የአሜሪካው ስፔስ ኤጀንሲ ናሳ እና ሀዋይ ዩኒቨርሲቲ በትብብር በሰሩት ጥናት እንዳመላከቱት ጨረቃ በራሷ ዛቢያ ላይ የምታደርገው ተፈጥሯዊ ዑደት መዛባትና የአየር ንብረት ለውጥ በፈረንጆቹ 2030 ሊከሰት ለሚችል የጎርፍ አደጋ ስጋት መንስኤ ሊሆን ይችላል ተባለ፡፡
አሜሪካ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተሰራው በዚህ ጥናትም እንደተመላከተው÷ከፍተኛው የጎርፍ መጥለቅለቅ የሚከሰተው በፈረንጆቹ 2030 ሲሆን ክስተቱ ለ አስር ዓመታትም ሊቀጥል እንደሚችል ተተንብይዋል፡፡
የአሜሪካ የባህር እና የከባቢ አየር አስተዳደር እንዳስታወቀው በፈረንጆቹ 2019 በአሜሪካ 600 የሚደርስ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሲከሰት ይህ አሃዝ ግን እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ በብዙ እጥፍ ሊጨምር ይችላል ነው የተባለው፡፡
ፊል ቶምሰን የተባለው የሃዋይ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና ዋና የጥናቱ መሪ እንዳመላከተው÷ በጨረቃ ዑደት መዛባት ምክንያት የሚከሰተው ይህ የጎርፍ አደጋ በሀሪኬን ምክንያት ከሚደርሰው ይልቅ በመጠኑ ዝቅተኛ የሆነ ውድመት ሊያስከትል ይችላል፡፡
እንደ ጥናቱ በአሜሪካ በወር ከ 10 እስከ 15 ያህል ጊዜ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ከተከሰተ ተፅዕኖው በንግድ ተቋማት እና በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች (ፓርኪንጎች) ላይ ስለሚበረታ በርካቶች ከስራቸው ሊስተጓጎሉ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡
የጎርፍ አደጋው ውሃማ በሆኑ የአሜሪካ ዳርቻዎች እንዲሁም እንደ ሃዋይ፣ ጉዋም፣ እና አላስካ ባሉ አካባቢዎች ሊበረታ እንደሚችልም ነው የተገለፀው፡፡
ኢ-መደበኛ የጨረቃ ዑደት አዲስ ክስተት እንዳልሆነና ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 1728 ተከስቶ እንደነበረም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡
ምንጭ÷አልጀዚራ
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች






