በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር / ኦነግ “ሲያትል ተሰባስበን ህብረት መሰረትን” ካሉት ውስጥ “የለሁበትም” ሲል መግለጫ አወጣ። ሲያትል ትመሰረተ የተባለው የኦሮሞ ልሂቃን ህብረት ጦርነት ከከፈቱ፣ ከውጭ አገራት መንግስታት ጋር ግንባር ከፈጠሩ፣ በውጭ አገራት ከሚረዱ ኃይሎች ጋር ሳይቀር አብሮ እንደሚሰራ ማስታወቁ አይዘነጋም። ፕሮፌሰር መረራ የሚመሩት ኦፌኮ በህብረቱ ውስጥ እንዳለበት ቢጠቀስም ቢያንስ እንደ ኦነግ አላስተባበለም። ኦነግ የያዘው አቋም በሕግ ላለመጠየቅ ሊሆን እንደሚችል አስተያየት የሰጡ አሉ።
የኦሮሞ ምሁራንና የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በሚል እራሱን የሰየመ የልሂቃን ቡድን ባሳለፍነው ሰሞን በዩናይትድ ስቴትስ ተሰብስቦ በኦሮሚያ ክልል፣ በኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ መቅወያየውቱን ገልጾ የፖለቲካ ግቡን አስቀምጦአ ነበር። በሕብረቱ ውስጥ እንደተወከለ የተነገረለት ኦነግ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ በስብስቡ ውስጥ የወከለው አካል አለመኖሩንና ይፋ አድርጓል። በይፋ “የለሁበትም” ሲል በሕግ ሊነሳበት የሚችለውን ስጋት ገፏል።
የኦሮሞ ምሁራን እና የፓለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በሚል እራሱን የሰየመ የልሂቃን ቡድን ባሳለፍነው ሰሞን በዩናይትድ ስቴትስ ተሰባስቦ ህብረት መመስረቱን ሲያስታውቅ ወዲያው የተነሳስው ጥያቄ “አገር ቤት ያሉት ኦነግና ኦፌኮ በሰላማዊ መንገድ እነታገላለን እያሉ እንዴት ከዚህ ህብረት ጋር ሊቀላልቀሉ ቻሉ” የሚለው ነበር።
በርካቶች እንደሚሉት በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የተለመደው የፖለቲካ ጨዋታ የሰላምና የመሳሪያ ትግሉን አንድ ላይ በስልት መጫወት ነው። መሪዎቹ ከተማ ተቀምጠው ወታደውራዊ ክንፎቻቸው በጫካ የተኩስ ትግል ያደርጋሉ በሚል የሚከሰሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ምላሻቸው ” ተለያይተናል። አብረን አንሰራም” የሚል ነው። አዲስ አበባ የተቀመጡት መሪዎቻቸው ይህን ይበሉ እንጂ አንድም ቀን በንጹሃን ላይ ለሚፈጽሙት በደል በገሃድ ሲቃወሟቸው አይሰማም።
ሲያትል ስብሰባ ተቀምጦ የነበረዉ ይኸዉ የልሂቃን ስብስብ ውስጥ በአገር ቤት በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ውስጥ የሚገኙ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ – ኦነሠ ) በማለት አንድ ድርጅት እንደሆኑ አድርጎ በመግለጽ በስብሰባው መሳተፋቸውን በአደባባይ አስታውቋል።
ይህ ከሆነ ከቀናቶች በሁዋላ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ባወጣው ይፋዊ መግለጫ በስብስቡ ውስጥ የወከለው አካል አለመኖሩንና ተሳትፎም አለማድረጉን አመልክቷል። ስለህብረቱም የሰማው በሚዲያ እንደህነ ጠቁሟል።
” …. የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች (ኦነግ-ኦነሠ፣ ኦፌኮ እና ኦነግ) አስፈላጊውን ለውጥ ለማምጣትና መጪውን ሽግግር ስኬታማ ለማድረግ በተደራጀ መንገድ የሚደረግ ያለውን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለመደገፍ መስማማታቸውንም በመግለጽ፤ ለተለያዩ አካላት አብሮ የመስራት ጥሪ አሰምቷል” ሲል ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ የጎጃም ፋኖ አድናቆቱን ጠቅሶ አብሮ ለመስራት መዘጋጀቱን ማስታወቁ አይዘነጋም።
ተፈጠረ በተባለው ህብረት ውስጥ ያለበት የኦሮሞ ነጻነት ግባር (ኦነግ) ግን በዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ተደርጓል በተባለው የውይይት መድረክ ላይ ተሳትፎ አለማድረጉንና ሰውም አለመወከሉን ጠቅሶ ስሙ ያለአግባብ ባልነበረበት ስፍራ መጠቀሱን ተቃውሟል፡፡ ፓርቲው ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፤ ኦነግ የሲያትል ውሳኔ በሚል ከተላለፈው የፖለቲካ አቅጣጫ ውስጥ ምንም አይነት ተሳትፎ እንደሌለውና ስሙም በዚያ መጠቀሱ ስህተት ነው ብሏል፡፡
የፓርቲው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ድሮ በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ተጨማሪ አስተያየት፤ “ኦነግ በዚህ ስብሰባ ላይ፣ አልተጋበዘም፣ አልተሳተፈም እንዲሁም የወጣው የአቋም መግለጫ እኛን የሚመለከተን አይደለም” ሲል ነው የገለጸው፡፡ ፓርቲያቸው ጉዳዩን ከማህበራዊ ሚዲያ መስማቱን የገለጸው ኦነግ አቋሙንም ለሚከተለው ህዝቡ ይፋ ማድረጉንም አቶ ዓለማየሁ አስታውቀዋል፡፡
ለኦሮሞ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የአንድነት ጥሪ ያቀረበው የአቋም መግለጫ ያወጣው የፖለቲካ ልሂቃን ስብስቡ ግን ፤ በኦሮሞ የፓለቲካ ኃይሎች መካከል የተጀመረው ውይይት እንዲቀጥልና ከሌሎች የአገሪቱ ሕዝቦችና ዜጎች ጋር ምክክር ለማድረግ ከስምምነት እንደተደረሰበት አሳውቋል። በዚህም ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ዓለማየሁ ድሮ፤ “እኛ በመሪህ ደረጃ የኦሮሞ ህዝብ እና የፖለቲካ መሪዎች አንደነት የምንደግፈው ቢሆንም ይሄን መድረክ በተመለከተ ግን ምንም ተሳትፎ ያላደረገበት በመሆኑ ውሳኔውንም እንደማይቀበለው” ነው የገለጸው፡፡
ኦነግ “ሁለት መንገድ አጣቀስክ” በሚል ላለመጠየቅ ሲል “እኔ የለሁበትም” ማለቱን የገለጹ ኦፌኮ ዝምታን መምረጡ አስገርሟቸዋል። “ቢያንስ ለፋቸው እንኳን እንዴት ተቃውሞ አላሰሙም” የሚሉ “ነገ መንግስት መሳሪያ ካነገቡ፣ ከተርምስ ኃይሎች ጋር አብራችሁ ትሰራላችሁ ብሎ ህግ ቢጠቅስ ምን ይመልሳሉ” ሲሉ ጠይቀዋል።
የኦነኝ መግለጫ ተከትሎ ኦፌኮ ምን አቋም እንዳለው ለማወቅ ለፕሮፌሰር መረራ ጥያቄ ለማቅረብ ብንደውልም ስላካቸው አይነሳም። ኦፌኮ መስል በሚሰጥበት ወቅት ምላሹን የምናትም እንደሆነ ከወዲሁ እናስታውቃለን።
ጃዋር ህብረቱ ከተፈጠረ ቀናት በሁዋላ በቅርቡ ለውጥ እንዲሚመጣ፣ መንግስትም እንደሚወድቅ የሚያበስር መልዕክት በማህበራዊ ገጹ ማሰራጨቱ ይታወሳል። ኦነግም ይህ ከሆነ በሁዋላ ነው መግለጫ በማውጣት “የለሁበትም” ያለው።

