Skip to content
  Wednesday 10 June 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የትግራይ ህዝብ የሰላም፣የህልውናው እና ደህንነቱ ዘብ እራሱ ህዝቡ ነው -ዶ/ር አብርሃም በላይ

    May 29, 20210

    በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው አሸባሪ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እርምጃ ተወሰደበት

    September 4, 20210

    Ethiopian Envoy Briefs Sudan Based Media On GERD

    July 4, 20210

    በአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በመሞከርና በምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት የተከሰሱ ተቀጡ

    June 21, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1875
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ልጆቻቸው መቀለ ዩኒቨርስቲ የቀሩባቸው ወላጆች የተመድ ፊት እያነቡ ነው “ልጆቻችንን አስለቅቁልን”

    July 23, 20210

    መከላከያ በኦሮሚያና አማራ ክልል የማጽዳት ስራ እንደቀረው አስታወቀ፤ አማራ ክልል መዋቅሩን እያጠራ ነው፤

    September 1, 20230

    “ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ ወቅታዊና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ችግሮች ለመፍታት አስቸጋሪ ነው”

    April 17, 20210

    “በተለመደው አሰራር ማስቀጠል የምንችለው ድህነትን ብቻ ነው” ሽመልስ አብዲሳ

    June 3, 20220

    “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች?”

    March 9, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1500
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይቲስት –
NewsSOCIETY

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሳይቲስት –

Ethioreview newsEthioreview news—February 24, 20210
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ፕሮፌሰር ሶስና ሀይሌ ይባላሉ።የቁስ ሳይንስና የምህንድስና ሊቅ ሲሆኑ፤የመጀመሪያውን የጠጣር አሲድ ነዳጅ ለዓለም ያስተዋወቁ ሳይንቲስት ናቸው።ከዚህ በተጨማሪ በዘርፉ ከ200 በላይ የምርምር ፅሁፎችን አሳትመው በ14ቱ የባለቤትነት መብት አግኝተዋል።ለነዚህ ስራዎቻቸውም በርካታ ሽልማቶችን አግኝተዋል።የዛሬው የሳይንስና ቴክኖሎጅ ዝግጅት እኝህን ሳይንቲስት ያስተዋውቃል።
ፕሮፌሰር ሶስና  ሀይሌ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ አሜሪካዊ የቁስ ሳይንስና የምህንድስና ሊቅ ናቸው። ያም ሆኖ ስኬታቸው አልጋ በአልጋ አልነበረም።በኢትዮጵያ በ1966 ዓ/ም በነበረው አብዮት አባታቸው እውቁ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ የደርግን መንግስት በመቃወማቸው የጥቃት ሰለቫ በመሆን ክፉኛ ቆስለው ለህክምና ከነ ቤተሰባቸው ሀገር ለቀው ሲወጡ ፕሮፈሰር ሶስና ገና የ10 ዓመት ልጅ ነበሩ።የአባታቸው ክፉኛ መጎዳትና የዕድሜ ልክ የአካል ጉዳተኛ መሆን የመጡበት ሀገር የተለየ ባህል፣ ቋንቋና የቀለም ልዩነት በዚያ በልጅነት  ዕድሚያቸው የተጋፈጡት አሁንም ድረስ የሚያስታውሱት ፈተና ነበር። 
«እውነት ለመናገር ልጆች የበለጠ ችግርን ይቋቋማሉ  ብዬ አስባለሁ። አላውቅም። ማለቴ  ተቋቋምነው።በእርግጥ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነበር።ነገር ግን ለወላጆቼ የበለጠ ከባድ ጊዜ ነበር ብዬ አስባለሁ። በጣም በልጅነት ዕድሜዬ ነው  ዩኤስ መኖር የጀመርኩት።ትንሽ ትንሽ አስታውሳለሁ።ብዙ አስፈሪ አልነበረም ።ነገር ግን በጣም እንግዳ ነገር ነበር።ኢትዮጵያ የት እንደምትገኝ የሚያውቅ የለም።ትምርት ቤት መስራት ይችላሉ ብለው አይጠብቁም።ወደ መካከለኛ ክፍል ይወስዱናል።ግን ተቋቋምነው።አሰቃቂ የሆነብኝ የሀገርና የማኅበረሰቡ ፍራቻ ሳይሆን በአባቴ ላይ የደረሰው ነው።»

ISEN on Twitter: "ICYMI: Meet Prof. Sossina Haile of @NorthwesternEng, our  new Co-Director: https://t.co/gmMd7trKpL #womeninSTEM… "
professor sossina haile


ይህንን ፈተና ተቋቁመው ግን ፕሮፌሰር ሶስና  በቁሳዊ ሳይንስና በምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን  ከአሜሪካው የማሳቹሴት የቴክኖሎጅ  ዩንቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በጎርጎሪያኑ 1988 ከካሊፎርኒያ በርክሌይ ዩንቨርሲቲ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በ1992 ከማሳቹሴት ዩንቨርሲቲ በተመሳሳይ የትምህርት መስክ አግኝተዋል። 
 በንድፈ ሀሳብ የቀሰሙትን ዕውቀት ወደተግባር ለመለወጥም በታዳሽና በዘላቂ የሀይል አቅርቦት ቴክኖሎጂ ዘርፍ በርካታ ምርምሮችን አድርገዋል።በጎርጎሪያኑ  1990ዎቹ መገባደጃ ላይም «ሱፐር ፕሮቶኒክ» የተባለ አዲስ ውህድ በመጠቀም የመጀመሪያውን ጠጣር የአሲድ ነዳጅ  በእንግሊዝኛው አጠራር  «ሶሊድ አሲድ ፊውል ሴል»በመፍጠር ለዓለም አስተዋውቀዋል።እሳቸው እንደሚሉት ፈጠራው ከሀይል አማራጭነቱ በተጨማሪ የአካባቢ ብክለትን የሚከላከል ጭምር ነው።
«የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጫ መንገድ ነው።ስለዚህ በኢንዱስትሪ በበለፀገው ዓለም የቅሪተ አካል ነዳጅን እንጠቀማለን።ፔትሮሌምን፣ ዘይትን የድንጋይ ከሰልን፣ ፣የተፈጥሮ ጋዝ እና ነዳጅ

DW Sendung Eco Afrika Burkina Faso

እንጠቀማለን። እኔ የፈጠርኩት ግን መኪናዎች ከሚጠቀሙት ተለምዷዊ ሞተር ጋር ሲነፃፀር በጣም ንፁህ በሆነ መንገድ የኤሌክትሪክ ኃይልን ማመንጨት የሚችል ነው።

መኪና የሚንቀሳቀሰው ውስጡ ያለውን ነዳጅ በማቃጠል ነው። ይህ ሂደት ብዙ ብክለትን ያስከትላል። ስለዚህ  ጠጣር ነዳጁ  ኤሌክትሪክ  እንዲያመርት በማድረግ በተለየ መንገድ የመጠቀም ዘዴ ነው ።ያም  በአከባቢ ጥበቃ ረገድ የበለጠ ዘላቂ ነው።»  
ፈጠራው በመላው ዓለም እየጨመረ የመጣውን የኤለክትሪክ ሀይል ፍላጎት ለማሟላት አስፈላጊ ሲሆን፤፤እንደ ኢትዮጵያ ታንዛኒያና ዩጋንዳ ላሉ ብዙ የፀሐይ ብርሃንና  የውሃ ኃይል  ላላቸው የምስራቅ አፍሪቃ  ሀገራት የኤለክትሪክ ሀይል አቅርቦትን ለማሻሻል የሚያስፈልገው፤የተሻለ የኤሌክትሪክ ፍርግርግ  ወይም ደግሞ የሀይል ማከማቻ ቢሆንም፤  በተለያዬ ሁኔታ የውሃ መቀነስ ቢያጋጥም፤እሳቸው የፈጠሩት የሀይል አማራጭ  እንደ ባትሪ ሊያገለግል እንደሚችልም ያስረዳሉ።
«እውነት ለመናገር ያለው  የውሃና የፀሀይ ሀይል አቅም የሀይል ፍላጎትን ለማሟላት በቂ  ነው።የሚያስፈልገው የሀይል ማከማቻ ነው። በተለይ ለፀሀይ ሀይል።የውሃ ሀይልም ቢሆን የተወሰኑ ዓመታት ዝናብ ሊኖር  የተወሰኑ ዓመታት ደግሞ ዝናብ ሊጠፋ ስለሚችል፤የረዥም ጊዜ ማከማቻ ያስፈልጋል።ስለዚህ በቤተሙከራ የሰራናቸው መሳሪያዎች የነዳጅ ህዋሶች ልክ እንደ ባትሪ ሊሰሩ ይችላሉ።ለአስፈላጊ  ጊዜ ሀይልን ያከማቻሉ።ያለ ብዙ ቴክኒካዊ ስራ የሀይድሮጅን ነዳጅ የመፍጠር አቅም አላቸው።ከዚያም የሀይድሮጅን ነዳጅ በመጠቀም ኤለክትሪክ ማምረት ይቻላል።» 
ሳይንቲስቷ ከጎርጎሪያኑ 1993 ጀምሮ በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ በረዳት ፕሮፌሰርነት፣ከ1996 ጀምሮ  በካሊፎርኒያ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት  የቁሳቁስ ሳይንስ ፕሮፌሰር በመሆን ለ 18 ዓመታት ያገለገለገሉ ሲሆን፤ በ2012 ዓ/ም በኢንጂነሪንግ እና በተግባራዊ ሳይንስ ክፍል ውስጥ ሊቀመንበር ሆነው ከተሾሙ ሁለት የመጀመሪያ ሴቶች አንዷ ናቸው። ከ 2015 ዓ/ም  ወዲህ ደግሞ በችካጎ በኖርዝ ዌስት  ዩኒቨርስቲ  በማስተማር ላይ ይገኛሉ።

More stories

“የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ፣ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ”

September 24, 2023

«ለአንድ ደቂቃ በያለንበት ቆመን ለኢትዮጵያ አምላክ ምስጋና እንድናቀርብ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ»

July 27, 2022

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮንትሮባንዲስቶች፣ የወንጀሉ ተባባሪ የኮሚሽኑ ሰራተኞችን እና የፖሊስ አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

April 5, 2021

ኤርትራዊያንን ጨምሮ የሌላ አገር ዜግነት ያላቸው ዶላር አጣቢዎችና አጭበርባሪዎች ተያዙ

August 7, 2022

«አባቴ 88 ዓመቱ  ነው።ግን ሁል ጊዜም  ይሰራል። ምክንያቱም ሊሰሩ የሚገባቸው ብዙ ህትመቶች እንዳሉ ያውቃል። ሊፃፍ የሚችል  ብዙ ታሪክ አለ። ሊሰራ የሚችል ብዙ  ነገር አለ።ስራ አያልቅም። እናም ለውጥ ማምጣት የምትችል ሰው ሆኖ ከተሰማህ በትክክል መቀዛቀዝ አትፈልግም።»

ከዚህ የማስተማር ስራቸው በተጨማሪ በፈጣን ባትሪዎች ፣መፈተሻዎች ወይም «ሴንሰሮች» የኤለክትሪክ ፓምፖች  እና ጠጣር የአሲድ ነዳጅ ላይ፣ «ቴርሞኤሌክትሪክ» እና «ፌሮኤሌክትሪክ»በተባሉ ሙቀትና ብረት ነክ  ኤለክትሪካዊ ቁሶች ላይ፣  እንዲሁም ለአነስተኛና ተንቀሳቃሽ  የሀይል ማመንጫዎች በሚሆኑ የመሣሪዎች  ላይ ምርምር ያደርጋሉ።አነስተኛ ዋጋ ባላቸው ግብዓቶች ላይ እሴት በመጨመር ወደ ምርት እንዲለወጥም ይሰራሉ። እነዚህ ስራዎቻቸው የሀይል አቅርቦትና አማራጭ መስክ ወደ አዳዲስ ግንዛቤ እና አፈፃፀም  እንዲሄድ አድርጓል።ከዚህ በተጨማሪ የፕሮፌሰር ሶስና ስራዎች በዓለም ላይ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማርካት ነፋስንና የፀሐይ ብርሃንን በመጠቀም ረገድ አዳዲስ መንገዶችን ፈጥረዋል።ፕሮፌሰሯ በመስኩ ከ200  በላይ የምርምር ፅሁፎችን ያሳተሙ ሲሆን፤በ14ቱ  የባለቤትነት መብቶችን ይዘዋል ፡፡
በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ ዕድል ላላገኙ  የማህበረሰብ ክፍሎች በሳይንስ ዘርፍ የትምህርት እና የምርምር እድሎችን እንዲያገኙ በማድረግ ንቁ ተሳታፊ ናቸው።ከዚህ አኳያ   በሳይንሱ ዘርፍ የሴቶች ተሳትፎ  ዝቅተኛ መሆን ዓለምን ብዙ አሳጥቷል ይላሉ።
  «ዓለም በቀላሉ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ብዙ ነገሮች አሉ።ነገር ግን በዚህ አስፈላጊ ጥረት ውስጥ ግማሹን የዓለም ህዝብ አለማካተት  በጣም ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ያሳጣል።ለሴቶች ለራሳቸውም ይህ አስደሳች ሙያ ነው።አስፈላጊ ግንቶችን መስራት ዓለምን የመለወጥ ተፅዕኖ አለው። ስለዚህ ማንንም መከልከል ተገቢ አይደለም። እኔ ለሴቶች የምመክረው ሞክሩት ትወዱታላችሁ። ሌሎች አትችሉም እንዲሏችሁ አትፍቀዱ።እኔ ሁል ጊዜ በሆነ መንገድ አንዳንድ አስተማሪዎች የሆነ ነገር መስራት እንደማልችል ሲያስቡ፤ ያ በጣም ነው የሚያስደስተኝ።ምክንያቱም እነሱ የተሳሳቱ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በጣም  በርተቼ ነው የምሰራው።» 
በሙከራና በንድፈ-ሃሳባዊ ምርምር አማካኝነት መሰረታዊ የሳይንስ ዕውቀትን በማስጨበጥ ለሙያው ላባረከቱት አስተዋፅኦ በርካታ ሽልማቶችን አግኝተዋል።ከነዚህም ጥቂቶቹ  በሳይንሱ ዘርፍ ለሰው ልጆች ህይወት መሻሻል ላበረከቱት አስታዋፅኦ ካገኙት የሰብአዊነት ሽልማት ጨምሮ፤ በጎርጎሪያኑ 1994 የብሔራዊ ሳይንስ ፋውንዴሽን ብሔራዊ የወጣት ተመራማሪ ሽልማትን፣በ1997 ቲ ኤም ኤስ ሮበርት ላንሲግ ሃርዲ ሽልማትን፣በ2000 ዓ/ም ከአሜሪካ የሴራሚክ ማኅበረሰብ ሽልማትን፣ በ2001 ዓ/ም የጄ.ቢ.ዋግነር ሽልማት ከኤለክትሮ ሜካኒካል ማኅበረሰብ  ተሸልመዋል። በማስተማርና በማማከር ስራ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የቁስ ሳይንስና የምህንድስና የሳይንስ ሊቃውንት በአሜሪካዊ የቁስ ሳይንስ  ሊቅ ዴቪድ ተርንቡል ስም በሚሰጠው ሽልማትም የ2020 ተሸላሚ ናቸው።
የዓለም አቀፍ የቁስ ሳይንስ ምርምር ማህበረሰብ፣የአፍሪካ እንዲሁም  የኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ ባልደረባም ናቸው።ፕሮፌሰር ሶስና ሀይሌ በርትቶ በመስራት የሚያምኑ ሳይንቲስት፣ እናት፣አማካሪና መምህር  ሲሆኑ፤ የወላጆቻቸው ትልቅ ድጋፍ  የስኬታቸው  ቁልፍ  መሆኑን ይገልፃሉ።ስኬትና ስራ መጨረሻ የለውም የሚሉት ፕሮፌሰር ሶስና፤ለወደፊትም  ይህንኑ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ይገልፃሉ።
«አባቴ 88 ዓመቱ  ነው።ግን ሁል ጊዜም  ይሰራል። ምክንያቱም ሊሰሩ የሚገባቸው ብዙ ህትመቶች እንዳሉ ያውቃል። ሊፃፍ የሚችል  ብዙ ታሪክ አለ። ሊሰራ የሚችል ብዙ  ነገር አለ።ስራ አያልቅም። እናም ለውጥ ማምጣት የምትችል ሰው ሆኖ ከተሰማህ በትክክል መቀዛቀዝ አትፈልግም።»ብዙ የሚከናወኑ ነገሮች አሉ።  እናም እንዳልኩት ይህንን ችግር የመፍታት አቅም እንዳለህ ከተሰማህ ፣ያንን ፍጥነት መቀነስ በእውነቱ መልካም አይደለም።ቤተሙከራዬ  ውስጥ  አነስተኛ ጅምር  ስራ  አለኝ። አሁንም እውነተኛ ቴክኖሎጂን ለመስራት እየሞከርን ነው። ከዩኒቨርሲቲ  ትምህርት እና  በምርምር ደረጃ  ከምንሰራው በተጨማሪ ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ የተወሰኑት በእውነተኛው ዓለም ለውጥ እንደሚያመጡ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ »

ፀሀይ ጫኔ  ሒሩት መለሰ dw amharic


  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups
    by VOE
    June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV
    by VOE
    June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”
    by VOE
    June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ
    by VOE
    June 7, 2026
  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups
    by VOE
    June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV
    by VOE
    June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”
    by VOE
    June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ
    by VOE
    June 7, 2026
NEWSSOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

የኢትዮጵያ አዲሱ የኢኮኖሚ ከተማ ግንባታ
መንግሥት ቢቢሲ እና ሮይተርስን ጨምሮ – ሰባት ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ትግራይ ክልል ገብተው እንዲዘግቡ ተፈቀደ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
News

ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

June 5, 20260
News

ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው?

June 3, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
TOP NEWS

ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups

June 7, 20260
TOP NEWS

Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV

June 7, 20260
AFRICA

Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»

June 7, 20260
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
Load more
Recent Posts
  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science” June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ June 7, 2026
  • ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ» June 7, 2026
  • ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ” June 6, 2026
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ June 5, 2026
  • Agricultural Sovereignty, Economic Transformation, and the Defiance of Extremism Ahead of the 7th National Election June 5, 2026
  • የዘለንስኪ ጥሪ፦ “ጦርነቱን ለማቆም ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ዝግጁ ነኝ” June 5, 2026
  • የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አደነቀ June 5, 2026
  • The Inverted Frontlines: How Secret Alliances and the Western Tigray Fault Line Threaten to Reignite Ethiopia June 4, 2026
  • Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia June 4, 2026
  • ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው? June 3, 2026
  • International Partner Welcomes Ethiopia’s 7th General Election, Calls for Inclusive Voting in Remaining Constituencies June 3, 2026
  • ዓለም አቀፍ አጋሮች የኢትዮጵያን 7ኛ አጠቃላይ ምርጫ በበጎ ተቀበሉ፤ June 3, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news