Skip to content
  Wednesday 10 June 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የትግራይ ህዝብ የሰላም፣የህልውናው እና ደህንነቱ ዘብ እራሱ ህዝቡ ነው -ዶ/ር አብርሃም በላይ

    May 29, 20210

    በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው አሸባሪ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እርምጃ ተወሰደበት

    September 4, 20210

    Ethiopian Envoy Briefs Sudan Based Media On GERD

    July 4, 20210

    በአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በመሞከርና በምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት የተከሰሱ ተቀጡ

    June 21, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1875
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ልጆቻቸው መቀለ ዩኒቨርስቲ የቀሩባቸው ወላጆች የተመድ ፊት እያነቡ ነው “ልጆቻችንን አስለቅቁልን”

    July 23, 20210

    መከላከያ በኦሮሚያና አማራ ክልል የማጽዳት ስራ እንደቀረው አስታወቀ፤ አማራ ክልል መዋቅሩን እያጠራ ነው፤

    September 1, 20230

    “ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ ወቅታዊና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ችግሮች ለመፍታት አስቸጋሪ ነው”

    April 17, 20210

    “በተለመደው አሰራር ማስቀጠል የምንችለው ድህነትን ብቻ ነው” ሽመልስ አብዲሳ

    June 3, 20220

    “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች?”

    March 9, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1500
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው?
NewsOPINION

ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው?

VOEVOE—June 3, 20260
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጃዋር “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምን ወለጋ ሄዱ? የዘር ጭፍጭፍ የፈጠራል” ባለበት ሰሞን በምስራቅ ሃረርጌ ጎረጉቱና መሰላ / እሱ ከተወለደበት አካባቢና ከአርሲ የሚዋሰኑ ቦታዎች ናቸው/ የሚነሳ ታጣቂ ኃይል በቅርቡ አካባቢውን እንደሚቆጣጠር ተናግሮ ነበር። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአርሲ አቅጣጫ እስከ መሰላ የሚነቀሳቀሰው ኃይል በጃዋር የሚደግፈና የሚረዳ ነው። ጃዋር ተሽቀዳድሞ በፌስ ቡክ ገጹ “እንቀነጥሳችኋለን” ለሚላቸው ክርስቲያኖች ተቆርቋሪ የሆነበት ሚስጢርም ይህ ነው። ወደፊት በመረጃ ተደግፎ የሚወጣ ይሆናል። 

ነጻ አስተያየት በሰለሞን ግርማ አዲስ አበባ

“ባለኝ የጎንዮሽ ግንኙነት የአርሲውን ግድያ ከሰማሁ በኋላ ይህ ጉዳይ ተደጋገመ። ገዳዮቹ እየታወቁ ለምን በገሃድ አይወገዙም? አዲስ አበባ ቢሮ ያላቸው ከእነዚሁ ከሚታወቁት ታጣቂዎች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ወይም አብረው የነበሩ ስለምን ዝም ይላሉ? ግድያውን አስመልክቶ መግለጫ የሚያወጡትና አካላት ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ ገዳዮቹን የሰላባው ቤተሰቦች ስለሚያውቁ ለምን ይፋ አያደርጉም? የሚለውን ጥያቄ ሳነሳ መልስ የሚሰጠኝ አጣሁ። የመንግስት አካላትም በተለይም ኦሮሚያ ክልልና የአካባቢው አስተዳደር ዝምታ ሊገባኝ አልቻለም” በማለት ያጫወቱኝ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ቅርብ የሆኑ አባት አገልጋይ ናቸው። የሳቸው ጥያቄና ስጋት የእኔም ነው። 

ግንቦት 23 እና ግንቦት 24 በነበረው ጥቃት ከክርስቲያኖች በተጨማሪ  ከአድማ በታኝ፣ ከሚሊሻ እንዲሁም ሙስሊም  የአካበቢው ነዋሪዎች ተገድለዋል። ግድያው የተፈጸመው በኦነግ ሸኔ መሆኑን ሰላባዎች አስታውቀዋል። ጃዋር መሃመድ በበኩሉ መንግስት ግድያውን እንደፈጸመ በብርሃን ፍጥነት “የክርድቲያኖች ተቆርቋሪ ነኝ” ብሎ አስታውቋል። ገዳይን ሳይሆን የንጹሃንን ሞት በማጉላት የአዞ እንባ የሚያነቡ ጉዳዩን የፖለቲካ አጀንዳቸው ማስፈጸሚያ አድርገውታል። ጃዋር ሜንጫውን ጥሎ በዘረጋው ድንኳን ውስጥ ገብተው የሚጮሁ ነፈዞችም በንጹሃን ሞት ጀርባ በሚሰራ ድራማ እየተንቦጫረቁ ነው። በተደጋጋሚ ንጹሃን የሚገደሉባት አርሲን የሚመሩ የአካባቢው፣ የክልሉ፣ የፌደራል መንግስት “የት ናቹህ” የሚሉ ፍትህ ፈላጊዎች ከጃዋር ድንኳን ርቀው ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።

More stories

ጎረቤት አልባነት “ጎንደርና አስመራ መሄድን ህልም ያደረገ የ47 ዓመታት ፖለቲካ”

June 3, 2022

የአሳብ አንድነት – የአስደማሚው አድዋ ሙዚየም ኪነ ህንጻ ትውውቅ በአርክቴክቱ

February 10, 2024

አጀንዳ “ጠላት ተከፋፍሏል ይህንን መከፋፈል እንዴት እናስፋው?” ትህነግ

January 27, 2022

የማይካድራ ሰማዕታትን እንዘክር ተዘከሩ “የጭካኔ ጥግ የታየበት እለት”

November 10, 2024

በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የጅምላ ግድያ ሲፈጸም ገዳዮች በድርጅታቸው ስም ወዲያው ኃላፊነት ይወስዳሉ። ለምን ግድያውን እንደፍጸሙ ይፋ ያደረጋሉ። አለያም ሰለባዎችን መሰረት ባደረጉ ምርመራዎች የገዳዮች ማንነት ይታወቃል። ያኮረፉ ወይም ለሆነ ዓላማ ንጹሃንን የሚገድሉ ሲያዙ ይናዘዛሉ። በአገራችን የሚሆነው የተገላቢጦሽ ነው። ገዳይን ሁሌም እየታወቀ እንቆቅልሽ እንዲሆን ይደረጋል። 

በአገራችን በተለያዩ ጊዜያት ህዝብ የሚያውቃቸው፣ በስም ለይቶ “ገደሉን፣ አፈናቀሉን” እያለ የሚጠራቸው ድርጅቶች ንጹኃን ይገድላሉ ኃላፊነት ግን አይወስዱም። የፖለቲካ፣ የዕምነት፣ አክቲቪስት ነን የሚሉ ወዘተ “ሰዎች በዕምነታቸው ተለይተው ተገደሉ” ከሚለው የዘለለ ገዳዮችን ለይቶ የመኮነን፣ የማውገዝ፣ የመቃወም እርምጃ አይወስዱም። ወይም በራሳቸው የግንኙነት ሰንሰለት ለማጣራት ሲሞክሩ አይታዩም። እንደውም የምስኪኖችን ሞት ለፖለቲካ ፍጆታ ለመጠቀም ሲረባረቡበት ነው የሚስተዋለው። ሰክነው የሚያስቡ ዜጎች የሚያሳስባቸው ይህ ነው። ገዳዮች ላይ ከመረባረብ ይልቅ ለሟቾች በማንባት ተደጋጋሚ ለቅሶ መቀመጥ የተመረጠ ይመስላል። ቢያንስ ቢያንስ የምርጫ እለት ይህ ግድያ መፈጸሙን በማንሳት መጠየቅ የሚወዱ አይታዩም። አይሰሙም። ይህን ለማድረግ የሚሞክሩ ደግሞ ይወገዛሉ። 

በኢትዮጵያ ሰላማዊ ሰዎችን ለይተው የሚገድሉ፣ የሚያግቱና የሚያፈናቅሉ ታጣቂዎች ይህን ድርጊት በተደጋጋሚ በተለያዩ አካባቢዎች ሲፈጽሙ መስማት ተለምዷል። ሰላማዊ ተጓዦችን በጥይት እሩምታ የሚያስፈራሩ፣ የሚገሉ “የብሄርሰብ ነጻ አውጪ ነን” ባዮችና መንግስት ውስጥ የተሰገሰጉ ቡችሎቻቸው ተባበረው አንድ አውቶቡስ ሙሉ ህዝብ በጠራራ ጸሀይ እያፈኑ ገንዘብ ሲቀበሉ፣ሲያሰቃዩ መስማት አዲስ ጉዳይ አይደለም።

የአርሲ እና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ባወጡት መግለጫ በምሥራቅ አርሲ አገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሺርካ እና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች 13 የርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መገደላቸውን፣ ከ280 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን እና የ101 ዓመት ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን” አመልክተዋል። ይህ ዜና ከተሰማ ጀምሮ ውርጋጦቹን ጨምሮ የሚታወቁት ፖለቲከኞች ሻማ እያበሩ በማህበራዊ ገጽ የለቅሶ ድንኳን እየጣሉ ነው። 

“በሌሎች ዓለማት ለምሳሌ ሂዝቦላ፣ አልቃይዳ፣ አልሸባብ ወዘተ ግድያም ሆነ እገታ ሲፈጽሙ ንብረት ሲያወድሙና የጅምላ ወንጀል ሲፈጽሙ ኃላፊነት ወስደው መግለጫ ያወጣሉ። በመግለጫቸው ወይም በቃለ ምልልስ ሳይሸማቀቁ  የፈጽሙትን ድርጊት ለምን እንደፈጸሙም ያብራራሉ። ይህ የተለመደ ነው” የሚሉ የህግ ባለሙያዎች በአርሲ በተደጋጋሚ ደረሰ የተባለው ግድያ የጥቃት አድራሾቹን ማንነት እነሱ ራሳቸው ኃላፊነት ወስደው ባያስታውቁም የአገሪቱ ሚዲያዎች የግልና የፖለቲካ ድርጅቶችን ጨምሮ የሚደብቁበት ምክንያት አሳሳቢ ነው እንደሆነ ይናገራሉ። አክለውም “ተጣርቶ ይቀርባል እየተባለ በዝምታ የሚታለፍበት አግባብ ግልጽ አይደልም፣ ይህም ሌላው አሳሳቢ ችግር ነው” ይላሉ። ይህ የህግ ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን የመልካም ዜጎች ሁሉ አስተያየት ነው። የኔም እምነት ነው። 

ጥቅምት 14 ለ15 ቀን 2018 ዓ.ም. በጉናና መርቲ ወረዳዎች 17 ክርስቲያኖች፣ ጥቅምት 17 ለ18 ቀን 2018 ዓ.ም. በሸርካ ወረዳ 3 ክርስቲያኖች እንዲሁም ጥቅምት 18 ለ19 ቀን 2018 ዓ.ም. በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 5 ክርስቲያኖች መገደላቸውን ተከትሎ ቅዱስ ሲኒኖዶስ መግለጫ ሲያወጣ ስለገዳዮቹ የተባለ ነገር አልነበረም። በወቅቱ የአገረ ስብከቱ ኃላፊ ስለገዳዮቹ ማንነት ሲጠየቁ “ይህንን ግለጽ አልተባልኩም” ብለው ነበር። የሲኖዶሱ ጸሀፊም በተመሳሳይ “የተላከልንን መግለጫ ተንተርሰን ነው መግለጫ የምንሰጠው” በማለት ስለገዳዮች ማንነት ምንም ሳይሉ ነበር ያለፉት።

በምሥራቅ አርሲ ዞን ሁለት ወረዳዎች እሁድ እና ሰኞ ዕለት በተፈጸሙ ጥቃቶች 13 ሰዎች መገደላቸውን እና አንድ ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን ነዋሪዎች እና የአካባቢው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገረ ስብከት ኃላፊዎች በገሃድ ሳይሆን “ምንጭ” እየተባሉ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ እነዚህ ምንጭ የተባሉት አካላት ስለገዳዮቹ ማንነት ለቢቢሲ ምንም አልነገሩትም።

ቅድሚያ ወስዶ ግድያውን የፈጽመው መንግስት እንደሆነ ያስታውቀው ጃዋር መሐመድ ነው። “በምዕራብ አርሲ ዞን ሄባኒ ወረዳ አርሲ ወረዳ 9ኙ ቀበሌ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ነው” በማለት እያስታውቀ፣ በአንድ ቀን 50 ተሽከርካሪዎች ተቃጠሉ በማለት የምርጫውን መስተጓጎል እየዘገበ ግድያውን መንግስት እንደፈጸመው ያስታወቀው ጃዋር ተፈናቃዮች “ሸኔ አረደን” ላሉት ምላሽ አልሰጠም። 

ከሶስት ሚሊዮን በላይ ተከታታይ ባለው የማህበራዊ ገጹ ለአፍሪካ ታዛቢዎች በአዲስ ስታንዳርድ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ መስጠቱን፣ ይህንንም ያደረገው በጽሁፍና በቃለ ምልልስ መሆኑን እያስታወቀ፣ ሞቱ ስለተባሉት የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮችና ተቃጠለ ስለተባለው ቤተ ክርስቲያን ቀድሞ ድንኳን የጣለው “ወደ እኛ ክልል ከመጣ አንገቱን በሜንጫ ነው የምንቆርጠው” በማለት የዘር ፖለቲካን ሲጠምቅና ግድያን በገሃድ ሲሰብክ የኖረው ጃዋር መሐመድ ነው። በዚህ በጀዋር መሐምድ የስላቅ ድንኳን ውስጥ ገብተው የሚያነቡት ደግሞ የቅርብ ጊዜ ጃዋር ማንነትን የዘነጉ ነፈዞች ናቸው። ለሚያስተውሉ ግን የጃዋር ቀድሞ መጮህ ብዙ ይናገራል።  

ጃዋር “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምን ወለጋ ሄዱ? የዘር ጭፍጭፍ የፈጠራል” ባለበት ሰሞን በምስራቅ ሃረርጌ ጎረጉቱና መሰላ / እሱ ከተወለደበት አካባቢና ከአርሲ የሚዋሰኑ ቦታዎች ናቸው/ የሚነሳ ታጣቂ ኃይል በቅርቡ አካባቢውን እንደሚቆጣጠር ተናግሮ ነበር። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአርሲ አቅጣጫ እስከ መሰላ የሚነቀሳቀሰው ኃይል በጃዋር የሚደግፈና የሚረዳ ነው። ጃዋር ተሽቀዳድሞ በፌስ ቡክ ገጹ “እንቀነጥሳችኋለን” ለሚላቸው ክርስቲያኖች ተቆርቋሪ የሆነበት ሚስጢርም ይህ ነው። ወደፊት በመረጃ ተደግፎ የሚወጣ ይሆናል። 

የምሥራቅ አርሲ አገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ከፍያለው ሸንቁጤ “እዚያ አካባቢ ትንሽ እርስ በርስ አለመስማማት አለ” በማለት ግድያዎች እየተፈጸሙ መሆናቸውን ለቢቢሲ ሲናገሩ፣ ሰኞ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም. በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ምርጫ መካሄዱን በማስታወስ በእነዚህ አካባቢዎች እርስ በርስ መጨራረስ የተደረሰው “ምርጫውን ለማደናቀፍ ይሁን ወይም ሌላ ምክንያት ስለመኖሩ አለመታወቁን” ጠቁመዋል። ይህ ለኔ ብዙ ይነግረኛል። ቢቢሲ ፈልጎም ይሁን ሳይፈልግ አድምቶ ያልጠየቀው ይህ ቁልፍ ጉዳይ በጃዋር የክርስቲያኖች ተቆርቋሪ መሆን ግልጥ ብሎ በመታየቱ የነገሩ መድበስበስ ይፋ አድርጎታልና ብዥታ የለም። 

ዋና ሥራ አስኪያጁ ጥቃቱ የተፈጸመው በምን ምክንያት እና በማን እንደሆነ ለይቶ ለመናገር አሁን እንደማይችሉ፣ በአካባቢው የፀጥታ አካላት እና የሚያጣራ ቡድን ማክሰኞ ዕለት ግንቦት 25/2018 ዓ.ም. መሰማራቱን ተናግረው ሁኔታዎች መረጋጋታቸውን አመልክተዋል። ተፈናቅለው የተቀመጡ፣ ሮጠው እየተታኮሱ ያመለጡ እነማን እንደሆነ የገለጿቸውን ገዳዮች እሳቸው ለምን ይደብቋቸዋል? ይህ “እኔ ቢቢሲን ብሆን እጠይቅ ነበር” ብዬ የማልፈው ጉዳይ ነው። 

በጥቃቱ የሞቱ ሰዎችን በተመለከተም “ግማሹ ዘጠኝ ይላል፤ ግማሹ ሰባት ይላል ይሄም ራሱ መጣራት አለበት” ብለዋል።

በአካባቢው ግንቦት 23 እና 24 የተኩስ እሩምታ እንደተከፈተ ጥቆማ እንደደረሰባቸው መረጃው እንዳላቸው የሚናገሩት ኃላፊው አንድ ቤተክርስቲያን ላይ “ትንሽ የእሳት አደጋ” መድረሱን በመግለጽ ይህንንም ወደ ቦታው የተሰማራው ቡድን አጣርቶ እንደሚያሳውቅ ተናግረዋል። ሙሉ በሙሉ መውደሙ ዋና ዜና የሆነውን ቤተክርስቲያን ትንሽ የእሳት አደጋ እንደደረሰበት ማመልክታቸው ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ሳለ እንዲያብራሩት አልተደረገም ወይም መረጃውን ከየት አመጡት አልተባሉም። የትኛው ወገን ነው ሃሰተኛ ? 

የተፈጠረውን በዝርዝር ለማስረዳት አጣሪ ቡድኑ የሚያመጣውን መረጃ አይተው ለመናገር እንደሚመርጡ በመግለጽ ኃላፊው ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል። ንግግራቸው ትክክል ቢሆንም፣ በተደጋጋሚ “ተጣርቶ ይገለጻል” እየተባለ የንጹሃን ደም እንደዋዛ ቀርቷልና እንዴት እንመን የእኔ ጥያቄ ነው። በዚሁ አስተያየቴን በምጽፍበት አዲስ ሪፖርተር የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ያቀደሙትን ግድያዎች አጣርቶ እንደሚያቀርብ ቃል ገብቶ የውሃ ሽታ መሆኑን ማስታወስ ግድ ያላል። 

የቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ግለሰብ በበኩላቸው በአካባቢው ባለፉት ስድስት ዓመታት “በሸኔ ታጣቂዎች” ጥቃት በተደጋጋሚ ሲፈጸም እንደነበር ገልጸው፤ የተወሰኑ ግለሰቦች ራሳቸውን ለመከላከል “በግላቸው መታጠቃቸውን” ይናገራሉ።

የተወሰኑ ሰዎች ከታጣቂዎቹ ጋር ሲታኮሱ ቀሪዎቹ ግን እየሸሹ ባሉበት መገደላቸውን ጨምረው ገልጸዋል። እነዚህ ስማቸው ያልተገለጸ የቤትክርስቲያን አገልጋዮች፣ “ገደሉን” ያሉዋቸውን በስም ጠቅሰዋል። እንዚህ ሰዎች እዛው ያሉ፣ በስፍራዉ የሆነውን በተደጋጋሚ የታዘቡ፣ ምን አለባትም በታምራት የተረፉ፣ ከዚያም ባለፈ የቀደሙትን ባልደረቦቻቸውን ቀብረው ታሪኩን ከስር መሰረቱ የሰሙ ምስክሮች ናቸው። እንግዲህ አቶ ጃዋርም ሆነ ጃዋር የጣለው ድንኳን ውስጥ ገብተው በጃዋር አዲስ ዜማ የሚፈተፍቱት ይህ ሃቅ እያለ ነው። እኔም በግል ያነጋገርኳቸው ተመሳሳይ ምላሽ ነው የሰጡኝ። 

አገልጋዮቹ ለቢቢሲ ሲናገሩ ግንቦት 23 እና ግንቦት 24 በነበረው ጥቃት ከአድማ በታኝ፣ ከሚሊሻ እንዲሁም ሙስሊም ከሆኑ የአካበቢው ነዋሪዎች የተገደሉ መኖራቸውን ጨምረው ገልጸዋል። ሚሊሻዎች መሞታቸው፣ ሙስሊሞች መሞታቸው በደን ከተገለጸ ዜናው ለታሰበለት ዓላማ ስለማያመች ያነሳቸው የለም። ሙስሊም፣ ሚሊሻም ሆነ ክርስቲያን ህይወታቸው እኩል ነው። የክስርስትና ኃይማኖት ተከታዮች ላይ መደጋገሙን ማጉላቱ አገባብ እንደሆነ እያመንኩ ሌሎችም ነብስ እንዳላቸው ሊታወቅ እንደሚገባ ለማሳሰብ እወዳለሁ። ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ሙስሊሞች አብረው ተግድለዋልና!!

ይህንን ሁሉ ስል የዞንና የወረዳ፣ የቀበሌ የመንግስት መዋቅር የት ነህ? የኦሮሚያ ክልል መሪዎች፣ የጸጥታ ሸርፉ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም፣ የፌደራል መንግስት ዝምታ በየትኛውም የሂሳብ ስሌት ትክክል እንዳልሆነ ዘንግቼ እንዳልሆነ መግለጽ እወዳለሁ። መንግስትንም ሆነ ክልሉን ከዛም አልፎ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች ላይ ጫና ፈጥሮ ፍትህ እንዲሰፍን ማስገደድ የሚቻለው “ሜንጫ አንስቶ እቀነጥሳለሁ” ሲል በነበረው ክርስቲያን ጠል ጃዋር ድንኳን ውስጥ ገብቶ ለእሱና መሰሎቹ ፍላጎት ማዳበሪያ በመሆን አይመስለኝም። 

ከሞቱት ወንድምና እህቶቻችን ህይወት ይልቅ የፖለቲካ ትርፋቸውን እያሰሉ በንጹሃን ደም የሚሞዝቁትን ማድመጥና ከነሱ ጋር ማበድ ለቀጣዩ ደህንነት ዋጋ አይኖረውም። ይልቁኑም ማን፣ ለምን፣ እንዴት፣ ምን ፈልጎ፣ ንጽሁሃንን በማንነት፣ በዕምነታቸው ሳቢያ ወዘተ እንዲህ መሰሉን ኢሰብአዊ ድርጊት ማን እንደሚፈጽመው ማስላቱና ይህ እንዲገለጥ የረጋ ጫና ማድረጉ ይበጃል። 

በመጨረሻም ጃዋር መሐመድ “ወደ ትውልድ አካባቢያችን ከመጣህ በሜንጫ አንገት ነው የምንቀነጥሰው” በማለት  በአደባባይ የዛተው ጃዋር ዛሬ “እንቀነጥሳችኋለን ላላቸው፣ እንዲፈናቀሉ አዋጅ ላውጣባቸው ክርስቲያኖች ተሟጋች ነኝ” ሲል አብሮ ማበዱ ሃቁን ስለሚደብቀው ጥንቃቄ ግድ ነው።

NEWSOPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

VOE

International Partner Welcomes Ethiopia’s 7th General Election, Calls for Inclusive Voting in Remaining Constituencies
Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
News

ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

June 5, 20260
News

ዓለም አቀፍ አጋሮች የኢትዮጵያን 7ኛ አጠቃላይ ምርጫ በበጎ ተቀበሉ፤

June 3, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
TOP NEWS

ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups

June 7, 20260
TOP NEWS

Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV

June 7, 20260
AFRICA

Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»

June 7, 20260
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
Load more
Recent Posts
  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science” June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ June 7, 2026
  • ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ» June 7, 2026
  • ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ” June 6, 2026
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ June 5, 2026
  • Agricultural Sovereignty, Economic Transformation, and the Defiance of Extremism Ahead of the 7th National Election June 5, 2026
  • የዘለንስኪ ጥሪ፦ “ጦርነቱን ለማቆም ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ዝግጁ ነኝ” June 5, 2026
  • የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አደነቀ June 5, 2026
  • The Inverted Frontlines: How Secret Alliances and the Western Tigray Fault Line Threaten to Reignite Ethiopia June 4, 2026
  • Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia June 4, 2026
  • ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው? June 3, 2026
  • International Partner Welcomes Ethiopia’s 7th General Election, Calls for Inclusive Voting in Remaining Constituencies June 3, 2026
  • ዓለም አቀፍ አጋሮች የኢትዮጵያን 7ኛ አጠቃላይ ምርጫ በበጎ ተቀበሉ፤ June 3, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news