Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Western Pressure on Ethiopia Intended to See Weak Gov’t, Nation – Scholars

    July 10, 20210

    Journalist demands UNWFP to tell truth about missing trucks

    October 3, 20210

    ብርሃኑ ባይህ እና አዲስ ተድላ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ

    December 19, 20200

    አብንና ባልደራስ ከተሸነፉ ” ውጤቱን አንቀበልም” ሊሉ የሚችሉ ፓርቲዎች እንደሚሆኑ ዲፕሎማቶች ገለጹ

    May 23, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሚስጥራዊ የቻይና ፖሊስ ጣቢያዎች በአሜሪካ ተገኙ

    December 19, 20240

    ሦስተኛው ዕድል እንዳይባክን … !

    May 21, 20220

    “Why I decided to extend my time at the club”

    May 24, 20230

    የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ዋና የጦሩ መሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ

    February 24, 20220

    “Ethiopia’s success reflects a new alternative for Africa’s development”

    January 29, 20240
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  የትህነግ ትግራይ ወዴት? የግል እስር ቤቶች በትግራይ አዲስ ኢንቨስትመንት ሆነዋል፤ ያፈነገጡ ዞኖች አሉ፤ የጸጥታ ዋስትና የለም
News

የትህነግ ትግራይ ወዴት? የግል እስር ቤቶች በትግራይ አዲስ ኢንቨስትመንት ሆነዋል፤ ያፈነገጡ ዞኖች አሉ፤ የጸጥታ ዋስትና የለም

Ethioreview newsEthioreview news—September 8, 20230
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ቀደም ባሉት ዓመታት የትህነግ ሰዎችና አብረዋቸው የሚሰሩ ሚስጢረኞች፣ እንዲሁም የሚታወቁ ባለ ብሮች ብቻ የሚያውቋቸው የግል እስር ቤቶች በአዲስ አበባና በአንዳንድ ክልልሎች እንደነበሩ ይታወሳል። በነዚህ እስር ቤቶች የሚታሰሩ በድርድር ከፍለው የሚለቀቁ ሲሆን እንደ አሁኑ ሚዲያ ባለመፍላቱ ይፋ አይሆንም ነበር። ይሁን እንጂ በሾርኔ በሚታወቁ አምዶች ፍንጭ ይሰጥ ነበር።

በወቅቱ ደህንነቱ የራሱ ልዩ እስር ቤቶች እንዳሉት ቢታወቅም የግል እስር ቤቶቹ ግን በመንግስት መዋቅር ስራ ባሉ ወይም በነበሩ ከፍተኛ ባለስልጣኖች የሚተዳደር ሃላፊነቱ የተወሰነ ግብር የማይጠበቅበት የግል የንግድ ተቋም እንደ ነበር። ታስረው በድርድር የወጡ ምስክርነታቸውን የሰጡበት ጉዳይ እንደነበርም አይዘነጋም።

አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ “ የአቶ መለስን ሌጋሲ ሳይሸራረፍ አስፈጽማልሁ” ብለው ጠቅላይ ሚኒስትር በሆኑ በዓመታቸው በፓርላማ “ የግል እስር ቤት ያለበት አገር ነው። ምን አድርግ ነው የምትሉኝ” ሲሉ ይህንኑ ጉድ ፓርላማ ላይ አስታውቀው እጅ በአፍ ማስጫናቸው አይዘነጋም። ዛሬ አቶ ጌታቸው ይህ የትህነግ አመል መቀለ ላይ በስፋት መተከሉን አጋልጠዋል።


“አፈቀላጤው” ርዕሰ መስተዳድር በትግራይ የኩዴታ ስጋት ውስጥ

ሰላማዊ ሰልፉ ሌላ እንደምታ እንዳለው የሚገልጹ እንደሚሉት ጉዳዩ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን መብላት ነው። ይህ በተቃውሞ ሰልፍ ስም አስተዳደሩን ለመብላት የተደረጃው ስብስብ ከጀርባ የሚመራው ባኮረፉ የትህነግ ሰዎች እንደሆነም ተመልክቷል።


More stories

“መንግሥት ቢያጠቃ ለምንድን ነው በቆቦ በኩል የምናጠቃው? የአላማጣን እና የግራ ካሱን ተራራ ልንገፋ?” አምባሳደር ባጫ ደበሌ

September 6, 2022

ሙሽራ ጨምሮ ሰባ አንድ ሰዎች ህይወት አለፈ፤ ከአንድ ቤተሰብና 33 ዘመድ አዝማዶች ሞተዋል

January 1, 2025

የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራዎች የተጨፈጨፉባቸው በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጥናት አጋለጠ

April 3, 2022

በአማራ ክልል ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል፤ “በተፈጠረው የሰላም እጦት ክልሉ ከፍተኛ ገቢ እያጣ ነው”

September 29, 2023

“ትግራይ እዚህ ደረሳለች” ሲሉ የሚገልጹ የሰሙትን ማመን ተስኗቸዋል። ትግራይ ውስጥ ያለው ጣጣ ተሰፍሮ የሚያልቅ አልሆነም። በፖለቲካው ቋንቋ ትግራይ እንደ ክልል አትቆጠርም። ተበጣጥሳለች። የበጣጠሷት ደግሞ “ ዋስትናዋ ነን” እያሉ የሚምሉት የትህነግ ሰዎች ናቸው። ህጓ ፈርሷል። ደንቧ ወላልቋል። ነዋሪዎቿ ዋስትና ቢስ ሆነዋል። ሕዝቡን ለጦርነት ቀስቅሶ የማገደው ትህነግ ዛሬ ተቧድኖ የጎበዝ አለቃና ዘራፊ ሆኗል። ይህ ሁሉ የተሰማው ከአቶ ጌታቸው ረዳ አንደበት ነውና ማስተባበል እንደማይቻል “ይሰመርበት” ያሉ ገልጸዋል። ለዚህ ይመስላል ትናንት ባተምነው ዜና አንድ እናት “ ምኑም አያምርም” ሲሉ ሃዘን ውስጥ ሆነው አስተያየታቸውን የሰጡት።

ወረዳዎች እና በታችኛው እርከን ያሉ አስተዳደራዊ መዋቅሮች የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል እንዳይሆኑ የተደራጀ ንቅናቄ እንዳለም በግልጽ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው የፌደራል መንግሥት ለትግራይ የአንድ ዓመት በጀት ብቻ መድቦ በመጀመሪያ ዙር 3 ቢሊየን ብር መቀበሉን አስታውቀው አንድ ታላቅ ሚስጢር ይፋ አድርገዋል። “ከ3 ቢሊዮኑ ለሲቪል ሠራተኛው የከፈልነው የአራት ወር ደሞዝ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ ለሲቪል ሰራተኛው ሳናወጣ ከ270 ሺህ በላይ ወታደሮችን ምግብ ማቅረብ ስለነበረብን ነው” ሲሉ አሁንም ትግራይ 270 ሺህ ወታደር እንዳላታ አመል፤ክልተዋል።

ለዚህ ይመስላል ሰለ ወልቃይት ሲናገሩ “በሃይል ማስመለስ እንችላለን” ብለዋል። ይሁን እንጂ አቶ ጌታቸው ወቅታዊ ሁኔታውን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም በትግራይ በኩል ያሉ ግዛቶችን በኃይል እናስመልስ የሚሉ ወገኖች እንዳሉ ይፋ አድርገዋል። “በኃይል ማስመለስ ይቻላል። ነገር ግን የፕሪቶሪያው ስምምነት ከእነ ብዙ ችግሮቹና እጥረቶቹ ከተቀበልን በኋላ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በፌደራል መንግሥት ዘንድ የስምምነቱ አፍራሽ ተደርገን እንዳንቆጠር መጠንቀቅ ያስፈልገናል” ብለዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መሪ “ አቶ ጌታቸው በኩዴታ ጣጣ ውስጥ ናቸው” በሚል አስቀድመን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖችን ጠቅሰን እንዳልነው እሳቸው ጉዳዩን አረጋግጠውታል። በዜናችን “አኩራፊ የትህነግ አመራሮች” እንዳልነው ቃል በቃል ባያጠቅሱትም፣ አቶ ጌታቸው አስተዳደሩ የማያውቃቸው የግል እስር ቤቶች ከፍተው ህዝብ እየገረፉ ገንዘብ የሚቀበሉ የመዋቅር ሰዎች መኖራቸውን ይፋ አድርገዋል።

አንዳንድ ወረዳዎችና የታች መዋቅሮች ከትግራይ ክልል አስተዳደር ውጭ ናቸው። አይታዘዙም፣ የሚባሉትን አይሰሙም። የጸጥታ ጉዳይ ቅንጦት ሆኗል። ይህን ለማረም የሚሰራ ስራ ትህነግን የማጥፋት ተደርጎ ተወስዷል። ዝርፊያው በታጠቁና መዋቅር ውስጥ ባሉ ወገኖች ነው። አቶ ጌታቸው ምንም ሳያስቀሩ የትግራይን ወቅታዊ ቁመናና የህዝቡን ስቃይ በይፋ ተናግረዋል።

“ ሲንጋፖር ትሆናለች፣ ጦርነት ባህሏ በመሆኑ ኮሽ ሳይል በሰላም ትኖራለች” እያለ ስለትግራይ ሲዘምር የነበረው ትህነግ የትግራይን ህዝብ ቁብ ነገር ለሌው ጦርነት ዳርጎ ካስፈጀና አካለ ጉዳተኛ ካስደረጋቸው በሁዋላም የሚጸጸት አልሆነም። የትግራይ ነዋሪዎች እንደሚሉት አስገድዶ መድፈር የየዕለት ተግባር ነው። መግደል ስራ ሆኗል። ይህ ሁሉ እየሆነ ለስልጣን ዳግም እርግጫው ተጀምሯል። መፈራረጁና በሰፈር ተቧድኖ ለሌላ እልቂት ማሟሟቅ ላይ የሚገኙ ለመሆናቸው የሚያመላክቱ ጉዳዮች መኖራቸውን አቶ ጌታቸው ” እንኳን ለህዝቡ ታጅበን ለምንሄድ ባለስልጣናትም ዋስትና የሚሰጥ የፀጥታ ሁኔታ የለም ” ሲሉ እንቅጩን ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ለመገናኛ ዘዴዎች መግለጫ ሲሰጡ የተገኘው የቪኦኤ ዘጋቢ እንዳለው እሳቸው የሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር መንግሥትንና ፓርቲን ለመለየት ወስኖ እየሰራ መሆኑ አልተወደደም።

አቶ ጌታቸው የሚመሩት አስተዳደር የጀመረውን አዲስ ያሉትን የአሰራር ሂደት በ”ፀረ-ህወሓት ” እንቅስቃሴ የፈረጁ የፓርቲው አመራሮች እንዳሉ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው አንዳንድ የክልሉ ወረዳዎች የጊዜያዊ አስተዳደር አካል እንዳልሆኑ በመግለፅም አዲስ ማህተም ለመጠቀም ፍቃደኛ እንዳልሆም ብለዋል። ይህ መዋቅር እንዳይዘረጋ የማደናቀፍ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል።  በስም ቦታዎቹን ባይዘረዝሩዋቸውም ንግግራቸው በትግራይ ማዕከል የሚባል ነገር አለመኖሩን፣ “እኛ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል አይደለንም” ያሉ ቡድንተኞች አካባቢያቸውን የማስተዳደር ስራ መጀመራቸው ትግራይ ቅርጽ ማጣቷን አመላካች ነው።

አቶ ጌታቸው ” በተደራጀ መልኩ የሚደረግ እንቅስቃሴ አለ፤ በዞን እና በወረዳዎች ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅር እንዳይኖረው የሚሰሩ አሉ። በዚህም ዋናው የሚጎዳው ህዝቡ ነው። ጠቃሚው ነገር የጊዜያዊ አስተዳደሩን ስራ ጨርሰን ከፌዴራል መንግሥት ጋርም ከነልዩነታችን መተማመናችንን ወደላቀ ደረጃ በማሳደግ በህዝብ የተመረጠ ፓርቲ ስልጣን የሚይዝበት ሁኔታ መፍጠር ነው። በዚህ ሂደት ግለሰቦች በተደራጀ መልኩ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አለ ፤ እንደ ፓርቲ ጉዳዩ እንቅፋት መሆኑን አንስተን ወደ ግምገማ እንገባለን ” በማለት ሊሆን ይገባል ብለው የሚያምኑትን ምኞታቸውን ገልጸዋል።

“በጀት መድበው የጊዜያዊ አስተዳደሩን ስራ ለማደናቀፍ የሚሰሩ አካላት አሉ” ያለቱ አቶ ጌታቸው “አደናቃፊ” ሲሉ በጥቅሉ የጠቀሷቸውን ቡድኖችም ይሁኑ ግለሰቦች ማንነት አላነሱም። በመግለጫው ወቅት ይህ ስለመጠየቁም የቪኦኤ መረጃ አላብራራም። በጓሮ የሚወጡ መረጃዎች ግን ዶክተር ደብረ ጽዮን የሚመሩት ሃይል ከተጠቀሰው ጉዳይ ጋር ስሙ በስፋት ይነሳል።

“የትግራይ ህዝብ ዳግም ወደ ጦርነት እንዳይገባ ሁሉም አይነት ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ እንሰራለን። በአማራ ክልል ሆነው የትግራይን ህዝብ ማጥፋት የሚፈልጉ አካላትን ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር አደጋ መፍጠር ወደማይችሉበት ደረጃ ለማውረድ ያለ ጥርጥር እንሰራለን ” ማለታቸው በተለይ የሻዕቢያን ሃይል ይሁን ሌላ አሁንም አላብራሩም። ፕሬዚዳንት ኢሳያስን ያላስደሰተው የሰላም ስምምነቱን ያስታወሱ እንደሚሉት ሻዕቢያ ከትግራይ ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ የፌደራል መንግስት ጥያቄ ማቅረቡን ከዚህ ጋር ያያይዙታል።

አቶ ጌታቸው በፕሪቶሪያ ስምምነት እና በሀገሪቱ ህገመንግስት መሰረት የትግራይ ክልል አስተዳደር ወደ ቀድሞው የመመለስና ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው ዳግም የማስፈር ጉዳይን አስመልክቶ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመርህ ደረጃ መስማማታቸውን ገልጸዋል። ይህ ሂደት በመጓተቱ በነዋሪው ህዝብ እና ተፈናቃዮች ላይ ችግሩ አሁንም መቀጠሉን አመልክተዋል። አቶ ጌታቸው በመርህ ደረጃ ስምምነት ተደረሰበት ያሉትን ጉዳይ አስመልክቶ አማራ ክልል ጥብቅ አቋም እንዳለው ያስታውሳሉ።

አቶ ጌታቸው በመግለጫቸው በክልሉ መንግሥት የማያውቃቸው እስር_ቤቶች መኖራቸውን ይፋ አድርገዋል። “ መንግሥት የማያውቃቸው እስር ቤቶች አሉ። ይሄን ጉዳይ የሚያከናውኑና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈፀሙትን ማሰር ጀምረናል። በዘመቻ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት እንይዛቸዋለን። ሰዎችን በመጥለፍ ገንዘብ የሚቀበሉ አሉ ፤ ኤርትራውያንን በመያዝ ብር እየተቀበሉ ናቸው። እነሱን ብቻ ሳይሆን የክልሉ ተወላጆች፣ሀብታም ቤተሰብ ያላቸውን እየያዙ ናቸው ፤ እነዚህ በመንግሥት መዋቅር ስም የሚንቀሳቀሱ ናቸው ፤ ሰላዮች ነን የሚሉ፣ በተለያዩ አደረጃጀቶች ስም የሚሰሩ ናቸው። ለማጣራት ረጅም ጊዜ ወስዶብናል ከዛሬ ጀምሮ ግን በሚቀጥሉት ቀናት ፍርድ የሚያገኙበት ስራ እንሰራለን። የራሳቸው እስር ቤት አቋቁመው ሰዎችን እየደበደቡ ገንዘብ እየተቀበሉ የሚሰሩ በስም የምናውቃቸው ሰዎች አሉ። ” ሲሉ አስደንጋጭ የሆነውን ሌላ የትግራይ መልክ ገልጸዋል። ቀደም ሲል ለዕርቅ ልመና ወደ ትግራይ  የሄዱ እናቶች እግር ላይ ወድቀው በለቅሶ “ለሰላም እጃችሁን አንሱልን፤ ታረቁ” ሲሉ የተመለሰውን መልስ ለሚያስቡ ዛሬ ትግራይና ሰላማዊ ነዋሪዎቿ የገቡበት የመከራ አረንቋ ለሌሎችም በአስቸኳይ ትምህርት የሚሆን ሆኗል።

በትግራይ ያለው የፀጥታ ችግር ከፍተኛ መሆኑን ያሳወቁት አቶ ጌታቸው ረዳ “ወጥቶ መግባት ቅንጦት ሆኗል ብለዋል። ” እንኳን ለህዝቡ ታጅበን ለምንሄድ ባለስልጣናትም ዋስትና የሚሰጥ የፀጥታ ሁኔታ የለም ፤ ይሄን ለማስተካከል ከስራ ውጭ የነበሩ የፀጥታ አካላትን ወደ ስራ የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈው ህዝቡን በማስተባበር ፀጥታ ለማስፈን ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል። አክለውም ከምንም በላይ የሁሉም ችግር ዋናው ምንጩ ፖለቲካዊ እንደሆነ ገልጸዋል።

ከእርዳት ምዝበራ ጋር በተያያዘ እስካሁን 482 እርዳታ መዝብረዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የገለፁት አቶ ጌታቸው እስካሁን እርዳታ ባለመጀመሩ ተፈናቃዮች በተለየ መንገድ ችግር ውስጥ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር በተያያዘም ሰልፍ እየወጡ ያሉት መንግሥት በአግባቡ ስራውን ባለመስራቱና የክልሉ የበጀት አቅም አነስተኛ በመሆኑ የተነሳ እንደሆነ ያስረዱት አቶ ጌታቸው መንግስታቸው በአግባቡ እንዳልሰራ የጠቀሱትን አላብራሩም። የበጀት ማነስን ቢያነሱም የቀመር ችግር ስለመኖሩ ቅሬታ አላነሱም።

በክልሉ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠርተውት ስለነበረው የተቃውሞ ሰልፍ አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ በክልሉ ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት እንዳለ አመልክተዋል። ፈንጂዎችም በብዛት መገኘታቸውን ተናግረዋል።

ሰልፍ ማድረግ መብት ቢሆንም ለህዝብ ደህንነት ሲባል የሚካሄደው ሰልፍ ጊዜው እና ቦታው እንዲቀየር ከሰልፍ መሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ አስታውቀዋል።

” መንግሥት የፀጥታ ኃይል ማሰማራት እችላለሁ በሚልበት ሰዓት እና ቦታው ሰልፍ ማካሄድ የተለመደ ነው ” ያሉት አቶ ጌታቸው ” አሁን ገና ተነጋግረን አልጨረስንም ፤ ስለ አካሄዱ የምንነጋገርበት ነገር አለ፤ የፀጥታ ችግር አለ ፤ ከፍተኛ የሆነ የፈንጂዎች መሰባሰብ ስራ፣  ለሁከት ከጎረቤት አካባቢ የመጡ መኖራቸው ስለተድረሰበት  የፀጥታ አካላት የሚያጣሩት ይሆናል። ሰልፍ የጠሩት አካላት ረብሻ ይፈጥራሉ ሳይሆን ይሄን አጋጣሚ ተጠቅመው ረብሻ በመፍጠር ትግራይን ዳግም ወደ ሁከት ለማስገባት ያቀዱ ኃይሎች አሉ ” ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

ዜናው ከቪኦኤ፣ ቲክቫህና ሚዛናዊ አስተያየት በመስጥት ከሚታወቁ የማህበራዊ አምደኞች መረጃ የተካተተበት ነው።


  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር
    በኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ አነጋጋሪ ሰው ናቸው። በሁለት ጽንፍ ተፈርጀው ይተቻሉ። በአንድ በኩል “ለኦሮሞ ሕዝብ ማንነትና ታሪክ የታገሉ ምሁር” የሚሏቸው አሉ።… Read more: ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ
     የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዶ/ር አኔት ዌበር Dr. Annette Weber ለኤርትራ መሪዎች ጣልቃ ገብነታቸውን እንዲያቆሙ አሳስበው መመለሳቸውን ተልትሎ በግል የኤክስ ገጻቸው… Read more: የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል
    ሻዕቢያ በአሜሪካ ባደራጀው የሳይበር አጥቂ አማካይነት በተግባር የሚውል የፕሮፓጋንዳ ሰነድ አዘጋጅቶ ማሰራጨቱን፣ ሰነዱ የተላከላቸው ለቪኦኢ አስታወቁ። ሰነዱ እሰክ ፊታችን አርብ ድረስ በሚደረገው የቅሰቀሳ… Read more: ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

የኤርትራ መንግሥት በእስራኤል በተፈጠረው ግጭት ሞሳድ ድጋፍ አድርጓል አለ ፤ ተመድ የኤርትራዊያንን በጅምላ መባረር ነቀፈ
የፕሮፌሰሩ ጥያቄ “እኛ ያለነው የት ጋ ነው?” የጩኸት ፖለቲካ የሚነዳት ኢትዮጵያ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news