Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  EDITORIA  ፖለቲከኞችና መሸተኞች ከዕምነት ሰፈር ውጡ፤ ሕዝብም ፖለቲካና ዕምነትህን ለይ!
EDITORIANews

ፖለቲከኞችና መሸተኞች ከዕምነት ሰፈር ውጡ፤ ሕዝብም ፖለቲካና ዕምነትህን ለይ!

Ethioreview newsEthioreview news—February 5, 2023
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የኢትዮጵያ ውሃ ልክ ከተበላሸ ቆይቷል። እንዲበላሽም የተደረገውም ሆን ተብሎ ነው። ሲበላሽም፣ አበላሾቹ በድል ስሜት ነግረውናል። እንዲበላሹና እንዲመክኑ የተደረጉ በርካታ የህዝብ ትሩፋቶች ናቸው። አንዷ ቤተክርስቲያን ስትሆን፣ እሷም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነች።በየጊዜው ፖለቲካ የሚያጠላባትና ለፖለቲከኞች በሯን መዝጋት ያልቻለችው ቤተክርስቲያን ባለፉት ሁለትና ሶስት አስርት ዓመታት ያጋጠማትና የተበጀላት መንገድ ከልብ ለሚመረምረው ያስደንግጣል። የሚደነግጥ ልብ ካለን!!

ሁሉም በሚባል ደረጃ ቤተ ዕምነቶች ጉዳቸው ብዙ ቢሆንም፣ ዛሬ ኦርቶዶክስ ቤት የተፈጠረው ግን ዕረፍት የሚነሳ በመሆኑ አቋማችንን ማሳወቅ ግድ ሆኖብናል። ኦርቶዶክስ ቤታችን፣ አገራችን፣ ታሪካችን፣ ናት። እምነት ሳይለይ ኢትዮጵያን የሚወዱ ሁሉ ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀና የሚሆኑትም በብዙ ምክንያት እንጂ እንዲሁ ሾላ በደፈናው ዓይነት አይደለም።

ዛሬ ይህቺ ቤተክርስቲያን ያጋጠማት ህመም ሁሉንም የሚያመው ይዞት የሚመጣው ጣጣ ሰፊ ከመሆኑ አንጻርና ጣጣው ከማዘንና ጸጸት የዘለለ ሊሆን እንደሚችል በማመን ነው። በተለይም ዕምነቱ ሰፈር ያሉትን ካድሬዎችና አልጠግብ ባዮች ነገሩን ወዴት ወዴት እየወሰዱት እንደሆን ስንመለከት ድንጋጤያችን ውሃ ልኩን ያልፋል። ለዚህ ነው ፖለቲከኞችና መሸተኞች ከዕምነት ሰፈር ውጡ፣ ሕዝብም ፖለቲካና ዕምነትህን ለይ ለማለት የወደድነው።

ዛሬ ማታ ማታ ማይክሮፎን ይዞ አስረሽ ምቺው ሲል የሚያድር አዝማሪ “ተነስ” እያለ ጥሪ እያሰማ ነው። ዛሬ በየጥጋጥጉ አረቄና ቁርጥ እየበላ በቀን ሶስቴ የሚዘሙት ” አትነሳም ወይ” እያለ ነው። ትናንት ወንጀለኛ የተባሉ የብሄር ግጭት ጠማቂዎች ” አረ ጎበዝ” እያሉ ነው። በቀን ሶስትና አራት ኪሎ ጫት የሚበሉና አምቡላ ሲግቱ የምናውቃቸው አንዛራጮች ” ወደፊት በሉለት” እያሉ ነው። አንዳችም የቅድስና ሰፈር ውስጥ ድርሽ የሚያደርግ ስራ የሌላቸው ስማቸውን እየተጠቀሙ ከየጎሬያቸው በመውጣት የተጋደል ከበሮ እየመቱ ነው? አገር ስትወረር ዞር ብለው ያልተነፈሱ፣ ዛሬ ታጋይ እየሆኑ ነው። የሚያሳዝነው ” እንወያይ፣ በሰላም ችግሩን እንፍታው” የሚሉት ላይ የሚጎርፈው ቤተሰብና ዘመድ አዝማዳቸው ላይ ሳይቀር የሚወርድባቸው ውርጅብኝ ዓላማው ምን እንደሆነ ሲታሰብ ነው። አደጋውም ገሃድ የሚታይ በመሆኑ ነው።

More stories

Top 5 biggest and powerful dictators in the world today. “Eritrea is worse than North Korea.”

April 16, 2023

ህዝቡ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ በሰጠው ድጋፍ አሸባሪው በየአካባቢው ድባቅ እየተመታ ነው- አቶ አገኘሁ ተሻገር

August 16, 2021

ፖሊስ የጎዳና ተዳዳሪ መስለው የሽብር ተልዕኮ የወሰዱ ያላቸውን አሰረ፤ የተያዙት በዝርፊያ ላይ የተሰማሩትን ጨምር 990 ናቸው

June 1, 2021

መከላከያ ሚኒስቴር ለዜጎች ደኅንነት ስለቀየሰው ስትራቴጂ ማብራሪያ ተጠየቀ

May 2, 2022

ክርስትና ” መስቀሉን መሸከም” የሚል ግልጽ መርህ እያለው ከሁሉም ወገን መስቀል ተሸክመው፣ ከካባቸው ጋር ካድሬነትን የደረቡ፣ በከርስና በድርሻ መታላታቸው እየታወቀ ይህ ሁሉ ግብ ግብ መታየቱ ” ምን እየሆንን ነው” ያሰኛል። የቤተክርስቲያን አናቷ ምን እንደሚመስል እየታወቀ ለመጋደል መንደርደር በምን መስፈርት ትክክል እንደሚሆን አይገባንም። ስለዚህ ህዝብ ” ንቃ” ለማለት እንወዳለን። ለማንና ለምን ዓላማ እንደሚደወልልህ እወቅ። ረጋ ብሎ መመርመር ለጥሩ ውሳኔ ይረዳል። ከጸጸትም ይጠብቃልና።

ይህንን ” ከርስ ተክር” ልዩነት፣ ግጭቶ የጥቅም በመሆኑ ነው “ከርስ ተኮር” የምንለው፤ ለፖለቲካ ዓላማቸው ለማዋል የሚራወጡትን ስናይ ድንጋጤያችን ይበዛል። ሃዘናችን ይገዝፋል። ልባችንም ምቱ ይጨምራል። ለምን ቢባል አያያዙ አያምርምና!! ነጥቦች እናንሳ

  • ለምን የ”እምነት አባቶች” ይጣላሉ? ስለምን በስጋ ጉዳይ ይጨነቃሉ? እንዴት መስቀል ተሸክመው፣ ታቦት ስር እየኖሩ፣ በየዕለቱ የፈጣሪን ስም እየጠሩ፣ … እንዴት ሴረኞች ሆኑ? ለምን አይፈሩም? አያፍሩም? አይጨነቁም? … ይህንና ይህን መሰሎችን ጥያቄዎች መመለስ ግድ ነው። “ክርስቶስን እናምናለን፣ ጥቁር የለበስነው ለዓለም በመሞታችን ነው” ካሉን ለምን ንብረት ቆጠራና የሃብት ክፍፍል አጀንዳ ሆነ?
  • እስኪ በሁሉም አቅጣጫ ያሉትን ዋና አባቶች ጀርባ እንመርምር። ቅድስናቸው ይሸታል ወይስ ሌላው የካድሬነት ጠረናቸው ይጎላል? የተሸከሙት መስቀልስ ያ በእምነት የተነገረን “መስቀሉ” ነው?
  • ከአናቱ የምርጫውና ፕትርክናው ጤኛ ነበር? ሸፍጡ የሚረሳ ነው? ከበትረ ስልጣኑ በፊት የነበረ ማንነት ለሲመት የሚያበቃ ነበር?
  • ችግር የፈጠሩትም ሆነ ችግር ፈጥረዋል በሚል የሚከሱት ምን የባህሪ ልዩነት አላቸው? ማን በምን ከአንዱ ይሻላል? እዚህ ላይ ጥቂት መልካሞች እዛና እዚህ ሊኖሩ እንደሚችሉ አይካድም። ግን አብዛኛውን ለማለት ነው።
  • ሁሉም ይሁን የተነሱት የልዩነት ጥያቄዎች እውን ለህዝበ ክርስቲያኑ ታስቦ ነው?
  • ለመሆኑ ቤተክርስቲያን በንግድና ጨረባ ቤቶች ተከባ ጉልላቷ ተሸፍኖ የንግድ ቤት ስትሆን፣ ሰው ቆሞ ማስቀደሻና መሳለሚያ ያጣበት የሱቅ በደረቴ አውድ ስትሆን የት ነበርን? የቤተሰቦቻችን መቃብር እየታረሰ ንግድ ቤት ሲገነባና ሲመዘበር ምነው ዝም አለን? ውብ የነበሩ ቤተክርስቲያናት በርሜላ ተራ ይመስል የገባያ ጩኸት መናኸሪ ሲሆኑ … ማፈርና ማዘን የነበረብን፣ ደንግጠን ለማስቆም መነሳት ይገባን የነበረው ደብሮቻችንን መሸቀጫ የማድረግ ዘመቻ ሲጀመር ነበር። እንዲህ ያለውን አካሄድ የሚቃወሙ ታቤላ እየተለጠፈባቸው በውግዘት ..

ብዙ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል። ከላይ በመግቢያ እንዳልነው ” ከሜሲ በላይ ሊከፈለኝ በተገባ ነበር” ከሚሉን ዘራፊ ፓስተሮች ጀመሮ የዕምነት ቤቶች ስለቆሸሹ ለክፉ ተግባራት ተጋልጠዋል። ይህንኑ ሌብነታቸውን ስለሚያውቁና ስለሚንቋቸው ፖለቲከኞች እንዳሻቸው ይነዱዋቸዋል። እነሱ ረክሰው ሕዝቡን ያዋርዱታል። አንድ መመሸጊያ፣ ድህነቱንና ብሶቱን መናዘዣ ቤት ቢኖረው፣ ይህንኑ ሊያሳጡት ደርሰዋል።

ምንም እንኳ የጸዳ ጀርባ ስለሌላቸው ብትንቅቋቸውም ፖለቲከኞች እባካችሁን ከህዝብ ብቸኛ ቅርስ ” ዕምነቱ” ላይ ውረዱ። የምታዛንፉት ፍትህና የምትዘርፉት ሳያንሳችሁ ይህን ህዝብ አታስቀይሙት። ስሜት ውስጥ ለመግባት የተደላደለ አቋም እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራውን ትውልድ በጥበብ አሳልፉት።

ምን ነክቷቸው እንደሆነ ባይታወቅም ዶክተር ብርሃኑ ነጋን የወቀሱት ዶክተር ዳናቸው እንዳሉት ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ፈተና ማለፍ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች ምን ያህል እንደሆነ አሳውቀውናል። እንደ ማህበረሰብም ሆነ እንደ አገር መውደቃችንን ያሳየን ፈተና፣ አገሪቱን የሚመሩዋት በአብዛኛው ወይም ከጥቂቶቹ በስተቀር ብቃቱ፣ አቅሙና የስብዕና ጥራት የሌላቸው እንደሆኑ አሳይቶናል። በግዢና በግብዣ በሚታደል ዲግሪ የተሽሞነሞኑት መሪዎች በገፍ በሌብነት ፈተና እያለፉ የመጡ ናቸውና ብዙ አንጠብቅ።

ኢትዮጵያ ለውጥ ትሻለች። ይህ ምንም ጥርጥር የለውም። ግን ለውጡ ሃይማኖትና እምነትን ታኮ በነውጥ እንዲመጣ የሚታሰብ ከሆነ እንደ አገር የማይመለስ ኪሳራ፣ ዳግም ሊያንሰራራ የማይችል ውድቀት ውስጥ እንቀረቀራለን። እንኳን ለጸሎት ቤት በሰፈር መቆሚያምም ላይኖረን ይችላል። በሃይማኖት ሰበብ የሚለኮስ እሳት ሲበላ አይመርጥም። ማንም ሰካራም ዳንክረኛና አርጥራጭ፣ በኢትዮጵያ ላይ የሴራ መርዝ እንዲረጩ የሚከፈላቸው፣ ለኢትዮጵያ መፍትሄ ለማበጀት ካይሮ ከተሰበሰቡ የሚገኝ በጎ ነገር የለምና እንጠንቀቅ። ለውጡ በድርጅት፣ በጥበብ፣ በምርጫ እናድርገው። ሶስት ዓመት ቀላል ጊዜ ነውና። ከዚ ውጭ በትርምስ ትርምስምስ ማለት እንጂ ሌላ ጥቅም አይገኝም። ለማዘን እንኳን ጊዜ አይኖረንም። ኢትዮጵያ የተሰራችበትን የጎሳ ፖለቲካና ህገ መንግስቷንም አንርሳ። ኢትዮጵያ ብዙ ነገሯ ዥጉርጉር ነው። አንድ ቀለም ብሎ ነገር የለም። ሚዲያም የራሱን ሃላፊነት ይወጣ። የተወረወረውን ሁሉ መለጠፍ አይጠቅምም። “እገሌ እንዲህ አለ” ብሎ ከማሰራጨትና ከማራባት በፊት መመርመር ደግ ነው።

ሰላም ይስጠን!!

editorialNEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
መንግስት እምነትና ብሄር ተገን ተደርጎ ምን ለመፈጸም እንደታሰበ “ደርሼበታለሁ፤ አልታገስም” አለ
ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመረጃ ኪነ ሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች አስመረቀ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2