Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News2  የውጭ ብድር ያነቃት ኢትዮጵያ!! “እዳዋን እንዴት ትክፈል?”
News2

የውጭ ብድር ያነቃት ኢትዮጵያ!! “እዳዋን እንዴት ትክፈል?”

Ethioreview newsEthioreview news—January 1, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ፊች ሬቲንግስ የተባለ ተቋም ለኢትዮጵያ የውጭ ብድር የመክፈል አቅም ከዚህ ቀደም የሰጠውን ምዘና ባለፈው ሣምንት ዝቅ አድርጓል። በተቋሙ ስሌት መሠረት እስከ መጪው ሰኔ ድረስ አገሪቱ 1.6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ብድር ወለድ መክፈል ይጠበቅባታል። አገሪቱ በጎርጎሮሳዊው 2024 ደግሞ ሌላ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ክፍያ አለባት።

መቀመጫውን በኒው ዮርክ ያደረገው ፊች ሬቲንግስ የተባለ ተቋም ለኢትዮጵያ የውጭ ብድር የመክፈል አቅም ከዚህ ቀደም የሰጠውን ምዘና ባለፈው ሣምንት ዝቅ አድርጓል። ዓለም አቀፍ የብድር ምዘና ኤጀንሲ የሆነው ተቋም ባለፈው ሣምንት ይፋ ባደረገው ሰነድ የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ አከፋፈል ምን ሊመስል እንደሚችል ትንበያ የሰጠ ነው። ከዚህ ቀደም በዚሁ ተቋም ምዘና ሲሲሲ (CCC) የሚል ደረጃ ተሰጥቶት የነበረው የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ የመክፈል አቅም ባለፈው ሣምንት ወደ ሲሲሲ ኔጌቲቭ (CCC-) ዝቅ ብሏል። 

በጀርመኑ ሔለባ ባንክ የኤኮኖሚ ትንተና ባለሙያው ፓትሪክ ሐይኒሽ ተቋሙ ለኢትዮጵያ ብድር የመክፈል አቅም የሰጠው ምዘና ከሲሲሲ (CCC) ወደ ሲሲሲ ኔጌቲቭ (CCC-) ቢቀየርም ሁለቱም “ዕዳ የመክፈል አቅም ዝቅተኛ መሆኑን የሚያሳዩ” በመሆናቸው “መሠረታዊ ለውጥ” እንደሌላቸው ይናገራሉ።

“በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት የብድር ሰነድ ለዓለም አቀፉ የካፒታል ገበያ የማቅረብ ዕቅድ የለውም” የሚሉት ፒተር ሐይኒሽ ምዘናው በቀጥታ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ የሚያሳድረው ጫና “የተወሰነ” ቢሆንም “ለውጭ ባለወረቶች እና ለውጭ ባንኮች አንዳች ምልክት የሚሰጥ በመሆኑ ጫና ሊኖረው ይችላል” ሲሉ አስረድተዋል።

More stories

ከምትሰራበት ቤት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ሰርቃ የተሰወረች ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለች

November 20, 2024

በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የተጣለው እገዳ ተነሳ

March 4, 2025

አጋቹ ተያዘ

March 6, 2023

በይነመረብ ማህበርዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ለውጥ ለማምጣት!!

November 29, 2022

ይኸ ለኢትዮጵያ ብድር የመክፈል አቅም የተሰጠ ምዘና በፕሪቶሪያ የተፈረመው በቋሚነት ግጭት የማቆም ሥምምነት ሊፈጥር ይችላል ተብሎ የሚጠበቀውን የመካከለኛ ጊዜ የማክሮ ኤኮኖሚ እና የፋይናንስ ሁኔታ መሻሻል ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው። ዓለም አቀፉ የአቅርቦት ሰንሰለት የገጠሙት ተግዳሮቶች ያሳያሉ ተብሎ የሚጠበቀው መቃለል እንዲሁም የመንግሥት የዕዳ ሁኔታ መሻሻል ለትንበያው ከግምት ውስጥ የገቡ ጉዳዮች ናቸው።

በፊች ግምት መሠረት ኢትዮጵያ 1.6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ወለድ ክፍያ እስከ መጪው ሰኔ ይጠብቃታል። በጎርጎሮሳዊው 2024 ደግሞ ሌላ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ክፍያ አለባት። በጎርጎሮሳዊው 2023 የውጭ ንግድ ሚዛን ጉድለት (Current Account Balance) እና የተጣራ የውጭ ቀጥተኛ መዋዕለ ንዋይ 1.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የፊች ትንበያ ያሳያል። በአሁኑ ወቅት አገሪቱ ያላት የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከአንድ ወር በታች ለሚሆን ጊዜ የሚበቃ ሸቀጦች እና አገልግሎቶችን ለመሸመት የሚችል ነው።  

“አሁን ባላት 1.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የሚገመት የውጭ ምንዛሪ ክምችት ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የሚጠበቅባትን ለመክፈል በጣም አስቸጋሪ ነው” የሚሉት የኤኮኖሚ ተንታኙ ፓትሪክ ሐይኒሽ “ይኸን ምዘና ዝቅ እንዲል ያደረገውም ይኸው ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ (G20’s Common Framework) በኩል የዕዳ አከፋፈል ማሻሻያ ለማድረግ የጀመረችው ሒደት በዋናነት በፊች ምዘና ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ ጉዳይ ነው። በማዕቀፉ ኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ለመክፈል የተፈጠረባትን ጫና የሚያቃልል ማሻሻያ ካልተበጀ እና ተጨማሪ የውጭ የፋይናንስ ድጋፍ ካላገኘች የውጭ ብድር የመክፈል ጫናው እንደሚባባስ ፊች አስታውቋል።

የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ ከተጀመረ ዓመት ከዘጠኝ ወራት ገደማ ያስቆጠረው የዕዳ አከፋፈል ማሻሻያ ድርድር ተጠናቆ ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ ለኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ጫና ፋታ ሊሰጥ ይችል እንደነበር ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። የዕዳ አከፋፈል ማሻሻያው ቢጠናቀቅ ኖሮ “ወደፊት መግፋት” ይቻል እንደነበር የገለጹት ዶክተር አብዱልመናን የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት አነስተኛ መሆን ጭምር አገሪቱ ዕዳዋን ለመክፈል ለገጠማት ተግዳሮት አስተዋጽዖ እንዳለው አስረድተዋል።

ለኢትዮጵያ ብድር የመክፈል አቅም በፊች ሬቲንግስ የተሰጠ ምዘና በፕሪቶሪያ የተፈረመው በቋሚነት ግጭት የማቆም ሥምምነት ሊፈጥር ይችላል ተብሎ የሚጠበቀውን የመካከለኛ ጊዜ የማክሮ ኤኮኖሚ እና የፋይናንስ ሁኔታ መሻሻል ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው።

ከኢትዮጵያ አበዳሪዎች የሚጠበቀው የዕዳ ማሻሻያ ግን እስካሁን ድረስ ይኸ ነው የሚባል እርምጃ አላሳየም። በቻይና እና በፈረንሳይ ተባባሪ ሊቀ-መንበርነት የሚመራው የኢትዮጵያ አበዳሪዎች ኮሚቴ እስካለፈው ኅዳር ድረስ ለአራት ጊዜያት ቢሰበሰብም ለአገሪቱ ሊደረግ ከሚችል የዕዳ አከፋፈል ማሻሻያ ላይ የተደረሰ ሥምምነት ስለመኖሩ በግልጽ የተባለ ነገር የለም። በፕሪቶሪያ በተፈረመው በቋሚነት ግጭት የማቆም ሥምምነት ጋብ ያለው የትግራይ ጦርነት እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሚጠበቀው የዕዳ ዘላቂነት ትንተና አለመከናወን ለዕዳ አከፋፈል ማሻሻያው መዘግየት አስተዋጽዖ አበርክተዋል።

የኢትዮጵያ ዕዳ ከአጠቃላይ አገራዊ የምርት መጠን 56 በመቶ ገደማ እንደሚሆን የሚናገሩት የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን የውጭ ብድር እስከ 28 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ገልጸዋል። ይኸን ለመክፈል ፈታኝ የሚያደርገው የብድር መጠኑ ብቻ ሳይሆን የአከፋፈል ውሉ ጭምር እንደሆነ የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው ይጠቅሳሉ።

ኢትዮጵያ የምትጠብቀው የብድር ጫና ትንተና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ውሳኔን ይፈልጋል።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ካለፈው ሰኔ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር ፕሮግራሞች ላይ ከባለሥልጣናቱ ጋር ግንኙነት መጀመሩን አስታውቋል። አገሪቱ ከተቋሙ የምትጠብቀው የብድር ጫና ትንተና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ውሳኔን ይፈልጋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት የተፈራረሙት ሥምምነት በጦርነቱ ምክንያት አገሪቱ ከልዕለ ኃያላኑ እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ያላትን ግንኙነት ሊያሻሽል እንደሚችል በርካታ የኤኮኖሚ ባለሙያዎች ተስፋ አድርገዋል። እንዲያም ሆኖ አሁንም ተጽዕኖ የሚኖራቸው ጉዳዮች እንዳሉ የሚናገሩት ፓትሪክ ሐይኒሽ  የተጠያቂነት ጉዳይ አንዱ መሆኑን አንስተዋል።

የአውሮፓ ኅብረት እና አሜሪካ ካስቀመጧቸው ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ የተጠያቂነት ጉዳይ መሆኑን የተናገሩት የኤኮኖሚ ትንተና ባለሙያው “ኢትዮጵያ እንዴት እንደምታስተናግደው ግን የምናውቀው ነገር የለም። በተዋጊዎቹ መካከል ባለፉት ሁለት ዓመታት ኃይለኛ ጥላቻ ስለነበር ጉዳዩ ውስብስብ ነው። ቢያንስ ይፋ በተደረገው ሥምምነትም ቢሆን ጉዳዩ በግልጽ ምላሽ አላገኘም። ይኸ የተጠያቂነት ጉዳይ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል” ሲሉ ተናግረዋል። ባለሙያው እንደሚሉት “በቤኒሻንጉል ጉምዝ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው የሰላም ሁኔታ ኢትዮጵያ ከለጋሾች ጋር በሚኖራት ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የዕዳ አከፋፈል ማሻሻያውንም ለተወሰኑ ወራት ሊያዘገይ ይችላል።”

የአውሮፓ ኅብረት ባለፈው ሣምንት ባወጣው መግለጫ የፕሪቶሪያው ሥምምነት በዘላቂነት ተግባራዊ መሆን ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ እንደሚያስችል አስታውቋል። ኅብረቱ የተኩስ አቁም፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እና ለዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ የልማት ትብብር እና የኤኮኖሚ ድጋፍን በሒደት መልሶ ለማስጀመር እንደሚፈቅድ ገልጾ ነበር።

ዘገባው የጀርመን ድምጽ ነው

እሸቴ በቀለ

home
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
Over 100,000 Ethiopian migrants return home in first 10 months: IOM
578 ዕድሜ ያስቆጠረው የኤሊ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News2

ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ ሊሆኑ አይገባም – በለጠ ሞላ

March 8, 2026
News2

ለክቡር የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝና ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የቀረበ ጥሪ

March 8, 2026
News2

ስምረት ፓርቲ የትግራይ ወጣት ለትህነግ ጀርባ መስጠቱን አስታወቀ

March 6, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2