Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  መረጃ ተኮር ግልፅ ደብዳቤ – ከገብረመድህን አርአያ
News

መረጃ ተኮር ግልፅ ደብዳቤ – ከገብረመድህን አርአያ

Ethioreview newsEthioreview news—July 13, 2021
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ጉዳዩ ፦ የህ.ወ.ሓ.ት.መስፋፋትና መሬት ነጠቃ!!

ክቡር የእትዮጵያ ህዝብ ሆይ ፤

ክቡር የእትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ፡

የማቀርበው አብዮቱታየ በኢትዩጵያ ህዝብና በርሶው አስተዋይ መሪነት የእልባት መፍትሄ እንደሚያገኝ በመተማመን ነው ።
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ፡በየካቲት ወር 1967 ዓ.ም ደደቢት በረሃ ከመውረዱ ጥቂት ቀደም ብሎ አዲስ አበባ ውስጥ ሆኖ በንድፈ ሃሳብ ያዘጋጀው ማኒፈስቶው ( የትግል ፕሮግራሙ ) ጥር ወር 1967 ዓ.ም. ኤርትራ ሳሕል በረሃ ወርደው የአንድ ወር ወታደራዊ ትምህርታቸው ያጠናቀቁ ቁልፍ አመራረቹ የሚሰጣቸው ትምህርት ጨርሰው የካቲት ወር 1967 ዓ.ም. ደደቢት በረሃ እንደገቡ ፡ተሰባስበው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት በሚል የዛሬው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ መሰረቱ ።
በዚሁ እንዳሉም ይዘዉት የመጡ ፀረ ኢትይዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት ፤ ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ፕሮግራማቸው እጅግ አጠናክረው በመፃፍ አዘጋጅተው ጨረሱ።
ይህ የአቋም ፖሊሲ ፕሮግራም፤በወቅቱ የነበሩ አመራሮች የማ.ገ.ብ.ት ወይም የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት የዛሬው ህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራሙ ኢትዮጵያ ዳግም ተመልሳ ሂወት እንዳትዘራ ሃገራዊ አንድነትዋ ፤የህዝብዋ አንድነትና ኢትዮጵያዊነቱ እንዲከስም እንዲጠፋ ተደርጎ የተዘጋጀ ፕሮግራም ፤ከየካቲት ወር 1967 ዓ.ም. እስከ ጥር ወር 1968 ዓ.ም.ጊዜ በመውሰድ የአንድ ዓመት ጥናትና እርምት ፈጀ ፤ተጠናቆ በመዝጋጀት በመጨረሻ በመፅሓፍ መልክ ተሰናድቶ ፤የካቲት ወር 1968 ዓ.ም
1 -በትግርኛ
2 -በአማርኛ
3 -በእንግሊዝኛ ተባዝቶ ተጠርዞ በየአስፈላጊነቱ ተሰራጨ።ይህ የህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም በብዙ ኢትዮጵያዊ እጅ ስለሚገኝ ዝርዝር መረጃው አላነሳውም ፤ለአብዮቱታየ መነሻ ሁለት ነጥቦች አቀርባለሁ ።
1ኛ ) ትግራይ ነፃ ሃገር ከአፄ ዮሓንስ 4ኛ ሞት በኋላ በተስፋፊውና ወራሪው ዳግማዊ ምኒሊክ መሪነት ነፃ ሃገር የነበረችው ትግራይ በአማራው ቅኝ ግዛት ሥር ወደቀች::ህዝብዋም ለመክራና ችግር ለስደት ለድንቁርና ወ.ዘ.ተ.ተዳረገ ይላል ።
2ኛ) የዳግማዊ ምኒሊክ ወራርና መስፋፋት ትግራይና ህዝብዋ በቅኝ ግዛቱ ሥር እንደተቆጣጠረ ፤ ዘመቻውን በማስፋት ዛሬ ኢትዮጵያ ተብላ በምትጠራው ሃገር አካባቢ የሚገኙ ነፃ ሃገር ሆነው ራሳቸውን ችለው ህዝባቸው የሚመሩ የነበሩ የተለያዩ ብሄር፤ ብሄረ ሰቦች፤ በአማራው ነፍጠኛ ሠራዊቱ ጥቃት ተፈፅሞባቸው፤ እነዚህንም በአማራው ስርአት ቅኝ አገዛዝ ሥር ከወደቁ በኋላ ኢትዮጵያ ተብላ የምትጠራው ሃገር በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ምኒሊክ የመሰረታት ሃገር ይህች የዛሬዋ ኢትዮጵያ ናት ።

More stories

«የቁንጥጫ ዲፕሎማሲ» የዲፕሎማሲው መንገድ መቀየር !

August 5, 2021

መልስ የሚሻ ዜግነታዊ ጥያቄ – ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ

May 9, 2021

… ሶርያ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የመን 20 ሚሊዮን ህዝብ እንደተራበና እንደተፈናቀለ …

January 29, 2021

የደብረፅዮን የጦርነት ታክቲክ 22

September 12, 2022

ትግራይም ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ስርአት በብረት ሃይል ትግል ነፃ ወጥታ የቀድሞው ሃገራዊን ነፃነትዋ ታስመልሳለች ።የራስዋንም መንግሥት ትመሰርታለች ። በዚሁ የህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም የተካተተው የትግራይ መንግሥት ሲመሰረት ለሚመሰረተው የትግራይ መንግሥት ድንበሩን ማስፋት ከሱዳን ሃገር በድንበር ማገናኘት የድርጅታችን ተግባር ነው።

የትግራይ መንግሥት ሰፋፊ የእርሻ መሬት በሌለበት ብቁ ሃገር ለመሆን ስለማይቻል ከጎንደር ጠ/ግዛት ሰሜን ጎንደር ወይም በቅድሞ አጠራሩ ሰሜን ቤጌምድር ፤ ወልቃይት ፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፡ቃፍታ ሁመራ (ሰቲት ሁመር) ወደ ትግራይ በማጠቃለል ከሱዳን ድንበር በቀጥታ ትግራይ ትገናኛለች ባለ ሰፊ የእርሻ መሬትም እንሆናለን ከዚሁ በማይለይ ከወሎ ጠ/ግዛት ከአለዋሃ ምላሽ እስከ ራያና ቆቦን በማካለል በትግራይ ግዛት ውስጥ ይሆናል ።

የህ .ወ.ሓ.ት. መሪዎች ይህን እቅድና ፖሊሲ ያዘጋጁት

1ኛ )አረጋዊ በርሄ
2ኛ) ግደይ ዘርአፅዮን
3ኛ )ስብሃት ነጋ
4ኛ) አባይ ፀሃየ
5ኛ )ሥዩም መስፍን
6ኛ) መለስ ዜናዊ ሲሆኑ ፤ በፕሮግራሙ እንደ ዋና የትግሉ አቋም አስገብተው ትግሉን ቀጠለ። ይህም በተግባር ለመፈፀም በተለይ በሰሜን ጎንደር እነዚህ የህ.ወ.ሓ.ት. መሪዎች ሙሉ በታጠቀ ኋይላቸው አሰማርተው የሰሜን ጎንደር ነዋሪው አማራው ግፍ ተፈፅሞበታል፤ገደሉት ዘሩን ለማጥፋት ለዓምታት ሰፊ እንቅስቃሴ አካሂደዋል ፤ ገደሉት ፤ አፈናቀሉት ፤ቀሪዉም በስደት ተበታተነ ። በወሎ ጠ/ግዛትም ተመሳሳይ ድርጊት ህ.ወ.ሓ.ት. ፈፅመዋል።

ድንበር ዘለል የመሬት መስፋፋት ሕገ ወጥ ወራር የመስፋፋት ፖሊሲ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በህ.ወ.ሓ.ት.መሪዎች ተባራዊ ተደረገ፤ አሁንም አልቆመም ህ.ወ.ሓ.ት.የመስፋፋት ፖሊሲው አጠናክሮ እየቀጠለበት ይገኛል።ይህ ፀረ ኢትዮጵያ አንድነት ፀረ ህዝብ ፤ደም አፋሳሽ ሃገር አፍራሽ ፤ አደገኛ ፋሽሽታዊ ፖሊሲም ነው ።

ህ.ወ.ሓ.ት. ያዘጋጀው ፕሮግራም ወደ ህዝብ ባሰራጨው ወቅት፤ ለመጀመሪያ ተቃውሞ የገጠመው፤ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ የትግራይ ህዝብ ነበር ፕሮግራሙን በማውገዝ ጭምር አልተቀበለዉም፤ የከተማውና የገጠሩ ነዋሪ ህዝብ ሁሉ ለማለት ይቻላል እሳት ውስጥ ከቶ አቃጠለው ።

ወያኔ የትግራይ ሃገር ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ስርአት ነፃ ለማውጣት ትግሌን ጀምሬ አለሁ ብሎ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ ለ5 ዓመታት በፅናትና በጥንካሬ ወያኔን የታገለው ግልፅና ስውር ጥቃቶች አድናቆት በሚሰጥበት የትግል ዘዴ የትግራይ ህዝብ ነው።

ቢታገለዉም አልተሳካለትም ፤በወያኔ ሃብት ንብረቱ እየተወረሰ ቤቱ ፈረሰ፤ እሱም እየታፈሰ ወንድ ሴት ወጣት ሽማግሌ፤ በቀንና ለሊት ከያለበት እየተያዘ እየታፈነ #06 –ሓለዋ ወያነ አስገብተው ጭካኔ በተሟላበት በማሰቃየት የሚቀብርበት ሰፊ ጉድጓድ ራሱን በመቆፈር ፤በቆፈረው ጉድጓድ በጅምላ እያስገቡ በጥይት ረሽነው ገድለው ጨረሱት ።
3ኛ)ከላይ የተጠቀሱ አመራሮች ኢትዮጵያና ህዝብዋም ጭምር አሁን ያሉበት ምስቅልቅልና ችግርም ያደረሱት እነዚህ ሰዎች ናቸው ፤የአማራው የዘር ማጥፋት ወንጀልም ፈፅመዋል። የኢትዮጵያ ሃገር ሉአላዊነት አፍርሰዋል። ዛሬ በኢትዮጵያ ሃገራችን በህ.ወ.ሓ.ት. እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ እንዳይደርስ ብሎ አስቀድሞ የተከላከለው የትግራይ ህዝብ የሂወቱ ቤዛ መስዋእትነት ከፍሎ ሂወቱ የገበረው ኢትዮጵያዊ ነው።
ኢትዮጵያ ሃገሬ በወያኔዎች ትፈርሳለች ህዝብዋም ለክፉ የመበታተን አደጋ ይደርስበታል ብሎ ስላመነ ስለ ተነበየ ነበር የመጀመሪያ የወያኔ ግፍ ቀማሽ ያደረገው። ያ የትግራይ ህዝብ ዛሬ የለም፤ ኢትዮጵያዊ ግዳጁ ፈፅሞ በወያኔዎቹ ተገድሎ ከዚች ዓለም ተሰናብቶዋል። የከፈለው ከባድ መስዋእትነት ግን በታሪክ ማህደር ውስጥ መዝገብ ተዘግቦ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ህዝብም ወንድሙ ለሆነው የትግራይ ህዝብ የከፈለው መስዋእትነት ሰሜን ጎንደር ፤ አለዋሃ ምላሽ እስከ ራያቆቦ ያንተ የትግራይ ህዝብ መሬት ነው ሲሉት የኔ አይደለም፡ ይህ መሬት ግዛቱ የጎንደር አማራ፤ የወሎ ግዛት እንጂ የትግራይ ግዛት ሆኖም አያውቅም የትግራይም አይደለም የትግራይ ህዝብ አማራ መሬቴን ቀማኝ ብሎ አያውቅም፤ የሚልበትም ምክንያት የለውም የህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም ትልቁ የስህተት ጥፋቱ እዚህ ላይ ነው በማለት አጥብቆ በመቃወሙ ከባድ መስዋእትነት ከፍሎ ያለፈ ኢትዮጵያዊ ነው።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ በፀሎት ሊዘክረው ይገባል
በሃገራችን ኢትዮጵያ እየታየ ያለውን በጣም አደገኛ የህ.ወ.ሓ.ት. የመሬት መስፋፋት ፖሊሲው የኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላምና የሃገር አንድነትና ለክፉ አደጋ የሚዳርግ ይበልጥ የሚጎዳ ደግሞ ንፅሁ ኢትዮጵያዊው የትግራይ ህዝብ ነው።

የህ .ወ.ሓ.ት መሪዎች የትግራይ ህዝብ ባላቸው የሃይል ጉልበት አፍነው በመያዝ የራሳቸው ፍላጎት መጠቀሚያ ፖሊሲ በማድረግ በስሙ እየነገዱበት እንደሸቀጥ ዕቃ መጠቀም የጀመሩት ደደቢት በረሃ ከወጡ ጀምሮ እንሆ እስከ ዛሬ ድረስ 43 ዓመት አስቆጥረዋል።

ይህ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ህዝብ ከባርነት ወለል በታች ሆኖ ፤በባሪያ ስርአት አገዛዝ የህ.ወ.ሓ.ት. ፖሊሲ መጠቀሚያና መነገጃ እያደረጉት ነው ።በማያምንበት በማይፈልገው በሰላማዊ ኑሮው በሂወቱ ከባድ እንቅፋቶች እየፈጠሩበት ነው።

የትግራይ ህዝብ ህ.ወ.ሓ.ት በተስፋፊ ፖሊሲው በጉልበቱ ከጎንደር፤ ከወሎ፤ ከአፋር፤ ወ.ዘ.ተ.በመስፋፋት ፖሊሲው በወረራ ወደ ትግራይ ያካለላቸው መሬቶች አያምንበትም አይቀበለዉም።

የህ.ወ.ሓ.ት. መንገድ በኢትዮጵያውያን ወንድማሞች የአንዲት ሃገር ልጆች መካከል ብጥብጥና ህውከት ፈጥሮ ፤የኢትዮጵያን አንድነትና ሉአላዊነት የመበታተነ እቅድና የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት የሚንድ ፖሊሲ ነው።ስለሆነም የጥቃቱ ሰለባ የትግራይ ህዝብ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ፤

ክቡር ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ

የትግራይን ህዝብ ከዚሁ አረሜኔ ፋሽሽት ወያኔ አድኑት ህ.ወ.ሓ.ት. እና ካድሬዎቹ፤ ደጋፊ አባሎቹ፤ ልዩ ፖሊሶቹ፤ የወያኔ ምልሻ፤ በኢትዮጵያ ህዝብ በሚፈጥሩት ችግርና እየፈፀሙት ያለውን ግፍ በተለይ በአማራው በጎንደር ጠ/ግዛት በወሎ ጠ/ግዛት በአፋር ወረዳዎች ፤ ግድያ እስራት ብዙ ነው።
ህ.ወ.ሓ.ት. ወያኔ በመስፋፋት ፖሊሲው የሚፈፅማቸው ያለውን ኢ-ሰብአዊ ተግባሩ በትግራይ ህዝብ ፍላጎት እየፈፀምኩት ነኝ በማለት ፋሽሽታዊ ድርጊቱን ፤ ንፁህ በሆነው ኢትዮጵያዊ በትግራይ ህዝብ እያላከከ ይገኛል። የትግራይ ህዝብ ግን በዚሁ ድርጊት ውስጥ የለበትም ፤እንዲያውም አያውቀዉም ጭምር።

ክቡር የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ

ክቡር የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ

ከዚህ በታች የሚታየው ካርታ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የድርጅቱ የቀድሞው አመራርና የአሁኖቹ መሪዎች ተሰባስበው የትግራይ ግዛት ይህ ነው ብለው አምነዉበት ያፀደቁት ነው። ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ያለ የተስፋፊ ፖሊሲ እቅድም ይህ ነው። ይህ የወያኔ ህ.ወ.ሓት.የተስፋፊነት ወረራ በይፋ ያወጁት በድርጅቱ ልሳን በሆነው Tigrai on line sep 6 2018 የመስፋፋት ፖሊሳቸው ግልፅ አድርገዉታል ፤ ካርታውን እንመልከት ወይኔ ቀደም ብሎ በወረራ ከይዘው በጎንደር ጠ/ግዛት ወልቃይት፤ጠገዴ፤ቃፍታ
4ኛ) ሑመራ፤ጠለምት ከወሎ ጠ/ግዛት ከላይ አለውሃ ምላሽ እስከ ራያና ቆቦ ፡ በተጨማሪ በሰሜን በኩል የአፋር ወረዳዎች እንደነ በራሕሌ፤ ዳሉል ወ.ዘ.ተ ፤ በጎንደር ከላይ አርማጮህ እስከ ታች አርማጮህ፤ ዓብድራፈዕ፤ መተማ፤ አብርሃ ጅራ፡ወሎ ጠ/ግዛት ደቡቡ ሁሉ ያጠቃለለ ነው ፡እነዚህ ሁሉ የትግራይ ግዛት ናቸው ብሎ የህ.ወ.ሓ.ት. የቀድሞውና የዛሬ መሪዎች የመስፋፋት የሃይል ወራራ በመፈፀምና ለመፈፀም እየተዘጋጁ ናቸው ።
ህዝብና መንግሥት ትክረት በመስጠት ይህ ወራሪው የወያኔ ሕገ ወጥ ተስፋፊነት ማስቆም ግዴታ ነው ። በስንት ሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ ከትውልድ ቦታው ተፈናቅሎ ተሰዶስ የት ሊገባ ነው ?
ክቡራን ሆይ ፤ የተስፋፊነት ወረራ ሃገርና ህዝብ ያጠፋል፤ ሃገር ያፈርሳል ፤ ሃገር ስርአተ አልበኝነት ያደርጋል፤ ይህ ከተከሰተ ደግም ሃገር ይፈርሳል ህዝብ ይበታተናል ሃገር የለም ።

የወያኔ የአሁኑ መስፋፋት የወረራው ፖሊሲም የሚፈፀምባቸው፤ ተፈፅሞባቸው የሚገኙ

1ኛ )የጎንደር አማራው ህዝብ
2ኛ )የወሎ አማራ ህዝብ
3ኛ )የአፋር ህዝብ ዋናዎቹ በሰለባው የተጠቁ ናቸው ።
ይህ የመስፋፋት ወረራ ፤ ፀረ ማንነት መብት ፖሊሲ ነው ፡ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. በማን አለብኝ ትእቢቱ የኢትዮጵያውያን መብትና ነፃነት በሃገራቸው ውስጥ በጠራራ ፅሓይ እየገፈፈ ነው ።
የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ይህ የቅኝ ግዛት መስፋፋት ማቆም አለበት ፡ይህ ካልተደረገ ኢትዮጵያና ህዝብዋ ወደ ክፉ አደጋ ይወድቃሉ ። የወያኔው ፋሽሽት የማፍያ ጥርቅም በኢትዮጵያ ሕግም በዓለም ሕግም ተገዶ ማቆም ይገባል፡ከዚሁ በፊትም በተስፋፊ ፖሊሲው የወረራቸው ቦታዎች ሁሉ የጎንደር ፤የወሎ፤ የአፋር መመለስ ግዴታው ነው። ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. የኢትዮጵያ ሉአላዊነት እያፈረሰ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት እየበጠበጠ ፀረ ሰላም ግፈኛ ፋሽሽት ድርጅት መቀሌ መሽጎ መኖር የለበትም ።
ይህ ከታች ካርታ የሚያመልክተው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ለመውረር የተዘጋጀበት የአማራ፤ የወሎ፤ የአፋር፤ መሬት፤ ወያኔ የራሱ በሆነው ልሳን( ትግራይ ኦን ላይን) በግልፅ ያወጀው የመስፋፋት ወራር ነው። የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት ይህ ደም አፋሳሽ ፤ሃገር አፍራሽ ፤ የህ.ወ.ሓ.ት. በጎንደር በወሎ በአፋር የመስፋፋት የሤራ እቅድ ከአሁኑ በሕግ ማቆም አለበት ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
ጥቅምት ወር 2011 ዓ.ም.

OPINION
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ካመጡ አይቀር እንዲህ ጠማቂውን ነው፤ የሚያንቅርርማ እዚህስ መች ጠፋ! (በድሉ ዋቅጅራ).
በአሸባሪው የትህነግ ተጠርጣሪ አባላት ላይ በዚህ ሳምንት ክስ እንደሚመሠረት ተገለጸ።
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2