አዲስ ጦርነት እያንዣበበ ነው። በግብጽ መሪነት ከሱዳን በሚነሳ ኃይል፣ የኤርትራ፣ ወያኔ፣ ከአማራና ኦሮሞ ክልል ጥቂት የተሸጡ በጋራ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያለመውን ጦርነት ለመክፈት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ሪፖርቶች እየጠቆሙ ነው። ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሁለት ዓመት ተኩል በኋላ አንድ ሚሊዮን ይሚጠጉ ንጹህ ዜጎችን ባረገፈው ጦርነት ዋና ተዋናይ የነበረው ሻዕቢያ ዋና ተዋናይ የሆነበት ትግራይን ማዕከል ያደረገው ጦሮነት ውጤቱ በሁሉም አቅጣጫ ፍርሃት አንግሷል።
ኢትዮጵያ ጦርነቱ የውክላና መሆኑን ጠቅሳ ዓለም እንዲያውቅ በጠየቀቸበት ደብዳቤ፣ በፓርላማና በተለያዩ መድረኮች ጦርነት እንደማትፈልግ ስታስታውቅ፣ ያነሳችው ጉዳይ ቢኖር ትንኮሳ ካለ ምላሹ የከፋ እንደሚሆን ብቻ ነው።
“በሰሜን ኢትዮጵያ ከሰላም ስምምነት ሁለት ዓመት ተኩል በኋላ ዳግም ውጥረቱ እየጨመረ ነው። ኤርትራ በአካባቢው አለመረጋጋትን ለመዝራት ያሰበች ይመስላል” ሲል የጀርመን ድምጽ እንግሊዝኛ አገልግሎት ባቀረበው ሰፊ ትንተና ኤርትራ ከጦርነቱ ያሰላችውን ጥቅም አትቷል።
በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሩን በኃይል ያፈረሰው የእነ ዶክተር ደብረጽዮን ቡድን ወታደራዊ መኮንኖቹን ለጦርነት ዝግጁ ማድረጉ ደግሞ አፍሪካን ኢንተለጀንስ አስታውቋል። ይኸው ቡድን ጦርነቱን ለመጀመር አራት የሲቪል እና አምስት ወታደራዊ አመራሮችን በጥቅሉ ዘጠኝ አባላትን ያካተተ ወታደራዊ የዕዝ ማዕከል (Military Command Post) ማደራጀቱን Africa Intelligence ከሰፊ ሀተታ ጋር አቅርቧል።
ከቀናት በፊት የኃይማኖት አባቶችን አዲስ አበባ ልኮ የነበረው የመቀሌው ቡድን ከሻዕቢያ ጋር በማበር ጦርነት ለመክፈት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ በርካታ ማሳያዎች አሉ። የጀርመን ድምጽ እንዳለው የሻዕቢያ ወታደሮች እስከ 10 ኪሎ ሜትር የኢትዮጵያን ክልል ዘልቀው ገብተዋል።
በመቀሌ ነዋሪ የሆነች ሴት “በአሁኑ ጊዜ ምንም ነገር ማቀድ አንችልም” ስትል ለDW ተናግራለች። “ለመዳን እየሞከርን ነው። ነገ አዲስ ጦርነት ሊነሳ ይችላል።” ብዙ ነዋሪዎችን ያጨናነቀውን የፍርሃት አየር ገልጻለች። “ሕይወት በሚያስደንቅ ሁኔታ ውድ ሆኗል ወደ ሥራ ተመልሰን ህይወታችንን ለመገንባት ሰላማዊ መፍትሄ እንፈልጋለን.” ስትል አክላለች።
በትግራይ የተከሰተው ክፍፍል፣ ይህንኑ የውስጥ መለያየት ተከትሎ የተፈጠረው አለመረጋጋትና የፖለቲካ ትርምስ በአንድ ወቅት የበላይነት የነበረውን ትህነግን ከውስጥ የስልጣን ሽኩቻ ጋር ተዳምሮ አድቅቆታል። ይህንኑ የትህነግ መሰባበርና ተጋላጭነት ሻዕቢያ እንደተጠቀመበት የኝኙነኡን መነሻ ያጠኑ ይገልጻሉ። ሻዕቢያን በማዕቀብ አስልሎ ሊውጠው የነበረው ትህነግ በሰሜን ዕዝ ላይ የክህደት ጦርነት ማካሄዱ ጥሩ አጋጣሚ የሆነለት ሻዕቢያ ተንደርድሮ ትግራይ በመግባት የፈጸመውን የሚናገሩ ወገኖች፣ ትህነግ ተመልሶ ሻዕቢያ ስር የወደቀው፣ በትግራይ የፈጸመውን ግፍ ሁሉ ረስቶ ተላላኪ የሆነለት በዚሁ መነሻ እንደሆነ የሚገልጹ ወገኖች “ሻዕቢያ ትህነግን እየተጠቀመበት ነው” ከሚለው የዲደብሊው ትንታኔ ጋር ይስማማ



