Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  SOCIETY  አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት
SOCIETY

አስጨናቂዋን ሰዓት ወደ ደስታ የቀየረው የኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ስኬት

Ethioreview newsEthioreview news—August 23, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

መነሻው ቀላል ነው፡፡ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን፡፡ “UTI” ይሉታል የጤና ባለሙያዎች፡፡ ለዚህ ምርመራ ነበር ታካሚዋ ጤና ጣቢያ የሄደችው፡፡ ቢሆንም ግን ከሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽኑ ተጨማሪ ሌላ ዱብዳ ተነገራት፡፡ ስለዚህም ተጨማሪ ምርመራ እና ሕክምና እንድታገኝ ወደ አለርት ሆስፒታል ተላከች፡፡

ምርመራው ቀጠለ የሲቲ ስካን ምርመራ፡፡ ውጤቱ ደረሰ፡፡ የሽንት ቱቦው ኢንፌክሽኑም ዳነ፤ ተረሳና ሌላ ጭንቀት፡፡ ከኩላሊት ከፍ ብሎ ካለ ሆርሞን አመ የሰውት ክፍል ላይ የወጣ ጤነኛ ያልሆነ እጢም ተገኘ::

ሰላም አበበ (ስሟ የተቀየረ) ትባላለች፡፡ ጤነኛ ያልሆነ እጢ አለብሽ ተብላለች፡፡ ያውም በሆድ ውስጥ፤ያስጨንቃል፡፡ የደረሰበት ያውቀዋል፡፡ ገና በ30 ዓመት ዕድሜዋ። ያላት አማራጭ ደግሞ ሆዷ ተቀዶ እጢው መውጣት ብቻ ነው፡፡

ካልሆነ እጢውም ይጨምራል፡፡ ካንሰርም ሊሆን ይችላል፡፡ በሕይወቷም ከባድ ችግር ይፈጥራል። ይህ እጢ ለሰውነት አስፈላጊ የሆኑ ሆርሞኖችን ከሚያመነጭ አድሬናል እጢ ላይ ነው የወጣው፡፡ እጢውም የሚገኘው ቀዶ ህክምናን ፈታኝ በሚያደርግ ቦታ በኩላሊት እና በጉበት መሃል፡፡ በኩላሊት በስተአናት፡፡ በቀኝ ጎን፡፡

More stories

ወገኛ ምርኮዎች !!

August 27, 2021

በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግሥት የሚተገበር የ550 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይጀመራል

January 29, 2022

በድንገተኛ የሞተር ብልሽት የፖላንድ አውሮፕላን አዲስ አበባ አረፈ

September 18, 2021

ኤርትራዊያን ስደተኞች “አሸባሪው ወራሪሃይል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ፈጽሞብናል” ሲሉ የዓለም ሕብረተሰብ ተማጸኑ

February 23, 2022

አለርት ሆስፒታል የኢንዶክራይን ቀዶ ህክምና ሰብ ስፓሺሊስ አልነበረም፡፡ ስለሆነም ታካሚዋ ለተሻለ ህክምና ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ሪፈር ተባለች። ሰላም ሰላም ትሆን ዘንድ ከጡት እና ኢንዶክራይን ቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት እንዲሁም የቀዶ ህክምና ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የህክምና ትምህርት ዲን የሆኑት ዶክተር ወንድወሰን አምታታው ያስፈልጓት ነበር፡፡ ተመረመረች፡፡

ዶክተር ወንድወሰን አምታታው ይናገራሉ።

“ሰላም እንደመጣች ከኢንዶክሮኒሎጂስት ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞች ጋር ሆነን ምርመራ አደረግንላት፡፡ ዕጢውም ቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልገው ወሰንን፡፡ ከቀዶ ጥገናው በፊት ግን ተጨማሪ ምርመራዎች ማሰራት ግድ ይሉ ነበር፡፡ ቢሆንም አልተሰራም፡፡ ሰላም እነዚያን ምርመራዎች ማድረግ አልቻለችም፡፡ ብዙው ምርመራ ሀገር ውስጥም የሉም፡፡

ያሉትም ምርመራዎች በጣም ውድና የታማሚዋ አቅም የሚፈታተን ነበር፡፡ ከቀዶ ሕክምናው በፊት ሜታኔፍሪን፣ ኖርሜታኔፍሪን፣ ሬኒን… የተባሉ የሆርሞን ምርመራዎች ልታሰራ ይገባል፡፡ ቢሆንም ታማሚዋ አቅሟ አልቻለም፡፡ አላሰራችም፡፡ አታሰራም፡፡ ያስጨንቃል”፡፡

ሌላም ጭንቀት አለ፡፡ ከሰመመንና ፅኑ ህሙማን ስፔሻሊስት ሐኪሞች ጋር ሌላ ምክክር ተደረገ። የሰመመን ህክምና ቡድንም መከረ ።በመጨረሻም ለታካሚዋ ተነግሯት Risk ወስደን ቀዶ ህክምናውን እንስራው ብለን ወሰንን። ሌላ አማራጭ አልነበረም። ታካሚዋም ስለ ሁሉም ነገር ተነገራት። ሰላምም “ፈጣሪ ያውቃል በውሳኔዎቻችሁ ሁሉ እስማማለሁ” አለች።

ቀጣዪ ጥያቄ ምን አይነት ቀዶ ህክምና? የሚለው ነው፡፡ “ይህን እጢ ለማውጣት የተለመደው ህክምና ትልቅ የሆድ ቀዶ ህክምና ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ቀዶ ህክምና ሆድ በመቅደድ ከሆነ ሰርጀሪው የሚጀመረው ከላይ ሆዷ ጀምረን በቀኝ ሆዷ መጨረሻ ድረስ መቅደድ ይኖርብናል፡፡

ይህም ከባድ ሰርጀሪ እና ረዘም ላለ ጊዜ የህመም ስቃይ ያለው ሲሆን በተጨማሪም ትልቅ ጠባሳ በሆዷ ላይ ጥሎ ያልፋል፡፡ ለአንዲት ለ30 አመት ሴት ይህንን ስቃይና ትልቅ ጠባሳ መተው በጣም ከባድ ነበር፡፡ ስለዚህ ምን አማራጭ አለ ብለን አሰብን”፡፡ ይላሉ የጡት እና ኢንዶክራይን ቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት ዶክተር ወንደሰን አምታታው፡፡

ሆድ ሳይከፍቱ የአድሬናል ዕጢ ቀዶ ሕክምና

ዶክተር ወንድወሰን ስለ ሕክምናው ሲናገሩ የአድሬናል ላፖራስኮፒክ ቀዶ ህክምና ትንንሽ ቀዳዳዎችን (ከአንድ ሳንቲም ባልበለጡ ለመሳሪያ ማስገቢያ ከ3-4 በሆኑ ቀዳዳዎች) በመፍጠር ካሜራና ለቀዶ ህክምና የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች በመክተት ቀዶ ሕክምናውን መሥራት የሚያስችል ነው።

ይም የረቀቀ የሕክምና ጥበብን የሚፈልግ እና ለታካሚዋ አጅግ በጣም የተሻለ ዘመናዊ የህክምና አማራጭ ነው ይላሉ፡፡ ዘመኑን የዋጀውን ቀዶ ሕክምና እንደ ተቋም በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ማድረግ አንችላለን ባለሙያም አለ ሲሉ ያስረዳሉ፡፡ የኢንዶክሪንና ጡት ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊስታቸውን በህንድ ሀገር የተማሩት ዶክተር ወንድወሰን አምታታው፡፡

እንዲህ ያለ ቀዶ ሕክምናም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአደጉት ሀገር ተመራጭ ሆኖ ይሰራል፡፡ ቀዶ ህክምናው ሆርሞን የሚያመነጭ ዕጢ ላይ እንደመሆኑ መጠን እጢው ሲቆረጥ ደም ይፈሳል፡፡ ስለዚህ በአንዴ እጢውን ቆርጠን እንዲሁም ደም እንዳይፈስ የተቆረጠው ቦታ ላይ ቆንጥጠው የሚይዙ ሀርሞኒክ ወይም ላይጌቸር የተባሉ ዘመናዊ መሳሪያዎች እጅግ አስፈላጊና ያለ እነዚህ መሳሪያዎች ሰርጀሪውን ማሰብ ከባድ ነበር ይላሉ ዶ/ር ወንድወሰን፡፡ ግን እኛ ጋር ሁለቱም ኖረው አያውቁም የሉንም፡፡ሆኖም ግን ባሉን መሳሪያዎች ልንሰራ ወሰንን ይላሉ።

ከኪያም የሕክምና ቡድኑ ተሟላ፡፡ አስፈላጊና አቅም የፈቀደው ሁሉ ነገር ቀረበ፡፡ ሰላም በሰመመን ሐኪሞች እና ረዳቶች ሀገር ሰላም ብላ ተኛች፡፡ ሆዷ ላይ አራት ቦታ መጠነኛ ቀዳዳ ተደረገላት። ከዚያም በካሜራ ታግዘን በስክሪን እያየን ቀዶ ህክምናውን ጀመርን ከአሁን አሁን አቁሙ የሚሉ አንደበቶችን ከሰመመን ሀኪሞቹ ለመስማት ጥረት በማድረግ። ሆኖም ግን ቀጥሉን ብቻ በመሰማት ሁለት ሰዓት የፈጀ ቀዶ ሕክምና ተደረገ፡፡

ቀዶ ሕክምናውም ተሳካ፡፡ በጥቂት ቀዳዳዎች እና ለአይን በማይታዩ ጠባሳወች ያ እጢ ተወገደ፡፡ እናም በክፍሉ ደስታ ሆነ፡፡ ሰላምም ከሰመመን ነቃች ከኦፕራሲዮን ቴብልም ወደ ማገገሚያ ክፋል ተዛወረች። ፈጣሪም ረዳት።

በሕክምና አገልግሎቱ 102 ዓመት ላስቆጠረው የካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ የመጀመሪያ የሆነው የላፖራስኮቲክ አድሬናሌክቶሚ (ሆድ ሳይከፈት ቀዶ ሕክምና) በስኬት ተጠናቀቀ፡፡ የወጣውም እጢም ወደ ኦንኮ ፓቶሎጅ ተላከ የተላከውም ውጤት ከሶስት ቀናት በኃላ ደረሰ፡፡ ካንሰር አይደለም ካንሰር የሌለው እጢ መሆኑም ተረጋገጠ። ትልቅ ብስራት ለተጨነቀችው የ30 ዓመቷ ወጣት። ዛሬ ሰላም ሰላሟን አግኝታ ፈጣሪዋን በማመስገን ላይ ትገኛለች።

ቀዶ ሕክምናውን በበላይነት የመሩት የጡት እና ኢንዶክራይን ቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት እንዲሁም የቀዶ ህክምና ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ወንድወሰን አምታታው በሕክምናው የተሳተፉት የቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ፍፁም ተረፈ-ጠቅላላ፣ አንሰቲዚሎጅስት ዶክተር ያለው ሁሴን እና ቡድኑ፣ ዶክተር ዳንኤል ዶር ጌታቸው ረዚደንት ሕኪሞች፣ አቶ ደረሰ ቶላ-ትሬንድ ላፓራስኮፒክ ስክረብ ነርስ እና ቡድኑ ስለሁሉም ውጤት ፈጣሪን እመስግነው የሕክምናው ስኬት አመርቂ መሆኑን ገልጸዋል።

መረጃውን ያደረሰን የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ታካሚዋ ከሕክምናው በኋላ በዓይን የማይታይ ጠባሳ ያክል ሽሮላት ድና መደቤቷ መሄዷን አሳውቋል።

Via EBC


SOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
“ዓለም እያዘነብን እየሳቀብን ነው አንድ እንሁን” ዘመነ፤ መከላከያ እርምጃ የወሰደባቸውን ዘረዘር
የደቡብ ሱዳን ወደ ቀውስ ማምራትና የተመድ ማስጠንቀቂያ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

August 22, 2025
SOCIETY

“በጠለምት ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ እንስሳት እየሞቱ ነው፤ ሕዝብ እየተሰደደ ነው”

August 18, 2025
Events

ማርታ አምስት ቀን በላስቲክ ጀልባ በባህር – ደባርቅ፣ ጣሊያን፣ ኖርዌይ፣ አዲስ አበባ – የባከነ ሕይወት

July 25, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2