Skip to content
VOE
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሔማን በቀለ – ታይም መፅሄት የዓመቱ ምርጥ ያለው ህልመኛ ታዳጊ ሳይንቲስት

    September 4, 2024

    በዩክሬን በኩል ወደ አውሮፓ የሚደርሰው የሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝ  ስራው እንዲቆም ተደረገ

    January 1, 2025

    በኦሮሚያ ክልል ማን፣ ምን ፈጸመ? የኢሰመኮ ሪፖርት

    August 5, 2025

    በኦሮሚያ በሌብነት ጉዳይ አናቱ ተፈርቷል፤ በ289 ሺህ ካሬ.ሜ.መሬት ላይ ማጣራት ተጀምሯል

    December 3, 2022

    የአፋር ክልል ከ፴ ዓመታት በሁዋላ በትግራይ ክልል የተወሰደበትን ኣንድ ቀበሌ “ነጻ አ ወጣሁ” አለ

    June 7, 2021
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News2  አሸባሪው ከወረራቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጣና ጦርነት እንዲያቆም የአፋር ክልል አሳሰበ
News2

አሸባሪው ከወረራቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጣና ጦርነት እንዲያቆም የአፋር ክልል አሳሰበ

Ethioreview newsEthioreview news—January 27, 2022
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

አሸባሪው ህወሓት እንደ አዲስ ከወረራቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጣና በቀጣናው የከፈተውን ጦርነት እንዲያቆም የአፋር ክልላዊ መንግስት አሳሰበ፡፡

አሸባሪው ህወሃት በአፋር ህዝብ ላይ ከሁለት ዓመታት ተኩል በላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ቢፈጽምበትም ለወንድም የትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ በርካታ ስራዎች በክልሉ መንግስት በኩል መሰራታቸውን ነው መገለጫው ያመለከተው።

የክልሉ መንግስት ከተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ጋር በቅርበት በመስራት ለትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ባለፉት ሶስት ዓመታት በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ለአብነት ጠቅሷል።

ነገር ግን በውሸት እና በሴራ አፉን የፈታው አሸባሪው ህወሃት በአፋር ኪልበቲ ረሱ (ዞን ሁለት) በተለያያዩ ወረዳዎች ወሰን ጥሶ ገብቶ በንፁሃን ዜጎች ላይ የከፈተውን ጦርነት አስመልክቶ መሰረተ ቢስ መግለጫ ማውጣቱን አስታውቋል።

More stories

መንግሥትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ለቀጣይ ምክክር ግብአት የሚሆኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ለመወሰን እየመከሩ ነው

May 21, 2024

አብን ለአራተኛ ጊዜ በአማራ ላይ ወረራ መፈጸሙን ጠቅሶ፤ ሕዝብ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበ

April 16, 2024

ኦነግ ጃዋር በመስረተው አዲስ ህብረት ውስጥ “የለሁበትም” አለ፤ ውስኔው ከሕግ ተጠያቂነት ለማለጥ ነው ተብሏል

August 5, 2025

ሩሲያ ከስፔስ ጥቃት ፈጸመች !!

February 24, 2022

እርስ በርሱ የሚጋጨውና በውሸቶች የታጨቀው የህወሃት መግለጫ የአፋርን እና የትግራይ ህዝብን በማጋጨት ያልተገባ ትርፍን ለማጋበስ ቆርጦ እንደተነሳ በግልፅ ቃላቶች በማሳየት እና የአፋርን መልካም ገጽታ ለማጠልሸት በሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ መሆኑን አመልክቷል።

ከአሁን በፊት በአፋር ክልል በርካታ ወረዳዎች ወሰን ጥሶ በመግባት በአሰ ዳ፣ በጋሊኮማ፣ በኡዋ፣ በጭፍራ፣ በሀደሌ ኤላ፣ በደርሳ ጊታ እና ሌሎች አካባቢዎች አሰቃቂ የዘር ማጥፋትን ጨምሮ በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳትን የሽብር ቡድኑ ማድረሱን አስታውሷል።

“ለሰላም ስል ወጥቻለሁ” የሚል የውሸት ማደናገሪያ ቢነዛም ወሯቸው ከነበሩ አካባቢዎች እንዲወጣ ቢደረግም በማግስቱ ከታህሳስ 10/2014 ጀምሮ በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች የደረሰበትን ኪሳራ ለማካካስ እና ለመበቀል በኪልበቲ ረሱ በአብኣላ በኩል እና በተለያዩ ወረዳዎች በኩል ግን ጥቃቶችን አቁሞ አያውቅም ብሏል።
ይህንንም የሽብር ቡድኑ የሚያደርሰውን ጥቃቶች እንዲያቆም የክልሉ መንግስት በተደጋጋሚ ሲያሳውቅ የቆየ ቢሆንም ቡድኑ ከባድ መሳሪያ ወደ ንፁሃን ዜጎች በመተኮስ ህይወት እየቀጠፈ እና ሆስፒታሎች፣ የጤና ተቋማት እና ትምህርት ቤቶችን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ ድብደባ እየፈፀመ መሆኑን ነው ያስታወቀው።

ከሰሞኑ ደግሞ በተደራጀ መልኩ በአብአላ፣ በመጋሌና ኤረብቲ ወረዳዎችን በመቆጣጠር እና በራህሌ ወረዳንም ከፊል ቀበሌዎች ድረስ ዘልቆ በመግባት ከባድ ጥቃት ከፍቶ ንፁሃንን በመግደል እና በማሳደድ ወረዳዎቹን እያወደመ እንደሚገኝና ከ220 ሺህ በላይ ንጹሃን ከቤት ንብረታቸው እንዳፈናቀለ የአፋር ክልል አስታውቋል።

አሸባሪው ቡድን መግለጫ ብሎ በሰጠው የውሸት ተረት ተረት ለአፋር እና ለትግራይ ህዝብ አሳቢ መስሎ የራሱን የሽብር ዕድሜውን ለማራዘም እና ህዝቦችን ለማባላት ባለፉት ሶስት ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረ ሴራ በመሆኑ ሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች የሽብር ቡድኑ የሚያሰራጫቸው የውሸት ፕሮፖጋንዳ እና ድራማዎች ሰለባ ሳይሆኑ ከወንድም የአፋር ህዝብ እና መንግስት ጎን በመሆን የትግራይ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጭቆናና አፈና ጊዜውን ሊያሳጥር ይገባል ሲል አሳስቧል።

አሸባሪው ቡድን የራሱን እድሜ ከማራዘም ውጭ ጭራሽ ቅንጣት ታክል ለህዝብ ሰብዓዊነት የሚሰማው አለመሆኑ የአፋር ንፁሃንን በመግደልና በማሸበር ብቻ ሳይሆን እየገለፀ ያለው፣ ከትግራይ እናቶች ጉያ መንጥቆ የሚያወጣቸውን በጦርነቱ በማሰለፍ እና በኪልበቲ ረሱ በኩል ለትግራይ ህዝብ ይደርስ የነበረውን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲስተጓጎል አካባቢው የጦርነት ቀጣና እንዲሆን ተደጋጋሚ ጥቃት በመፈፀምም ነው ብሏል።

ቡድኑ ርሃብን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም እና የፖለቲካ ትርፍ በመፈለግ እየፈጸመ ካለው የሽብር ተግባሩ እንዲወጣ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት እና የሽብር ቡድኑ በተደጋጋሚ የሚያወጣቸውን የውሸት ማወናበጃ መግለጫዎችን ሳይሆን መሬት ላይ ያለውን እውነታ በመረዳት ይህን ድርጊቱን በቃ እንዲል ጥሪ አቅርቧል።

በአካባቢው አንድም የመንግስት ኀይል በሌለበት እና “የኤርትራ ወታደሮች እና ቀይ ባህር አፋር” በሚል በበሬ ወለደ ወሬ ሽፋን ንጹኃን ላይ የሚያደርሰውን የጅምላ ጭፍጨፋ እንዲያቆም እና ገብቶ ከነበረባቸው የአፋር ወረዳዎች እና ቀበሌዎች በአስቸኳይ እንዲያወጣ እንዲደረግ ክልል ጠይቋል።

የክልሉ መንግስትም ሆነ የአፋር ህዝብ ለትግራይ ህዝብ በቡድኑ ወረራና ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደርስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር የሚሰራ ይሆናልም ብሏል።

POLITICS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
The West fears Russia is about to attack Ukraine. But that’s not the way Russians are seeing it on TV
አፋር ጄኖሳይድ እየተፈጸመ ነው፤ መንግስት የት ነው? እነዚህ ልጆች ምን አደረጉ?
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News2

ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ ሊሆኑ አይገባም – በለጠ ሞላ

March 8, 2026
News2

ለክቡር የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝና ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የቀረበ ጥሪ

March 8, 2026
News2

ስምረት ፓርቲ የትግራይ ወጣት ለትህነግ ጀርባ መስጠቱን አስታወቀ

March 6, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2