የያሬድ ጥበቡ ነገር
ብአዴን የተሰኘው ድርጅት በድን ሆኖ የኖረው ከአፈጣጠሩ ጀምሮ እንደ እስስት ተለዋዋጭ ባህሪ ባላቸው እንደ ያሬድ ጥበቡ( Yared Tibebu) አይነት ሰዎች በመመራቱ ይመስለኛል። አቶ ያሬድ ህወሓትን ከማምለኩ ውጪ በምንም ጉዳይ ላይ ጠንካራ አቋም ኖሮት አያውቅም። ዛሬ ያንቆለጳጰሰውን ነገ ተነስቶ ያለበቂ ምክንያት ሲቃወመው ታያለህ። ዝም ብሎ በነዱት ነው የሚነዳው።
(እንደ እኔ እንደ እኔ በየጊዜው አቋማቸውን የሚቀያይሩ ግልብ ሰዎች ሲያጋጥሙን እንደ ወንዝ ሳይሆን “እንደ ያሬድ ነው የሚነዱት” ብንል ሁላችንም ሊያግባባን የሚችል አገላለፅ ይሆናል ብየ አስባለሁ
ይህ ግለሰብ ከህወሓት አሽከርነቱ ተላቆ አሜሪካ መኖር ከጀመረ በርካታ አመታት ያስቆጠረ ቢሆንም አሁንም ድረስ ሞቶ የተቀበረውን ድርጅት ከማምለክ አልተመለሰም። በአንድ ወቅት “በረከት ስምኦን እና አዲሱ ለገሰ እንደ እንጀራ ይርቡኛል፤ እንደ ውሃ ይጠሙኛል” ብሎ ጉድ እንዳላስባለን አሁን ደግሞ ” ፃድቃን ገብረ ተንሳይ የአዲሱ የትግራይ ሰራዊት መሪ ሆኖ መምጣቱ በትግራይ ተስፋ እንዳልቆርጥ ያደርገኛል” ሲል እያስደመመን ይገኛል። ከወረዱ አይቀር እንደዚህ ነው።
ያሬድ እና መሰሎቹ ከሚፈፅሙት ድርጊት የተረዳሁት አንድ ነገር የወያኔ አሽከር ሆኖ ያገለገለ ግለሰብ በአካል ነፃ ቢወጣም አዕምሮው መቼም ቢሆን ከባርነት መላቀቅ የማይችል መሆኑን ነው። ለዚህም ይመስለኛል በመጦሪያ እድሜያቸው በረሃ የገቡት የቀድሞ ጌቶቹ ተአምር ይሰራሉ ብሎ ያመነው። አሁን እኮ አቶ ያሬድ የቀረው “መለስ ይመለሳል፤ ፃድቃን ያፀድቃል” ማለት ብቻ ነው
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር።… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች






