Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Western Pressure on Ethiopia Intended to See Weak Gov’t, Nation – Scholars

    July 10, 20210

    Journalist demands UNWFP to tell truth about missing trucks

    October 3, 20210

    ብርሃኑ ባይህ እና አዲስ ተድላ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ

    December 19, 20200

    አብንና ባልደራስ ከተሸነፉ ” ውጤቱን አንቀበልም” ሊሉ የሚችሉ ፓርቲዎች እንደሚሆኑ ዲፕሎማቶች ገለጹ

    May 23, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሚስጥራዊ የቻይና ፖሊስ ጣቢያዎች በአሜሪካ ተገኙ

    December 19, 20240

    ሦስተኛው ዕድል እንዳይባክን … !

    May 21, 20220

    “Why I decided to extend my time at the club”

    May 24, 20230

    የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ዋና የጦሩ መሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ

    February 24, 20220

    “Ethiopia’s success reflects a new alternative for Africa’s development”

    January 29, 20240
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  SOCIETY  “የምንወዳደረው ከብዙ ሯጮች ጋር ነው” አብይ አሕመድ ለታላቁ ሩጫ
SOCIETY

“የምንወዳደረው ከብዙ ሯጮች ጋር ነው” አብይ አሕመድ ለታላቁ ሩጫ

Ethioreview newsEthioreview news—January 23, 20220
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

” … የኢትዮጵያ ሩጫ አሸናፊ ሆኖ ብቻ እንዲጠናቀቅ አንፈልግም። ኢትዮጵያችን ሪከርድ እንድትሰብር ጭምር እንፈልጋለን። የምንወዳደረው ከብዙ ሯጮች ጋር ነው። ከድህነት ጋር እንፎካከራለን፤ ከጎጠኝነት ጋር እንፎካከራለን፤ ከብልሹ አሠራር ጋር እንፎካከራለን፤ ከዋልታ ረገጥነት ጋር እንፎካከራለን፤ ከውጭና ከውስጥ አፍራሾች ጋር እንፎካከራለን፤ ያለ ምንም ጥርጥር ግን ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፤ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ሪከርድን ማንም እንዳይደረስበት አድርጋ ትሰብረዋለች”

የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልዕት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

ኢትዮጵያ በታላቁ ሩጫ ላይ ናት!

እንኳን ለ21ኛው የታላቁ ሩጫ ዝግጅት አደረሳችሁ፤

More stories

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ብክለቱን ማቆም ካልቻለ ከቦታው እንዲነሳ በፍርድ ቤት ተወሰነበት

November 29, 2024

ከፌጦ የጤና በረከቶች በጥቂቱ

June 10, 2024

ሲስተር አሠጋሽ ጎሳ ሰማኒያ ጊዜ ደም በመለገስ የሴቶችን ክብረወሰን ያዙ

March 16, 2021

በኢትዮጵያ የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ ማዕከል ለማቋቋም የሚስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

March 22, 2025

ታላቁ ሩጫ ለእኛ ከጤና፣ ከመዝናኛና ከኢኮኖሚ ጥቅሞቹ በላይ ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያ በታላቁ ሩጫ ላይ ስለሆነች። ድህነትንና ኋላ ቀርነትን፣ ግጭትንና ጦርነትን፣ መለያየትንና መከፋፈልን ከኋላዋ ጥላ፤ ብልጽግናንና ሥልጣኔን፣ ሰላምንና መቻቻልን፣ አንድነትንና መግባባትን ለማስፈን ኢትዮጵያ ወደፊት እየሮጠች ነው።

አንድ የስፖርት ሰው ማሸነፍ ከፈለገ አምስት ነገሮች ያስፈልጉታል። የአካል ብቃት፣ በቂ ዝግጅት፣ ትጥቅ፣ ዲሲፕሊንና በመወዳደሪያው ላይ በጊዜውና በቦታው መገኘት። ኢትዮጵያም መደመር በሚባለው ጎዳና ብልጽግና የተባለውን ሜዳልያ ለማግኘት እየሮጠች ነው። በዚህ ሩጫ እንድታሸንፍ በሁለም መስኮች የመወዳደር ብቃት እንዲኖራት ማድረግ አለብን። ኢትዮጵያውያን በቂ የአካል፣ የመንፈስና የአስተሳሰብ ዝግጅት ያስፈልገናል።

ለድሉ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ትጥቅ ወሳኝ ነው፤ ራሳችንን ከብዙ አጥፊ ነገሮች የሚጠብቅ ሀገራዊ ዲሲፕሊን ያስፈልጋል። የምንወዳደረው ከዓለም ጋር ስለሆነ በተገቢው መድረክ፣ ጊዜው ሳያልፍብን ተወዳዳሪ ሆነን መገኘትም አለብን። ዛሬ በዚህ ታላቅ ሩጫ ላይ የምትሳተፉ ሁሉ እያንዳንዱን ምእራፍ ስትሮጡ እየሮጠች ያለችውን ኢትዮጵያን እንድታስቧት አደራ እላለሁ።

የኢትዮጵያ ሩጫ አሸናፊ ሆኖ ብቻ እንዲጠናቀቅ አንፈልግም። ኢትዮጵያችን ሪከርድ እንድትሰብር ጭምር እንፈልጋለን። የምንወዳደረው ከብዙ ሯጮች ጋር ነው። ከድህነት ጋር እንፎካከራለን፤ ከጎጠኝነት ጋር እንፎካከራለን፤ ከብልሹ አሠራር ጋር እንፎካከራለን፤ ከዋልታ ረገጥነት ጋር እንፎካከራለን፤ ከውጭና ከውስጥ አፍራሾች ጋር እንፎካከራለን፤ ያለ ምንም ጥርጥር ግን ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፤ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ሪከርድን ማንም እንዳይደረስበት አድርጋ ትሰብረዋለች።

ታላቁ ሩጫ እንዲመሠረትና ታላቅነቱን እንዳከበረ እንዲቀጥል ያደረጉትን ሁሉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ። በተለይም የሀገራችን ኩራት፤ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፤ በመከራዋም ሆነ በደስታዋ ቀድመው ከሚደርሱላት አንዱ የሆነውን አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴን በዚሁ አጋጣሚ በራሴና በኢትዮጵያ ስም አመሰግነዋለሁ። ታላቅ ሰው ማለት ታላቅነቱን እንደጠበቀ፤ ለሀገሩ ታላቅ ሥራ የሚሠራ ማለት ነው። ሰው ያልፋል፤ ታሪክና ሥራ ግን ሲናገሩና ሲያስከብሩ ይኖራሉ።

ኃይሌ በዓለም አደባባይ ኢትዮጵያን በክብር አስጠርቷታል፤ ለብዙ ተተኪ አትሌቶች አርአያ ሆኗል። በተለያዩ ጥረቶች የሚገኝን ገንዘብ እንዴት ወደ ኢንቨስትመንት መቀየር እንደሚቻል ኃይሌ ምሳሌ ነው። ኃይሌ አትሌት ብቻ ሳይሆን መካሪ፣ አስታራቂ፣ ሽማግሌ ነው። ሀገሩ ስትደፈርም እንደ ነብር የሚቆጣ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ቀልድ የማያውቅ መሆኑን በተደጋጋሚ አይተናል። ኢትዮጵያ እንደ ኃይሌ ያሉ ሚልዮኖችን ትፈልጋለች።

ባለፉት ሃያ ዓመታት ታላቁ ሩጫ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ማሰባሰብ ችሏል፤ በዓመት አንዴ ስለ ሰላም፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ አብሮነት ልባቸውን እንዲሰጡ አድርጓል። በሐይማኖታዊ በዓላት አብረው መሆን ያልቻሉ ዜጎች በታላቁ ሩጫ ተቃቅፈው ይሮጣሉ፤ በብሔረሰባዊ መሰባሰቦች አንድ ላይ መሆን ያልቻሉ ሕዝቦች ታላቁ ሩጫን ጠብቀው ይገናኛሉ። ኃይሌን በታላቁ ሩጫ ስናመሰግነው ዝግጅቱ ለአትሌቲክስ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ አኳያ ብቻ ሳይሆን፥ ኢትዮጵያዊ መሰባሰብን፣ ኢትዮጵያዊ ትስስርን፣ ኢትዮጵያዊ መቀራረብን የምንፈጥርበት፤ በብሔር፣ በቋንቋና በሐይማኖት የማንታጠርበት፣ የሁላችን የሆነ ታላቅ ዝግጅትን ስላስጀመረልን ጭምር ነው።

በዚህ አደባባይ በታላቁ ሩጫ ለመሳተፍ የመጣችሁት ሁሉ ኢትዮጵያን በልባችሁ ይዛችሁ እንደምታሸንፉ አምናለሁ። ብሔር፣ እምነት፣ የፖለቲካ አመለካከትና ጾታ ሳይለያችሁ አንድ ላይ ዛሬ እንደሮጣችሁት ሁሉ፤ ኢትዮጵያ በሁሉም ነገር አሸንፋ ሪከርድ እንድትሰብር አንድ ሆናችሁ በዓለም አደባባይ እንድትሮጡ አደራ እላለሁ።

ይሄ ታላቅ ሩጫ በምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች፣ ከዚያም በመላዋ አፍሪካ፤ ብሎም በመላው ዓለም የኢትዮጵያን ስም የሚያስጠራ ታላቅ ክንዋኔ ሆኖ እንደሚስፋፋ አምናለሁ። ለዚህም መንግሥት አስፈላጊን ድጋፍ ሁሉ ይሰጣል። ለኢትዮጵያ እንሩጥ፤ አንድ ሆነን ከሮጥን ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጥር 15፣ 2014 ዓ.ም

SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

ዳያስፖራው ያሰባሰበውን ገንዘብ በማጭበርበር ወደ ሌላ አካውንት ያዘዋወሩ የንግድ ባንክ ሰራተኞች ተያዙ
Violence triggers diplomatic push to save Sudan
Related posts
  • Related posts
  • More from author
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

August 23, 20250
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 20250
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 20250
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news