Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  የደሴዋ እብድ እና አሜሪካ!!
News

የደሴዋ እብድ እና አሜሪካ!!

Ethioreview newsEthioreview news—November 21, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በዱሮ ጊዜ በደሴ ከተማ ውስጥ የምትኖር አንዲት እብድ ነበረች፡፡ ከእለታት በአንዱ ቀን በጧት ተነሳችና “እዚህ ከተማ ቤት ይቃጠላል፣ እዚህ ከተማ ቤት ይቃጠላል…”በማለት እየዞረች ስትለፈልፍ ዋለች አሉ፡፡ እብድ ስለሆነች እሷ የምትለውን ልብ ብሎ የሰማት፣ ነገሬ ብሎ ያዳመጣት ሰው አልነበረም፡፡ ከእብድ ፍሬ ያለው ነገር ይነገራል ብሎ ከቁብ የቆጠራት አልነበረም፡፡ በዚያው እለት ምሽት ላይ በደሴ ከተማ በአንዱ ሰፈር የእሳት ቃጠሎ ተነሳ፡፡ ብዙ ቤቶች ተቃጠሉ፡፡ በርካታ ንብረት ወደመ…ያቺው የደሴዋ እብድ በማግስቱ ጧት ተነሳችና በየሰፈሩ መዞር ጀመረች፡፡

በየሄደቺበት ቦታ ሁሉም ሰው የሚያወራው የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ቤት ስለመቃጠሉ፣ ንብረት ስለመውደሙ ነው፡፡ ገረማትና “የሚሰማኝ ጠፍቶ ነው እንጂ እኔ ተናግሬ ነበር፡፡ እዚህ ከተማ ቤት ይቃጠላል ብዬ ነበር…” አለች አሉ፡፡ የሚገርመው ነገር ቤቱን ያቃጠለቺው እሷ ራሷ ነበረች፡፡ “እዚህ ከተማ ቤት ይቃጠላል፣ እዚህ ከተማ ቤት ይቃጠላል…”ስትል ያረፈደቺው እሷ ራሷ ማታ ቤት እንደምታቃጥል እቅድ ይዛ ስለነበር ነው…

አሜሪካ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለቺው ተግባር ከደሴዋ እብድ ጋር ተመሳሰለብኝ፡፡ አሜሪካ፤ “ወያኔ አዲስ አበባ ይገባል፡፡ እነሱ ሲገቡ በከተማዋ ችግር ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ዜጎቼን ቶሎ ከአዲስ አበባ ውጡ…” በማለት በአደባባይ መናገር ከጀመረች ሰነበተች፡፡ እንዲህ ያለው ራእይ፣ እንዲህ ያለው ነብይነት ለአሜሪካ ብቻ እንዴት ሊገለጥላት ቻለ? አሜሪካ ለብቻዋ የምታውቀው ነገር ይኖር ይሆን?

ወያኔ አዲስ አበባ መግባቷ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ በ1983 ደርግን ጥለው አዲስ አበባን ተቆጣጥረዋል፡፡ በከተማዋ ግን ምንም የተፈጠረ ተዓምር አልነበረም፡፡ ሰላማዊ ህዝብ ላይ ትኩረት ያደረገ የተቃጠለ ቤት አልነበረም፡፡ የወደመ ንብረት አልነበረም፡፡ ዜጎች እርስ በርስ አልተጨፋጨፉም፡፡ ያኔ የአሜሪካም የአውሮፓም ኤምባሲዎች በአዲስ አበባ ነበሩ፡፡ እነዚህን ኤምባሲዎች ማንም አልነካቸውም፡፡ አንድም የውጭ ሀገር ዜጋ ጥቃት አልደረሰበትም፤ የተገደለ ፈረንጅም አልነበረም፡፡

More stories

“አርባ ዘጠኝ አስከሬን ቀበርኩ” – በጭና ሟቾች ከ200 በላይ ሆኑ፣ የታፈኑ አሉ

September 8, 2021

ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት – የሚተገበሩ ወሳኝ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

August 8, 2022

“የምናስተውላቸው ሀገራዊ ፈተናዎች እንደ ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን እንደ ማኅበረሰብም መውረዳችንን አመላካቾች ናቸው፡፡” ረ/ፕ ሽመልስ ኃይሉ

April 5, 2021

“አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች

October 9, 2023

ዛሬ ምን የተለየ ነገር ተፈጥሮ ነው አሜሪካኖቹ እንዲህ ጭንቅ ጥብብ ያሉት? አሜሪካኖቹ የሚያውቁት ነገርማ አለ! ያ ነገር እነርሱ ራሳቸው ለአዲስ አበባ ከተማችን ያጠመዱላት ወጥመድ ይሆን? እና እንደ ደሴዋ እብድ የሚያደርጉትን ወይም በወያኔ አማካይነት የሚያስደርጉትን እየነገሩን ይሆን? ደግሞስ ወያኔዎቹ የአሜሪካ የቁርጥ ቀን ወዳጆች ናቸው፡፡ ዜጎቻቸውን በማስወጣት ስራ ተጠምደው ከሚባዝኑ ወዳጆቻቸውን ወያኔዎች “ተው ዜጎቼን አትንኩ” አይሏቸውም እንዴ?

ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት እንችል ዘንድ ወደ ኋላ መለስ ብለን የአሜሪካንን እና የወያኔን ወዳጅነት እንመልከት… ህወሓት ከደርግ መንግስት ጋር ሲያደርግ በነበረው የትጥቅ ትግል ወቅት በርካታ ፈረንጅ ወዳጆችን እንዳፈራ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ካናዳዊው ፕሮፌሰር ጆን ያንግ ነው፡፡ ጆን ያንግ በዚያ ወቅት ለBBC በጋዜጠኛነት ይሰራ ነበር፡፡

እናም ለዘገባ በሱዳን በኩል ወደ ትግራይ ገባ፡፡ ጋዜጠኛው
ጆን ያንግ ዘገባውን ሰርቶ አልተመለሰም፡፡ የወያኔዎቹ “አድቬንቸር” (ጀብድ) ብቻ ሳይሆን እነ መለስ ዜናዊ ጤፍ በሚቆላው ምላሳቸው ሰውየውን አንዳች አዚም ጫኑበት፡
፡ ለዓመታት አብሯቸው እዚያው ቆየ፡፡ እየዘገበም፣ አብሯቸው እየታገለም፣ ታሪካቸውን እየመዘገበም አብሯቸው ቆየና በ1983 አብሯቸው አዲስ አበባ ገባ፡፡ እንደገባም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል ከእነ ዶ/ር መረራ ጉዲና ጋር ያስተምር ጀመር፡፡ በዚያው ወቅት በእንግሊዝኛ “Peasant Revolution in Ethiopia: Tigray People Liberation Front 1975 – 1991” (ማለትም፤ “የገበሬ አብዮት በኢትዮጵያ፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ከ1967–1983”) በሚል ርእስ የህወሃትን የትግል ሂደት የሚያወሳ መጽሐፍ አሳትሟል፡፡ጆን ያንግ እስከ አሁን ድረስ ከህወሓት ጎን ነው፡፡ የዛሬ ዓመት “The looming long civil war that could break Ethiopia” ማለትም “ኢትዮጵያን ሊሰብር የሚችል ረጅም የእርስ በርስ ጦርነት” በሚል ርእስ የወያኔ አጋርነቱን የሚያሳይ መጣጥፍ በመጻፍ ጓዳዊ ኃላፊነቱን ተወጥቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት 71ኛው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አንቶኒ ብሊንከን የመለስ ዜናዊ የቅርብ ወዳጅ ነበሩ፡፡ የብሊንከነረ ባለቤት ልጅ ስትወልድ መለስ ዜናዊ “አራስ ለመጠየቅ” ወደ አንቶኒ ብሊንከን ቤት አሜሪካ አቅንቶ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ ዛሬ አንቶኒ ብሊንከንን የህወሓት ነገር እንቅልፍ የነሳቸው ከወያኔ መሪዎች እና ከህወሓት ጋር ያላቸው የተለየ ግለሰባዊ ወዳጅነት ነው፡፡

ምስክርነትም የሚጸድቀው ሦስት ሲሆን ነው፡፡ አንድ የወያኔ ወዳጅ ልጨምርላችሁ፡፡ከአንቶኒ ብሊንከን የቅርብ ረዳቶች ውስጥ አንዷ ጄል ስሚዝ ትባላለች፡፡ ጄል ስሚዝ ለህወሃት አመራር ቅርብ ናቸው፡፡ እኚህ ሴት ላለፉት 40 ዓመታት ከህወሓት ጋር ዝምድና አላቸው ተብሏል፡፡ ጄል ስሚዝ በመለስ ዜናዊ የአስተዳደር ዘመን የህወሓት እና የአሜሪካ የስለላ ድርጅት – CIA አገናኝ ነበሩ ይባላል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ ጄል ስሚዝ የትግራይ የረድኤት ድርጅት በሆነው በኤፈርት ውስጥ ለሦስት ዓመታት በኃላፊነት ሰርተዋል፡፡ በወቅቱ የኤፈርት መሪ የነበረው ተክለወይኒ አሰፋ ይህንኑ ተናግሯል ተብሏል፡፡ በዚህም ምክንያት “ጄል ስሚዝ ለህወሓት ከሞንጀሪኖ እኩል ናት” የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ፡፡

እንግዲህ እነዚህ ዝምድናዎች ናቸው ህወሓትንና አንዳንድ የአሜሪካ ባለስልጣናትን በማይበጠስ ክር ያስተሳሰራቸውና በ“ፍቅር እስከ መቃብር” መርህ ያቆራኛቸው፡፡ ለዚህም ነው የአሜሪካ መንግስት ለአሸባሪው ቡድን ከወታደራዊ የሳተላይት መረጃ ማቀበል እስከ አማካሪነት እያገለገለች ያለቺው፡፡ እዚህ ላይ “አሜሪካ እና የደሴዋን እብድ የሚያመሳስላቸው ነገር ምንድነው?” የሚል ጥያቄ ይነሳ ይሆናል፡፡ የደሴዋ እብድ ምሽት ላይ ቤት የማቃጠል እቅድ ስለነበራት ጧት ላይ “እዚህ ከተማ ቤት ይቃጠላል፣ እዚህ ከተማ ቤት ይቃጠላል…” ስትል ዋለች፡፡

አሜሪካም ኢትዮጵያን የሚያምሱትን፣ አዲስ አበባን በደም አበላ ለማጥለቅለቅ የተዘጋጁትን ህወሓትንና ሼኔን ለሽብርና ለጭፍጨፋ ማሰማራቷን ስለምታውቅ፣ እነዚህ የሽብር ኃይሎች በአዲስ አበባ ከተማ የዘረጉትን የጥፋት መዋቅር ስለምታውቅ፣ ህወሓትና ሸኔ በአዲስ አበባ ሁከትና ብትብጥ በማነሳሳት ህዝቡን እርስ በርስ ለማጫረስ እቅድ ማውጣታቸውን ስለምታውቅ፣ በአዲስ አበባ ያሉ የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች የታጠቁትን መሳሪያ የህወሓት አማካሪ የሆነቺው አሜሪካ በደንብ ስለምታውቅ፣… እንደደሴዋ እብድ “ህወሓት ወደ አዲስ አበባ ሲገባ በአዲስ አበባ ሽብርና እልቂት ስለሚኖር ዜጎቼ በአስቸኳይ ውጡ…” የሚል ውትወታ፣ ጩኸትና ማስፈራራት እያሰማች ነው፡፡

በርግጥ አሜሪካ ዜጎቿን ከአዲስ አበባ እንዲወጡ ማድረጓ መብቷ ነው፡፡ ከፈለገች ኤምባሲዋንም መዝጋት ትችላለች፡፡ የህወሓትና የሸኔ ስፖንሰር መሆን ግን በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ላይ ወረራ መፈጸም መሆኑን ወዳጅም ጠላትም ሊያውቀው ይገባል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ሀገራችን ፈርሳ፣ ህዝባችን ተጨፍጭፎ እያየን እጃችንን አጣጥፈን የምንቀመጥ እንደማይሆንም ግንዛቤ መውሰዱ ጠቃሚ ነው፡፡

የደሴዋ እብድ እና አሜሪካ
(አብዱራህማን አህመዲን- የቀድሞ ፓርላማ አባል)

NEWSOPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ውጭ አማራጭ ገበያ እየፈለገች ነው
ከደባርቅ ወደ ጎንደር ተጭኖ ሊወጣ የነበረ የጦር መሳሪያና ተተኳሽ ጥይት ተያዘ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2