የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት ስምምነት አደረገ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን ውይይት ማድረጉና መስማማቱ ተገልጿል።
በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ የልዑካን ቡድን ከጀርመን የመረጃና ደኀንነት ተቋማት የልዑካን ቡድን ጋር በነበራው ቆይታ በቀጣናዊ፣ ዓለም አቀፋዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝርና በጥልቀት ተወያይቷል። ከውይይቱ በኋላም ተቋማቱ በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል።
የኢትዮጵያና የጀርመን የመረጃና የደኅንነት ተቋማት ሽብርተኝነትን ፣ሕገ-ወጥ የገንዘብና የሰዎች ዝውውርን እንዲሁም ሌሎችንም ወንጀሎች በጋራ ለመከላከል የመረጃ ልውውጥ ማድረግም የስምምነታቸዉ አካል መሆኑን የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልገሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከዉ መረጃ አመልክቷል።
በሌላ ዜና በአዲስ አበባ እና በዴንቨር ከተሞች የሁለትዮሽ ስምምነት የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል። ስምምነቱን አስመልክቶ ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት የስምምነቱ ትኩረት የሁለቱን ከተሞች ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር በንግድ ፣ በኢንቨስትመንት እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።
“በአለም የንግድ ቀን ፕሮግራም ላይም ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ ምርቶችን አቅርበናል” ያሉት ከንቲባዋ በዴንቨር ከተማ ከአቀባበል ጀምሮ በቆይታቸው ለተደረገላቸው መስተንግዶ ከንቲባ ሃንኮክን እና ባልደረቦቻቸውን አመስግነዋል። ኢዜአ
ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም ሆነ የተጠቀሱት አካላት ስለሚሰሙት ቁጥር ስፍር የሌላቸው መረጃዎች በአዎንታም…
ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማህበርን ዓመታዊ እራት ለመታደም ተሰብስበዋል። ከ2600 ባልይ…
“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም ሳይቆዩ አሁን ወዳሉበት ደረጃ ደረሱ። የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምንት መፈረሙን…
አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ አደጋ ጊዜ እርስ በርስ የሚረዱበትን አዲስ የጋራ መከላከያ ስምምነት ረቂቅ ለማዘጋጀት…
የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት” መሆኑን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ። ምርመራው ቀጥሎ ማስተባበያው ሃሰት ከሆን የከፋ ቀጣት…


