Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  law  General  መጥፋት – አንድ ሰው ጠፋ የሚባለው መቼ ነው? በኢትዮጵያ ህግ
Generallaw

መጥፋት – አንድ ሰው ጠፋ የሚባለው መቼ ነው? በኢትዮጵያ ህግ

Ethioreview newsEthioreview news—May 22, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የሰው ልጅ በአንድም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ከሚኖርበት ስፍራ በራሱ ወይም በሌሎች ምክንያቶች የሚሄድበት እና በዛም አጋጣሚ በሚፈልጉት ሰዎች ይኑር ይሙት የማያውቁበት አጋጣሚ አለ፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተሰቡ እና በስሩ የሚገኙ ንብረቶች ለማን እንዴት እንደሚደረግ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ በዚህ ፅሁፍ ስለመጥፋት ውሳኔ ትርጓሜ፣ የመጥፋት ውሳኔ በማን እና እንዴት እንደሚሰጥት፣ የመጥፋት ውሳኔ የሚያስከትለው ውጤት እንዲሁም የመጥፋት ውሣኔን ውጤት ቀሪ የሚያደርጉ ምክንያቶችን በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

አንድ ሰው ጠፋ የሚባለው መቼ ነው

በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 154(1) መሰረት አንድ ሰው ጠፋ የሚባለው ከጠፋ እና ከሁለት አመት ወዲህ ወሬው ያልተሰማ እንደሆነ ነው፡፡ ይህ በሆነ ጊዜ የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጥ በማናቸውም ባለጉዳይ ሊጠየቅ ይችላል፡፡

የመጥፋት ውሳኔ በማን እና እንዴት ይሰጣል

More stories

ሿሿ – ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 25 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

May 20, 2023

አሸባሪ ቡድኑ በአማራና በአፋር የፈጸማቸውን ወንጀሎች የሚያጣራ ግብረ ኃይል ሥራውን ጀመረ

December 27, 2021

በአደገኛ ዕፅ ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች ከ2 ዓመት እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ

October 24, 2024

የሃጫሉ ገዳዮች የተባሉት ” ጥፋተኛ” ተባሉ

July 5, 2021

የመጥፋት ውሳኔ የሚሰጠው የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጥበት የተጠየቀበት ሰው ዋና መኖሪያ አድርጎ በሚኖርበት ቦታ የሚገኝ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ማንኛውም ባለጉዳይ የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጥ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ሲያቀርብ ማስታወቂያ ይወጣል፡፡ ማስታወቂያውም ፍርድ ቤቱ በሚወስነው ሁኔታ እና የጠፋው ሰው በመጨረሻ ዋና መኖሪያነት ይኖርበት በነበረበት ቦታ እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ማስታወቂያው ይጠቅማል ብሎ በሚያምንበት ቦታ ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ የጠፋው ሰው መሞት በሚመስል መልኩ መጥፋቱ ከተሰማው የመጥፋት ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ውሳኔውን በሚሰጡበት ወቅት ግን የነገሩን አካባቢያዊ ሁኔታ፣ ጠባይ እና መጥፋቱ የተገመተው ሰው ለንብረቱ አስተዳዳሪነት ወኪል ማስቀመጡ እንዲሁም ግለሰቡ ወሬው እንዳይሰማ የከለከሉ ምክንቶችን መመርመር ይጠበቅበታል፡፡ የሚሰጠው የመጥፋት ውሳኔ እስከ 1 አመት ማቆየት ወይም ወይም ስለ መጥፋቱ የሚሰጠው ፍርድ ውጤቱ የሚኖረው ውሳኔው ከተሰጠ ከ1 አመት በኋላ እንዲሆን መወሰን ይችላል፡፡ በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በሚሰጠው ውሳኔ የጠፋው ሰው የመጨረሻ ወሬዎች የተሰሙበትን ቀን መወሰን ይችላሉ፡፡

የመጥፋት ውሳኔ የሚያስከትለው ውጤት

የመጥፋት ውሳኔ በውርስ እና በጋብቻ ላይ ውጤትን የሚያስከትል ነው፡፡ የመጥፋት ውሳኔን ዳኞች ሲወስኑ ጠፋ የተባለው ሰው የሞተ የሚመስልን ማስረጃ ካረጋገጡ በኋላ በመሆኑ የጠፋው ሰው ልክ እንደሞተ ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ ጋብቻ ለሚፈርስባቸው ምክንያቶች አንዱ በሞት ምክንያት ስለሆነ እና የመጥፋት ውሳኔም የጠፋው ሰው እንደሞተ የሚቆጠር በመሆኑ ጋብቻ ይፈርሳል፡፡ ስለውርስ የሚደነግገው አንቀፅ ስር ውርስ የሚከፈተው አውራሽ ከሞተ በኋላ በመሆኑ የመጥፋት ውሳኔም እንዲሁ የጠፋውን ሰው እንደሞተ ስለሚያስቆጥረው ውርሱ ይከፈታል፡፡

 ጋብቻን በተመለከተ፡- የጠፋ ሰው ጋብቻ የሚፈርሰው መጥፋት ማስታወቂያ ፍርድ የመጨረሻ በሆነበት ቀን ነው ሲል የፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 183 ይደነግጋል፡፡ የመጨረሻዎቹ ወሬዎች ከተሰሙበት በኋላ የተፈፀሙት የወንዱ ወይም የሴቲቱ ጋብቻ ጠፋ የተባለው ሰው ካልሆነ በስተቀር ማንም ሊቃወም እንደማይችል አንቀፅ 183(2) ያስረዳል፡፡ ነገር ግን የመጥፋት ማስታወቂያ ክስ በተጀመረበት ቀን ጠፋ የተባለው ሰው በህይወት መኖሩን ዓቃቤ ህግ ካረጋገጠ በፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ አንቀፅ 183(3) መሰረት መቃወሚያ ሊያቀርብ ይችላል፡፡

 ውርስን በተመለከተ፡- ጠፋ የተባለው ሰው የመጨረሻዎቹ ወሬዎች ከደረሱ በኋላ በህይወት ቢኖር ኖሮ እርሱ ሊወርስ በሚችለው የአወራረስ ስርአት መሰረት ለእርሱ ሊደርስ የሚቸለውን ድርሻ ግምት ውስጥ ሳይገባ የውርስ ስርአቱ ይፈፀማል፡፡ ከፍትሀብሔር ህግ አንቀፅ 184(1) ሀሳብ የምንረዳው ነገር ጠፋ የተባለው ሰው ምንም እንኳን በቦታው ባይኖርም የውርስ ድርሻው ይቀመጥለታል ማለት ነው፡፡ ለዚህም አብሮ ወራሽ የሆኑት ጠፋ ለተባለው ሰው ድርሻ መብቶች መድህን እንዲያሲዙ ፍርድ ቤት ሊያዛቸው ይችላል፡፡
የጠፋ ሰው ላይ እዳ፣ ውርስ የመሳሰሉት መብቶች ያላቸው እንደሆነ መጥፋትን በሚወስነው ፍርድ መጨረሻ ከሆነበት ቀን አንስቶ እንደሞተ ተቆጥሮ የመብቶቹ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በአንቀፅ 185(1) ስር ተደንግጓል፡፡ ጠፋ የተባለው ሰው መብት ተካፋይ ብቻ ሳይሆን የሚያወርሰው ነገርም ሊኖረው ሲችል ጠፋ የተባለው ሰው ኑዛዜ ያለው እንደሆነ ውርሱ የሚከፈተው የመጨረሻ ወሬው በተሰማበት ቀን ባለጉዳዮቹ (ወራሾቹ) በሚያነሱት ጥያቄ መሰረት ኑዛዜ ይፈሳል (ያነገራል)፡፡ ጠፋ የተባለውን ሰው የውርስ ንብረቶችን አጠቃቀም በተመለከተ እንደ መልካም ቤተዘመድ አባት ሆኖ ጠፋ የተባለው ሰው ሊመለስ ቢችል እንኳን በሚል ተመላሽ ስለሚሆን የንብረቶቹን ዋስ እንዲጠራ ወይም ማረጋገጫ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቶች ሊያስገድድ ይችላል፡፡
የጠፋውን ሰው ንብረት ባለይዞታ የሆነ ሰው በሶስት ወር ውስጥ የተቀበላቸውን ንብረቶች በስራ ላይ ማዋል እንዳለበት እንደተጠበቀ ሆኖ ንብረቱ የጠፋውን ሰው ልጅ ለማቋቋም ከሆነ በስጦታ ማስተላለፍ ይቻላል፡፡ የመጥፋት ውሳኔ የተሰጠበት ሰውን ንብረት በማንኛውም ሁኔታ በስጦታ ማስተላለፍ እንደማይቻል ተደንግጓል፡፡

የመጥፋት ውሣኔን ውጤት ቀሪ የሚያደርጉ ምክንያቶች

ጠፍቷል የተባለው ሰው መመለስ(የመጣ) እንደሆነ፣

ጠፍቷል የሚባለው የፍርድ ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ በህይወት ለመኖሩ አስረጂ የተገኘ እንደሆነ፣

የመጨረሻ ወሬዎቹ የተሰሙበት ተብሎ ከተወሰነው ግዜ በሌላ ጊዜ መሞቱ አስረጂ የተገኘ እንደሆነ መሆኑን በፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 170 ስር ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡

ጠፋ የተባለው ሰው ስለመመለስ

በፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 171 መሠረት ጠፋ የተባለው ሰው በተመለሰ (በመጣ) ጊዜ ንብረቶቹን በሚገኙበት አኳኋን መልሶ የመረከብ እንደዚሁም የተሸጡትን ንብረቶች ዋጋ የማግኘት መብት እንዳለው በግልጽ ተመልክቷል፡፡ ይህን የህግ ሀሳብ በሚያስረግጥ ሁኔታ ጠፋ የተባለው ሰው ንብረት መሸጡ ከተረጋገጠ ከተጠቀሰው ድንጋጌ አኳያ ሊረከብ የሚገባው የተሸጠውን ንብረት ሣይሆን የሽያጩን ዋጋ ነው በማለት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 30298 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ ነገር ግን በተንኮል እና በክፉ ልቦና ካልሆነ በስተቀር ጠፋ የተባለውን ሰው ንብረት ገቢዎች በይዞታቸው ስር አድርገው ሲጠቀሙ የነበሩትን ገቢ እንዲመልሱ አይጠየቁም፡፡

በአጠቃላይ በአንድ ሰው በመጥፋቱ ምክንያት በቤተሰብ እና በንብረቶች ላይ ውጤት ያለው በመሆኑ በዳኞች የመጣፋተ ውሳኔ ሲተላላፍ ከፍትሀብሔር ህጉ መንፈስ አንፃር ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል፡፡ እንዲሁም ጠፋ የተባለው ሰው ሊመለስ የሚችልበት አግባብ ስለሚኖር ለንብረቶቹ ዋስትና ማስያዝ ላይ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

ስለዚህ አንድ ሰው ከዋና መኖሪያ ከጠፋ ማንም ሰው የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጥ ለማመልከት ይችላል፡፡ የመጥፋት ውሳኔን ለመስጠት ዳኞች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ከህጉ የምንረዳው ነው፡፡ ለዚህም የሰውየውን መጥፋት ለመረዳት ዳኞች ከዓቃቤ ህግ ጋር በመተባበር በማናቸውም ቦታ ይልቁንም የጠፋው ሰው የመጨረሻ ይኖርበት ከነበረው ቦታ እና በመጨረሻ መኖሩ የታየበት ቦታ ጠፋ የሚባለው ሰው ስለመኖሩ ምርመራ እንዲደረግ በማዘዝ እንደሆነ የፍትሐብሄር ህግ አንቀፅ 156 ስር ተደንግጓ እናገኘዋለን፡፡
ይኸውም ዓቃቤ ህግ ስለመጥፋቱ የቀረበውን ማመልከቻ እና ማስረጃዎች ፍርድ ቤቱ ወደ ትክክለኛ ውሳኔ ለመድረስ የሚያስችለውን ማስረጃ ዓቃቤ ህጉን ተቃርኖ የበለጠ እንዲረጋገጥ በማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ ዳኞች የጠፋው ሰው አጠፋፍ ‹መሞት የሚመስል› መሆኑን የማረጋገጥ ግዴታ ይጣልባቸዋል፡፡ መጥፋቱን ከተረዱት በፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 157 መሰረት የመጥፋት ውሳኔ የመጨረሻ ወሬዎቹን የተሰማበትን ቀን በመጥቀስ ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡
በሌላ በኩል ዳኞቹ ያገኙት ማስረጃ ወደሞት የሚያመዝን መስሎ ከታያቸው ‹የሞት ማስታወቂያ› ፍርድ ይሠጣሉ ሲል የፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 157(1) ደንግጓል፡፡ ዳኞች እንደነገሩ ሁኔታ የመጥፋት ውሳኔውን ወይም የመጥፋት ውሳኔ ማስታወቂያን ለአንድ አመት መቅጠር የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን የመጥፋት ውሳኔው ከተጠየቀ ከአንድ አመት በኋላ ወይም ሰውየው ከጠፋ አምስት አመት በኋላ የመጥፋት ውሳኔ መሰጠት አለበት፡፡

በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

Via minister ⚖️ justice

law
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ኖርዌይ፣ አየርላንድና ስፔን ፍልስጤምን በነጻ አገርነት እውቅና እንደሚሰጡ ይፋ አደረጉ
የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ግብይት ሳይኖር ደረሰኝ ሲሸጡ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
law

ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል የፈጸሙ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ

September 20, 2025
law

እነ ቀሲስ በላይ በሙስና ወንጀል ሊፈርድባቸው እንደማይገባ ጠቅሰው ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ ሆነ

July 26, 2025
law

የአዲስ አበባ የከንቲባ ፅ.ቤት ፕሮቶኮልን ጨምሮ 12 ተከሳሾች በሌብነት ተከሰው ተፈረደባቸው

July 23, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2