“ድርጅታችን ኦቪድ ግሩፕ በሀሰተኛ የመረጃ እና በስም ማጥፋት በተሳተፉ አካላት ላይ ክስ መስርቷል” ሲል በላከልን መግለጫ አመልክቷል። የድርጅቱን ዓላማ፣ መርህና ራዕይ እንዲሉም ያከናወናቸውን ተግባራት አስረድቶ ” ስሜ ጠፍቷል” ሲል ክስ መመስረቱን ገልጿል።
“… ያለስማችን ስም ለሰጡን፣ ያለተግበራችን በሐሰት በድርጅታችን ስምና ብራንድ ላይ ሐሰተኛ መረጃ ባቀረቡና ባሳራጩ በአገር ውስጥና በውጭ በሚገኙ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ላይ አስፈላጊውን መረጃ አሰባስቦ በውጭ በሚገኙ ድርጅቶቹ በኩል ክስ የመሰረተ መሆኑንም ያሳውቃል” ያለው የድርጅቱ መግለጫ፣ “ጉዳዩንም ድርጅታችን በሕግ ተከታትሎ ለማስወሰን በአሜሪካ ፣ በጀርመንና በእስራዔል አገራት በውጭ በሚገኙ አጋር ደርጅቶቹ በኩል ጠበቆችን ቀጥሮ ክትትል እያደረገ ይገኛል” ብሏል።
ድርጅቱ በአማራ ክልል የተቀሰቀስወን ጦርነት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ወይም ከተሞች የማጎሪያ ካምፖችን የሚሰራ ብቸኛ ተቋም መሆኑ ተጠቅሶ በስፋት መረጃ ሲሰራጭ ሰንብቷል። ይህንኑ መረጃ የተቀባበሉ ድርጅቱን ሲከሱና በወንጀለኛነት ሲፈርጁትም ነበር። ይህንኑ መረጃ “የስም ማጥፋት ነው” ሲል በተጠቀሱት አጋር ኩባንያዎቹ አማካይነት ክስ መመስረቱን ከማስታወቁ ድርጅቱ በምን ያህል ኪሳራና መጠን ክስ እንደሚመሰርት ይፋ አላደረገም። መግለጫው ከስር ያለው ነው።
ከኦቪድ ግሩፕ ሐሰተኛ መረጃን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
ድርጅታችን ኦቪድ ግሩፕ በሀሰተኛ የመረጃ እና በስም ማጥፋት በተሳተፉ አካላት ላይ ክስ መስርቷል፡፡
በኮንስትራክሽን ዘርፉ ለ20 ዓመታት በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ግንባታን በማከናወን ከፍተኛ ልምድ ያካበተው ደርጅትቻችን በ2006 ዓ.ም በርካታ ደርጅቶችን አቅፎ ወደ ኦቪድ ግሩፕ ማደግ ችሏል፡፡ ግሩፑ በአሁኑ ሰዓት የ30 የማኑፈክቸሪንግ ፣የትራንስፖርትና ትምህርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ግዙፍ ደርጅቶችና 12 የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ጥምረትን እውን ለማድረግ ”Our Vision is Development ወይም ራዕያችን ልማት ነው” በሚል መሪ ቃል በትጋት እየሰራ ያለ ሀገር-በቀል ተቋም ነው፡፡
በስራ ላይ ያሉትም ሆነ በመቋቋም ላይ ያሉት ተቋማት በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት በሚተጉ ሰራተኞችን በባለቤትነት የሚያቅፉና የሚተዳደሩ ሲሆን ይኸውም ድርጅታችን ኦቪድ ግሩፕን በአይነቱ ልዮ ያደርገዋል።
ለ 20 ዓመታት ያክል በርካታ ግንባታዎችን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን በተለይ በኮምፕረስ እርዝ ብሎክ ፣በማግኒዥየም ቦርድ እና ፓኔሎች፣ የፕላስቲክ ፎርም ወርክ (ሞላዲ) ፣ላይት ጌጅ እስቲል፣ኬ-ስፓን ካስት ኢን ሲቱ ኮንክሪት እና ኩምካንግ አሉምኒየም ፎርም ወርክ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግንባታዎችን በማከናወን በአገራችን የመጀመሪያው በመሆን ሰፊ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ድርጅታችን ኦቪድ ግሩፕ ሥራዎቹን በአገር ውስጥ ካሉና እና በውጭ አገራት ከሚገኙ ስመጥር ደርጅቶች ጋርም ጥምረት ያለው በመሆኑ ዓለምዓቀፋዊ ቅርጽና ተወዳዳሪነት መርህን መሰረት አድርጎ የተቋቋመ ነው፡፡ ተቋማችን ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች ጋር ጥምረት ለመመሰረት ያስቻለውም ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ ተሳትፎና ድጋፍ የገለልተኛነት መርሆችን በተግባር አክብሮ የሚያንቀሳቀስ በመሆኑ ነው፡፡
ኦቪድ ግሩፕ በአገር ውስጥ እና ከውጭ አገራት ስመጥር ኩባንያዎች ጋር ያለውን ጥምረት በመጠቀም በመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚስተዋለውን የፍጥነት እና የጥራት ችግር ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፍጥነት እና ጥራትን በመጨመር በከተሞች እየታየ ያለውን ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት በተግባር የተረጋገጠ መፍትሄ ይዞ የመጣ ሀገር በቀል ደርጅት ነው፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ በጀት ከ60 ሺህ ቤቶች በላይ ያያዘ ዘመናዊ ከተማ ለመገንባት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያከናወነ ያለ ድርጅት መሆኑንም ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
የድርጅታችን ራዕይ እንደ ስያሜያችንና መሪ-ቃላችን የኢትዮጵያን ፍጹም እድገትና ልማት እንዲሁም ዓለምዓቀፋዊ ጥምረት እንዳለው ደርጅት ደግሞ የገለልተኝት መርሆችን አክብሮና አውቆ እንደሚሰራ ለማንም አካል ግልጽ ሆኖ እያለ የደርጅታችን ስምና ብራንድ ላይ ጉዳት ለማድረስ ሐሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በአንዳንድ አካለት ተስተውለዋል፡፡
ለዚህም ድርጅታችን በቸልተኝነት ያለስማችን ስም ለሰጡን፣ ያለተግበራችን በሐሰት በድርጅታችን ስምና ብራንድ ላይ ሐሰተኛ መረጃ ባቀረቡና ባሳራጩ በአገር ውስጥና በውጭ በሚገኙ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ላይ አስፈላጊውን መረጃ አሰባስቦ በውጭ በሚገኙ ድርጅቶቹ በኩል ክስ የመሰረተ መሆኑንም ያሳውቃል፡፡ ጉዳዩኑም ድርጅታችን በሕግ ተከታትሎ ለማስወሰን በአሜሪካ ፣ በጀርመን እና በእስራዔል አገራት በውጭ በሚገኙ አጋር ደርጅቶቹ በኩል ጠበቆችን ቀጥሮ ክትትል እያደረገ ይገኛል፡፡
ድርጅታችን ኦቪድ ግሩፕ በመልካም ስሙና ተግባሩ የሚታወቅና ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከ300 ሚሊየን ብር በላይ መድቦ 2 ሺህ እናቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በቀን እስከ 288 ሺህ እንጀራን የሚጋግር የእንጀራ ፋብሪካን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖቻችን በአዲስ አበባ ከተማ በሰባት የተለያዩ ቦታዎች እንዲሁም በአማራ ክልል በባህርዳርና በማንኩሳ ከተማ የመኖሪያ ቤት በመገንባት፣ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰባችንን ክፍሎች የምግብ አቅርቦት በማድረግ ሰፊ ድጋፍ እያደረገ ያለ ደርጅት ሲሆን ይህንኑ ተግባርም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የድርጅታችንን መልካም ስምና ተግባር እንዲሁም ጠንካራ የገለልተኝነት መርሆችን የሚያውቁ ቅን ግለሰቦች መረጃው ከድርጅታችን ጋር ፈጽሞ ግንኙነት የሌለው ሐሰተኛ መረጃ መሆኑን ተረድተው ድርጊቱን በጽኑ በማውገዛቸው ተቋማችን ልባዊ ምስጋናውን ማቅረብ ይፈልጋል፡፡
ኦቪድ ግሩፕ (ራዕያችን ልማት ነው)
OVID GROUP (Our Vision Is Development)
- ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
- ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርትአዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
- “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
- አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነውቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
- የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለችቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች







