በሕግ ወጥ መልኩ በዘመን ትህነግ በየክልሉ ተቋቁመው የነበሩና ልዩ ኃይሎች ፈርሰው ወደ መከላከያ ወይም ፖሊስ እንዲገቡ በተወሰነው መሠረት የቴዎድሮስ ክፍለ ጦር ጥሪውን ተቀበሎ ወደ ካምፕ ገብቷል።
መንግሥት ያቀረበውን የልዩ ኃይል ሪፎርም ተቀብለው ሰላምን መርጠው ወደ ሕጋዊ መንገድ የመጡ የቴዎድሮስ ክፍለ-ጦር የልዩ ኃይል አባላትን የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ደማቅ አቀባበል አደርጎላቸዋል። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደ ቤተሰቦቻቸው ተንጠባጥበው ለተበተኑ የልዩ ኃይል አባላትም በፈለጉት ማለትም የክልል ወይም የፌደራል ፖሊስ ወይም የመከላከያ ሰራዊቱን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
ዶ/ር ወንደሰን የተባለ ግለሰብ ከመስከረም አበራ ጋር ሲያወራ የተቀዳ ተብሎ በተሰራጨው የድምጽ ቅጂ ላይ እንደሚሰማው በጎንደር ያለውን ልዩ ኃይል ለማስካድ የተሠራው ሥራ መክሸፉን የሚገልጽ ነበር። ሤራውን እምቢ ብለው ወደ ካምፕ የገቡትን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩትን በተመለከተ ለምን እንደገቡ መስከረም ለጠየቀችው ወንደሰን ሲናገር “እንጃባታቸው” በማለት ነበር የመለሰው።
ጎንደር የቅርቡን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ማርሽ በመቀየር በተደጋጋሚ ወሳኝ ሚና ስትጫወት ቆይታለች፤ ይህ ሦስተኛዋ ነው።

ከለውጡ በፊት የነበረውን ኦሮሙማ እንቅስቃሴ “የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው” በሚል ገልብጦ ለውጡን አገር አቀፍ ይዘት እንዲኖረው ማርሻ የቀየረው ጎንደር፣ የፖለቲካውን ትግል እንዲነድና የትህነግ/ህወሃት መጥፊያ እንዲቃረብ በማድረጉ ሲጠቀስ እንደሚኖር ያወሱ ወገኖች፣ የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በምላሹ “የአማራ ደም የኔም ደም ነው” ሲሉ የትግሉን አቅጣጫ በመቀበልና በማስተጋባት፣ በትህነግ የተፈራውን የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ የትግል አንድነትን በማግነን ታሪክ መሠራቱን ገልጸዋል።
ሁለተኛው የዛሬ ሁለት ዓመት በወለጋ እና በሌሎች አካባቢዎች ማንነትን መሠረት ያደረገ የጅምላ ጭፈጨፋ ሲካሄድ የአማራ ክልል በሰላማዊ ሰልፍ መናወጥ ጀመረ። የዚህ ነውጥ ፊት አውራሪ ግን ከጀርባ ሆኖ ይዘውረው የነበረው በደርግ ጊዜ በተከሰተው ድርቅ የረሃብተኛውን ብር ሰርቆ ከአገር በኮበለለው ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ነበር።
በሁሉም የአማራ ክልል ቦታዎች እየተቀጣጠለ ይሄዳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት እንቅስቃሴ ጎንደር ሲደርስ ተነፈሰ። ኦሮሞን ወንጅሎና በኦሮሞ ላይ ጽንፈኛ አቋም ይዞ ይወጣል የተባለው ጎንደር የችግሩን ምንጭ ነቅሶ አወጣው፤ እንቅስቃሴውም በረደ።
በሰሜን ሸዋ በተለይ አጣዬ በንጹሃን ዜጎች ላይ የደረሰውን ዘር የለየ ጭፍጨፋ በመቃወም አደባባይ የወጡት የጎንደር ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች “የከዳን ኦህዴድ እንጂ ወንድም የኦሮሞ ሕዝብ አይደለም” የሚል መፈክር አጉልተው በማሳየት ያሳዩት ተቃውሞ በወቅቱ “ሥልጡን” ተብሏል። ጽንፈኛ አመለካከት ላላቸው ደግሞ ታላቅ መልዕክት እንደሆነ ነው የተጠቆመው።
አሁን ለሦስተኛ ጊዜ ልዩ ኃይሉን መከታ በማድረግ፣ በወልቃይት በማስፈራራት ወደ አመጽ እንዲገባ ሲዋከብ የነበረው በተለይ የጎንደር ልዩ ኃይል ሁኔታዎችን አመዛዝኖ በውስጥና በውጪ ኃይሎች የተደገሰውን ሤራ አክሽፏል። ከልዩ ኃይል ውስጥ በስመጥር እንደሆን የሚነገርለት የቴዎድሮስ ክፍለ ጦር የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ ወደ ካምፕ ገብቷል። ጎንደርም ታሪክ በመሥራት ኢትዮጵያን እየታደገች ትቀጥላለች።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም ሆነ የተጠቀሱት አካላት ስለሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው መረጃዎች በአዎንታም…
ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማህበርን ዓመታዊ እራት ለመታደም ተሰብስበዋል። ከ2600 ባልይ…
“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም ሳይቆዩ አሁን ወዳሉበት ደረጃ ደረሱ። የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምንት መፈረሙን…









