Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  ትህነግ ያወደመውንና ያደረሰውን ኪሳራ ስሌት የፌደራል ፖሊስ ይፋ አደረገ፤ ሶስት ቢልዮን ደርሷል
News

ትህነግ ያወደመውንና ያደረሰውን ኪሳራ ስሌት የፌደራል ፖሊስ ይፋ አደረገ፤ ሶስት ቢልዮን ደርሷል

Ethioreview newsEthioreview news—February 10, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጁንታው የህወሓት ቡድን በፈፀመው የሀገር ክህደት ወንጀል በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ ከአገልግሎት ሊገኝ የሚገባ ከ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ተቋማቱ እንዲያጡ ማድረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ቡድኑ በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊትና የመንግስት ተቋማት ጥበቃ ላይ በነበሩ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ላይ የሀገር ክህደት ወንጀል መፈጸሙን ኮሚሽኑ አስታውሷል፡፡

በዚህም በኢትዮ-ቴሌኮም፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድና ኤርፖርቶች ድርጅት እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚገኘው የደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንም ኮሚሽኑ አስታውቋል ።

በዚህ መሰረት በአካባቢው በሚገኙ የኢትዮ ቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ላይ ጁንታው ባደረሰው ጉዳት ተቋሙ ማግኘት ከሚገባው 1 ቢሊየን 370 ሚሊየን 828 ሺህ 689 ብር ማጣቱን በምርመራ መረጋገጡንም ነው ያስታወቀው።

More stories

“ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

April 7, 2021

የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤ አንገታቸው የተቀላ መኮንኖች ፊልም ሊታዩ ነው

May 13, 2021

ከሱዳን የተነሳ የትህነግ ሃይል (ሳምሪ) ሳይዋጋ ሙሉ በሙሉ ተማረከ

August 11, 2021

የመንግስት ማጅራት መቺዎች ፈተና ሆነዋል – ሃላፊዋ አምነዋል

May 9, 2022

በተጨማሪም በተቋሙ ላይ ሊደርስ የነበረና ግምቱ ከ39 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ብር የሆነ የበይነ መረብ ጥቃት ማክሸፍ መቻሉንም ጠቅሷል።

በተመሳሳይ በሰሜን በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ቡድኑ ባደረሰው ጉዳት ተቋሙ 329 ሚሊየን 167 ሺህ 524 ብር ማጣቱ ተረጋግጧልም ነው ያለው።

በዚሁ ጥቃት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በወልቃይት ንዑስ ጣቢያ፣ በማይጨው ንዑስ ጣቢያ፣ በአላማጣ ንዑስ ጣቢያ እና በአሸጎዳ መቐለ ንዑስ ጣቢያዎች ላይ ውድመት የደረሰ ሲሆን በእነዚህ ንዑስ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ጣቢያዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት የምርመራ ቡድኑ በገንዘብ መጠን አስልቶ ወደ ፊት እንደሚገልጽም ጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ቡድኑ በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ላይ ባደረሰው ጉዳት 14 ሚሊየን 49 ሺህ 70 ሊትር ነዳጅ ከመቐለ ነዳጅ ዴፖ በህገ-ወጥ መንገድ ተቀድቶ የተወሰደ ሲሆን በዚህም ድርጅቱ ማግኘት የሚገባውን 258 ሚሊየን 190 ሺህ 998 ብር ማጣቱ በምርመራ ተረጋግጧል ብሏል።

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ አየር መንገድና ኤርፖርቶች ድርጅት ላይ በተፈጸመው ጥቃትም በባህር ዳርና በጎንደር አውሮፕላን ማረፊያዎች ላይ የተተኮሰ ሮኬት በመሰረተ-ልማት ላይ 43 ሚሊየን 349 ሺህ 784 ብር የሚገመት ጉዳት ማድረሱንም ገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም በረራ ወደ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ አክሱም፣ መቐለ፣ ሁመራ፣ ደሴ፣ ላሊበላ፣ ሰመራና ሽሬ ባለመደረጉ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 147 ሚሊየን 640 ሺህ 223 ብር ማግኘት ከሚገባው ገቢ ላይ ያጣ ሲሆን ሁለቱ ድርጅቶች በድምሩ190 ሚሊየን 990 ሺህ 8 ብር የሚገመት ገንዝብ ማጣታቸው ታውቋል።

በሌላ በኩል ጁንታው የህወሓት ቡድን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ቅርንጫፍ በሚገኘው የደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ ሰራተኛ የሆኑትን የተለያዩ ግለሰቦች በመጠቀም በወቅቱ የትግራይ ክልል መንግስት የንግድ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ በነበሩት በዶክተር አብርሃም ተከስተ ትእዛዝ ሰጭነት በአንድ ቀን ብቻ በህገወጥ መንገድ 800 ሚሊየን ብር አውጥተው የተወሰዱ መሆኑ በምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን ከዚህ ባንክ የወጣው ገንዘብ የት እንደደረሰ ወደፊት ምርመራው ሲጠናቀቅ የሚገለጽ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በአጠቃላይ ጁንታው የህወሓት ቡድን በፈፀመው የሀገር ክህደት ወንጀል በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ ታላላቅ መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ ከአገልግሎት ሊገኝ የሚገባው 2 ቢሊየን 949 ሚሊየን 177 ሺህ 220 ብር ተቋማቱ እንዲያጡ ማድረጉንየኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለጹን የዘገበው ፋና ነው።

  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማሳካት ከኮንፌደሬሽን ወደ ፌደራሊዝም ልንመለስ ይገባል !!
Sudan imposes curfew in 3 states to contain protests
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2