ተመድ፣ በአማራ ክልል የምግብ ሥርጭትን ጨምሮ የረድዔት ሥራዎቹን ለጊዜው ሊያቆም መኾኑን ከአንድ የድርጅቱ ሚስጢራዊ ሰነድ ላይ መመልከቱን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
ድርጅቱ የረድኤት ሥራውን ለማቆም ያሰበው፣ በክልሉ ውስጥ በረድዔት ሠራተኞች ላይ ጥቃቶች መደጋገማቸውን ተከትሎ እንደኾነ ሰነዱ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል።
ካለፈው ዓመት ጥር እስከ ነሃሴ ድረስ 5 የዕርዳታ ሠራተኞች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለው፣ አስሩ እንደቆሰሉና 11 እንደታገቱ ሰነዱ ያመለክታል ተብሏል።
በርካታ ለጋሾችና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች ግን፣ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሕዝብ ለአደጋ ይጋለጣል በማለት የድርጅቱን ሃሳብ እንደተቃወሙት ሮይተርስ ጨምሮ ዘግቧል።
በሌላ ዜና የኢትዮጵያ እና ኤርትራ የስልክ ግንኙነት መቋረጡ ተሰማ!
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ ጠ.ሚ አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት 2010 ዓ.ም ጀምሮ ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት መልካም ግንኙነት የስልክ፣ የትራንስፖርት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በእጅጉ ተሻሽሎ እንደነበር ይታወቃል፡፡
የኤርትራ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የመስራት እና የመኖር ከዘመዶቻቸው ጋር ለመገናኘት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የስልክ አገልግሎት ክፍት ሆነው እስከ ቅርብ ወራቶች አገልግሎት አግኝተዋል፡፡
ይሁንና በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ቅር የተሰኘው የኤርትራ መንግስት ግንኙነቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መጥቶ ባሳለፍነው ወር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን ጉዞ አቋርጧል፡፡
ኤርትራም ከኢትዮጵያ ጥቅም በተቃራኒው ከቆሙ እንደ ግብጽ ያሉ አገሮችን ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ በሶማሊያ ጉዳይ አስተያየቶችን በመስጠት የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በእጅጉ እያሽቆለቆለ መጥቷል፡፡
በቅርቡ የመከላከያ ሰራዊት ኢታማጆር ሹም ብረሃኑ ጁላ የኤርትራን ሰራዊት በትግራይ ጦርነት ወቅት ፈጥሞታል ያሉትን ማስታወቃቸው ይታወሳል
ሰሞኑን ደግሞ ኤርትራንና የኢትዮጵያ የሚያገኛኘው የስልክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የኤርትራ ስደተኞች ተናግረዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸውን በስልክ ይገኛኙ እንደነበር ገልጸው ሰሞኑን ግን የስልክ አገልግሎት መቋረጡን ተናግረዋል በሚል የተለያዩ ወገኖች እየዘገቡ ነው::


