Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ስለ እንጀራ እናት አሜሪካ – በአውቀቱ ስዩም
News

ስለ እንጀራ እናት አሜሪካ – በአውቀቱ ስዩም

Ethioreview newsEthioreview news—May 24, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

አሜሪካ የነጮች ምድር ስትሆን የጥቁሮች ደግሞ ምድረ-ፋይድ ናት፤
ለምሳሌ አንድ የፈላበት ጎረምሳ ፈረንጅ መቶ ጎራሽ ጠመንጃ ታጥቆ ወደ አንድ ምኩራብ ወይም ወደ አንድ የኤሽያ ማሳጅ ቤት ገብቶ ይተኩሳል፤ በፊቱ ያገኘውን ሁሉ ይገነዳድሳል ፤ ፖሊሶች ይደርሱና ከብበው፤ በላዩ ላይ ያሳ መረብ ጥለው ይይዙታል፤ ከዚያ” ቃታ የሳብክበት ጣትህ ወለም ሳይለው አይቀርም ማሳጅ እናደርግልህ “ “የተኩስህም ድምጽ ጆሮህን ሳይጎዳው አይቀምና እናሳክምህ” ብለው በአምቡላንስ ይወሰዱታል፤ በምላሱ ድንጋይ ቀቅሎ ማብሰል የሚችል ጠበቃ ይቀጠርለታል፤ አንድ ነገር ነከቶት ነው እንጅ በጤናውማ እንዲህ ያለ እልቂት አይፈጽምም” ብለው የሆነ የአአምሮ ህመም ይፈበርኩለታል፤ ከዚያ ወይ በሀኪም ቤት አለበለዝያም በማረሚያ ቤት ውስጥ ኦርጋኒክ ምግብ እየበላ በኦርጋኑም እየተጫወተ ቀሪው እድሜውን እንዲያሳልፍ ይፈቅዱለታል::


ጥቁር ከሆንክ ሌላ ነው፤ ፖሊስ ባለበት አካባቢ ገላህን አሳክኮህ እጅህን ወደ ሽንጥህ ከሰደድህ “ ሊተኩስብን ነው” ብለው ጥይት ያራግፉብሀል ፤ ሳታስበው ማኖ ነክተህ “በቁጥጥር ስር ውለሀል” ካሉህ ፤ “ ጀንትል ሜን! ካቴናው ከኔ ይሁን ወይስ ከናንተ “ እያልህ መተባበር ነው ያለብህ፤ “ያዙኝ ለቀቁኝ ካልህ” ይይዙሃል፤ ግን በህይወት አይለቁህም! ትንሽ ከተፈራገጥህ አንተን አያርገኝ፤ አፈር ያስግጡሀል፤ አሜሪካ ከተሞች ውስጥ አፈር በቀላሉ አይገኝም፤ ግን ካፍጋኒስታም ቢሆን አስመጥተው ያስግጡሀል፤

እስካሁን የጻፍኩት ግነት እንደበዛበት ለኔም ታውቆኛል ፤ ያም ሆኖ በኩሸቱ ውስጥ እውነት እንዳለበት አይጠፋሺም፤

አሜሪካ ከሌሎች አገሮች ጋራ ያላት ግኑኝነት በፍትህ ላይ ሳይሆን ባሰላለፍ ላይ የተመሰረተ አንደሆነ ከዚህ ጽሁፍ አንባቢ የተሰወረ አይደለም!

More stories

«የቁንጥጫ ዲፕሎማሲ» የዲፕሎማሲው መንገድ መቀየር !

August 5, 2021

መልስ የሚሻ ዜግነታዊ ጥያቄ – ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ

May 9, 2021

… ሶርያ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የመን 20 ሚሊዮን ህዝብ እንደተራበና እንደተፈናቀለ …

January 29, 2021

የደብረፅዮን የጦርነት ታክቲክ 22

September 12, 2022

ከአመታት በፊት፥ ሰአሊው ወዳጄ ግዛቸው ከበደ ቤት ያየሁት ነገር ትዝ አለኝ፤ ጋሽ ተምትሜ የተባሉ ጥሮተኛ ሽማግሌ አልፎ አልፎ እየመጡ ወዳጄን ይጎበኙታል፤ መጠነ ሰፊ ቁልምጫና ውዳሴ አጉርፈውለት ሲያበቁ አንድ አምሳ ብር ይፈልጡታል፤
አንድ ቀን እንደልማዳቸው መጥተው ዳር ዳር ሲሉ ግዛችው” ልጅ የለዎትም?” ሲል ጠየቃቸው፤
“አለቺኝ!” አሉ ጋሸ ተምትም” ግን እምትበላ ናት”
ከራስዋ አልፋ ለሌላ ለመትረፍ አልደረሰችም ፤ ማለታቸው ነው ፤

አገራችንም እንደ ጋሸ ተምትሜ ልጅ “ እምትበላ ናት፤ የበላችበትን ሂሳብ የሚዘጉትም ሀብታም አገሮች ናቸው ፤ ያለ ሀብታም አገሮች ረድኤት በቀንጃ በሬ ታርሶ ሞሰቡዋ ደርበብ እንደማይል እናወቃለን፤ ኢትዮጵያ ግብጥና ኢራቅን ተከትላ ፥በስድሰተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ የአሜሪካ ተረጣቢ አገር ናት፤ ይሄንን ረድኤት ቢወስዱብን ሌላ ቀለብ ሰፋሪ አሰናድተናል? ወይስ የልብ ኩራት ብቻ ያሳድረናል?

“ አሜሪካ በኛ ጣልቃ አትግባ” እሚለው ንግግር ከመፈክርነት ያለፈ ትርጉም አሚኖረው ጣልቃገብነትን የሚመክት ጉልበት፥ እውቀት እና ሀብት ሲኖረን ነው፤ ካልተሸዋወድን በቀር እኒህን ጸጋዎች በቅርብ ርቀት እንኳ እንደማናያቸው እናውቃለን፤ ሽቅብ የሚያዳልጣቸውን ሰዎች ፉከራ ወደጎን ትቶ የቤታችንን ጣጣ መፍታት አና የዲፐሎማሲ ብልጠት ላይ መትጋት አይሻልም? አንድ የበራለት ወያላ አንዳለው፡ “ ከማያዋጣ ጉልበት ፤በህግ አምላክ ማለት”

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“The US meddle in our internal affairs is completely unacceptable.”
Down With U.S. Senate Resolution 97, “Ethiopia Colonization Act of 2021”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2