አስቀድሞ በአንድነት፣ በኅብረት እና በቁርጠኝነት በቃን ብሎ መነሳት፣ በጋራም ሰላምን መጠበቅ ግድ ይላል። ያ ካልኾነ ግን  ከንፈር መምጠጡ ይቀጥላል። ሞቱም እንደዚያው ይኾናል።
አሚኮ

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

“የኢትዮጵያን ህልውና የሚበይኑት የተፈጥሮ ሀብቶች…”
ግብጽ 5ኛውን ሙሌት ተከትሎ ለጸጥታው ምክር ቤት ሮሮ አሰማች
Related posts
  • Related posts
  • More from author
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 20250
TIPS 1

Almost a third of people in Gaza not eating for days, UN food programme warns

July 26, 20250
TIPS 1

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios

July 20, 20250
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news