Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  «በ1976-77 ዓ.ም ከቀድሞው ላስታ አውራጃ ወለጋ እንዲሰፍሩ ከተደረጉት እኔና እናቴ እንገኝበታለን» Fisseha Tegegn
News

«በ1976-77 ዓ.ም ከቀድሞው ላስታ አውራጃ ወለጋ እንዲሰፍሩ ከተደረጉት እኔና እናቴ እንገኝበታለን» Fisseha Tegegn

Ethioreview newsEthioreview news—April 2, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በ1976-77 ዓ.ም ከቀድሞው ላስታ አውራጃ ወደተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በግዳጅ ተወስደው እንዲሰፍሩ ከተደረጉት ላስቴዎች መካከል እኔና እናቴ እንገኝበታለን፡፡ በወቅቱ በነበሩት የገበሬ ማህበራት አማካኝነት ከየአካባቢው ቤተሰቦች እንዲመረጡ ከተደረገ በኋላ እኛም ወደ ሌላ ቦታ ተወስደው እንዲሰፍሩ ከተወሰነባቸው መካከል በመሆናችን እኔ፣ እናቴና እኛን ለመሸኘት በሚል የእናቴ ወንድም አጎቴ ሆነን ከገጠሯ ‘ብርግነት’ ‘ሰማይ ቀበሌ’ ጎጥ ተነስተን ጉዟችንን ወደ ሙጃ ከተማ አደረግን፡፡

ወደ ሙጃ ስንሄድ ከብርግነት እስከ ሙጃ ድረስ በእግር ከሁለት ሰአት በላይ ስለሚወስድ አጎቴ እኔን እሽኮኮ አድርጎ ያንን ተራራና ሸለቆ ወጥተንና ወርደን ሙጃ ደረስን፡፡

ሙጃ ስንደርስ አሁን ‘ሶስት ጎዳና’ የሚባለው አካባቢ ከተለያዩ የአካባቢያችን ጎጦች የመጣው የሕዝብ ማዕበል ጎዳናውን ሞልቶት ስለነበር የአቧራው ጢስ ላይ የህብረተሰቡ ዋይታና ለቅሶ ተጨምሮበት በቅርበት ያለ ሰውን እንኳን ማየት ያስቸግር ነበር፡፡ ሙጃ ላይ ከተሰባሰብን በኋላ ያ ሁሉ ወዴት እንኳን እንደሚወሰድና የትኛው ምድር ላይ እንደሚያርፍ የማያውቅ ሕዝብ ጋር ሆነን በወታደሮች ታጅበን ሙጃን ለቀን በእግር ወደ ኩልመስክ ጉዞ ጀመርን፡፡ አጎቴ ከእኔና ከእናቴ ጋር መሄድ ስለማይችል ከእህቱ ጋር ተላቅሰው፣ እኔንም እቅፍ አድርጎ እያለቀሰ ተሰነባብቶን ተለያየን፡፡

እናቴ አልፎ አልፎ እኔን እያዘለች፣ መንገዱና ጸሃዩ ሲያደክማት ደግሞ አውርዳኝ እጄን ይዛ አብሬያት ከጎኗ እየተራመድኩ ከአካባቢያችን ሕዝብ ጋር ኩልመስክ ደረስን፡፡ ኩልመስክ ስንደርስ በርካታ የጭነት መኪናዎች ተሰልፈው ቆመው ወደነበሩበት አቅጣጫ በወታደሮቹ መሪነት ከሄድን በኋላ ስማችን እየተጠራ ወደ የምንሄድባቸው አካባቢዎች ወደተዘጋጁት የጭነት መኪኖች ሄደን እኔና እናቴ ወደ ወለጋ የሚሄደው የጭነት መኪና ላይ ተሳፈርን፡፡ በግዜው ግን ወዴት እንደሚወስዱን እንኳን ምንም መረጃ የለንም ነበር፡፡ መንገድ ላይ የሚሞተው የሞተበት መንገድ አቅራቢያ ያለ ዱር ውስጥ እየተቀበረ፣ የተረፍነው ደግሞ ህመማችንና የመንገዱን ስቃይ እየቻልን ከቀናት ፈታኝ ጉዞ በኋላ እንደምንም ወለጋ ደረስን፡፡ እኔና እናቴ የነበርንበት የጭነት መኪናን የሞላነውና በሌሎች በርካታ የጭነት መኪኖች ተጭነው አብረውን ወለጋ የገቡ ወገኖቻችን ቄለም የሚባለው ስፍራ ልዩ ስሙ ‘ቄጦ’ የሚባል አካባቢ ስንደርስ ሰው ይቅርና እንስሳ እንኳን የማይታይበት እልም ያለ ስፍራ ላይ በኬሻ የተበጃጀ ግዜያዊ የመጠለያ ጣቢያ ተዘርግፈን ኑሯችንን በዛው አደረግን፡፡

More stories

«የቁንጥጫ ዲፕሎማሲ» የዲፕሎማሲው መንገድ መቀየር !

August 5, 2021

መልስ የሚሻ ዜግነታዊ ጥያቄ – ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ

May 9, 2021

… ሶርያ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የመን 20 ሚሊዮን ህዝብ እንደተራበና እንደተፈናቀለ …

January 29, 2021

የደብረፅዮን የጦርነት ታክቲክ 22

September 12, 2022

ጊዜያዊ የሰፈራ ጣቢያው ውስጥ የነበረው ህይወት እጅግ በጣም አስቸጋሪና ፈታኝ በመሆኑ እጅግ የከፋ ቀን በአንድ ቀን ብቻ እስከ 150 ሰው ያህል ህይወቱን በበሽታ፣ ብርሃብና በድካም አጥቶ በጅምላ የሚቀበርበት ቦታ ነበር፡፡

አቅም የነበራቸው ወጣቶችና ጎልማሶች ቦታውና የኑሮው ሁኔታ እጅግ በጣም አስቀያሚ መሆኑን በመረዳታቸው ከሰፈራ ጣቢያው ለማምለጥ ሲሞክሩ ጣቢያውን በሚጠብቁት ታጣቂዎች፣ እነሱን ካለፉ ደግሞ በየጫካው በተሰገሰጉ ሽፍቶች በጥይት እየተለቀሙ የጅብ ‘ራትና የአሞራ ምግብ ሆነዋል፡፡ ያንን ሁሉ መሰናክል አልፈው ወደየመጡበት ቀዬ የተመለሱ አንዳንድ ሰዎችን በቅርቡ አግኝቼ ሳናግራቸው ሁሉም በአንድነት የሚሉት ነገር ቢኖር “በህይወታችን ትክክለኛውን ውሳኔ የወሰንበት ቀን” የሚል ነው፡፡ እንዲህ እንዲያስቡ ያደረጋቸው እዛው ወለጋ በቀሩ ወዳጆቻቸውና ወገኖቻቸው ላይ በየግዜው እየደረሰ ያለውን ግፍና ሰቆቃ ስለሚያውቁ ነው፡፡

በሰፈራ ጣቢያው የተፈጠረው ተላላፊ በሽታና አስቀያሚ የኑሮ ሁኔታም ወገናችንን መግደሉን አላቆመም ነበር፡፡ በየእለቱ የሰውን ልጅ በጅምላ የመቅበሩ ሂደት እየቀጠለ ሄዶ የእኔም እናት እዛው ሰፈራ ጣቢያ ውስጥ ከዚህ አለም በሞት በመለየቷ የቄለሟ ቄጦ የምትባል ስፍራ መሬት እናቴን ጨምራ በጅምላ መቅበሯን ቀጠለች፡፡

ወደማናውቀው ስፍራ ተወስደን ህይወታችንን እንዲህ እየመራን እያለን ከጎናቸው እናት ወይም አባት የሌላቸው ህፃናትን ከሌላው የሰፈራ ጣቢያው ነዋሪ ለየት በማድረግ እዛው በአቅራቢያው ለልጆች ብቻ የሚሆን ሌላ በኬሻ የተሰራ መጠለያ ውስጥ አስቀምጦ ህፃናትን የሚረከብ ግለሰብም ሆነ በጎ አድራጎት ድርጅት እስኪመጣ ልጆችን በትኩረት መርዳት በማስፈለጉ እናቴን ያጣሁት እኔም ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት ወደተቀመጡበት መጠለያ ገባሁና እጣ ፈንታዬን መጠበቅ ቀጠልክ፡፡ እድለኛ ነበርኩና እኔና ሌሎች ወደ 50 የምንጠጋ ህፃናት የወለጋዋ ቄለምንና እናቴ የተቀበርችባት ቄጦን ለቀን ሌላ ጉዞ ጀመርን፡፡ እኔ የተወሰድኩት በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን ወደሚያሳድገው የሐረር ኤስ. ኦ. ኤስ የህፃናት መንደር (SOS Children’s Village Harar) ነበር፡፡

እንደኔ እድለኛ ሳይሆኑ ቀርተው የእኔ እጣ ያልደረሳቸውና እዛው ወለጋ ቄለም ውስጥ የቀሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን የነበራቸው ብቸኛ አማራጭ ወዴት እየተወሰዱ እንደሆነ እንኳን ሳያውቁት ያረፉበት ጫካና ባዶ ቦታን የመኖሪያ ስፍራ አይነት ስሜት እንዲሰማቸው በማድረግና ያሉበትን ስፍራ የህይወታቸው ቀጣይ እድሜን የሚመሩበት አካባቢ ለማድረግ የሚችሉትን አድርገው ኑሯቸውን እዛው መመስረት ነበር፡፡ ያ እንኳን ለኑሮ ይቅርና በአካባቢው እንኳን የሚያልፍ ሰው የማይገኝበት ቦታን መንደር መስርተው፣ ልጆችና የልጅ ልጆችን እያዩ ኑሯቸውን ቀጠሉ፡፡ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ከዛ አካባቢ ውጪ የሚያውቁት ሌላ አለም የለም፡፡ ወላጆቻቸውና አያቶቻቸውም ቢሆኑ ህይወታቸውን በስፍራው በማቅናታቸውና ባዶ የነበረን ቦታ ወደ የሰው ልጅ መኖሪያነት በመቀየር ኑሮና ሁኔታዎች አስገድደው ያስጀመሯቸው ህይወትን አምነው ተቀብለው ባረፉበት ቀዬ ለኑሯቸው የሚሆን መኖሪያ ስፍራን መስርተው መኖር ቀጠሉ፡፡

እነዚህ ስንት መከራና ችግርን አልፈው ህይወትን እየመሩ ያሉ ወገኖች ግን ህወሓትና ኦነግ የሚባሉ ጉደኞች በዘሩት አማራና ኢትዮጵያዊነትን የሚጠላ፣ ዘርን መሰረት ያደረገና የሰውን ልጅ የፖለቲካ መቆመሪያ ያደረገ ፖለቲካዊ መዋቅር ምክንያት እጅግ አስቃቂና ዘግናኝ ወንጀሎች እየተሰሩባቸው ነው፡፡

ሰላማዊ ሰውን መግደል፣ ማፈናቀልና ማሳደድ፣ ንብረቶቻቸውን ማውደም ጀግንነት የሚመስላቸው ፖለቲከኞች፣ ጠባብ ብሄርተኞች፣ ቅልብ ምሁራንና በስልጣናቸው እስካልተመጣባቸው ድረስ የሌላው ሰው ነፍስና ህልውና ግድ የማይሰጣቸው ባለስልጣናትና አመራሮች እነዚህ ምስኪን ወገኖቻችንን መቆመሪያ አድርገዋቸዋል፡፡

ስንቱን ግፍና መከራ አልፈው ካቀኑት የአገራቸው መሬት እንደ ወራሪ እየታዩና የመወያያ አጀንዳ ብቻ ተደርገው እየተቆጠሩ እንዲፈናቀሉና ተሰደው ሌላ ጫካ ውስጥ እንዲገቡ ተገደዋል፡፡ የማንም አረመኔ ፖለቲካዊ ህልም ማሳኪያ ለመሆን ተብሎ ወገኖቻችን ከራሳቸው መሬት ላይ የሚፈናቀሉበትና የሚገደሉበት ሁኔታ ማብቃት አለበት፡፡ የሃገራቸው መሬት ነው! የራሳቸው መሬት ነው! ጫካን መንጥረው ነፍስ ዘርተውበት ህይወታቸውን እየመሩበት ያሉበት፣ ልጅና የልጅ ልጆቻቸውን ያዩበት የሃገራቸውና የራሳቸው መሬት ነው! ለእነዚህ ንጹሃንና ምስኪኖች ደህንነት አቅም የሌለው መንግስት መንግስት ከመባል ይልቅ የሕግ ከለላ ያለው ወንበዴ ቢባል ይሻላል፡፡

በተለይ በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችና በሐረር፣ በድሬ ዳዋ፣ በአዲስ አበባና በአንዳንድ የደቡብ ክልል አካባቢዎች በየግዜው እየተተገበሩ ያሉት ፖለቲካዊና ተያያዥ እንቅስቃሴዎች አማራን እንደጠላት የሚፈርጁና በሃገሩ እንዲሸማቀቅ የሚያደርጉ ሻጥር የሞላባቸው ተግባራት በቀጥታም ሆነ ኢ-ቀጥታዊ በሆነ መንገድ የህግና የመንግስት ከለላ ያላቸው፣ በደህንነትና የጸጥታ አስከባሪዎች አድሏዊ አሰራር የሚደገፉ ናቸው፡፡

ይሄ ግፍ እስከመቼ ነው የሚቀጥለው? መቼስ ነው የሚያበቃው?

[ከታች ያያያዝኩት ፎቶ ወለጋ ክፍለሃገር ቄለም ቄጦ ውስጥ እያለን የተሞላ ቅፅ ነው]

Via Fisseha Tegegn FB

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
አማራ ክልል በሚገደሉ ንጹሃን ጉዳይ መንግስት አስቸኳይ መፍትሄና እንዲሰጥ አሳሰበ፤
ሀሰተኛ ዶላር ሲያዘዋዉሩ የተደረሰባቸው አራት ግለሰቦች እያንዳንዳቸዉ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ!
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2