Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!
NewsSOCIETY

በ2018 ጓደኞቼ ዩኒቨርስቲ ይገባሉ፤ በድህነት ከተማ ሄዶ መማር ይልቻለው ታዳጊ ለቅሶ!

Ethioreview newsEthioreview news—August 22, 2025
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። ላለፉት ሁለት ዓመታት ወደ ትምህርት ቤት አልሄድኩም። ትምህርት ባይቋረጥ ኖሮ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዩኒቨርሲቲ የምገባበት ጊዜ ነበር። ቤተሰቦቻቸው የገንዘብ አቅም ያላቸው የእድሜ አኩዮቼ ወደ ባሕር ዳር ሄደው ተምረው አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲ ሊገቡ ነው። እኔ ግን ሁለት ዓመት እድሜዬን ያለ አግባብ አባከንኩኝ” የሚለው የምሥራቅ ጎጃም ዞን እጁ እነሴ ወረዳ አሚኮ ያነጋገረውና ስለሚፈራ ስሙን የደበቀ ታዳጊ ነው።

ይኸው ታዳጊ አሁንም ትምህርት ሊጀመር በመኾኑ ደስታውንም ገልጿል። ተደርጎ በነበረው በሙከራ የምዝገባ ጊዜ መመዝገቡንም አስታውቋል። እሱ ብቻ ሳይሆን በፍርሃት ስማቸውን እየደበቁ በቤተሰባቸው፣ በልጆቻቸውና በአካባቢው ማህብረሰብ ላይ በግራና በግል የደርሰውን ውድቀት የገለጹ ብዙ ናቸው።

ይህን መስማት በእጅግ ያማል። ማሰብ ለሚችሉ ሁሉ ዕረፍት የሚሰጥም አይደለም። ጉዳዩ ከከርስና ከዩቲዩብ ሽቀላ፣ እንዲሁም በግርድና ከሚገኘው ትራፊ በላይ ነው። የዚህ ልጅ አስተያየት የልብ ውስጥ ለቅሶ ነው። ሲቃ ነው። “እድሜዬን፣ የወደፊት ትልሜን፣ እድሌን ወዘተ ተነጠኩ ” እያለ እያነባ ነው። ማን ይረዳው? እንዲህ ያሉትን ታዳጊዎችና ቤተሰቦቻቸውን ማን ያሳባቸው? እንደዚህ መሰል ሚሊዮን ለጋ ታዳጊዎች ላይ ፈርዶ የ”ሰበር” ዜና ነጋዴ የመሆንን ዝቅጠት በየትኛውም ቋንቋ መግለጽ አይቻልም። በማንኛውም ዓይነት ምሳሌ ማስረዳት አይቻልም። እንደውም እንደ መዓት የሚታይ ነው። በዕርግጥም ማዓት …..

የአማራ ክልል ቢሮ የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቅድመ ዝግጅት እና አጀማመርን አስመልክተው ባቀረቡት ሪፖርት “በአማራ ክልል 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አልሄዱም” ብለዋል። ይህን ጉድ፣ ይህን ውድቀት፣ ይህን በታዳጊና ሕጻናት ላይ በግፍ የተወሰደ የጅምላ ግፍ የሚያወራርደው ማን ይሆን?

More stories

ሶማሊላንድ በፀጥታ ስጋት ምክንያት የግብፅ የባሕል ቤተመጽሐፍን መዝጋቷን አስታወቀች

September 12, 2024

የአሜሪካ መንግስት በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገለፀ!!!!

February 17, 2021

“የአሜሪካ መንግስት ለምርጫ ጉዳይ አልላከኝም” ጄ ፍሪ ፌልትማን – አፍሪቃ ህብረትና አራት ዓለም አቀፍ ተቋማት ምርጫ ይታዘባሉ

May 12, 2021

ዶ/ር ዳንዔል- በማይካድራው ጭፍጨፋ የትህንግ አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመኖሩ መረጃ የለም

March 27, 2021

አሁን እየወጡ ባሉ መረጃዎች ከበፊቱ የተሻለ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ይመለሳሉ ከሚለው ተስፋ ሰጪ ዜና ጎን ለጎን ወላጆች ስጋት ውስጥ መግባታቸው እየተሰማ ነው። አባት ስለልጆቹ አስተያየት ለመስጠት የሚሰጋበትና ስሙን የሚደበቅበት የአማራ ክልል እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል?

በአማራ ክልል “ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ አሁን በክልሉ ባለው ግጭት” ምክንያት ጉዳት የደረሠባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባት 112 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ማስታወቁ ይታወሳል። ችግሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶች እንዳይሄዱ ማገድ ብቻ ሳይሆን መማሪያ ስፍራዎችም መውደማቸው ” ምን? ለማን ታስቡ እየተደረገ ነው?” የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

የቢሮው ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክተር ዘመነ አበጀ በጦርነቱ እና በአሁኑ ግጭት በርካታ ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸውን ሲገልጹ፣ ለአብነት በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አስታወቀው ነበር።

ቢሮው ባስጠናው ጥናት መሠረት በአጠቃላይ በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች ወደ አገልግሎት ለመመለስ ያስገልጋል የተባለው 112 ቢሊየን ብር ትምህርት ቤቶችን ከመገንባትና መጠገን በተጨማሪ ተጓዳኝ የትምህርት ሥራዎችን ለማከናወን የሚውል ነው።

በሰሜኑ ጦርነት 4 ሺህ ትምህርት ቤቶች በአማራ ክልል መውደማቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ማስታወቁ ይታወሳል። ከዚህ ውስጥ የተጠገኑት ከ10 በመቶ በላይ አለመሆኑም ተገልጿል።

በዚሁ የሰላም ችግር ሳቢያ በ2017 የትምርት ዘመን 40 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ሳይካሄድ፣ አንድም ትምህርት ቤት ያልተከፈተባቸው 17 ወረዳዎች መኖራቸው የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) በህዳር ወር መግለጻቸው አይዘነጋም።

ይህንና ሌሎች ሰፊ ጉዶችን የተሸከመው የአማራ ክልል በውስጡ የነገር አገር ተረካቢ የሆኑ ታዳጊዎችን ተስፋ እየመከነም ነው። ታዳጊው እንዳለው እድሚያቸው እየተሰረቀ፣ ተስፋቸው እየጠወለገ፣ ብርሃናቸው እየደበዘዘ፣ ስሜታቸው እየቀዘዘ፣ አስተሳሰባቸው እየተበላሸ ነው። ለዚህ ሁሉ ቀውስ፣ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ታዳጊዎችና ሕጻናት ጉዳት ታሪክ ማንን ይጠይቅ ይሆን?

በትምህርት ብቻ ሳይሆን አምቡላንስ የሚነድበት አማራ ክልል፣ የጤና ጣቢያ የሚወድመበት፣ ማዳበሪያ አርሶ አደር ጋር እንዳይደርስ የሚደረግበት፣ የሕዝብ የገንዘብ ተቋማትና የልማት ድርጅቶች የሚዘረፉበት አማራ ክልል ከዚህ ችግር ቢላቀቅ እንኳስን እንዴት ዳግም ተመልሶ ያገግም ይሆን?

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በርካታ ትምህርት ቤቶች ላለፉት ሁለት ዓመታት አላስተማሩም። ብዛት ያላቸው ተማሪዎችም ከትምህርት ገበታ ውጭ ኾነው ቆይተዋል፡፡ በ2018 የትምህርት ዘመን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለማስጀመር የክረምት የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ፡፡ ቤተሰብ “መጨረሻውን ያሳምረው” እያለ ነው። ተማሪዎችም በቁጭት የሚከፈትበትን ቀን እየጠበቁ ነው። ትምህርት ለማስጀመር ከመጋቢት ወር ጀምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ውይይት ሲካሄድ ቆይቶ ነው ምዝገባ የተጀመረው። ይህ ነበር “ሰበር ዜና” ግን ትርፍ የለውም !!

የተጠቀምነው የጥር ወር ዳታን ጭምር ነው!!


NEWSSOCIETY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ራስ – በኢትዮጵያዊያን በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች IA መጠቀም የሚያስችለው መተግበሪያ
አረምና መልከ ብዙ ዝርፊያ በኢትዮጵያ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2