Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ፡ ‘ቡልዶዘር’ የተባሉት የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት የጆን ማጉፉሊ ማን ነበሩ?
News

ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ፡ ‘ቡልዶዘር’ የተባሉት የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት የጆን ማጉፉሊ ማን ነበሩ?

Ethioreview newsEthioreview news—March 18, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ ነው ሙሉ ስማቸው። ቡልዶዘር ነው ቅጽል ስማቸው።

ሲወለዱ የጭሰኛ ልጅ ነበሩ። ሲሞቱ ግን ፕሬዝዳንት ነበሩ። ቡልዶዘር የሚለው ቅጽል ስም ከየት መጣ? ቡልዶዘር (ሺዶማ) የተባሉት ያለምክንያት አይደለም።

ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፊት የሥራና ከተማ ሚኒስትር ነበሩ። መንገድ በስፋት ያሠሩ ነበር ያን ጊዜ። የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ነፍሳቸው ነበር ማጉፉሊ። ሕዝቡ ቡልዶዘር ሲል ቅጽል አወጣላቸው። ይህ ቅጽል ስም ግን ኋላ ላይ እየሰፋ ሄዶ መነሻውን ሳተ። ቡልዶዘር የሚለው ስም ሰውየው የመንግሥት ወጪን በመቀነስና ሙሰኞችን መጠራረግ ስለሚወዱም ነው ተባለ። የአስተዳደር ዘያቸው መጠራረግ ስለነበር ስሙ የተስማማቸው ይመስላል።

ማጉፉሊ ሚዲያ ማስደንበር ይወዳሉ፤ ነጻ ድምጾችን ያፍኑም ነበር። ተቃዋሚዎችን አሸብረዋል። ሆኖም ሞታቸውን ያጀበው ያ ሳይሆን ለኮሮናቫይረስ ያሳዩት የነበረው ንቀት ነበር። ምናልባት እሱው ይሆን ከዚህ ዓለም ያሰናበታቸው?

More stories

«የቁንጥጫ ዲፕሎማሲ» የዲፕሎማሲው መንገድ መቀየር !

August 5, 2021

መልስ የሚሻ ዜግነታዊ ጥያቄ – ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ

May 9, 2021

… ሶርያ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የመን 20 ሚሊዮን ህዝብ እንደተራበና እንደተፈናቀለ …

January 29, 2021

የደብረፅዮን የጦርነት ታክቲክ 22

September 12, 2022

“ኮሮናቫይረስ ጂኒ ነው”

ኮሮናቫይረስ ታንዛኒያ ሲገባ ማጉፉሊ ተበሳጩ። ሕዝቡ ቀን ተሌት እንዲሠራ እንጂ ቤቱ እንዲቀመጥ በፍጹም አይፈልጉም። አንድ መላ ዘየዱ። “ሕዝቤ ሆይ! ለዚህ ተህዋሲ አትንበርከክ! ቤተክርስቲያን ሄደህ ጸልይ እንጂ በፍጹም ቤት አትቀመጥ” አሉ። ሕዝቡም ያን አደረገ። “ኮሮና ጂኒ ሰይጣን ነው እንጂ ተህዋሲ አይደለም” የሚለውን ሐሳብ በሕዝባቸው ውስጥ አሰረጹ። ሳይንስ ግን ሰውየውን ታዘባቸው። ቫይረሱም ሳይናደድባቸው አልቀረም።

ከሰኔ 2020 ጀምሮ ማጉፉሊ አገሬ ታንዛኒያ ከኮቪድ-19 ተህዋሲ ነጻ ነች ሲሉ አወጁ። ጭምብል ማጥለቅን ተሳለቁበት። ኮቪድ-19ን ንቀው የዜና ማድመቂያ አደረጉት። በአገራቸው አልበቃ ብሎ ጎረቤት አገሮች የእንቅስቃሴ ገደብ ሲያደርጉ “የማይረቡ ፈሪዎች” አሏቸው። ለምዕራቡ ተንበርካኪ አድርገው ሳሏቸው።

ማጉፉሊ በ2015 የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ፣ ታንዛኒያ የሚያስፈልጓት ዓይነት ፕሬዝዳንት ሆነው ነበር የተገኙት። ሙስናን የሚጸየፉና በሥራ የሚያምኑ። ቀን ተሌት ቢሠሩ አይደክማቸውም።

ቡልዶዘራዊነታቸውን አጠናክረው ቀጠሉበት። ውጤት ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ነድፎ የማስፈጸም አቅማቸው ተደነቀላቸው። ለሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ምሳሌ መሆን ጀመሩ። ገና ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡ በመጀመርያው ቀን የገንዘብ ሚኒስቴር ቢሮ ሄዱ።

ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው ተሟልተው አልተገኙም ነበር። ማጉፉሉ ጦፉ። ይህን በፍጹም እንደማይታገሱ እቅጩን ተናገሩ። ከሥራ የቀረ አለቀለት። ለደመወዝ ቀን ብቅ እያለ የሚጠፋ “ጎስት ዎርከርስ” እየተባለ የሚጠራን ታንዛኒያዊ ጠራርገው አባረሩ። ሥራውን የማይፈልግ የመንግሥት ሠራተኛ ብቻ ነው ከዚያ ወዲህ ከቢሮ ሥራ የሚቀር።

ማጉፉሊ የዛቻ ብቻ አይደለም፤ የድርጊት ሰው ናቸው። ከሥራ የሚቀሩትን ብቻ ሳይሆን ሙሰኛ አለቆችን ጠራርገዋል። አንዳንድ ጊዜ ሹመኞችን የሚያባርሩት ታዲያ በቀጥታ በብሔራዊ ቴሌቪዥን እየታዩ ጭምር ነበር። ለሌላው መቀጣጫ እንዲሆኑ። በዚህ ጊዜ ቡልዶዘር ኑርልን አላቸው አገሬው። እሳቸውም ተበረታቱ። ማጉፉሊ ገና ድሮ ወጪ የሚባል ነገር ያበሳጫቸዋል። በተለይ ያልተገባ ብልጭልጭ ወጪ ታንዛኒያ ማውጣት የለባትም ብለው በጽኑ ያምኑ ነበር። “ምክንያቱም ድሆች ነን” ይላሉ።

ማጉፉሊ በሥራ በዘመቻዎች በመሳተፍ ሠርተው ያሳዩ ነበር
የምስሉ መግለጫ,ማጉፉሊ በሥራ በዘመቻዎች በመሳተፍ ሠርተው ያሳዩ ነበር

በዚህ የተነሳ በድምቀት ይከበሩ የነበሩ በርከት ያሉ ክብረ በዓላትን አስቀርተዋል። በ54 ዓመታት የታንዛኒያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የነጻነት ቀን እንዳይከበር ያደረጉት እሳቸው ናቸው። “ቸበርቻቻ አያስፈልግም ሥራ ነው እንጂ” አሉ። “ሕዝቤ ሆይ! ነጻ የምትወጣው የነጻነት በዓልን በማክበር ሳይሆን ተግቶ በመሥራት ነው፤ ስለዚህ እጅህ መቁሸሽ አለበት” ሲሉ ጮኹ።

ማጉፉሉ ሕዝቡን በማዘዝ ወደ ቅንጡ ቤተ መንግሥት የሚገቡ ሰው አልነበሩም። እሳቸውም በዘመቻ ይሳተፉ ነበር። ሠርተው ያሳያሉ። ለምሳሌ የቤተ መንግሥቱን ደጅ የሚጠርጉት እሳቸው ራሳቸው ነበሩ። ኃላፊዎቻቸው በሆነ ባልሆነው ወደ አሜሪካና አውሮፓ ይጓዙ ነበር። ለሕክምና፣ ለጉብኝት፣ ወዘተ። ይህ ሁሉ የሚሆነው በሕዝብ ገንዘብ ነበር።

አንድ ኃላፊ የውጭ አገር ጉዞ ቢያደርግ ወዮለት ብለው ደነገጉ። ተፈጻሚም ሆነ።

ይህ እርምጃቸው በታንዛኒያውያን ዘንድ እጅግ ተወዶላቸው ነበር። እንዲያውም በማኅበራዊ የትስስር መድረክ መነጋገርያ ሆነው ነበር። “ማጉፉሊ ቀጥሎ ምን ያደርጋሉ” የሚል የድራምባ ሐረግ (Hashtag) ተፈጥሮም ነበር። ማጉፉሊ ከአገራቸው ባሻገር በሌሎች አፍሪካውያን ዘንድ ውስጥ ውስጡን አድናቆት ማግኘት ጀማምረውም ነበር።

ለምሳሌ በ2017 አንድ እውቅ የኬንያ ፕሮፌሰር በዳሬ ሰላም ዩነቨርስቲ ተገኝተው በሰጡት የአደባባይ ዲስኩር “አፍሪካ አዲስ አስተዳደር ያሻታል” ካሉ በኋላ ይህ አፍሪካን የሚለውጠውን የአስተዳደርም ዘዬ “ማጉፉሊኬሽን” ሲሉ ሰይመውታል።

ማጉፉሊ በዚህን ያህል ተጽእኖ መፍጠር ቢችሉም የዲሞክራሲ ጸር ሆነው ነበር የሚታዩት። ተቃዋሚ በማሽመድመድ፣ ነቃፊዎቻቸውን ነቅሶ በማሰር፣ ነጻ ሚዲያን በማፈን ስማቸው ይነሳል።

line

ጆን ማጉፉሊ በአጭሩ

  • እንደ አውሮፓውያኑ በ1959 በሰሜን ምዕራብ ታንዛኒያ ቻቶ በሚባል ቦታ ተወለዱ
  • በዳሬ ሰላም ዩኒቨርስቲ ኬሚስትሪና ሒሳብ ትምህርትን አጠኑ
  • የሒሳብና ኬሚስትሪ መምህር ሆነው ማገልገል ጀመሩ
  • በ1995 ለመጀመርያ ጊዜ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆኑ
  • እንደ በ2000 ዓ.ም የካቢኔ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ
  • እንደ በ2015 የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ
  • እንደ በ2020 ደግሞ ለ2ኛ ጊዜ ምርጫ አሸንፈው ፕሬዝዳንት ሆኑ
line

ማጉፉሊ መጀመሪያ ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡ በሁለተኛ ወራቸው የፓርላማ የቀጥታ ሥርጭት እንዳይተላለፍ አገዱ። ያን ጊዜ ሰበብ ያደረጉት ወጪ ቅነሳን ነበር።

ተቃዋሚዎች ግን ይህ ነገር ለሳንሱር እንዲመች አድርጎ የፓርላማን ክርክር ለሕዝብ ለማቅረብ ነው ብለው ከሰሷቸው። እንዲያውም ይህን እርምጃ ተቃውመን ሰልፍ እንወጣለን አሉ። ሆኖም ሰልፉ በማጉፉሊ ሰዎች እውቅና ተነፈገውና ታገደ።

በ2017 ደግሞ ማጉፉሊ የታንዛኒያው ራፐር ናይ ዋ ሚቴጎ ዘፈን ዘፈነባቸው። ሚቴጎ ሙዚቃውን በለቀቀ በሰዓታት ውስጥ ራሱን እስር ቤት አገኘው።

ይህ ዘፋኝ በራፕ ሙዚቃው ያዜመው ግጥም በደምሳሳው ሲተረጎም እንዲህ የሚል ስንኞች ነበሩበት፣

እስኪ ንገሪኝ አገሬ፣

ነጻነት አለ ወይ በሰፈሬ

ያሻኝን ብዘፍን ጉራማይሌ

አገኘው ይሆን ራሴን ከከርቸሌ?

ማጉፉሊ ራፐሩን እንደምኞቹ ከርቸሌ ወረወሩት። በዳሬ ሰላም ማዕከላዊ እስር ቤት ታጎረ። በዚህም ማጉፉሊ ለትችት ቦታ እንደሌላቸው አሳዩ።

ማጉፉሊ ለሚዲያ ርዕስ የሚመቹና አንዳንዴም አስቂኝ ሰው ነበሩ።

ለምሳሌ ይህን ተቺ ሙዚቃ ያቀነቀነውን ናይ ዋ ሚቴጎን ከአንድ ቀን በኋላ ከእስር ሲያስፈቱት አንድ ምክር መከሩት። “ስለ ግብር አጭበርባሪዎች ሙዚቃ ሥራልኝ” በማለት።

ፕሬዝዳንት ማጉፉሊን ግብር አጭበርባሪዎች በጣም ያናድዷቸው ስለነበር ነው ለዘፋኙ ይህን ምክር የሰጡት።

በ2017 ደግሞ ዋንኛ ተቃዋሚያቸውና የምክር ቤት አባሉ ቱንዱ ሊሱ ቤታቸው ሳሉ ተተኮሰባቸውና ክፉኛ ቆሰሉ። የማጉፉሊ ሰዎች እንዳደረጉት ይታመናል። ሆኖም ሰውየው እንደምንም ድነው ከ3 ዓመት በኋላ ተገዳዳሪያቸው ሆነው ለፕሬዝዳንትነት ተወዳደሩ።

ሚስተር ሊሱ የግድያ ሙከራ እንደተረገባቸውና ታንዛኒያን እየመሯት ያሉት ሰው አምባገነን እንደሆኑ በተደጋጋሚ ይናገሩ ነበር። ማጉፉሊ እስከወዲያኛው ያሰናብቱታል ቢባልም ተፎካካሪያቸው እንዲሆን ፈቀዱለት።

ጁሊየስ ኔሬሬ
የምስሉ መግለጫ,ማጉፉሊ የአስተዳደር ዘይቤያቸው የተቀዳው ከአገሪቱ የነጻነት አባት ጁሊየስ ኔሬሬ እንደሆነ ይነገራል

ምዕራብ ጠልነትና ማጉፉሊ

ማጉፉሊ ምዕራባዊያን አፍሪካን በዝብዘዋታል ብለው ያምናሉ። ስለዚህ በተራችን እነሱን መበዝበዝ አለብን ሲሉ ያስባሉ። በዚህ ረገድ በየጊዜው የውጭ ድርጅቶችን የሚያስጨንቁ አዳዲስ መመርያዎችን ያወጡ ነበር። ከነዚህ መሐል የካናዳው ባሪክ ወርቅ እህት ኩባንያ የሆነውን አካሺያ ማዕድን ድርጅትን 190 ቢሊዮን ዶላር ለመንግሥት ክፈል ብለው አነቁት።

ለምንድነው የምከፍለው ቢላቸው፣ በቃ እስከዛሬ የከበሩ ማዕድናትን ከታንዛኒያ ስታወጣ ነበር። ገቢህን ስንደምረው ታንዛኒያ ይህን ያህል ማግኘት እንዳለባት ደረስንበት አሉት። ኩባንያው ደነገጠ። ከብዙ ድርድር በኋላ 300 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ።

ከዚህ ዕለት በኋላም ይህ የካናዳው ባሪክ ወርቅ አውጪ ኩባንያ ከሚያወጣቸው ማዕድናት 50 ከመቶውን ለመንግሥት ገቢ እንዲያደርግም ተገደደ። ማጉፉሊ የአስተዳደር ዘይቤያቸው የተቀዳው ከአገሪቱ የነጻነት አባት ጁሊየስ ኔሬሬ እንደሆነ ይነገራል። እሳቸውም ይህንን ብለውት ያውቃሉ። ማንም እንዴት አገሬን መምራት እንዳለብኝ ሊነግረኝ አይገባም ይሉ ነበር።

በአንድ ወቅት ኮሮናቫይረስ የእንቅስቃሴ ገደብን በተመለከተ የተናገሩት ይህንኑ የሚመሰክር ነበር።

“አባቶቻችን ምን ማድረግ እንዳለባቸው እየተነገራቸው አይደለም ያስተዳደሩን።…እንዲህ ዓይነት ቤት ዘግታችሁ ተቀመጡ የሚል መመርያ የሚያወጡ ሰዎች ከሩቅ ሊያስተዳድሩን ነው የሚሹት። የእኛ አባቶች እንዲህ አይነቱን ነገር አይቀበሉም ነበር” ሲሉ ምዕራባዊያንን ተችተዋል። “ድህነት ምን ማለት እንደሆነ አውቀዋለሁ”

ማጉፉሊ ከጭሰኛ ቤተሰብ በሰሜን ምዕራብ ቻቶ በሚባል ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ነው የተወለዱት። “ድህነትን በደንብ አውቀዋለሁ” ይሉም ነበር። እሳቸው ልጅ እያሉ ታንዛኒያን የሚያስተዳድሯት ጁሊየስ ኔሬሬ ነበሩ።

“ቤታችን ከጭቃ ነበር የተሰራው፣ በልጅነቴ ከብቶችን አግድ ነበር። ቤተሰቤን ለመታደግ ወተትና ዓሳ እያዞርኩ ነበር የምሸጠው። ድህነት ምን ማለት እንደሆነ ለእኔ አትነግሩኝም፤ ለዚህ ነው ድሆችን ለማገዝ ፖለቲካ ውስጥ የገባሁት” ሲሉም ተናግረዋል። ማጉፉሊ ጭሰኛ ሆነው ተወልደው ፕሬዝዳንት ሆነው ሞቱ። በተወለዱ በ61 ዓመታቸው።

BBC Amharic

  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    by Ethioreview news
    April 26, 2026
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ደብረጽዮን እንደጻፉት በማስመሰል በእንግሊዛዊቷ ተዘጋጅቶ ለአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ሊላክ የተዘጋጀ ደብዳቤ መያዙ ተሰማ
ለትግራይ ከአዲስ አበባ ክተት ተጠራላት፤ የትግራይ ወጣቶች ቢራ መጠጣታቸው ተወገዘ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • INTERVIEW
    • law
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • ያበደው
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2