Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  ገለልተኝነት የራቀው ‹ገለልተኛው ተቋም
News

ገለልተኝነት የራቀው ‹ገለልተኛው ተቋም

Ethioreview newsEthioreview news—December 17, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ዛሬ የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብቶች ምክር ቤት ከተቋቋመለት ዓላማ ውጪ በሆነና በማይመለከተው ጉዳይ ገብቶ የፖለቲካ አጀንዳን ለማስፈፀም ቀጠሮ ይዟል፡፡ ምክር ቤቱ የስብሰባውን መጠራት ያልፈቀደችውን አፍሪካ ዘንግቶ፤ በአንዲት አፍሪካዊት የነፃነት ምልክት በሆነች አገር የውስጥ ጉዳይ ገብቶ ሊያቦካ ተሰናድቷል፡፡ ለዚህ መንደርደሪያ ደግሞ እነአምነስቲ ኢንተርናሽናል አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዲሉ በገባባቸው ቦታዎች ሁሉ የዘር ጭፍጨፋን እየፈፀመ ያለውን የአሸባሪው ሕወሓት ወንጀል ችላ ብለው ‹በምዕራብ ትግራይ የጦር ወንጀል እየተፈፀመ ነው› የሚል ድምዳሜን ጥቂት ሰዎችን በስልክ አናግሮ ያጠናቀረውን የፈጠራ ሪፖርት አውጥቷል፡፡ ይህ ደግሞ ለሽብርተኛው አፎች ሰርግና ምላሽ ሆኗል፡፡

ምዕራባዊያኑ አፍሪካን በቅኝ ግዛት ለመቀራመት በርሊን ላይ ሲመክሩና የበርሊኑን ስምምነት ሲያጸድቁ የመምከሪያ አዳራሹ በር ለአፍሪካ እና አፍሪካዊያን ዝግ ነበር፡፡ በርሊን ላይ በተደረሰው የቅርጫ ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ ለጣሊያን ታጭታ ነበር፡፡ ቅኝ ገዢዎቹ በዚያ አዳራሽ ውስጥ ባስቀመጡት ቀመር መሰረት አብዛኛዎቹን የአፍሪካ አገራት በቅኝ ገዢነት ተቀራምተው ሃብታቸውን መዝረፍና ሕዝባቸውን መበዝበዝ የቻሉ ቢሆንም በኢትዮጵያ በኩል የመጣው ወራሪ ግን ሊሳካለት አልቻለም፡፡

የኢትዮጵያን በተፈጥሮ ሃብቶች የበለጸገ ምድር ለመበዝበዝ ቋምጦ የመጣው የፋሺስት ጣሊያን ጦር በጀግኖቹ እና ልባሞቹ የኢትዮጵያ ልጆች አይሆኑ ሆኖ ሲመለስ እግረመንገዱን ለምዕራባዊያን እና ለመላው ዓለም አንድ መልዕክት ይዞ ነበር የተመለሰው፡፡ ይኸውም ኢትዮጵያ ምንም ደሃ እና የጥቁር ሕዝብ አገር ብትሆንም ለቅኝ ግዛት ግን የማትንበረከክ መሆኗን የሚገልጽ ነው፡፡ ታሪክ ራሱን ደገመ እንዲሉ ፅንፈኛ የሆኑት አንዳንድ ምዕራባዊያን እና መሪያቸው አሜሪካ ዛሬም ከብዙ ዓመታት በኋላ የአፍሪካዊት አገርን ጉዳይ ያለአፍሪካዊያን ፍላጎት በመምከር ያንን ያረጀ እና ያፈጀ አካሄዳቸውን ለመድገም እየተጋጋጡ ይገኛሉ፡፡ እነ አሜሪካ እና በእሷ የሚዘወሩ ምዕራባዊያን አገራት እንደፈለጋቸው የሚጠመዝዙት የተባበሩት መንግሥታት በስሁት ውሳኔዎቹ የበርካታ ሉኣላዊ አገራትን ኅልውና ተዳፍሯል፡፡

ይህን የተረዱ የአፍሪካ አገራት የሁሉም የሆነው የተባበሩት መንግሥታት በተለይም የፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካዊያን ቋሚ መቀመጫ ሊኖረው ይገባል የሚለውን ጥያቄ ማቅረብ ጀምረው፤ ጉዳዩ ወደ ንቅናቄነት ከፍ እያለ ነው፡፡ ፍጹም ባለተረጋገጠ እና በበሬ ወለደ ትርክት ኢራቅ እና ሊቢያ የዘመተው አሜሪካ መራሹ የኔቶ ጦር ንጹሃን ዜጎችን ለሞት፣ ስደትና እንግልት ሲዳርግ አገራቱን ሙሉ በሙሉ በማወደም አይ ኤስ አይ ኤስን የመሳሰሉ የሽብር ቡድኖች መፈንጫ አርጓቸዋል፡፡

More stories

“አርባ ዘጠኝ አስከሬን ቀበርኩ” – በጭና ሟቾች ከ200 በላይ ሆኑ፣ የታፈኑ አሉ

September 8, 2021

ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት – የሚተገበሩ ወሳኝ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

August 8, 2022

“የምናስተውላቸው ሀገራዊ ፈተናዎች እንደ ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን እንደ ማኅበረሰብም መውረዳችንን አመላካቾች ናቸው፡፡” ረ/ፕ ሽመልስ ኃይሉ

April 5, 2021

“አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች

October 9, 2023

ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ እንዲሉ እጇን ለማስጠምዘዝ ያለፈቀደችውን ኢትዮጵያ ባለዋለችበት እየከሰሷት እና የማዕቀብ ናዳ እያወረዱ ሊያፍረከርኳት ያልተቆጠበ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተለይ አሸባሪው ሕወሓት ድል እያደረገ ሲመስላቸው በኢትዮጵያ እየሆነ ያለውን ለመስማት የዝሆን ጆሮ ስጠኝ የሚሉት እነዚሁ አገራትና ተቋማት መንግሥት ከመከላከል ወደ ፀረ ማጥቃት ገብቶ በቀናት ውስጥ አንጸባራቂ ድሎችን ሲቀዳጅ እና የሽብሩ ቡድኑ አፍንጫ እዚህ ሲመታ ከዚያ ማዶ የእነርሱ አይን ማልቀስ ይጀምራል፡፡

ይህ ሲሆን የሰብኣዊ መብት መጣስ የሚለው አጀንዳ ይራገባል፤ የዴሞክራሲ እጦት የመልካም አስተዳደር ችግር ያሳስባቸዋል፤ የመግለጫ እና ዕቀባ ጋጋታ ማስፈራሪያ ሆኖ ይዥጎደጎዳል፡፡ የዚሁ ዘመቻ አካል የሆነውና ዛሬ በጄኔቫ የሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብቶች ምክር ቤት የጠራው ልዩ ስብሰባ አንድ ሦስተኛውን ቁጥር የሚይዙትን የድርጅቱ አባል የሆኑ የአፍሪካ አገራትን በማግለል በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ እየተጠበቀ ነው፡፡ ልዩ ስብሰባው እንዲጠራ ሲጎተጉት ሰንብቶ የተሳካላትን የአውሮፓ ኅብረት ጥያቄ በመቀበል ፊርማቸውን ካኖሩት መካከል አንድም አፍሪካዊ አገር አለመኖሩ ግን የሚያስተላልፈው መልዕክት ከፍ ያለ ነው፡፡

በዛሬው ልዩ ስብሰባም ድምፅ እንደሚሰጡ ከሚጠበቁት 47 አገራት ውስጥ የአፍሪካ አገራትና ሌሎች ለእውነት የቆሙ ኃይሎች ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙ ይጠበቃል፡፡ የሆነው ሆኖ ኢትዮጵያ ግን በልዩ ስብሰባው የሚተላለፈውን ማንኛውንም ውሳኔ አልቀበልም ስትል ከወዲሁ ይፋ አድርጋዋለች፡፡ የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽንም ግልፅ ደብዳቤን ያወጣ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብቶች ምክር ቤት አካሄድ ከዚህ ቀደም በኮሚሽኑና በመንግሥታቱ የሰብኣዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር የተደረገውን ጥምር ምርመራ እውቅና የሚነፍግ ነው ሲል ተቃውሟል፡፡

ምክር ቤቱ መስራት የነበረበት የጋራ ጥምር ሪፖርቱ ምክረሐሳቦች እንዲተገበሩ ድጋፍ ማድረግ እንጂ በራሱ ተቋምም ተሳትፎ ጭምር የተደረገን ሃቀኛ ምርመራ ትቶ ሌላ አጀንዳ ለመቅረፅ መሞከር እንዳልነበርም አሳውቋል፡፡ እዚህ ላይ ዋናው ቁምነገር የተባበሩት መንግሥታት ገለልተኛ ስለመሆኑ ጥያቄዎች እየተነሱበት ከመሆኑም ባሻገር በቀጣዮቹ ጊዜያት ተቀባይነቱ እና ተደማጭነቱ እንደሚያሽቆለቁል ጠቋሚ ነው፡፡ ስብስቡ የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ ፍላጎቶችን እና የፖለቲካ አጀንዳዎች ማስፈጸሚያ ሆኖ እያገለገለ ነው በሚል እየተወቀሰም ይገኛል፡፡ በተግባርም እያደረገው ነው፡፡ ይህ የመንግሥታቱ አግላይ አካሄድ በፍጥነት እየበለጸጉ ያሉ እና የአንድ አካል ፈላጭ ቆራጭነት ዘመን አብቅቷል ብለው በሚያኑ ቻይና እና ሩሲያን በመሳሰሉ አገራት ዘንድም ተቀባይነትን እያጣ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሄዶ ሄዶ ምናልባትም ለድርጅቱ ኅልውና አደገኛ ሊሆን ይችላል እየተባለ ነው፡፡

በነስረዲን ኑሩ ታኅሣሥ 8/2014 (2014) walta


NEWSOPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Erdoğan meets leaders at 3rd Turkey-Africa Summit
Jack Dorsey says he’ll continue running both Square and Twitter
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2