በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ አማርኛ ቋንቋ ማስተማር ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ የስፑትኒክ አለም አቀፍ የዜና አገልግሎት ድርጅት እና ሬዲዮ÷ በሩሲያ – አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተስፋዎች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
ውይይቱ በአሌክሳንደር ጎርቻኮቭ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፈንድ እና በሰብአዊ እርዳታ ማእከል ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን÷ በሩሲያ እና በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር አድማስ” ለመፍጠር ያለመ የባለሙያዎች እና ትምህርታዊ ዝግጅት አካል መሆኑ ተጠቁሟል።
በውይይቱ ላይ ከሩሲያ እና አፍሪካ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የታሪክ ተመራማሪ ምሁራንና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ከፈረንጆቹ መስከረም 2023 ጀምሮ ቢያንስ አራት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች ለህጻናት የአማርኛ እና የስዋሂሊ ቋንቋ ማስተማር እንደሚጀምሩ ይፋ አድርገዋል።
ማስሎቭ አክለውም በአዲሱ ልዩ መርሐ-ግብር በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ዮሩባ ቋንቋን የሚያስተምሩበትን ዕድልም እየተመቻቸ መሆኑን ነው የገለፁት።
ወደ አፍሪካ በፍጥነት ፊትን ለማዞር ከኢኮኖሚው ጋር በቀጥታ ሊሰሩ የሚችሉ ፍጹም የተለዩ ባለሙያዎችን ማፍራት ያስፈልጋል ሲሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
አፍሪካ አንድ ትልቅ አህጉር ብቻ ሳትሆን የተለያዩ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖት እና ህብረ ብሔራዊ ማንነቶች ያሉባት አህጉር መሆኗን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡
ሩሲያ የአፍሪካ ልሂቃን ዲግሪ ለማግኘት ከሚሄዱባቸው አገሮች አንዷ እንደነበረች ያነሱት በውይይቱ የተሳተፉት ምሁር ቱንዴ አጂሌዬ÷አሁን ላይ ሩሲያ እና አፍሪካ የትምህርት ልውውጡን መቀጠል አለባቸው ሲሉ አክለዋል።
እንደ ምሁሩ ገለጻ በግብርና፣ በኃይል እና ኢንቨስትመንት ላይ ያለውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑንም አፅንዖት በመስጠት ተናግረዋል።
(ኤፍ ቢ ሲ)
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም ሆነ የተጠቀሱት አካላት ስለሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማህበርን ዓመታዊ እራት ለመታደም ተሰብስበዋል።… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም ሳይቆዩ አሁን ወዳሉበት ደረጃ ደረሱ። የፕሪቶሪያ የሰላም… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ አደጋ ጊዜ እርስ በርስ የሚረዱበትን አዲስ የጋራ መከላከያ ስምምነት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት” መሆኑን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። ምርመራው ቀጥሎ ማስተባበያው ሃሰት ከሆን… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች







