Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  law  በሕግ ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ሰው “ድርጅት” የወንጀል ተጠያቂነት በኢትዮጵያ
law

በሕግ ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ሰው “ድርጅት” የወንጀል ተጠያቂነት በኢትዮጵያ

Ethioreview newsEthioreview news—November 21, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በዘመናዊ የህግ ሥርአት የተፈጥሮ ሰው ብቻ ሳይሆን በህግ በግልፅ በተደነገገ ጊዜ ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ድርጅትም የወንጀል ተጠያቂነት ያለበት መሆኑን ማወቅና ድርጅቶችን በወንጀል ተጠያቂ ከሚያደርጉ የወንጀል ተግባራት መታቀብ ያስፈልጋል፡፡


   መግቢያ


በሕግ ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ፡፡ እነሱም የተፈጥሮ ሰው እና በሕግ ሕጋዊ ሰውነት የተሰጠው ሰው ናቸው፡፡ በሕግ ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ሰው ማለት የንግድ ድርጅቶች፣ ማህበራት እና መሰል ሌሎች ድርጅቶችን የሚመለከት ነው፡፡ የተፈጥሮ ሰው ወንጀል ሲሰራ በህግ እንደሚጠየቅ ሁሉ የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በወንጀል የሚጠየቅበት ሁኔታ በህጉ ተመልክቷል፡፡ በዚህ ፅሁፍ በሀገራችን ድርጅት በወንጀል የሚጠየቅበትን ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን እንዳስሳለን፡፡

  የድርጅት ምንነት


በሀገራችን የድርጅት የወንጀል ተጠያቂነትን በተመለከተ መነሻ የሆነው የወንጀል ህጉ አንቀፅ 34 ሲሆን ለድንጋጌው አላማ የድርጅትን ምንነት ትርጓሜ ሰጥቶ እናገኛለን፡፡ በዚህ ድንጋጌ ንኡስ አንቀፅ 4 መሰረት “ድርጅት” ማለት መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ወይም ሕዝባዊም ሆነ ግላዊ መዋቅር ያለው አካል ሲሆን ለንግድ፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለፖለቲካ፣ ለሃይማኖት ወይም ለሌላ ሕጋዊ ዓላማ የተቋቋመንና በመንግስት ዕውቅና ያገኘን ማናቸውንም ማኅበር እንደሚያጠቃልል ደንግጓል፡፡ ሆኖም የመንግስት አስተዳደር አካላት ወይም ተቋማት በህግ ሰውነት የተሰጣቸው ቢሆንም በዚህ ድንጋጌ ውስጥ በድርጅትነት የሚሸፈኑ አይደሉም፡፡

  ድርጅት በወንጀል የሚጠየቅበት ሁኔታ

More stories

ሿሿ – ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 25 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

May 20, 2023

አሸባሪ ቡድኑ በአማራና በአፋር የፈጸማቸውን ወንጀሎች የሚያጣራ ግብረ ኃይል ሥራውን ጀመረ

December 27, 2021

በአደገኛ ዕፅ ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች ከ2 ዓመት እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ

October 24, 2024

የሃጫሉ ገዳዮች የተባሉት ” ጥፋተኛ” ተባሉ

July 5, 2021


የሕግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በወንጀል ተጠያቂ ሊሆን የሚችለው በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 34 በተመለከቱት ሁኔታዎች ነው፡፡ ይኸውም
 አንድ የወንጀል ድርጊት በድርጅት ከተፈፀመ አስቀጪ እንደሆነ በህጉ በግልፅ ሲደነገግ እና
 ከሀላፊዎቹ ወይም ከሰራተኞቹ አንዱ ከድርጅቱ ሥራ ጋር በተያያዘ የድርጅቱን ጥቅም በህገወጥ መንገድ ለማራመድ በማሰብ ወይም የድርጅቱን ህጋዊ ግዴታ በመጣስ ወይም ድርጅቱን በመሳሪያነት ያለአግባብ በመጠቀም በዋና ወንጀል አድራጊነት፣ በአነሳሽነት ወይም በአባሪነት ወንጀል ካደረገ ነው፡፡

  የድርጅትን የወንጀል ተጠያቂነት ያካተቱ ህጎች


ድርጅት በወንጀል ሊጠየቅ የሚችለው አንድ ወንጀል በድርጅት በተፈፀመ ጊዜ ድርጅቱ በወንጀል ሊጠየቅ እንደሚችል በህጉ በግልፅ ሲደነገግ ነው፡፡ ይህን መነሻ በማድረግም በሀገራችን በሥራ ላይ ያሉ በርካታ የወንጀል ድንጋጌዎችን ያካተቱ ልዩ ህጎች ድርጅት በወንጀል ተጠያቂ የሚሆንባቸውን ሁኔታዎች ደንግገዋል፡፡ ለአብነት የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 881/2007 በአዋጁ አንቀጽ 5፣ በፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 132፣ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀፅ 33፣ በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀፅ 18፣ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀፅ 17 እና የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥር አዋጅ 1177/2012 አንቀፅ 22(11) ይጠቀሳሉ፡፡

   ህጋዊ ሰውነት በተሰጠው ድርጅት ላይ የሚጣል የወንጀል ቅጣት


ድርጅት በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝም ድርጅትን እንደተፈጥሮ ሰው ማሰር ስለማይቻል  በድርጅት ላይ በዋናነት የሚጣለው ቅጣት በወንጀል ህጉ አንቀፅ 90(3) የተመለከተው የገንዘብ መቀጮ ነው። ይህ ማለት አንድ ወንጀል በተፈጥሮ ሰው ሲፈፀም በእስራት የሚያስቀጣ ከሆነ እና  ወንጀል ፈፃሚው ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ሆኖ ከተገኘ ለእስራቱ ተመጣጣኝ ነው ተብሎ በህጉ በተደነገገው የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ማለት ነው፡፡ ከመቀጮ በተጨማሪ በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ድርጅት እንዲታገድ፣ እንዲፈርስ፣ እንዲዘጋ ሊወሰን እንደሚችል ከወንጀል ሕጉ አንቀፅ 34(2) መረዳት ይቻላል፡፡

በወንጀል ህጉ አንቀጽ 90(3) መሰረት የመንግስት የአስተዳደር አካላትን ሳይጨምር የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት በወንጀል ተካፋይ ሆኖ ሲገኝ የድርጅቱ ሀላፊዎች ወይም ሰራተኞች በየግላቸው መጠየቃቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጅቱ ወንጀል ተጠያቂ ተደርጎ
1. እስከ 5 አመት ቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ አስር ሺህ ብር
2. እስከ 5 አመት ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ ሀያ ሺህ ብር
3. እስከ 10 አመት ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ ሀምሳ ሺህ ብር
4. ከ10 አመት በላይ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር፣ መቀጮ እንዲከፍል ይወሰንበታል፡፡
የህግ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ጥፋተኛ የተባለበት ድንጋጌ በመቀጮ ብቻ ሚያስቀጣ በሆነ ጊዜ ደግሞ በድርጅቱ ላይ ሚጣለው ቅጣት የመቀጮውን አምስት እጥፍ እንደሚሆን በወንጀል ህጉ አንቀፅ 90(4) ተደንግጓል፡፡  
ሆኖም ይህ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 90 የተደነገገው ቢኖርም በልዩ ህጎች የተለየ ቅጣት ሊቀመጥ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀፅ 18 መሰረት
1. በቀላል እስራት ወይም እስከ 5 አመት ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል እስከ አምስት መቶ ሺህ ብር
2. ከ5 አመት እስከ 15 አመት ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል ከአምስት መቶ ሺህ እሰከ አንድ ሚሊዮን ብር
3. ከ15 እስከ 20 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል ከአንድ ሚሊዮን እስከ ሁለት ሚሊዮን ብር
4. ከ20 አመት በላይ በሆነ እስራት ወይም ሞት ለሚያስቀጣ ወንጀል ከሁለት ሚሊዮን እስከ ሶስት ሚሊዮን ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡

በተመሳሳይ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ ቁጥር 1176/2012፣ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2012 እንዲሁም የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ ቁጥር 881/2007 ለድርጅት ተፈፃሚ የሚሆን የየራሳቸውን የመቀጮ መጠን ደንግገዋል፡፡


    ማጠቃለያ
በአጠቃላይ በዘመናዊ የህግ ሥርአት የተፈጥሮ ሰው ብቻ ሳይሆን በህግ በግልፅ በተደነገገ ጊዜ ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ድርጅትም የወንጀል ተጠያቂነት ያለበት መሆኑን ማወቅና ድርጅቶችን በወንጀል ተጠያቂ ከሚያደርጉ የወንጀል ተግባራት መታቀብ ያስፈልጋል፡፡

ፍትህ ሚኒስቴር

law
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የትህነግ ታጣቂዎች በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ትጥቅ እየፈቱ ወደ ተሃድሶ ማዕከላት መግባት ጀመሩ፤ መንግስት 1 ቢሊዮን መደበ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
law

ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል የፈጸሙ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ

September 20, 2025
law

እነ ቀሲስ በላይ በሙስና ወንጀል ሊፈርድባቸው እንደማይገባ ጠቅሰው ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ ሆነ

July 26, 2025
law

የአዲስ አበባ የከንቲባ ፅ.ቤት ፕሮቶኮልን ጨምሮ 12 ተከሳሾች በሌብነት ተከሰው ተፈረደባቸው

July 23, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2