በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጠበቃ ነኝ በማለት በርካታ ክሶችን ተከራክሮ የረታው ግለሰብ በባለሥልጣናት በቁጥጥር ስር ዋለ።
ግለሰቡን በተመለከተ የሚወጡ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት “ጠበቃው” ከመታሰሩ በፊት ከከፍተኛው ፍርድ ቤት ጀምሮ አስከ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ድረስ 26 ጉዳዮችን ይዞ በመከራከር ለመርታት ችሏል።
ግለሰቡ ሊያዝ የቻለው ለኬንያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ተገቢው ትምህርት እና ብቃት ሳይኖረው በማስመሰል በዘርፉ በመሰማራቱ ከተለያዩ ሰዎች ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ነው።
የሕግ ባለሙያዎቹ ማኅበር በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ግለሰቡ፣ ጠበቃ እንዳልሆነ እና በኬንያ ውስጥ በጠበቅና እንዲሠራ የሚያስችለው ፈቃድ የሌለው ነው።
“ግለሰቡ በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጠበቃ እንደሆነ እና የማኅበሩ አባል መሆኑን በመግለጽ ሲያጭበረብር ነበር” ሲል ማኅበሩ ከሷል።
የሕግ ባለሥልጣናት ጨምረውም ግለሰቡ ተገቢው ትምህርት እና ፈቃድ ሳይኖረው ለምን ያህል ጊዜ በጥብቅና እንደሠራ ባይገለጹም በርካታ ጉዳዮችን ለማሸነፍ መብቃቱ ተነግሯል።
ብሪያን ምዌንዳ በሚል ስም የሚታወቀው ይህ ግለሰብ ከዚህ ቀደም በአገሪቱ ውስጥ አሳሳቢ ሆኖ የነበረው “ሙንጊኪ” የተባለው የወንጀል ቡድን መሪን በመወከል በቴሌቪዥን በተለላፈ የፍርድ ሂደት ላይ ተሳትፎ እንደነበር ይነገራል።
ግለሰቡ ሐሰተኛ መሆኑ ከተነገረ በኋላም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ይኽው ቪዲዮ በስፋት እየተዘዋወረ ይገኛል።
የኬንያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ግለሰቡ ተመሳሳይ ስም ያለውን ሕጋዊ ጠበቃ ግለ ታሪክ ከማኅበሩ ድረ ገጽ ላይ በመውሰድ እርሱን መስሎ ሲያጭበረብር ቆይቷል ብሏል። BBC
- ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed GroupsVOA NEWS – The Ogaden National Liberation Front (ONLF) categorically rejects claims of affiliation with armed groups and reaffirms its unwavering commitment to the peace agreement with… Read more: ONLF Rejects Claims of Affiliation With Armed Groups
- Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETVIn an incisive broadcast on EBC English analyzing the architectural shifts of Ethiopia’s 7th General Election, renowned scholar Professor Alemayehu G. Mariam declared that the nation’s democratic… Read more: Beyond the Ballot: How Professor Alemayehu G. Mariam Explains Ethiopia’s Democratic ‘Escape Velocity’ on ETV
- Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”VOE June 06, 2026 – Although genetic engineering is a relatively new field of science—spanning no more than 40 years—it is currently transforming the world of medicine.… Read more: Dr. Jote Tafese: “Curing Incurable Diseases Through Science”
- ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስቪኦኢ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም – የዘረ መል ምህንድስና (Genetic Engineering) ዕድሜው ከ40 ዓመታት የማይበልጥ አዲስ የሳይንስ ዘርፍ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት የሕክምናውን ዓለም በከፍተኛ ሁኔታ እየለወጠ… Read more: ዶ/ር ጆቴ ታፈሰ- መድኃኒት አልባ ሕመሞችን በሳይንስ መፈወስሰዎችን – ከሞት አፋፍ መመለስ
- ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»ቪኦኢ ሰኔ 30 ቀን 2018 – ከካርዲፍ የመጣችው የ64 ዓመቷ አዛውንት ካረን ቦንሃም፣ የጡት ካንሰር እንዳለባት በወቀችበት ወቅት እንደማንኛውም ታካሚ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብታ ነበር። “የካንሰር ምርመራና… Read more: ኬሞቴራፒን ማስቀረት የተቻለበት አዲስ ተስፋ፡ የ64 ዓመቷ ካረን የ«ዳግም መወለድ»







