Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  SOCIETY  በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ
SOCIETY

በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

Ethioreview newsEthioreview news—December 14, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በአሸባሪው ህወሓት ግፍና ስቃይ የደረሰባቸው የመንግስት ሠራተኛው ህያው ምስክርነት። አንዳንዴ ሞት ቅርብ ይሆንና ብርቱ የሚባሉት ሳይቀሩ በትንታ አሊያም በእንቅፋት ሞቱ ሲባል ይሰማል። በድንገት በተቀመጡበት አሊያም እንደተኙ ህይወታቸው አለፈ የሚባል ልቦለድ መሰል ታሪክ የሚሰማበት አጋጣሚም አለ።

‘አትሙቺ ያላት ነፍስ’…እንዲሉ የዛሬው ባለታሪክ ገጠመኝ ግን ከእዚህ በተቃራኒው ነው። ባለታሪኩ አቶ እምወደው ነጋሽ ይባላሉ። በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽህፈት ቤት የኦዲት አስተባባሪ ናቸው።

አሸባሪው ህወሓት በእብሪት በወረራቸው አካባቢዎች ንጹሃን ዜጎች በጭካኔ ገድሏል፤ አሰቃይቷል፤ለዘመናት ከኖሩበት፣ ወግ ማዕረግ ካዩበት ቄያቸው፣ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል። ታዳጊ ሕፃናትን ሳይቀር ሴቶችን ደፍሯል፤የቻለውን ሀብት ንብረት ዘርፏል፤ ያልቻለውን አውድሟል፣ የእምነት ተቋማትን አርክሷል፤ አቃጥሏል።

አቶ እምወደውም የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች አረመኔያዊ የጭካኔ ተግባር ገፈት ቀማሽ ከሆኑ ንጹሃን ዜጎች መካከል አንዱ ናቸው። ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ’ እንዲል ሀገራዊ ቢሂሉ ህይወታቸው በተዓምር ተርፋ ይኸው ዛሬ የሽብር ቡድኑ በንጽሃን ዜጎች ላይ ያደረሰው ግፍ፣ ስቃይና መከራ ህያው ምስክር ሆነዋል።

More stories

ወገኛ ምርኮዎች !!

August 27, 2021

በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት የሚተገበር የ550 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይጀመራል

January 29, 2022

በድንገተኛ የሞተር ብልሽት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ አረፈ

September 18, 2021

ኤርትራዊያን ስደተኞች “አሸባሪው ወራሪሃይል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ፈጽሞብናል” ሲሉ የዓለም ሕብረተሰብ ተማጸኑ

February 23, 2022

ባለታሪኩ ገጠመኛቸውን እንደተረኩት፤ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ህይወታቸውን ለመንጠቅ ከድብደባ ጀምሮ የጠብመንጃ አፈሙዝ ወድረው እስከ ማስፈራራትና ማሰቃየት የደረሱ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን ፈጽሞባቸዋል።

ህይወታቸውን ለመንጠቅ የመሳሪያ ምላጭ ተስቦባቸዋል። ህይወታቸው ግን በተዓምር ተርፋለች። የሽብር ቡድኑ የጭካኔ ተግባር በታሪክ ተከትቦ ለትውልድ የሚቀመጥ የዘመኑ ጥቁር ጠባሳ ነውም ይላሉ።

የሽብር ቡድኑ በደረሰባቸው አካባቢዎችም የፈጸመው አረመኔያዊ ድርጊት በንጹሃን ላይ አዕምሯዊ፣ ስነልቦናዊና አካላዊ ጠባሳ ጥሎ ስለማለፉ “ራሴ ህያው ምስክር ነኝ” ሲሉም ያክላሉ።

አቶ እምወደው ጳጉሜን 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጧት ከአንድ አዛውንት ጋር ተቀምጠው የሆድ የሆዳቸውን እያወጉ ሳለ በአካባቢው የጥይት ድምፅ ይሰማ ጀመር። ተኩሱ እየጨመረ ይመጣል። የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ሳያሰቡት ከአዛውንቱ ደጃፍ ደርሰው ወደ ቅጥር ጊቢው ይዘልቃሉ። አቶ እምወደውም ሳያስቡት ከታጣቂዎቹ እጅ ይወድቃሉ። የአሸባሪው ታጣቂዎች ቀበቷቸውን አስፈትተው፣ ጫማቸውን እና የጣት ቀለበታቸውን አስወልቀው፤ ኪሳቸውን በርብረው ያገኙትን ቤሳ ቤስቲን  ሳይቀር ይወስዳሉ።

በዚህም ሳያበቁ ይዘውት በነበረው አካፋ፣ ዱላና  በክላሽንኮቭ ጠብመንጃ ሰደፍ እየተፈራረቁ በጭካኔ እንዳይሞቱ እንዳይሽሩ አድርገው ነርተዋቸዋል፤ አሰቃይተዋቸዋልም። የብሬንና የዲሽቃ ጥይት በጀርባቸው አሳዝለው፣ በትከሻቸው አሸክመው በባዶ እግራቸው ረጅም መንገድ ይዘዋቸው ተጉዘዋል። በጉዞ ላይ እንዳሉም ድብደባው አልቀረላቸውም። በወቅቱ የደረሰባቸውን ስቃይና እንግልት እንዲህ ሲሉ ነው በአንደበታቸው የገለጹት።

 “ከታጣቂዎቹ አንደኛው አንበርክኮ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ አፈሙዝ ደቅኖ አሰቃይቶኟል።ብቻ ህይወቴ  የተረፈው በተአምር ነው። ሰውነቴ በደረሰብኝ ድብደባ ላሽቋል፤ መታዘዝ ተስኖታል።” ታጣቂዎቹ በመኪናቸው ላይ እንዲወጡ ያዟቸዋል። በድብደባው ላሽቆ የዛለው ወገባቸው፣ እግር እጃቸው ግን ሊታዘዛቸው አልቻለም። በዚህም የተነሳ የተባሉትን መፈጸም ተሳናቸው። መኪናው ላይ ለመውጣት ያለ የሌለ ሃይላቸውን አሰባስበው ተፍጨረጨሩ ግን አልቻሉም። የጥረታቸው ውጤት መልሶ መላልሶ ከአስፋልት መንገድ  ላይ  መውደቅ ብቻ ሆነ። በዚህ ስቃያቸው የተናደደው ሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች አለቃ በንዴት ጦፎ ያብዳል።እና “በመኪና ሂድበት” የሚል ትዕዛዝ ይሰጣል። ይህን የሰሙት አቶ እምወደው የቀራቸውን እንጥፍጣፊ አቅም አሟጠው ያንገላቷቸው በነበሩት ታጣቂዎች እየተጎሸሙ፣ ተወርውረው መኪናው ላይ ያርፋሉ። ታጣቂዎቹ አሁንም እየተቀባበሉ ከላይ፤ ታች እንደ ቅሪላ እየነረቱ እንደ አሰቃዩዋቸው ይተርካሉ።

በአሳር በመከራ መኪናው ላይ እንደወጡ አንደኛው ታጣቂ ሽጉጥ አፈሙዝ ግንባራቸውን መቶ ያንበረክካቸዋል። በዚህ ሳያበቃ ካንበረከካቸው በኋላ ሽንቱን ግንባራቸው ላይ ይሸናል። “ተንበርከክ ሲሉኝ የጠበኩት ሞት ነበር” ሲሉ ነው ሁኔታውን ለማስታወስ በዝምታ የኋልዮሽ በሃሳብ የነጎዱት። ሴቶቻቸው ጭምር ማንነታቸውን የሚያጎድፍ ክብረነክ ቃላትን ተጠቅመው እንደ አዋረዷቸው ይገልጻሉ። በጭካኔ በትራቸው በማድቀቃቸው ስላልረኩ ድንገት ሳያስቡት ቀኝ እጃቸውን መርፌ ይወጓቸዋል። ከዚያ በኋላ እንቅልፍ ስለወሰዳቸው የሆኑትን አያውቅም፤ አሁንም አያስታውሱትም። ከመኪናው ጠርዝ ላይ አስተኝተዋቸው ሲወጡና ሲወርዱ መረማመጃ አድርገው ረጋግጠው አሰቃይተዋቸዋል። ስቃያቸውን እንዲህ ያስታውሱታል።

“አንደኛው ታጣቂ ጩቤ አውጥቶ አንዴ አንገቴ ላይ፣ ሌላ ጊዜ ከንፈሬ ላይና ሆዴ አካባቢ በማስጠጋት እየዛተ ለመሰንዘር ሲቃጣ ተስፋ ቆረጥኩ፤ መሞቴን አምኜ ሬሳዬን የት እንደሚጥሉት ብቻ ነበር ሳስብ የነበረው” ይላሉ አቶ እምወደው፣ “አይና” ከተማ እንደገቡ በማግስቱ እንዲገደሉ ተወሰነ። የሚቀበሩበትን ጉድጓድም ራሳቸው እንዲቆፍሩ ትእዛዝ ተላለፈ ሲሉ ሁኔታውን እንዲህ ይተርካሉ።

የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በግፍ የፈጸሙባቸውን የጭካኔ ተግባር ሲያስታውሱት አሁንም ይዘገንናቸዋል። አፍረተ ሥጋቸውን ጨምሮ በአካላቸው ላይ ያደረሱባቸው ጉዳት ለስነልቦና ችግር ዳርጓቸዋል።

በቀኝ እጃቸውና በመቀመጫቸው ላይ የወጓቸው መርፌ ምን እንደሆነ በሕክምና ማረጋገጥ ስላልቻሉ ሰላም ነስቷቸዋል። ‘ትረፊ ያላት ነፍስ’ እንዲል ሀገራዊ ቢሂሉ አቶ እምወደው በተአምር ከሞት ተርፈው ዛሬ ታሪክ ነጋሪ ሆነዋል። አሸባሪው ህወሓት በንጽሃን ዜጎች ላይ የፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ህያው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። በሽብር ቡድኑ የግፍና የጭካኔ ድርጊት ህይወታቸው እንደ ዋዛ የተቀጠፈ ወገኖቻችንን  ቤት ይቁጠራቸው ሲሉ የደረሰባቸውን ስቃይና እንግልት ቋጭተዋል። ከኢዜአ የተወሰደ


SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ዓብይ እና ፓን-አፍሪካኒዝም
የአብን አመራሮች “ህግና ስርዓት የማይከበር ከሆነ ኢትዮጵያ ትግራይን ስለመግፋት ማሰብ አለባት”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 2025
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 2025
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2