Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  TIPS 1  አቡነ ማትያስ ለጌታቸው ረዳ እና ለደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ምክር እና ተግሳፅ አስተላለፉ ” ቆም ብላችሁ አስቡ “
TIPS 1

አቡነ ማትያስ ለጌታቸው ረዳ እና ለደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ምክር እና ተግሳፅ አስተላለፉ ” ቆም ብላችሁ አስቡ “

Ethioreview newsEthioreview news—January 23, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

” እየሄዳችሁበት ያለው መንገድ ሁሉንም የሚያጠፋ ፤ የተገኘችውንም ሰላም የሚያደፈርስ በመሆኑ ህዝባችሁ የሚሰጣችሁ ምክር እና ተግሳፅ ተቀብላችሁ በስክነት እና በማስተዋል የህዝባችሁን ጥያቄ እንድትመልሱ አደራ እንላለን ” – ቅዱስነታቸው

ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት  ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ምክር እና ተግሳፅ አስተላለፉ።

ቅዱስነታቸው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ጥር 6/2017 ዓ/ም በፃፉት ደብዳቤ ነው።

ቅዱስነታቸው በዚሁ ደብዳቤ ፤ ሁለቱን አመራሮች በአካል አግኝተው ለማነጋገር  እንዳልተሳካላቸው ገልፀው ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ መሄዳቸው አሳስቧቸው ለመሪዎቹ ሃሳባቸው በፅሁፍ ለመገለፅ መገደዳቸው አስፍረዋል።

አመራሮቹ በትግራይ ያለው ጊዜ የማይሰጥ ተደራራቢ ችግር ከመፍታት ይልቅ ከመደማመጥ እና መከባበር በወጣ አኳኋን  እርስ በርስ በመዘላለፍ መጠመዳቸው እንዳሳዘናቸው ጠቅሰዋል።

መሪዎቹ ጥበብን እና የሰለጠነ አሰራርን እንዲታጠቁ መክረዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ፤ ” ካህናት አበው ፣ የቤተክርስትያን ሊቃውንት ፣ ምእመናን ፣ የአገር ሽማግሌዎች የዕድሜ ባለፀጎች በሃዘን እያነቡ አካሄዳችሁን እንድታስተካክሉ ሲለምኗችሁ እና ሲመክሯችሁ ሰክናችሁ ማሰብ እና ማዳመጥ የተሰናችሁ ምክንያት ምን ይሆን ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።


” ‘ የእኔ አካሄድ ብቻ ነው ልክ ‘ በሚል እልህ እና አስተሳሰብ የፈረሰ እንጂ የተገነባ ህዝብ እና አገር የለም ” ሲሉ በአፅንኦት ያስገነዘቡት ቅዱስነታቸው ፤ ” የናንተ መለያየት አልበቃ ብሎ በአንድነት እና በመከባበር የኖረውን ህዝብ ለማራራቅ እየሄዳችሁበት ያለው ርቀት ህዝብን ለማገልገል መቆማችሁን ጥያቄ ውስጥ የሚከት የጥፋት እና የመጠፋፋት መንገድ በመሆኑ ቆም ብላችሁ አስቡ ” ሲሉ አሳስበዋል።

ይህ ሳይሆነ ከቀረ መሪዎቹ እየተከተሉት ያለው የጥፋት መንገድ የተገኘውን ሰላም የሚያደፈርስ አገርን እና ህዝብን ለከባድ ቀውስ የሚያጋልጥ እንደሆነ አስረግጠው ገልጸዋል።

የተፈጠረው የሃሳብ አለመጣጣም ለመፍታት ከአመራሮቹ አቅም በላይ እንዳልሆነ ያስታወሱት ቅዱስ ፓትርያርኩ ፥ መሪዎቹ ችግሮቻቸው በጥበብ እና በሰለጠነ አሰራር በመፍታት ጅምር ሰላሙን በማፅናት ህዝባቸውንና አገራቸውን በልማት ለመካስ ከልብ እንዲተጉ የአባትነት ምክራቸውን ደግመው ደጋግመው አስተላልፈዋል።

ጥር 6/2017 ዓ.ም ተፅፎ ዛሬ ጥር 11/2017 ዓ.ም በበዓለ ጥምቀቱ ይፋ የሆነው የቅዱስነታቸው የምክር እና የተግሳፅ ደብዳቤ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት መድረሱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ አባል በስልክ ደውሎ አረጋግጧል።እስካሁን ለደብዳቤው የተሰጠ ምላሽ የለም።

Via Tikvah

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ሩስያ ከዩክሬን ጋር ሰላም ካልፈጠረች ከባድ ቅጣት ይጠብቃታል” ዶናልድ ትራምፕ ሩስያን አስጠነቀቁ
የትግራይ ታጣቂ አመራር መኮንኖች ጊዚያዊ አስተዳደሩ እንዲገለበጥ መወሰናቸውን አስታወቁ፤ ድብረጽዮን የማይመሯት ትግራይ …
Related posts
  • Related posts
  • More from author
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 2025
TIPS 1

Almost a third of people in Gaza not eating for days, UN food programme warns

July 26, 2025
TIPS 1

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios

July 20, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2