Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Western Pressure on Ethiopia Intended to See Weak Gov’t, Nation – Scholars

    July 10, 20210

    Journalist demands UNWFP to tell truth about missing trucks

    October 3, 20210

    ብርሃኑ ባይህ እና አዲስ ተድላ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ

    December 19, 20200

    አብንና ባልደራስ ከተሸነፉ ” ውጤቱን አንቀበልም” ሊሉ የሚችሉ ፓርቲዎች እንደሚሆኑ ዲፕሎማቶች ገለጹ

    May 23, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሚስጥራዊ የቻይና ፖሊስ ጣቢያዎች በአሜሪካ ተገኙ

    December 19, 20240

    ሦስተኛው ዕድል እንዳይባክን … !

    May 21, 20220

    “Why I decided to extend my time at the club”

    May 24, 20230

    የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ዋና የጦሩ መሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ

    February 24, 20220

    “Ethiopia’s success reflects a new alternative for Africa’s development”

    January 29, 20240
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  TIPS 1  አብይ አህመድና – የእስር፣ የእገታ፣ የግድያ ሙከራና “የእረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” ዘመቻ መክሰም
TIPS 1

አብይ አህመድና – የእስር፣ የእገታ፣ የግድያ ሙከራና “የእረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” ዘመቻ መክሰም

Ethioreview newsEthioreview news—October 19, 20240
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በኢትዮጵያ ታሪክ የክብር ኒሻን ተሸልመው በሰላም ከስልጠን የወረዱ ኢታማዡር ጀነራል ሳሞራ የኑስ በትግርኛ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን እንዲያስሩ ከደህንነት ኃላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋ ለቀርበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ አነጋጋሪ ሆኗል። ጉዳኡ አነጋጋሪ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸውም ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በሁዋላ በዚህ ደረጃ ትህነግ ሊያጠፋቸው የወሰኑበት ምክንያት ነው። በተለይም የቀድሞው የኢንሳ ዳሬክተር ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጠላት ስለሆኑ “ልንታገላቸው ይገባል ሲሉ ኮነኑ የቀድሞው የኢንሳ ዳሬክተር “አስወግዱት” ተብለን ነበር ካሉትና ዲጂታል ወያኔ “እረኛውን ምታ መንጎቹ ይበተናል” በሚል ይፋ ያደረገው ዘመቻ ዋና አጀንዳ ሆነዋል።

የቀድሞው የኢንሳ ዳሬክተር የነበሩት ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ጠላት ስለሆኑ ልንታገላቸው ይገባል” ሲሉ ወደ ትግራይ ካፈገፈጉ በሁዋላ በይፋ ሲናገሩ እንዳስታወቁት ” ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አስወግዱት” ብለዋቸው እንደነበር ማስታወቃቸው በወቅቱ ከፈተኛ መነጋገሪያ ጉዳይ እንደነበር የሚታወስ ነው። በውቅቱ ግን አብይን የማስወገዱ ውሳኔ ቸል የተባለው ምንም አያመጣም የሚልና ኦርሞ ይቆጣል ከሚል ፍርሃቻ እንደነበር የቀድሞ የኢንሳ ኃላፊ አመልክተዋ ነበር። በቃለ ምልልሳቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጋር የተነጋገሩት እንደወረደ

  • እኔ ግን ” ወደ ኦሮሞዎቹ ሄዶ ወደ ላይኛው እርከን ከወጣ ችግር ይፈጥርብናል።ሳናባረው እዚሁ ከኛ ጋር እንዳይላወስ አድርገን ኩርምት ብሎ እንዲቀመጥ በማድረግ contain እናደርገዋለን ” አልኩት።
  • መለስ ዜናዊ ግን ” ኖ ኖ ምክንያት ካገኘህለት ዝም ብለህ ብቻ አስወግደው” አለኝ ።
  • እኔም ” ምክንያት እማ ሞልቷል ብዬ 4 እና 5 ምክንያቶችን ጠቅሼ አቢይን አባረርኩት “
    -አቢይ በዚህ ተበሳጭቶ አልቃቅሶ ወጣ። ጀነራሉ ይህን አስከትለው ሌለም ሌላም እያሉ ይቀጥላሉ

ለውጡን ተከትሎ “ዲጂታል ወያኔ” በሚል የተቋቋመው ሰራዊት በዋናነት በማህበራዊ ሚዲያ፣ በመገናኛ አውታሮችና በተገኘው አጋጣሚ ሆኑ “እረኛውን ምታ መንጋው ይበተናል” መሪ አጀንዳ ይዘው መነሳታቸው፣ በሚያስገርም ሁኔታ ሰባት ቀን ሃያ አራት ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ የተተከለ ዘመቻ ሲያካሂዱ እንደነበር፣ አሁን በሽንፈትና በበጀት ምክንያት ቢፋዘዝም እንዳልቆመ መረጃ ያላቸው በተደጋጋሚ ይፋ ማድረጋቸው እየተነሳ ዛሬ መነጋገሪያ ሆኗል። መነጋገሪያ የሆነውም “ለምን በዚህ ደረጃ ትህነግ አብይን ፈራ ወይም ጠላ ወይም ሊያጠለቸው በጀት በጀተ” የሚለው ነው።

ከዚህ ሁሉ ወጥመድና ዕቅድ ተርፈው ግዙፍ ኃይል የገነቡት፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑት አብይ አህመድ ” ያደረገልኝን ስለማውቅ እግዚአብሄርን አመስግናለሁ” ያሉበት ምክንያት እያደር ይፋ እየሆነ ነው። አብይ አህመድ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲያኮበኩቡ ጀምሮ ሲሽከረከሯቸው የነበሩት አስደንጋጭ መረቦች እንዴት እንደመከኑ በራሱ ትንግርት ነው። ማንንም ለማሰርና ለማስወገድ ፍርሃቻ ያልነበረው ትህነግ እሳቸው ጋር ሲደርስ በዚህ ደረጃ ምን አብረከረከው?

More stories

ቡድኑ [እነ ደብረጽዮን] ለስልጣን ሲሉ ማናቸውንም ጥፋት ከመፈጸም ወድሁዋላ እንደማይሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስጠነቀቀ

November 10, 2024

አቡነ ማትያስ ለጌታቸው ረዳ እና ለደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ምክር እና ተግሳፅ አስተላለፉ ” ቆም ብላችሁ አስቡ “

January 23, 2025

በኬንያ የተቀሰቀሰው የቀረጥ ተቃውሞ ወደ ዝርፊያና ውድመት በማምራቱ ህግ እንዲያስከብር ጦሩ ታዘዘ

June 26, 2024

ከፍተኛ የኦነግ ሰራዊት አመራሮች የሰላም ጥሪ ሊቀበሉ ነው፤ የበታች አመራሮች እጅ እያሰጡ ነው

April 13, 2024

አብይ አህመድን ስልጣን በያዙ ማግስት በሰኔ ለማሰናበት ሙከራ ተድርጉል። ገና መቀመጫቸው ያልጠነከረው አብይ አሕመድ በጠዋቱ የግድያ ሙከራ ማስተናገዳቸው ብቻ ሳይሆን ለውጡን ባልተቀበሉ ቅሬቶች መፈንቅለ መንግስትም ተሞክሮባቸዋል። ከመካከል እምቢ ሲል ከክልል ማፍረስ ለመሞከር በአማራና በሶማሌ ክልል መንግስት ለመፈንቀል ተሞክሮ አሳዛኝ ሪኮርድ ተመዝግቧል። ይህን ሁሉ አልፈው ባዶውን ቤት ገንብተው ወደ ህግ ማስከበር የተሸጋገሩት አብይ በቀጣይ ትግሉ እነደሚቀንስላቸው ቢነገርም ” ኢትዮጵያዊ ” መሆናቸው የእግር እሳት የሆነባቸው ከውስጥና ከውጭ ተናበው የሚያደርጉትን ዘመቻ ገዝግዝ ህዝብ እይነጥፈው እንደሚሄድ በግል አምናለሁ። ምስክሩም ከህግ ማስከበሩ ዘመቻ በሁዋላ “ተምስገን፣ አረፍን” የሚለው ድምጽ ጎልቷልና ….

የጄነራል ሳሞራ ዩኑስ ቃለ ምልልስ ይፋ ያደረገውን የእስር ጥያቄ ተከትሎ፣ የተሰማው ትህነግ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ” አብይን ከህዝብ የመነጠሉ ስራ ስኬታማ ነው” በሚል መገምገሙ ነው። ይህ ግምገማ የተደረገው ጦርነቱ ቢጀመር አብይ አሕመድ ደጋፊ ስላጡ በአጭር ቀን ውስጥ ማስወገድ ይቻላል የሚል ድምዳሜ ለመያዝ እንደነበር ግምገማውን የተከታተሉን በመጥቀስ በወቅቱ ዘግበን ነበር።

ከሰኔ 16 የግድያ ሙከራ፣ ወታደሮች በመላክ በቤተመንግስት አብይን ለማፈን ከተደረገው ሙከራና እነ ጃዋር ኦህዴድን በይፋ ማፍረሳቸውን በሚዲያ ለማወጅ ደቂቃዎች ሲቀሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደርሰው እንዳከሸፉ ለተከታተሉ በርካታ ጥያቄ ያጫረውና ያለፈውን ያስታወሰው የጄነራል ሳሞራ ቃለ ምልልስ ነው።

” መዋጋት ርስት አይደለም። ለ42 ዓመታት በውግያ ቆይቻለሁ። እኔ እጣ ፈንታዬ መዋጋት ነው ብዬ አላምን ፤ አቋሜ ውግያ አያስፈልግም ይቁም የሚል ነበር ፤ አሁንም አቋሜ ያው ነው የተለወጠ የለም !! ” ጄነራል ሳሞራ የኑስ

ከሰሞኑን የቀድሞው የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሳሞራ የኑስ አነጋጋሪ ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር። ከረጅም ጊዜ በኃላ ወደ ሚዲያ ቀርበው ቃላቸውን የሰጡት ብራኸ (ከፍታ) ለተሰኘ በዩትዩብ ላይ ለሚተላለፍ ፕሮግራም ነበር።

በዚሁ ቃለ ምልልስ የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከመተካታቸው በፊት በእሳቸው (ጄነራል ሳሞራ) እና በአገር ድህንነት ሃላፊ በነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ መካከል አለመጣጣም እንደነበር አስታውቀዋል። በዚህም ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር እያሉ እንዲያስሯቸው ሲጠይቋቸው በአቶ ጌታቸው አሰፋ ሲጠየቁ ” አላስርም ! ” ማለታቸውን አንሰተዋል።

” ያኔ ዐብይን እሰረው ተብዬ አይሆንም ካልኩኝ ዛሬም ልክ ነኝ። ምክንያቱ እኔ የሰራዊት መሪ እንጂ የሲቪል ፓለቲከኛ አሳሪና መሃሪ አይደለሁም። መከላከያ ሲቪል ፓለቲከኛ የማሰር ስልጣንና መብት የለውም” ሲሉ ይፋ እንዳደረጉት የአቶ ዴታቸው አሰፋን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸውን በዝርዝር አስረድተዋል።

“በውቀቱ አብይ የአንድ ታላቅ ክልልና ህዝብ አመራር ነበር። ታላቁ ህዝብ ማለት ኦሮሞ ነው። ያኔ የኦሮሞ ህዝብ መሪ የፓለቲካ ድርጅት የነበረው ኦህዴድ ነው። የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አብይ ነበር። በተጨማሪም የፓርላማ የህዝብ ተመራጭ አባል ነበር” ሲሉ ማሰር ያልቻሉበትን ፖለቲካዊና ስነልቦናዊ ምክንያታቸውን ይፋ አድርገዋል። “አብይ ያኔ መታሰር ከነበረበት ጥንካሬና ድክመቱ ወደ ሳራሞራ ሳይሆን ወደ ፓርለማ ነው የሚወሰደው። ከፓርላማ ካለፈ ወደ ያኔው የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ይቀርባል” በማለትም ሂደቱ እንዴት ሊስተናገድ እንደሚገባ አስረድተዋል።

የኢህአዴግ ሊቀመንበሩና ጠ/ ሚንስትሩ የዐብይ ድክመት ልክ ነው ብሎ ካመነበት ከፓርላማ ሃላፊነቱ ማንሳት እንደሚኖርበት ሳሞራ አመልክተዋል። ካልሆነም ሃይለማርያም ደሳለኝ ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የማሰር ስልጣን ስለሌላቸው ጉዳዩን ወደ ኦህዴድ ሊመሩት እንደሚገባም ሳሞራ ዩኑስ መናገራቸውን ቲክቫህ ወደ አማርኛ መርልሶ ካቀረበርው ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል።

“ኦህዴድ ካመነበት ደግሞ ይታሰር ብሎ ከወሰነ የሚመለከተው የህግ አካል እንጂ ሳሞራ ዐብይን የማሰር ስልጣን የለውም ” ሲሉ አቋማቸውን ይፋ ያደረጉት ሳሞራ ዩኑስ ጦርነትን አጥብቀው እንደሚቃወሙ፣ አስቀድመውም ጦርነት እንዳይካሄድ ምክር ሲሰጡ እንደነበር ተናግረዋል።

ጀነራሉ በዚሁ ጦርነትን በሚቃወመው አቋማቸው ሳቢያ በርካታ ሃሜቶችና ትችቶች ሲሰነዘርባቸው እንደነበር ይታወሳል። ለዚሁ ያለፈ ትችት መልስ ይሆን ዘነድ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ በርካታ ጉዳዮች አንስተዋል። በተለይም ” ጄነራል ሳሞራ ከፌዴራል መንግሥት ጋር ወግነው በድብቅ ጦርነት መርተዋል ተሳትፈዋል ” ለሚለው ወሬ “ጦርነቱ የከበዳቸው የትግራይ ፓለቲከኞች ለድክመታቸው መሸፈኛ የፈጠሩት ምክንያት ነው ፤ ጦርነቱ ሲጀመርም ሆነ ሲፋፋም ከቤተሰቦቼ ጋር አዲስ አበባ ነበርኩ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

መዋጋት ርስት እንዳልሆነ ፤ ለ42 ዓመታት በውግያ እንደቆዩ፣ እጣ ፈንታቸው ውግያ ነው ብለው እንደማያምኑ፤ አቋማቸው ውግያ አያስፈልግም የሚል እንደሆነ ፤ ይህ አቋማቸው አሁን ድረስ የጸና እንደሆነ ተናግረዋል።

ጦርነቱ በተጀመረ ማግስት መንግስትንና ጀነራሎቹን ጦርነቱ እንዲቆም እንደጠየቁ፣ እስከ መጨረሻ ድረስም ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ ጥረት እንዳደረጉ ያወሱት ጀነራል ሳሞራ፣ “የትግራይ ህዝብ ሃያ ዓመት እየቆጠረ መዋጋትየለበትም” ብለዋል። የትግራይ ህዝብ ጦርነት እንደሰለቸው፣ የሰላም አርአያ መሆን እንደሚፈልግ፣ ፓለቲከኞችም የህዝበ ሰላም መጠበቅ እንዳለባቸው በቃለ ምልልሳቸው አመልክተዋል።

“እምነታቸው የትግራይ ህዝብ መዋጋት የለበትም” የሚል እንደሆነ ያመለከቱት ጀነራሉ፣ እንደ አመራር ህዝቡ ወደ ውግያ መግፋት አግባብ እንዳልሆነ አውግዘው ተናግረዋል። ውግያ ሲጀመር አከባቢ ጠ/ሚ አብይን እና አቶ ግርማ ብሩን አግኝተው ውግያ እንዳይጀመር እንደጠየቁ ፤ እነሱም እንደ አመራር የሰጧቸው መልስ እንዳለ አምልክተዋል። መልሳቸውን በትርጉሙ መረጃ ውስጥ ምን እንደነበር ግን አልተብራራም።

በትግራዩ ጦርነት በትግራይ ህዝብ ላይ እልቂት መፈጸሙን እንደሚያምኑ፤ የትግራዩ ጦርነት መንስኤ የፓለቲካ ብልሽት ፤ የአመራሮች መበስበስና ከህዝብ አገልጋላይነት መውጣት ውጤት እነደሆነ፤ የአማራ ኤሊቶች የትግራዩ ጦርነት አንዲጋጋል ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ በርካታ እላፊ ነገሮች እንደተናገሩ፤ የትግራዩ ጦርነት ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የተወጣጡ ወታደሮች የተሳተፉበት ቢሆንም የሁሉም ክልሎች ህዝብ ደግፎታል ተሳትፎበታል ማለት እንዳልሆነ አመልክተዋል።

በትግራይ ጦርነት የሻዕብያ ሃይል አጋጣሚው በመጠቀም የትግራይን ህዝብ ያለ ስሙ ስም በመስጠት አንገቱ ለማስደፋትና ለማጥፋት እንደዘመተ ሳሞራ በቁጭት ስሜት ተናግረዋል።

ከጦርነቱ በፊት ከምርጫው ጋር ተያይዞ የነበሩት የእልህ አገላለጾችና አካሄድ እንዲቆሙ በሁለቱም በኩል ሲገስጹ እንደነበር፤ ጦርነቱ እንዳይነሳ ፤ ከዛም እንዲቆም ብዙ ጥረት እንዳደረጉ፤ ያልተዘጋጁበትን፣ ያላመኑበትን ወግያ እንደማይሳተፉ፣ እንደማይዋጉ በይፋ አቋም መያዝቸውን አስታውቀዋል።

የጄነራሉ አቋም ዛሬ በሰጡት ቃለ ምልልስ የተሰማ ወይስ ቀደም ሲል የነበረ? ለሚለው ቲክቫኽ ከ5 ዓመታት በፊት በ2012 ዓ.ም ህዳርና ታህሳስ ወር ላይ እንዲሁም ጦርነቱ ተጀምሮ የፌደራል መንግስት መቐለ በተቆጣጠረበት ወቅት የካቲት 2013 ዓ.ም በአካልና በስልክ ባደረገው ግንኙነት የሰጡትን ምላሽ አስታውሷል።

ጀነራል ሳሞራ ሀገራዊ ኒሻን ተሸልመው በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ በመቐለ ከተማ ፕላኔት ሆቴል አግኝቶ ቲክቫኽ ሲያናግራቸው በዚህም በዚያም በወጣቶች የሚታይ የነበረው የጦረኝነት ስሜት ፓለቲከኞቹ በማርገብ ሃላፊነታቸው እንዲወጡ ወታደራዊ ምክር ሰጥተው እንደነበር በማስታወስ አቋማቸው አውዳሚው ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት የተያዘ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።

ጥር 2012 ዓ/ም ደጀና ላይ 45ኛው የህወሓት የምስረታ በዓል ለማክበር ለተሰባሰቡት ወጣቶች ባሰሙት ንግግር፣ ወጣቶች ከዚህም ከዚያም ያሉ ፓለቲከኞች በሚለኩሱት ጦርነት ገብተው እንዳይቃጠሉ የሚያስገነዝብ አባታዊና ወታደራዊ ምክር አስተላልፈው ነበር። ጦርነቱ ከተጀመረ እና ከተባባሰ በኃላ በሰጡትም አስተያየት ጦርነትን ከበፊቱ የባሰ እንደተጠየፉት ገልፀውለት ነበር።

“አብይን አስወግደው አለኝ” – በቁጭት እየወጡ ያሉ ሚስጢሮች

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

በዓለም መድረክ ኢትዮጵያን ከፍ ያደረጉ ታዳጊዎች
Israel eyes Somaliland base bid to counter threats from Yemen’s Houthis, bolster security
Related posts
  • Related posts
  • More from author
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 20250
TIPS 1

Almost a third of people in Gaza not eating for days, UN food programme warns

July 26, 20250
TIPS 1

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios

July 20, 20250
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news