Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Western Pressure on Ethiopia Intended to See Weak Gov’t, Nation – Scholars

    July 10, 20210

    Journalist demands UNWFP to tell truth about missing trucks

    October 3, 20210

    ብርሃኑ ባይህ እና አዲስ ተድላ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ

    December 19, 20200

    አብንና ባልደራስ ከተሸነፉ ” ውጤቱን አንቀበልም” ሊሉ የሚችሉ ፓርቲዎች እንደሚሆኑ ዲፕሎማቶች ገለጹ

    May 23, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሚስጥራዊ የቻይና ፖሊስ ጣቢያዎች በአሜሪካ ተገኙ

    December 19, 20240

    ሦስተኛው ዕድል እንዳይባክን … !

    May 21, 20220

    “Why I decided to extend my time at the club”

    May 24, 20230

    የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ዋና የጦሩ መሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ

    February 24, 20220

    “Ethiopia’s success reflects a new alternative for Africa’s development”

    January 29, 20240
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  «የተጀመረው ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል» ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት
News

«የተጀመረው ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል» ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት

Ethioreview newsEthioreview news—June 9, 20220
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በወቅታዊ ሀገራዊ የደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣

ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት፣ ከአንድ ወር በፊት፣ ሚያዝያ 14 ቀን 2014 ዓ.ም.፣ ሀገራዊ የጸጥታ ሁኔታን በጥልቀት መገምገሙ ይታወሳል። በዚያ ግምገማውም እንደ አልሸባብ፣ ሸኔና ጁንታ ያሉ የሽብር ኃይሎችን ሁኔታ ተመልክቷል። ከኮንትሮባንድ፣ ከሕገ ወጥ ታጣቂዎች፣ ከጽንፈኛ የሚዲያና የፖለቲካ ቡድኖች፣ ከአክራሪ ሃይማኖተኞችና ከሙሰኞች የሚመጡ ፈተናዎች በሀገር ላይ ያስከተሉትን ሥጋት ተመልክቷል። የመንግሥት መዋቅር የጥራትና የቁርጠኝነት ችግሮች እንደታዩበትም ገምግሟል።

እንዲሁም የውጭ ጠላቶቻችንን ሤራና የውክልና ጦርነቱን ሁኔታ በጥልቀት መርምሯል።

More stories

በመተከልና ሌሎች አካባቢዎች ተፈጥረው በነበሩ ግጭቶች የሱዳንና የግብፅ እጅ እንዳለበት ተገለጸ

March 5, 2021

የመከላከያን ጨምሮ የአሜሪካንን ሚስጢር “ለትውልድ አገሩ አቀብሏል” የተባለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ” ብሄራዊ ጀግና” እየተባለ ነው

October 1, 2023

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ወይም ሞት እያለ ነው

March 22, 2022

“የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር ” ዐቢይ አህመድ ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገለጹ

December 8, 2021

ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ በሚያዝያ ወር ባደረገው ስብሰባው እነዚህ ፈተናዎች በሀገርና በሕዝብ ላይ ያሳደሩትን ሥጋትና ፈተና በሚገባ ተንትኖ አስቀምጦ ነበር። የሕዝቡ የደኅንነት ሥጋትና ሀገራዊ አለመረጋጋት መባባሱን፤ ሕዝብ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ እየተደረገ መሆኑን፤ በሃይማኖትና በብሔር አክራሪነት የተነሣ የሀገርን አንድነት ለመሸርሸር እየተሠራ መሆኑን፤ የሕገ ወጥ ታጣቂዎች ዐቅም እየጨመረ የሕጋዊ መዋቅሮች ዐቅም እየደከመ መምጣቱን፤ የሕገ ወጥ ታጣቂዎች መበራከትና መጠናከር ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ፈተና መሆኑን፤ ሕገ ወጥ ቡድኖቹ የሕዝቡን ሰብአዊና ማኅበራዊ መብቶች እየጣሱ ሕዝብ መሰቃየቱን፤ በጠቅላላ ሥርዓት አልበኝነት እንዲስፋፋ ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረለት መሆኑን፤ ይህም ለውጭ ጠላቶቻችን ዕድል እንደፈጠረላቸው፤ ነገሩ በአስቸኳይ ካልተስተካከለ ሀገርን ወደ ከፋ አደጋ እንደሚያስገባ በሚያዝያ ስብሰባው መገምገሙ ይታወቃል።

እነዚህን ችግር ፈጣሪዎችና በሕዝቡ ላይ ያንዣበቡ ፈተናዎች በዝምታና በትዕግሥት ማየቱ አደገኛውን ቀይ መሥመር እንዲታለፍ እንደሚያደርግ ታምኖበት ነበር።

መንግሥት ችግሮችን በሆደ ሰፊነት እያለፈ፣ በጊዜ ብዛት ቀስ በቀስ ለማረም የተከተለው ስልት እንደ ድክመትና ዐቅመ ቢስነት መታየቱን የደኅንነት ምክር ቤቱ አረጋግጧል። ሕዝቡ በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ውይይቶችና በተወካዮቹ አማካኝነት መንግሥት ጠበቅ ያለ የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲሠራ እየወተወተ መሆኑን ምክር ቤቱ ተመልክቷል።

ችግሮችን በውይይት፣ በሀገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች በኩል ለማረም የተደረጉ ጥረቶች መጠነኛ ውጤት ማምጣታቸውን ተረድቷል። የተወሰኑ አካላት በሕጋዊ መሥመር ለመሥራት መወሰናቸውን፤ ወደ መደበኛ የጸጥታ ተቋማት ገብተው ለመሠማራት መወሰናቸውን ተገንዝቧል።

አንዳንድ አካላትም ወደ ሰላማዊ ኑሮ ለመመለስ ያደረጉትን ውሳኔ በሚያዝያው ስብሰባው በክብር ተቀብሎት እንደነበር ይታወሳል።

መንግሥት የሰጠውን የሰላም ዕድል ያልተጠቀሙና በሕገ ወጥ ተግባራት ከመሠማራት ያልተቆጠቡ አካላትን በተመለከተ የደኅንነት ምክር ቤቱ በሚያዝያ ወር ባደረገው ውይይት የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጦ ነበር፡-

• በተደራጁና ያለፈቃድ በታጠቁ ቡድኖች ላይ ሕግን የማስከበር ሥራ መሠራት እንዳለበት፣

• በሁሉም አካባቢዎች የሚታዩ ሕገ ወጥ ተግባራት በፍጥነት መስተካከል እንዳለባቸው በየአካባቢው የሕዝብ ቅሬታ ምንጮች የሆኑ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በፍጥነት ማስተካከል እንደሚገባ፣

• ግጭት ቀስቃሽና ጽንፈኛ የሚዲያ አካላት፣ የፖለቲካ ቡድኖችና አክቲቪስቶች ሕጋዊውን ሥርዓት ብቻ እንዲከተሉ የሚያደርግ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ፣

• የመንግሥትን መዋቅር በማጥራት፣ ሚናውን ለይቶ በቁርጠኝነት እንዲሠራና ሕዝብና መንግሥት የጣሉበትን ኃላፊነት እንዲወጣ የሚያደርግ ተግባር እንዲከናወን አቅጣጫዎች ተቀምጠው ነበር።

በዚህ መሠረት የተከናወኑትን ተግባራት ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ረቡዕ ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓም ባደረገው ስብሰባ በጥልቀት
ገምግሟል።

በግምገማውም መሠረት የመንግሥትን ኃይልን በብቸኝነት የመጠቀም ሕጋዊ ሥልጣን የሚገዳደሩ ኃይሎችንና የሕገ ወጥነት ተግባራትን ወደ ተገቢው ሥርዓት የማስገባቱ ሥራ በታቀደለት መንገድና በተሻለ ጥራት እየተከናወነ መሆኑን፤ ሥራውም የታለመለትን ግብ እያሳካ እንደሆነ አረጋግጧል።

በኦሮሚያ ክልል በተከናወነው አኩሪ ሥራ የሸኔን ልዩ ልዩ ቡድኖች በመደምሰስ፣ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን በማምከን፣ በጠላት እጅየነበሩ አካባቢዎችን መልሶ በመቆጣጠር፣ መዋቅሩን በማጥራት፣ ሕዝብን በማወያየትና በማሰለፍ ውጤታማ ሥራ መከናወኑን ለማወቅ ተችሏል።

በሺዎች የሚቆጠሩ የሸኔ አባላት መገደላቸውን፣ መማረካቸውንና በፈቃዳቸው እጅ መስጠታቸውን ከሪፖርቶቹ ተረጋግጧል። አያሌ የጦር መሣሪያዎችና ቁሳቁሶች ከሸኔ አባላት ተማርከዋል።

መንግሥታዊ መዋቅሩን በሚገባ በማጥራት፣ ለአመራር
ብቁ የማድረግ ተግባር በመልካም ሁኔታ ተከናውኗል።
በአማራ ክልል በተሠሩ ሥራዎች ሕዝቡን ለእፎይታ ያበቁ ተግባራት መከናወናቸውን የደኅንነት ምክር ቤቱ ገምግሟል። በዚህም መሠረት ከጸጥታ ተቋማት የከዱ አባላትን በመያዝ፣ በተለያዩ ወንጀሎች የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል፤ ተበትነው ለጸጥታ ሥጋት ሲሆኑ የቆዩ የጦር መሣሪያዎችን በማሰባሰብ፣ በሕገ ወጥ ተግባር ተሠማርተው የነበሩ አክቲቪስቶችን ሥርዓት በማስያዝ፣ ሕዝቡ የሰላምና የጸጥታው አካል እንዲሆን አወያይቶ በማሰለፍ፣ የተሻለ ሥራ መሠራቱን ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ
ተመልክቷል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተደረገውን ሰላምና ጸጥታ የማስፈን እንቅስቃሴ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ በገመገመበት ወቅት አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውን ተገንዝቧል። የታጠቁ ሽፍቶችን ሥርዓት ከማስያዝና ከመደምሰስ አንጻር፣ ሕገ ወጥ ተግባትራን ከመቆጣጠር፣ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎችን ከመሰብሰብ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቦታቸው ከመመለስ አንጻር የተከናወኑ ተግባራት
ለውጥ ያመጡ መሆኑን ለመመልከት ተችሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደቡብና በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታትም የታጠቁና የተደራጁ ሽፍቶችን መልክ ከማስያዝ፣ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ከመግታት፣ በተለያዩ ማኅበረሰቦች መካከል የሚከሠቱ ግጭቶችን
ከማስቀረትና ከመፍታት፣ ሕገ ወጥ ተግባራትን ከመቆጣጠር፣ የመንግሥት መዋቅርን ከማጥራት አንጻር ሥራዎቹ በታቀዱት መሠረት መከናወናቸውን አረጋግጧል። በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና በኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ሊደረግ ታስቦ የነበረው የአልሸባብ እንቅስቃሴ በጸጥታ አካላት ቅንጅት መክሸፉን ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ተመልክቷል።

አልሸባብ ከጁንታውና ከሸኔ ጋር በተደጋጋሚ ሊያደርጋቸው የሞከራቸው ትሥሥሮች በተጠና የጸጥታ አካላት ኦፕሬሽን እንዲመክኑ መደረጋቸውን አረጋግጧል።

ዓለም አቀፍ የሚዲያ ትኩረትን ለመሳብ የሚሞክሩ የጥፋት ኃይሎች በመዲናችን አዲስ አበባ ላይ የተለያዩ የጥፋትና ጸጥታ የማደፍረስ እንቅስቃሴዎችን በተደጋጋሚ ሲሞከሩ የጸጥታና የደኅንነት ተቋማቱ የተናበበ አካሄድ እንዳከሸፈው ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ገምግሟል።

በዝርፊያና በከተማ ወንጀሎች ላይ ተሠማርተው የከተማውን ነዋሪዎች ሲያማርሩ የቆዩ አካላትን ተከታትሎ በሕግ ጥላ ሥር ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራትም ውጤታማ ለውጥ ማምጣታቸውን የደኅንነት ምክር ቤቱ ተመልክቷል።

ከላይ የተገለጡት ሰላምንና ጸጥታን የማስከበር ሥራዎች በቁርጠኝነትና በመሥዋዕትነት የተከናወኑ ናቸው። ለዚህም በሥራ የተሳተፉትን ሁሉ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ያመሰግናል። የፖለቲካ መዋቅሩ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የፈጸሙት የሀገርን አንድነት፣ ሰላምና ብልጽግና የማረጋገጥ ሥራ ውጤታማ የሆነው መላው ሕዝብ በዓላማው አምኖ፣ በሥራው አብሮ በመሰለፉ መሆኑ ይታመናል። ኢትዮጵያ ሕዝቦቿ በነጻነትና በሰላም የሚሠሩባት፣ የሚንቀሳቀሱባትና የሚያመርቱባት ሀገር እንድትሆን ሕገ ወጥነት በምንም መልኩ ዕድል ሊያገኝ አይገባም።

ሕገ ወጥነት – የብሔርን፣ የሃይማኖትን፣ የፖለቲካ ቡድንን ወይም የሚዲያና የአክቲቪስትነትን ካባ ቢደርብም፣ ሕገ ወጥነት መሆኑ አይቀርም። አይጥ ምንም ዓይነት ቀለም ብትቀባ አይጥ መሆኗና ንብረት ማበላሸቷ አይቀርም።

ውድ ኢትዮጵያውያን፣

ስለ ጸጥታና ደኅንነት እየተናገርን በሕግ ከተቋቋሙ የጸጥታ መዋቅሮች ውጭ የታጠቁ የጸጥታ አደረጃጀቶች እንዳሻቸው እንዲሆኑ መፍቀድ ተገቢ አይደለም። በሀገር ውስጥ ኃይልን በብቸኝነት የመጠቀም መብት ለመንግሥት የተሰጠ መብት ነው። ዜጎች በሰላም ጊዜ አልሚ፣ በጦርነት ጊዜ ተፋላሚ መሆናቸው ከጥንትም የነበረ ነው። ያ ማለት ሀገር ስትወረር ሁሉም ለሀገሩ ተፋላሚ ይሆናል፤ ሀገር ሰላም ስትሆን ደግሞ ሁሉም ወደ ሕጋዊ ማሕቀፍ ይገባል ማለት ነው።

ከዚህም በተጨማሪ በሚዲያ፣ በአክቲቪስትነት፣ በፖለቲካ ቡድን እና በብሔር ስም የሚደረግ ሀገር የማፍረስ ሤራን መንግሥት በምንም መልኩ እንደማይታገሥ መታወቅ አለበት። የሃይማኖት ተቋማት የሰላምና የጤናማ ማኅበረሰብ መገንቢያ ማዕከላት እንጂ የአክራሪዎችና የሀገር አፍራሾች መናኸሪያ እንዲሆኑ ሊፈቀድ አይገባም። ሃይማኖቶች በስማቸው ጥፋት የሚፈጽሙ ነውረኞችን መቆንጠጥ ሲገባቸው ችላ በማለታቸው ጥፋት ፈጻሚዎቹ የልብ ልብ እየተሰማቸውና ተቋማቱን እንደከለላ በመቁጠር በድርጊታቸው ቀጥለውበታል።

በሀገራችን ሃይማኖት ተኮር ጥፋቶች በዘላቂነት ሊቀንሱ የሚችሉት አንዱ ወደሌላው ጣት በመቀሰር ሳይሆን ሁሉም በቅድሚያ በራሱ ተቋም ውስጥ የሚሸሸጉ ጥፋት ፈጻሚዎችን ምሽግ ለማሳጣት ሲችል ነው። ለዚህ ደግሞ ምእመናንና የሃይማኖት አባቶች የሚገባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል።

በአጠቃላይ የተጀመረው ሰላምና ጸጥታን የማስፈን፣ ሕግና ሥርዓትን የማስከበር፣ ብሎም የኢትዮጵያን ብልጽግና በጽኑ መሠረት ላይ የመገንባት ተግባር ከግብ እንዲደርስ፤ የተጀመረው ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤቱ ጥሪ ያቀርባል።

የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት
ሰኔ 1፣ 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

“የፌደራል ፖሊስ አባላት ነን”በማለት ወንጀል የፈፀሙ በቁጥጥር ስር ዋሉ
የዳውድ ኢብሳ ደብዳቤና የጸጋዬ አራራ ተቃውሞ ተገጣጠመ፤ ጃዋር አዲስ ቀለበት ውስጥ ገብቷል
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news