Skip to content
  Wednesday 10 June 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የትግራይ ህዝብ የሰላም፣የህልውናው እና ደህንነቱ ዘብ እራሱ ህዝቡ ነው -ዶ/ር አብርሃም በላይ

    May 29, 20210

    በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው አሸባሪ በጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እርምጃ ተወሰደበት

    September 4, 20210

    Ethiopian Envoy Briefs Sudan Based Media On GERD

    July 4, 20210

    በአዳማ ከተማ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በመሞከርና በምርጫ ጣቢያ የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት የተከሰሱ ተቀጡ

    June 21, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1875
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ልጆቻቸው መቀለ ዩኒቨርስቲ የቀሩባቸው ወላጆች የተመድ ፊት እያነቡ ነው “ልጆቻችንን አስለቅቁልን”

    July 23, 20210

    መከላከያ በኦሮሚያና አማራ ክልል የማጽዳት ስራ እንደቀረው አስታወቀ፤ አማራ ክልል መዋቅሩን እያጠራ ነው፤

    September 1, 20230

    “ሁሉንም ያማከለ ዴሞክራሲያዊ ስረዓተ መንግስት ካልተመሰረተ ወቅታዊና ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ችግሮች ለመፍታት አስቸጋሪ ነው”

    April 17, 20210

    “በተለመደው አሰራር ማስቀጠል የምንችለው ድህነትን ብቻ ነው” ሽመልስ አብዲሳ

    June 3, 20220

    “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች?”

    March 9, 20220
    Prev Next Showing 1 Of 1500
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News2  በሌብነት የተጠረጠሩ 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ታሰሩ
News2

በሌብነት የተጠረጠሩ 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ታሰሩ

Ethioreview newsEthioreview news—October 18, 20230
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ ከተገልጋዮች የሚነሱ ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ከመሰረቱ ለመፍታት ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተወጣጣ ግብረ-ኃይል ሕገ ወጦችንና ሙሰኞችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ለረጅም ጊዜ የተቀናጀ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ ቆይቷል ይላል ጉዳዩን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን የተላከው መግለጫ።

በመሆኑም ከተቋማቱ የተወጣጣውና ጉዳዩን እየተከታተለ ያለው የጋራ ግብረ-ኃይሉ በመግለጫው እንዳመለከተው፤ ተገልጋዮች በመደበኛ የመንግሥት ስርዓት የሚፈልጉትን የፓስፖርትና መሰል አገልግሎቶችን በአፋጣኝና በአነስተኛ ዋጋ ማግኘት ሲችሉ፤ ተጠርጣሪዎች የፈጠሯቸው የተንዛዙና እና የተወሳሰቡ አሠራሮች ዜጎችን ለከፋ እንግልት ከመዳረግ ባሻገር ላልተገባ ወጪ ሲዳርጉ ነበር፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቅ በሙስና ተግባር መሰመራታቸውና የግል ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ እንደነበር ያመለከተው ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተወጣጣው ግብረ-ኃይል ፤ ግለሰቦቹ በአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ የተሰጣቸውን ስልጣንና ሐላፊነት ወደ ጎን በመተው ለግል ጥቅማቸው ሲሉ በዜግነት ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የውጭ ሀገራት ዜጎች፣ በወንጀል ተከሰው የጉዞ ሰነዳቸው ለታገደባቸውና ሐሰተኛ የማንነት መገለጫ ላላቸው ሕገወጦች ጭምር የፓስፖርት፣ ሊሴፓሴና ቪዛ አየር በአየር በመሸጥ እና በማስተላለፍ፤ መንገደኞች በሌሉበት ጉዞ እንዳላቸው በማስመሰል እና የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ተለያዩ ሀገራት እንደተዘዋወሩ የሚገለፅ ማሕተም በማዘጋጀት ተግባር ተሰማርተው ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ተመልምለው ያለፉ እንደሆኑ በማስመሰል ግለሰቦች ባልተገባ መንገድ ለሥራ ወደ ተለያዩ የዓረብ ሀገራት እንዲወጡ በማድረግ እንዲሁም የሕጋዊ ግለሰብን ፓስፖርት ፎቶግራፍ በመቀየር ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽሙ እንደተደረሰባቸው የግብረ-ኃይሉ መግለጫ ጠቁሟል።

More stories
ሚኒስትር ዳኤታ

“ልዩ ኃይሎችን መልሶ ማደራጀት ትጥቅን ከማስፈታት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም”

April 7, 2023

“የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውክልና አለኝ” ዜጎችን የሚያጭበረብሩ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ ክትትል እየተደረገ ነው”

May 29, 2025

መከላከያ በስንዴ ምርት ራሱን ለመቻል እርሻ ጀመረ

May 29, 2023

የአሜሪካ ኤምባሲ የጉብኘት ቪዛ የተደረገ የፖሊሲ ለውጥ

July 20, 2025

እነዚህ ወንጀለኞች ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች የጥቅም ትስስር በመዘርጋት ሙስና ሲፈጽሙ ከመቆየታቸውም ባሻገር፤ ሐሰተኛ የማንነት መታወቂያዎችን በማዘጋጀት ተግባር ላይ ተሰማርተው ከነበሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ጋርም ግንኙነት በመፍጠር ወንጀሉን ሲፈፅሙ እንደቆዩ ታውቋል።

ይህን ተከትሎም ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተወጣጣው ግብረ-ኃይሉ ባደረገው ክትትል ከ200 በላይ የሚሆኑ በሕገወጥ መንገድ የተዘጋጁ ፓስፖርቶች እንዲመክኑ የተደረገ ሲሆን፤ የወንጀል ድርጊቱም መንግሥትን በሚሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ እንዳሳጣው በመግለጫው ተመልክቷል።

በጉዳዩ ላይ ምርመራ ሲያደርግ የቆየው ግብረ -ኃይሉ መግለጫ እንዳመለከተው፤ በአዲስ አበባ ከተማ፤ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በወንጀሉ የተሳተፉ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሲያገለግሉ የነበሩ ከከፍተኛ አመራርነት እስከ ባለሙያ ያሉ 42 ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በዙሁ መሰረትም በወንጀል ድርጊቱ ተሰማርተው ከተገኙና በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከልም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ አዋልሶን ጨምሮ ዘመድኩን ጌታቸው፣ ከድር ሰዒድ ስሩር፣ አስቻለው እዘዘው፣ አብዱላሂ አሊ መሀመድ (አብዱላሂ ጃርሶ)፣ ቴዎድሮስ ቦጋለ፣ ጌትነት አየለ፣ ጀማል ገዳ፣ ሙላት ደስታ፣ ጅላሎ በድሩ፣ ገነት ኃ/ማርያም፣ ደገፋ ቤኩማ ፣ ወንድይፍራው ሽመልስ ገ/ሰንበት እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተወጣጣው ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

በተያዙት ተጠርጣሪዎች ዙሪያ የሚደረገው ምርመራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽም፤ በግለሰቦቹ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ያላቸው ዜጎች ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉም ገልጿል፡፡

በዚህ ኦፕሬሽንም የተለያዩ ፓስፖርቶች፣ የተለያዩ ሀገራት የብር ኖቶች፣ ሐሰተኛ መታወቂያዎች፣ አየር በአየር የወጡ ሊሴ ፓሴዎችና የታተሙ ቪዛ ካርዶች በተጠርጣሪዎቹ መኖሪያ ቤትና የሥራ ቦታ በተደረገ ብርበራ በኢግዝቢትነት መያዛቸወን ግብረ -ኃይሉ አመልክቷል።

ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተወጣጣው ግብረ -ኃይል በእንደዚህ አይነት ሕገ ወጥ ተግባር ዙሪያ የሚያካሂደውን ምርመራ፣ ክትትልና ኦፕሬሽን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፤ ለኦፕሬሽኑ መሳካት ማኅበረሰቡ ላሳየው የተለመደና ቀና ትብብር ምስጋናውን አቅርቧል፡፡


  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups
    VOA NEWS – The Ogaden National Liberation Front (ONLF) categorically rejects claims of affiliation with armed groups and reaffirms its unwavering commitment… Read more: ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV
    In an incisive broadcast on EBC English analyzing the architectural shifts of Ethiopia’s 7th General Election, renowned scholar Professor Alemayehu G. Mariam… Read more: Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”
    VOE June 06, 2026 – Although genetic engineering is a relatively new field of science—spanning no more than 40 years—it is currently… Read more: Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ
    ቪኦኢ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም – የዘረ መል ምህንድስና (Genetic Engineering) ዕድሜው ከ40 ዓመታት የማይበልጥ አዲስ የሳይንስ ዘርፍ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት… Read more: ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ
  • ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»
    ቪኦኢ ሰኔ 30 ቀን 2018 – ከካርዲፍ የመጣችው የ64 ዓመቷ አዛውንት ካረን ቦንሃም፣ የጡት ካንሰር እንዳለባት በወቀችበት ወቅት እንደማንኛውም ታካሚ ከፍተኛ ድንጋጤ… Read more: ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»
home
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

የቀበሌ 14 ተጫዋቾችን 90 ደቂቃ ብቻ አጫውቶ የተበጫጨቀው ታኬታ አስገራሚው ሪፖርት
ከሕግ ውጭ ፓስፖርት በመስጠት የሌብነት ወንጀል የተጠረጠሩ 28 ግለሰቦች ፍ/ቤት ቀረቡ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News2

የዘለንስኪ ጥሪ፦ “ጦርነቱን ለማቆም ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ዝግጁ ነኝ”

June 5, 20260
News2

ትራምፕ እና ኔታንያሁ በስልክ በቁጣ መነጋገራቸው ይፋ ሆነ

June 2, 20260
News2

ብሔራዊ ጥቅምን አሳልፎ ለመስጠት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ባለድርሻ ሊሆኑ አይገባም – በለጠ ሞላ

March 8, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
TOP NEWS

ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups

June 7, 20260
TOP NEWS

Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV

June 7, 20260
AFRICA

Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ

June 7, 20260
ENTERTAINMENT

ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»

June 7, 20260
News

ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ”

June 6, 20260
Load more
Recent Posts
  • ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups June 7, 2026
  • Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV June 7, 2026
  • Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science” June 7, 2026
  • ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ June 7, 2026
  • ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ» June 7, 2026
  • ህወሃት በፕሪቶሪያው ስምምነት ፍርስራሽ ላይ ! አዲስ የህወሃት የጦርነት ማስጠንቀቂያና “አሸማግሉኝ” June 6, 2026
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! – ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ June 5, 2026
  • Agricultural Sovereignty, Economic Transformation, and the Defiance of Extremism Ahead of the 7th National Election June 5, 2026
  • የዘለንስኪ ጥሪ፦ “ጦርነቱን ለማቆም ከፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት ዝግጁ ነኝ” June 5, 2026
  • የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫውን አደነቀ June 5, 2026
  • The Inverted Frontlines: How Secret Alliances and the Western Tigray Fault Line Threaten to Reignite Ethiopia June 4, 2026
  • Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia June 4, 2026
  • ጃዋር ለአርሲው ግድያ ቀዳሚ ተሟጋች ሆነ፤ “እንቀነጥሳችኋለን” ያለበትን ሜንጫ የት ጣለው? June 3, 2026
  • International Partner Welcomes Ethiopia’s 7th General Election, Calls for Inclusive Voting in Remaining Constituencies June 3, 2026
  • ዓለም አቀፍ አጋሮች የኢትዮጵያን 7ኛ አጠቃላይ ምርጫ በበጎ ተቀበሉ፤ June 3, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news