Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው
News

የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

Ethioreview newsEthioreview news—June 1, 2022
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችናን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላትን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ

በሠሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የተለያዩ ወንጀሎችና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የፈጸሙ አካላትን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነ መሆኑን የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል ገለጸ።

ፍትህ ሚኒስቴር በጦርነቱ ምክንያት የተፈጸሙ ወንጀሎችና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመርና ድጋፍ ለማድረግ የተቋቋመውና ጉዳዩን በበላይነት የሚያስፈጽመው የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ዛሬ ለአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች ገለጻ አድርጓል።

የግብረ ኃይሉ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ታደሰ ካሳ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ጦርነቱን ተከትሎ በማንኛውም ወገን የተፈጸሙ ወንጀሎችና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተመረመሩ ነው።

More stories

ሩሲያ የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አስታወቀች

April 11, 2021

ባሕር ዳር – በሕገ ወጥ መንገድ በግለሰብ ቤት በበርሜል የተከማቸ ነዳጅና ቤንዚን ተያዘ

February 3, 2021

በትህነግ ሽንፈት ዋዜማ- የአሜሪካ ወታደሮች ከወር ተኩል በኋላ ወደ ጅብቲ ይጓዛሉ

November 29, 2021

ከታሪክ ተምረን በክብርና በአንድነት እንኖራለን!

April 27, 2021

የምርመራ ሥራውን የሚያካሂዱ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ከ150 በላይ የዘርፉ ባለሙያዎች መዋቀራቸውን ገልጸው ባለሙያዎቹ ለጊዜው በአፋርና በአማራ የምርመራ ሥራቸውን መጀመራቸውን ነው ያስረዱት።

በመሆኑም ቡድኑ በሰሜን ሸዋ፣ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በኮምቦልቻ ከተማ፣ በደሴ ከተማ፣ በጃማና ወረኢሉ አካባቢዎች፣ በወልዲያና አካባቢው፣ በላሊበላ ከተማ፣ በዋግ ኸምራ ዞንና በአፋር ክልል መሰማራቱን ጠቁመዋል።

የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል በሁሉም ቡድኖች ተፈጽመዋል የተባሉ ወንጀሎችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የተመለከቱ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች የማሰባሰብ ሥራ ውስጥ መሆኑን ገልጸዋል።

በአፋርና በአማራ ክልል የተፈጸሙ ወንጀሎችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር የሚያስችል የምርመራ ዲዛይን መዘጋጀቱንም ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በወልቃይት ጠገዴና በቃፍታ ሁመራ ወረዳዎች ተፈጽሟል የተባሉ የመብት ጥሰቶችን የሚመረምር ቡድን መዋቀሩን ጠቅሰው የሁኔታዎች መሟላትን ተከትሎ ወደ ሥራ የሚገባ ይሆናል ብለዋል።

በሌላ በኩል በአክሱም ከተማ በመከላከያ የሠራዊት አባላት ተፈጽመዋል የተባሉትን ግድያዎች በተመለከተ ምርመራው የመከላከያ ሠራዊት ከትግራይ መውጣቱን ተከትሎ መቋረጡን ጠቁመው ይህም በቀጣይ ምቹ ሁኔታ ሲፈጠር ዳግም ይጀመራል ነው ያሉት።

በትግራይ ኃይሎች በማይካድራ የተፈጸሙትን የጅምላ ግድያዎች የተመለከቱ መረጃዎች ተሰባስቦ የፍርድ ሂደት መጀመሩንም ነው የገለጹት።

በተጓዳኝም በመከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ፍርድ ቤት ሥር ጉዳያቸው የታየና በእንጥልጥል ያሉ የወንጀል ጉዳዮች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል በተፈጸሙ ወንጀሎችና የመብት ጥሰቶች ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያደርጋቸው ተግባራት ዓለም አቀፍ መርሆዎችን በተከተለ መንገድ እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብትና የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት አቻ ተቋም የጋራ ምርምራ ውጤትና ምክረ ኃሳቦችን ተከትሎ የሚከናወን መሆኑንም ነው ያነሱት።

የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል ያዋቀራቸው የምርመራ ቡድኖች ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የተከተሉ እንዲሆኑ ለማስቻል የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ መቆየቱም ተጠቁሟል።

ግብረ ኃይሉ የሚያከናውናቸው የምርመራ ሥራዎች በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ቅቡልነትን ማግኘታቸውን ጠቁመው ይህም ትልቅ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እንዳለው መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የምርመራ ቡድኑ በቀጣይ መረጃ ባሰባሰበባቸው አካባቢዎች ክስ ወደ መመሥረት ሂደት የሚገባ ሲሆን ምርመራ ባልተካሄደባቸው አከባቢዎች የምርመራ ሥራውን እንደሚያካሂድ ዶክተር ታደሰ ገልጸዋል።

ግብረ ኃይሉ በተለይም በአማራና በአፋር ክልሎች ያካሄዳቸው የምርመራ ሥራዎች በአመዛኙ እየተጠናቀቁ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ሪፖርቱ ይፋ ይሆናል ብለዋል።

ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የአውሮፓ አባል አገራት አምባሳደሮች የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል ያቀረበውን ገለጻ ተከትሎ ውይይት አድርገዋል።

ENA

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ቢቢሲ ዜና ቀየረ፣የኦባሳንጆ መቀለ መግባት ከጠ.ሚ አብይ የናይጀሪያ ቆይታ ጋር አያያዘ
አንድ መቶ አስራ አንድ አገሪቱን በብሄርና በሃይማኖት የሚንጡ ህገወጥ ድረ ገጾች ተለዩ፤ አስሩ ተያዙ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2