Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News2  የሶማሊያ ምርጫ ፣የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ በአፍሪቃ
News2

የሶማሊያ ምርጫ ፣የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ በአፍሪቃ

Ethioreview newsEthioreview news—May 15, 2022
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ከአንድ ዓመት በላይ ሲጠበቅ የነበረው የሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነገ ይካሄዳል።በነገው ምርጫ አሸንፎ ስልጣን የሚይዘው ፕሬዝዳንት የሰርጎ ገቦች ጥቃትና ረሀብ ያስከትላል ተብሎ የሚያሰጋውን ድርቅ ጨምሮ በርካታ ፈተናዎች ተጋርጠውበታል። በበርካታ የአፍሪቃ ሀገራት በድህነትና በኮሮና ሰበብ ህጻናት በግዳጅ ለጉልበት ስራ መዳረጋቸው ከቀድሞው ብሷል።
የሶማሊያ የሕግ መምሪያና የሕግ መወሰኛ ምክርቤቶች ከ15 ወራት በላይ የዘገየውን የሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ነገ ያካሂዳሉ። ጎሳን መሰረት ባደረገው በዚህ ለስድስተኛ ጊዜ በሚካሄድ  ቀጥተኛ ባልሆነ  ምርጫ 39 እጩዎች ይወዳደራሉ። በተለምዶ ፎርማጆ የሚባሉትን ስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ፣ የቀድሞዎቹን ፕሬዝዳንቶች ሸሪፍ ሼክ አህመድ እና ሀሰን ሼክ ሞሐመድን እንዲሁም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን አሊ ኬህሬን ከእጩ ተወዳዳሪዎቹ መካከል ናቸው። የራስ ገዝዋ የፑንትላንድ ፕሬዝዳንት ሰዒድ አብዱላሂ ዳኒና የቀድሞ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፋውዛ ዩሱፍ አደንም ለፕሬዝዳንትነት ይወዳደራሉ። ፋውዛ ዩሱፍ አደን ብቸኛዋ ሴት ፕሬዝዳንታዊ እጩ ናቸው። ፋውዛ ሶማሊያን ለመምራት ትክክለኛዋ ፕሬዝዳንት እኔ ነኝ ይላሉ። ብመረጥ ሃላፊነቴን በአግባቡ እወጣለሁ ብለዋል። 
« ሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ፍትህ ለሁሉም፣የኤኮኖሚ ማሻሻያዎች ያስፈልጓታል። ትክክለኛዎቹ ሰዎች ሴቶችም ወንዶችም በትክክለኛው ቦታ መቀመጣቸው መረጋገጥ አለበት።እኔ ብመረጥ የኔ መንግሥት፣ በህገ መንግሥቱ መሰረት ሃላፊነቱን ይወጣል። ሁሉን አሳታፊና የሰብዓዊ መብቶችንም የሚያከብር ይሆናል። »
ሁሉም እጩዎች የሶማሊያን የተከማቹ ችግሮች ለመፍታትና በአሸባብ ጥቃት፣በዋጋ ግሽበትና በድርቅ ለሚሰቃዩ ዜጎች እፎይታ ለማምጣት ቃል ገብተዋል። ፎርማጆ ከዓመት በፊት በአዋጅ ስልጣናቸውን ለማራዘም ያደረጉት ሙከራ በተቀናቃኝ አንጃዎች መካከል ግጭት በማስነሳት በመቅዲሾ የጎዳና ላይ ውጊያን ቀስቅሶ ነበር። በኋላም ፎርማጆ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግፊት ጠቅላይ

Somalia Abstimmung Gesetzesentwurf zur Verlängerung der Amtszeit von Präsident Mohamed Abdullahi Mohamed

ሚኒስትር መሐመድ ሮብሌ በተቀናቃኝ ወገኖች መካከል መግባባት እንዲፈጥሩ ቢሰየሙዋቸውም በተዛባ አካሄድና በፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና  ሂደቱ አዝጋሚ ሆኖ ቆይቷል። በፎርማጆና በሮብሌ መካከል የተፈጠረው ጠብ ችግሩን በማባባስ የምርጫው ሂደት እንዲዘገይ ምክንያት ሆኗል። ሆኖም ከአንድ ዓመት በላይ የተገፋው የሶማሊያ ምርጫ ነገ ቢካሄድም ለሀገሪቱ መጠነ ሰፊ ችግሮች መፍትሄ ማምጣቱን የሚጠራጠሩ ያመዝናሉ። ከመካከላቸው በሶማሊያ የጎሳ ፖለቲካ ደስተኛ ያልሆኑት የፖለቲካ አራማጅ አያንሌ አብዲራሂማንአንዱ ናቸው ። 
« ቀጥተኛ ያልሆነው ምርጫ የእስከዛሬውን የሶማሊያ የፖለቲካ ምስቅልቅ የሚቀይር አይሆንም። ምክንያቱም 329 የምክር ቤት አባላት ብቻ ናቸው የሀገሪቱን ተራ ህዝብ እጣ ፈንታ የሚወስኑት። ሆኖም ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ወደፊት የሚያራምድና ህዝቡም የወደፊት መሪዎቹን በዴሞክራሲያዊ መንገድ ወይም በአንድ ሰው፣ አንድ ድምጽ አማካይነት እንዲመርጥ ያደርጋል ብለን እጠብቃለን።
በሶማሊያ ምርጫ እያንዳንዱ ህዝብ ድምጽን በቀጥታ አይሰጥም።275 ቱ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባላትና 54ቱ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት በአጠቃላይ 329 የምክር ቤት አባላት ናቸው በሚስጥር ድምጽ መስጫ የሶማሊያን ፕሬዝዳንት የሚመርጡት። ሶማሊያ ከጎርጎሮሳዊው 1991 ዓም አንስቶ ጠንካራ መንግሥት የላትም። አሸባብ የተባለው ቡድን በምዕራባውያን የሚደገፈውን የሶማሊያ መንግሥት ለመጣል ውጊያ ያካሂዳል።መቅዲሾን ጨምሮ በሌሎች የሶማሊያ ከተሞችም ተከታታይ ጥቃቶችን ይጥላል። ከቅርብ ጊዜዎቹ ጥቃቶች መካከል ባለፈው ሳምንት 10 የብሩንዲ ሰላም አስከባሪዎች የተገደሉበት በአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪዎች ጦር ሰፈር ላይ የደረሰው ጥቃት አንዱ ነው።የአሸባብ ኃይሎች ከቅርብ ወራት ወዲህ ይዞታቸውን አስፍተዋል።በአሁኑ የሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማንም ያሸንፍ ማንም የሚጋፈጠው አጣዳፊ ጉዳይ አሳሳቢው የሀገሪቱ ጸጥታ ነው።ውስን በሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች ሽምያ በተጠመዱ የክልል መንግስታት የተፈጠረውን ውጥረት ማርገብም ሌላው ከተመራጩ ፕሬዝዳንት የሚጠበቅ ተግባር ነው ።

የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ በአፍሪቃ

TABLEAU | Internationaler Tag gegen Kinderarbeit 2021 | Äthiopien

የካሜሩን ዋና ከተማ ያውንዴ መንገዶች በታዳጊ ወጣት የጎዳና ነጋዴዎች ተጨናንቀዋል። እድሜያቸው ከሰባት እስከ 14 ዓመት የሚሆኑት እነዚሁ ታዳጊ ወጣቶች እስከ ውድቅት ድረስ ከትላልቅ አደባባዮች አይጠፉም። ትምህርት ቤት ተዘግቶላቸዋል። ይሁንና እረፍት የላቸውም።
 «በአዲሱ የትምህርት ዘመን ለትምህርት የሚያስፈልጉኝ መጻህፍት እንዲገዙልኝ ወላጆቼን ለማገዝ ውኃ እሸጣለሁ።» 
የስምንት ዓመቱ ኬቪን ነው ይህን የሚለው።የአስር ዓመቷ ሊያም ለትምህርቷ የሚያስፈልጋትን ገንዘብ ለማግኘት ኦቾሎኒ ትሸጣለች። እነዚህና ሌሎች ወጣቶቹ የሚገፉት ይህን መሰል ሕይወት የትምህርት ቤት ዳይሬክተር የሆኑትን ሻንታል ዛንጋን ያሳስባቸዋል።
 «ህጻናት በጎዳና ንግድ መሰማራታቸውን እቃወማለሁ። ህጻናት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው። ሆኖም እኛ ወደ ጎዳና ከለቀቅናቸው ማን ሊጠብቃቸው ነው?» 
በዓለማችን የህጻናት ሰራተኞች ቁጥር 160 ሚሊዮን ይገመታል።ከነዚህም አብዛኛዎቹ አፍሪቃ ውስጥ ነው የሚገኙት። ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት በምህጻሩ «አይ ኤል ኦ» እንደሚለው ከሰሀራ በረሀ በስተደቡብ በሚገኙ ሀገራት ከ72 ሚሊዮን በላይ ህጻናት በተለያዩ ስራዎች ተሰማርተዋል።ይህም ማለት ከአምስት ልጆች አንዱ የችግሩ ሰለባ ነው። በተለይ በኮሮና ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ህጻናት ለጉልበት ብዝበዛ መዳረጋቸው አልቀርም።የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ እንደሚለው የህጻናትን የጉልበት ብዝበዛ ለማስቆም ከ20 ዓመት በፊት የተጀመረው ጥረት ለመጀመሪያ ጊዜ ተገቷል። ድርጅቱ እንደሚለው የህዝብ ቁጥር  መጨመር ፣በተለያየ ጊዜ የሚከሰቱ ቀውሶች፣ የከፋ ድህነት፣በቂ የማኅበራዊ ጥበቃ እርምጃዎች ባለመወሰዳቸው ባለፉት አራት ዓመታት ተጨማሪ 17 ሚሊዮን ህጻናት ከሰሀራ በስተደቡብ ባሉ ሀገራት በስራ እንዲሰማሩ አድርጓል።

TABLEAU | Internationaler Tag gegen Kinderarbeit 2021 | Malawi, Lilongwe
More stories

ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለች

November 20, 2024

በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የተጣለው እገዳ ተነሳ

March 4, 2025

አጋቹ ተያዘ

March 6, 2023

በይነመረብ ማህበርዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጥ ለማምጣት!!

November 29, 2022

ህጻናቱ የጎዳና ነጋዴዎች ለፀሐይና ቁር እንዲሁም  ለትራፊክ አደጋ የተጋለጡ ናቸው።በየቀኑ ወሲባዊ ጥቃት ሊደርስባቸውም ይችላል።የ12 ዓመቷ ጁልየተ ሌማና በያዉንዴ ጎዳናዎች ስለሚደርሱ አደጋዎች በቅጡ ታውቃለች፤በእናትዋ ትዕዛዝ ጎዳና ላይ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ትሸጣለች። አንዳንዴ ገበያ ውስጥ አለያም በመንገድ ላይ ባለመኪናዎች ነው በቀጥታ የምትሸጠው። እርስዋ እንደምትለው በቅርቡ አንዲት ጓደኛዋ ሞተር ቢስኪሌት በላይዋ ላይ ሄዶባታል። ይህን መሰሉ አደጋ ብቻ አይደለም የሚያሳስባት ፤አምሽተው መስራታቸውም ጭምር እንጂ። አንዳንዴ ቤት የምንሄደው በውድቅት ለሊት ስለሆነ፣አቅጣጫው ሊጠፋን ይችላል ትላለች። ካሜሩናዊቷ የመብት ተከራካሪ ፓውሊን ቢዮንግ እንደሚሉት ከሆነ፣በካሜሩን ህጻናትን ማሰራት በሕግ የተከለከለ ነው። 
«ካሜሩን ለህጻናት ጥበቃ ማድረግን የተመለከቱ በርካታ ሕጎችን አጽድቃለች። እነዚህ ሕጎች ሊከበሩ ይገባል።ሆኖም እንዳለመታደል ሆኖ በከተማችን ከእለት ወደ እለት የህጻናት ጉልበት በወላጆቻቸው ይበዘበዛል። ይህ የተለመደ አይደለም።»
ሲሉ የሴቶችና ህጻናት ትምሕርት ሊግ ሃላፊም የሆኑት  ቢዩንግ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
ህጻናት በለጋ እድሜያቸው እንዲሰሩ ከሚያስገድዷቸው ምክንያቶች ዋነኛው ድህነት ነው።በታንዛንያና በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ህጻናት ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ህልውና ሲሉ በማዕድን ማውጫ ስፍራዎች ይሰራሉ።በደቡብ ሱዳን ደግሞ በወታደርነት እየተሰለፉ ሕይወታቸውን ለአደጋ ያጋልጣሉ።በግብርናም ይሰማራሉ።  የሚያገኙት ገንዘብ ግን አነስተኛ ነው።በአይቮሪ ኮስት ካካዋ በሚመረትባቸው ስፍራዎች  በህጻናት ላይ ተመሳሳይ  በደል ይደርሳል። ሆኖም በዚያ የሚገኘው በዱቄት ወተት ምርት የሚታወቀው ኔስሌ የተባለው ኩባንያ ስሙን ለማደስ ምርቱ በሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ለህጻናቶች ትምሕርት ቤት ይገነባል፤ለሴቶች ደግሞ የመሰረተ ትምሕርት ዘመቻ ያካሂዳል።ይሁንና የኔስሌ የፕሮግራም ሃላፊ ቱሴንት ሉክ ንጉዌሳን ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ህጻናት አሁንም

TABLEAU | Internationaler Tag gegen Kinderarbeit 2021 | Südsudan, Nyamlel

በአንዳንድ የካካዋ እርሻዎች ውስጥ ይሰራሉ።
በናይጀሪያም የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ከባድ ችግር ነው። አይ ኤል ኦ እንደሚለው ከአፍሪቃ ግዙፍ ኤኮኖሚ በምታንቀሳቅሰው በናይጀሪያ ፣ በዓለም አቀፍ ሕግጋት ተቀባይነት ባይኖረውም፣ እድሜያቸው ከአምስት እስከ 11 ዓመት ከሚሆኑ የናይጀሪያ ህጻናት 43 በመቶው በተለያዩ ስራዎች ላይ ይገኛሉ። ሰሜን ምሥራቅ ናይጀሪያ ውስጥ በምትገኘው ማይዱጉሪ የሚኖር አንድ ወጣት አባቱ ስፌት እንዲማር እንዳመጡት ይናገራል።አንዳንድ ጊዜ የሚያገኘው ገንዘብ ከግማኅ ዩሮ ያነሰ ነው። 15 ልጆች ያሏቸው አባቱ ልጆቻቸው ቤተሰቡን የሚደጉም ገንዘብ እንዲያመጡ ጎዳና ወጥተው እንዲነግዱ ያደርጋሉ።ህጻናቱም ለቤተሰብ ሲሉ ብዙ መስዋዕትነት ይከፍላሉ። የመማርና የተሻለ ሕይወት የመምራት እድላቸውም ይጨናገፋል።  
በተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች ፣ 193ቱ የተመድ አባል ሀገራት አስገድዶ ማሰራትን፣ዘመናዊ ባርነትን በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ከቦታ ወደ ቦታ ማሻገርን ህጻናትን ለውትድርና መመልመልን ጨምሮ ልዩ ልዩ  የህጻናት ጉልበት ብዝበዛዎችን እስከ ዛሬ ሦስት ዓመት ድረስ ለማስቆም ቃል ገብተዋል።ይሁንና ችግሩ እልባት የማግኘቱ ተስፋ እስከዚህም ነው።የማይዱግሪዋ የመብት ተሟጋች ሉሲ ዩዋና ለዚህ መፍትሄ የሚሉት ቅጣት ነው  ። 
«እንደ ወላጅ ለልጆቻችን ያለንን ማቅረብ እንጂ እነርሱ ለኛ ሊያቀርቡ አይገባም። መንግስት የሆነ ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል።  በቤት ሰራተኝነት ፣በልመና የተሰማሩ ልጆችን መንግስት መያዝ አለበት።ህጻናት  ልጆቻቸውን በቤት ሠራተኝነት የሚያስቀጥሩ  ወላጆች ሊታሰሩ ይገባል።ይህን የሚያደርጉ ወላጆች ፍርድ ቤት መቅረብ አለባቸው፤ወይም ቅጣት ሊጣልባቸው ይገባል።»

via – DW

home
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
የሞት ቅጣት የሚያሰጋቸው ጀማል እና ሀሰን
DPM And FM Demeke Mekonnen Confers With EU Special Envoy To The Horn Of Africa
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News2

ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ ሊሆኑ አይገባም – በለጠ ሞላ

March 8, 2026
News2

ለክቡር የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝና ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የቀረበ ጥሪ

March 8, 2026
News2

ስምረት ፓርቲ የትግራይ ወጣት ለትህነግ ጀርባ መስጠቱን አስታወቀ

March 6, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2