Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  ትህነግ “የብልጽግና መንገድ እንጀምር” አለ፤ ለትግራይ ህጻናት ዕልቂት ተጠያቂው ማን ነው?
News

ትህነግ “የብልጽግና መንገድ እንጀምር” አለ፤ ለትግራይ ህጻናት ዕልቂት ተጠያቂው ማን ነው?

Ethioreview newsEthioreview news—September 11, 2022
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ብልጽግናን እንደማይቀላቀል አስታውቆ ወደ ትግራይ ያፈገፈገው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ ” በአዲሱ አመት ግጭቱን አቁመን ለሰላም እድል በመስጠት የሰላም እና ብልጽግና መንገድ እንጀምር ” ሲል በይፋ የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጁን አስታወቀ። መግለጫውን ተከትሎ “ላለቁት የትግራይ ህጻናት ተጠያቂ ማን ሊሆን ነው? ለዚህ ለዚህ ለምን ውጊያ ውስጥ ገባ?” በሚል ደጋፊዎቹ ጥያቄ እያነሱ ነው።

ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት “አፍንጫቸውን ይዘን ቅድመ ሁኔታ ተቀብለው ወደ ድርድር እናመጣቸዋለን። ካልሆነም እንወጋቸዋለን” በማለት ዶክተር ደብረጽዮን መግለጫ ሰጥተው ነበር። መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታ ለመደራደር ፈቃደኛ መሆኑ ባስታወቀ ማግስት የትህነግ አመራሮችና የሰራዊት መሪ በሃይል ሁሉንም እንደሚያከናውኑ ደጋገመው ሲናገሩ ደጋፊዎቻቸው ድል እንደሚያደርጉ ያምኑ ነበር።

ከመንግስት ወገን አንድም መረጃ በይፋ ሳይሰጥ “ወረራውን መከትኩ፣ በሚገባው ቋንቋ አነጋገርኩት” በሚል ከሚሰጥ መጠነኛ ምላሽ ውጪ ዝርዝር የማይቀርበበት ጦርነት እያደር በትህነግ ሰዎች መግለጫና የድረሱልኝ ጥሪ የጠራ መልክ እየያዘ መምጣቱን በርካቶች በማህበራኢ ገጾቻቸው እየዘገቡ ነው። የምስልና የድምጽ መረጃዎችም አልፎ አልፎ እያቀረቡ ነው። በትህነግ በኩልም ዝርዝር የማይቀርብበበትና ደጋፊዎቹም እንደወትሮ ይህ ተያዘ፣ ይህ ተለቀቀ በማለት መረጃ ያማያካፍሉበት ይህ ጦርነት በሳምንት ውስጥ መልኩን ቀይሮ ወደ ተማጽኖ ተቀይሯል።

ትህነግ ዛሬ ባሰራጨው መግለጫውብ ከመንግስት ጋር ለሚጀምረው የሰላም ንግግር አቶ ጌታቸው ረዳንና የቀድሞውን ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያከተተ ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን መሰየሙን አመልክቷል። መንግስት አስቀድሞ ተደራዳሪ የሰየመ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ትህነግ ዛሬ ላወጣው መግለጫ በይፋ ያለው ነገር የለም። ከቀናት በፊት ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ” የሚያሸንፉ ሲመስላቸው ዝም ይላሉ፣ ሲሸነፉ ይጮሁላቸዋል” ሲሉ መንግስት ስራውን እንደሚሰራ አስታውቀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የአገር መከላከያ በፈለገው የአገሪቱ ክፍል የመቀመጥ መብት እንዳለው፣ ትግራይ የኢትዮያ፣ ኢትዮጵያም የትግራይ እንደሆነች አስታውቆ ትህነግ በትግራይ ህዝብ ላይ እንዲፈነጭና አግቶ እንዲያሰቃይ ካሁን በሁዋላ እንደማይፈቀድለት በይፋ አስታውቋል።

  • ኦፍሪካ ህብረት የኦባሳንጆን የስራና የሃላፊነት ጊዜ ካራዘመ በሁዋላ፣
  • ለአንድ ዓመት ትህነግ ይዟቸው የቆያቸውን አካባቢዎች ካስረከባ በሁዋላ፣
  • መቀለ ዙሪያዋ ከተከበበ በሁዋላ፣
  • ሰፊ ቁጥር ያላቸው ታዳጊዎች ህይወት ከገበረ በሁዋላ፣
  • በሁሉም ግንባር ሽንፈት እንደደረሰበት ካመነ በሁዋላ – “አልቀበለውም፣ አላምነው” ሲለው የነበረውን የአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት ለመቀበል መወሰኑን ይፋ ማድረጉ ድርጅቱ ከደጋፊዎቹ ሊለየው እንደሚችል እየተሰማ ነው። እንደ ቀደመው ጦርነት ከማሳደድ ይልቅ እየቆረጠ በርጋታ ሰብአዊ ጉዳት ያደረሰው የመከላከያ ሰራዊትና የጥምር ጦሩ በየትኛውም ጊዜ መቀለን መቆጣጠር እንደሚችሉ በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት የትህነግ ሃይሎች ለድርድር ቅድመ ሁኔታ ሲሉ የነበሩትን ሁሉ ወደ ጎን ትተው ጠረጴዛ መምረጣቸው አስገርሟል። ጦርነቱ ለነሱ ስልጣን ሲባል ሲደረግ እንደነበር ማረጋገጫ ተደርጎም ተወስዷል።
  • ወልቅይትና ጠገዴ ስማቸው ሳይነሳ
  • መሰረታዊ አገልግሎት ቅድሚያ ይሟላ ሳይባል
  • የመከላከያ ሃይል ለቆ ይውጣ፣ የአማራ ሃይል ይነሳ የሚለው ጥያቄ ሳይነሳ
  • ኤርትራ ትውጣ የሚል ቅድም ሃሳብ ያልተካተተበት የትህነግ መግለጫ በአዲሱ አመት ግጭት አቁመን ለሰላም እድል በመስጠት የሰላምና ብልጽግና መንገድ እንጀምር” ብሏል። በአፍሪካ ህብረት የሚመራው የሰላም ሂደት እንደሚቀበልም ይፋ አድርጓል። ድርድሩ ተአማኝ እንደሚሆንም እምነቱ እንደሚሆን አምልክቷል።
More stories

“ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

April 7, 2021

የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤ አንገታቸው የተቀላ መኮንኖች ፊልም ሊታዩ ነው

May 13, 2021

ከሱዳን የተነሳ የትህነግ ሃይል (ሳምሪ) ሳይዋጋ ሙሉ በሙሉ ተማረከ

August 11, 2021

የመንግስት ማጅራት መቺዎች ፈተና ሆነዋል – ሃላፊዋ አምነዋል

May 9, 2022

የተሰየሙት የተዳራዳሪ ቡድን አባላት ወደፊት በሚደረገው ድርድር “የትግራይን መንግስት” እንዲወክሉ ስልጣን እንደተሰጣቸው ጠቅሶ ትህነግ ባሰራጨው መግለጫ ተደራዳሪ ቡድኑ በአጭር ጊዜ ወደ ድርድር እንደሚገባ አመክቷል።

የአፍሪካ ህብረትን ሲዘልፍና ገለልተኝነቱ ሲያጣጥል የነበረው ትህነግ በህብረቱ ጥላ ስር በሚካሄደው ድርድር እንደሚሳተፍ ያረጋገጠው አሜሪካ በይፋ በድጋሚ የአፍሪካ ህብረትን አደራዳሪነት እንደምትቀበል ይፋ ካደረገች በሁዋላ ነው። ግልጽ ባይሆንም በትናትናው ዕለት አሜሪካ በወኪሏ አማካይነት የኢትዮጵያን አንድነትና ብልጽግና እንደምትደግፍ ይፋም አድርጋ ነበር።

“ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር አፋጣኝና በጋራ ስምምነት ለሚደረግ ተኩስ አቁም ዝግጁ ነኝ” ያለው ትህነግ መንግስት ትህነግን ለመንቀል እስከ መጨረሻ የሚገፋ ከሆነ ምን ሊያደርግ እንደሚችል አልገለጸም። መንግስትም ይህ እስከተጻፈ ድረስ ያለው ነገር የለም።

መጀመሪያ “አማራ ወዳጅ ነው። የመናወራርድበት ሂሳብ የለም” በሚል መግለጫ የተጀመረው የትህነግ አዲስ አካሄድ የተፈለገውን ውጤት ሳያመጣ፣ እንዲያውም ደጀኑንን ያነቃነቀና ያነሳሳ በመሆኑ ” የተባበሩት መንግስታትና የጸጥታው ምክር ቤት በሃይል ይድረስልን” ወደሚለው የ “ድረሱልን” ጥሪ ተቀየረ። በድብዳቤው የኤርትራና ኢትዮጵያ ጦር ከኤርትራ እንዲወጡ፣ መሰረታዊ አገልግሎት ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲጀመር፣ የተያዙ አካባቢዎች እንዲለቀቁ እንዲደረግ” የጠየቀው ደብዳቤ ይዘት በቀናት ውስጥ ተቀይሮ “ልደራደር ዝግጁ ነኝ” ወደሚለው አጭርና ግልጽ ደብዳቤ ተቀይሯል።

“ለተከሰተው አሳዛኝ ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት የምንችለው በሰላማዊ ውይይት ብቻ እንደሆነ እናምናለንም” ሲል ጥሪውን ያቀረበው ትህነግ “አትታመንም” የሚል ምላሽ በማህበራዊ ሚዲያ እየጎረፈለት ነው። ደጋፊዎቹ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ዝም ሲሉ “ትህነግን ማመን ቀብሮ ነው” በሚል መንግስት እንዳይታለል “ውርድ ከራስ” በሚል የሚያስጠነቅቁ ጥቂት አይደሉም።

በሁለቱም ወገን ተቀባይነት ያላቸው ሸምጋዮች እንደሚጨመርና ፤በሂደቱ በሁለቱም ወገኖች መካከል የእርስ በርስ መተማመን እንዲፈጠር የሚያግዙ፣ አፈጻጻምን የሚከታተሉ እንዲሁም አስፈላጊውን መመሪያና ምክር የሚሰጡ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እንደሚሳተፉም እንደሚፈልግ አስታውቆ ትህነግ ለበተነው መግለጫ መንግስት ምን ምላሽ እንዳለው እስካሁን ይፋ አልሆነም።

አቶ አሕመድ የተባሉ በማህበራዊ ገጻቸው መንግስት እንዳይታለል፣የሠራዊቱ ድካም ከንቱ እንዳይሆን ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ሲያሳስቡ ያለፉት 7 ቀናት ትህነግ ምን እንዳለ አመልክተዋል።

  • August 22: በምንም ተአምር አፍሪካ ኅብረት አደራዳሪ አይሆንም
  • August 24: ተወረናል፣ የሰላም በሮች ዝግ ናቸው፣ ማንኛውንም እርምጃ ወስደን ወረራውን እንቀለብሳለን
  • August 31: እስካሁን የተካሄደው ጦርነት ትጥቃችንን 100% ጨምሮታል፣ ሺህ ገድለናል፣ ሺህ ማርከናል
  • September 1: የትግራይ ሀይል በሙሉ ወረራውን ይቀልብስ
  • September 7: የጸጥታው ምክርቤት በኃይል ጣልቃ ይግባ
  • September 9: አሜሪካ የትግራይ ሀይሎችን መርዳት አለባት
  • September 11: ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የአፍሪካ ኅብረት ያደራድረን፣ ለአዲስ አመት ብልፅግና ስንል ሰላምን መርጠናል

መንግስት በይፋ ባይገልጽም የትግራይ ክልልን እየመራ ያለው ትህነግ ልክ እንደ ቤኒሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ፣ ሲዳማ፣ ወዘተ ክልል በውክልናው መጠን የሚደርሰውን ተቀብሎ ለመኖር እንዲወስን፣ በአገሪቱ በጀት የተገዛውን ክባድ መሳሪያ፣ መድፍ፣ ታንክ፣ ሮኬት እንዲፈታ፣ የፖሊስ ሃይሉን ልክ እንደ ሌሎች ክልሎች ህገመንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት እንዲያደራጅ፣ የወሰንና የቦታ ይገባናል ጥያቄ በህገመንግስቱ መሰረት እንደሚታይ አምኖ ወደ ሰላም እንዲመጣ መሰረታዊ የመርህ ጥያቄ ሲያቀርብ መቆየቱን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሃመር ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከህወሓት ባለሥልጣናት ጋር መወያየታቸውን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ማስታወቁ አይዘነጋም።

አፍሪካ ህብረት የትህነግን ውሳኔ አድንቆ ሁሉም ወገኖች ለድርድር እንዲዘጋጁ ጥሪ በማቅረብ መግለጫ አውጥቷል። ከአፍሪካ ህብረት ጋር ሃመር መነጋገራቸውንና ተጨማሪ አደራዳሪ ሃይሎች እንዲሳተፉ ከስምምነት መድረሳቸውን ትላንት አስታውቀው ስለነበር የትህነግ መግለጫ እንደ ትልቅ ጉዳይ የሚታይ እንዳልሆነና የሚረዷቸው አካላት ያሏቸውን ከጭነቅታቸው የተነሳ ማድረጋቸውን በርካቶች እየገለጹ ነው።

ሙሳ ፋኪ ማህማት በዛሬው መግለጫቸው፤ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚደረገው ድርድር “ዓለም አቀፍ አጋሮችን” እንደሚያካትት ማመላከታቸው ዛሬ በወጣው መግለጫ ተመልክቷል።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
2014 《በፅናት ያለፍንበትና ዓመቱን በድል አድራጊነት የተሽጋገርንበት ወቅት》
የደብረፅዮን የጦርነት ታክቲክ 22
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2