Skip to content
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
  • News
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    Western Pressure on Ethiopia Intended to See Weak Gov’t, Nation – Scholars

    July 10, 20210

    Journalist demands UNWFP to tell truth about missing trucks

    October 3, 20210

    ብርሃኑ ባይህ እና አዲስ ተድላ ምህረት ሊደረግላቸው ይችላል ተባለ

    December 19, 20200

    አብንና ባልደራስ ከተሸነፉ ” ውጤቱን አንቀበልም” ሊሉ የሚችሉ ፓርቲዎች እንደሚሆኑ ዲፕሎማቶች ገለጹ

    May 23, 20210
    Prev Next Showing 1 Of 1866
  • Design
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ሚስጥራዊ የቻይና ፖሊስ ጣቢያዎች በአሜሪካ ተገኙ

    December 19, 20240

    ሦስተኛው ዕድል እንዳይባክን … !

    May 21, 20220

    “Why I decided to extend my time at the club”

    May 24, 20230

    የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ዋና የጦሩ መሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ

    February 24, 20220

    “Ethiopia’s success reflects a new alternative for Africa’s development”

    January 29, 20240
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • Video
    video

    ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ የሰጡት ማብራሪያ

    July 4, 2024
    video

    የህብታቸውን ምንጭ የሚያውቁ አይሰጉም! ማብራሪያ

    June 22, 2024
    video

    የሀገር አቀፍ የምክክር ሂደት ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት

    June 4, 2024
    video

    የምክክር ሂደት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ ያደረጉት ሙሉ ንግግር

    June 4, 2024
    Prev Next Showing 1 Of 5
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • News
  • Design
  • Video
  • Categories
    • News
      • Europe
      • Politics
        • Reaction
          • Feedbacks
          • Opinions
            • Poeple
            • Reports
      • US
      • World
    • Design
      • Architecture
      • Devices
      • Inspiration
      • Trends
    • Events
      • Movies
      • Music
      • Social media
      • Stars
    • Featured
      • Lifestyle
      • Technology
      • Tourism
      • Travel
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
  • Home Demo news
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  News  “ጥቅምት 24የተፈጸመዉ ጥቃት መቼም ቢኾን፣ በየትኛውም ቦታ ሊደገም የማይገባውና ታሪክ የማይረሳዉ አስከፊ ድርጊት ነው፡፡ ” – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
News

“ጥቅምት 24የተፈጸመዉ ጥቃት መቼም ቢኾን፣ በየትኛውም ቦታ ሊደገም የማይገባውና ታሪክ የማይረሳዉ አስከፊ ድርጊት ነው፡፡ ” – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Ethioreview newsEthioreview news—November 5, 20230
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሀገሩ ክብር የሚከፍለው መስዋዕትነት በተግባር ከታየባቸው ቀናት መካከል ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም አንዱ ነው፡፡ በዕለቱ በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የደረሰው ጥቃት በሀገራችን ታሪክ ጥቍር ጠባሳ አሳርፎ ያለፈ ክስተት ነው፡፡ ይህ በሠራዊቱ አባላት ላይ የተፈጸመዉ ጥቃት መቼም ቢኾን፣ በየትኛውም ቦታ ሊደገም የማይገባውና ታሪክ የማይረሳዉ አስከፊ ድርጊት ነው፡፡

በሠራዊታችን ላይ የተፈጸመዉ ጥቃት ሀገራችንን ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈለ፣ ወደ አውዳሚ ጦርነት ጎትቶ ያስገባንና ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሰ በመኾኑ ሊረሳ የማይችልና ሊደገም የማይገባዉ አሳፋሪና አሳዛኝ የታሪክ አንጓ ነው፡፡ ምንም እንኳን ጥቃቱን ተከትሎ የተገባበትን ጦርነት በሠላም ስምምነት መቋጨት ቢቻልም ቀኑ በታሪካችን እንደ ነውር መቆጠር ያለበት ተግባር የተፈፀመበት ቀንና ትምህርት የሚወሰድበት ክስተት በመሆኑ ዕለቱ ሁሌም ሊዘከር ይገባል፡፡

ይሄንን ቀን የምናስበው ለቂምና ለበቀል አይደለም። ያ ስሕተት እንዳይደገም ነው። እናቶች የሚያለቅሱበት፤ ወጣቶች የሚማገዱበት፣ የሕዝቦች ትሥሥር የሚላላበት፤ ቤተሰብ የሚበተንበት፣ የሀገር ሀብት የሚወድምበት የጦርነት መንገድ ይብቃ ለማለት ነው።

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም የተፈጸመዉን ጥቃት በመቀልበስ በኢትዮጵያ ላይ ተከፍቶ የነበረዉን ጦርነት በጋራ ርብርብ መክተን የሀገራችንን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት አስጠብቀናል፡፡ ይህም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚደረግ ማንኛውም ጥረት ሊሳካ እንደማይችል ፅኑ ማሳያ ነው:: በመሣሪያ ኃይል ሥልጣን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት በኢትዮጵያ ምድር ሊሳካ እንደማይችል አረጋግጧል፡፡

More stories

በመተከልና ሌሎች አካባቢዎች ተፈጥረው በነበሩ ግጭቶች የሱዳንና የግብፅ እጅ እንዳለበት ተገለጸ

March 5, 2021

የመከላከያን ጨምሮ የአሜሪካንን ሚስጢር “ለትውልድ አገሩ አቀብሏል” የተባለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ” ብሄራዊ ጀግና” እየተባለ ነው

October 1, 2023

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ወይም ሞት እያለ ነው

March 22, 2022

“የኢትዮጵያ አምላክ እንደ ወትሮው ከእኛ ጋር ነበር ” ዐቢይ አህመድ ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገለጹ

December 8, 2021

መንግሥት ለዘላቂ ሀገራዊ ሰላምና ለሀገር አንድነት ሲል ችግሩን በሠላማዊ መንገድ ለመቋጨት የወሰነው፤ ተመሳሳይ ስሕተቶች በየትኛውም አካባቢና ጊዜ እንዳይደገሙ ትምህርት እንዲወሰድበት ለማስቻል ነው፡፡ መከላከያ ሠራዊትን ማጥቃት መደገም የሌለበት ትልቅ ስሕተት መኾኑን በዚህ ወቅት በየጥሻዉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች ሊገነዘቡት ይገባል፡፡

መከላከያ ሠራዊታችንን ማጥቃት የሀገራችን የኅልውናዋ የመጨረሻ ምሽግን መንካት እንደኾነ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በየመንደሩ እየዞሩ የሕዝብን ሰላም የሚነሱ፣ ዝርፊያ የሚፈጽሙና ሀብት የሚያወድሙ አካላትም እየሄዱበት ያለው መንገድ የስህተት መሆኑን ተገንዝበው መከላከያ ሠራዊታችን ላይ የሚፈፅሙትን ትንኮሳ ሊያቆሙ ይገባል፡፡

ወንዝ የማያሻግር የፅፈኝነት ዓላማ አንግበው የሚንቀሳቀሱ የመንደር ታጣቂዎች፤ ትልቅ ሀገራዊ ራእይ ሰንቆ የተሰለፈዉን መከላከያ ሠራዊታችንን በማጥቃት ምንም አይነት ድል እንደማያገኙ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ዘብ የቆመው ሰራዊታችን ዛሬም በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል፡፡

መከላከያ ሠራዊታችን በጥቅምት 24 የደረሰበትን ጥቃት አልፎ፣ ሀገራችን ላይ የተከፈተውን ጦርነት መክቶና የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት በመሥዋዕትነቱ አስከብሮ ኢትዮጵያን ከታላቅ አደጋ ታድጓል፡፡ በዚህ ወቅት መከላከያ ሠራዊቱ ለሀገራችን እየከፈለ ያለዉን ክቡር መሥዋዕትነት በማቃለል የሐሰት ቅስቀሳ የሚያሰራጩ አካላትም ከባለፈው ስህተት ተምረው ከእኩይ ተግባራቸው ሊታቀቡ ይገባል፡፡

ጥቅምት 24 ጥቃት የተፈጸመበት ጀግናዉ ሠራዊታችን አሁን ላይ የበለጠ ዐቅሙን በሰው ሃይል፣ በስነምግባር፣ በመሳሪያ፣ በቴክኖሎጂና በወታደራዊ ሳይንስ ገንብቶ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን ከማንኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ ጥቃት ጠብቆ ኢትዮጵያን ወደላቀ ከፍታ ለማሸጋገር በሚችልበት አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ምንግዜም ፍላጎታቸው ሰላም፣ ልማትና አብሮነት ብቻ ነው፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንም እነዚህን የሕዝብና የመንግሥት ፍላጎቶች እውን ለማድረግ ማንኛዉንም መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው፤ እየከፈለም ነው፡፡ ይሁን እንጅ አንዳንድ ቅጥረኞች የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የሐሰት ዘመቻዎችን ከፍተው የሰራዊቱን ክቡር ስም ለማጠልሸት ሲሞክሩ ታይቷል፡፡ ሆኖም ሠራዊታችን እንኳን ከሃሰተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በተፈጸመበት ጥፋት እንኳ የማይንበረከክ ፅኑ መሰረትና ኢትዮጵያዊ ጀግንነት የተላበሰ መኾኑን ወዳጅም ጠላትም ያውቀዋል፡፡

መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም በተለመደው ደጀንነቱ ሠራዊቱን ለላቀ ድልና ክብር እያበረታታ ይገኛል።ይህንን ተግባሩንም አጠናክሮ ሊቀጥልበት ይገባል፡፡ መከላከያ ሠራዊትን የማጥቃት የባንዳነት ተግባር በማንኛውም ወቅትና ሁኔታ ሊወገዝ የሚገባው ተግባር ነው፡፡ ለዚያም ነው ዘንድሮ የጥቅምት 24ን ለሦስተኛ ዓመት ስናስብ ይህ አይነት የሃገር ክህደት እንዳይረሳም እንዳይደገምም የምንዘክረው፡፡

ክብር ለሀገር ሉዓላዊነት ለተሠዉ ጀግኖች!!

ይቅር እንላለን ግን አንረሳም፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት


  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
    ዘፈኑ ገና ከመለቀቁ በፊት ጀምሮ በተከታታይ አየሩን የያዙት መረጃዎች ሁሉ በኦፊሳል ከቴድሮስ ካሳሁን፣ ከባለቤቱ ወይም በህግ የሚታወቁ ወኪሎቹና ተቋማትን ምንጭ ያደረጉ አልነበሩም። ይህ እስከታተመ ድረስ ቴዲም… Read more: ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
    አዲስ ሪፖርተር ዜና – “ቅዳሜ ምሽት፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ታዋቂው ሂልተን ሆቴል በደመቀ ድባብ ውስጥ ነበር። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች የኋይት… Read more: ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
    ለሶስት አስርት ዓመታት በማዕቀብ ተቆልፎባት የኖረችው ኤርትራ በኢትዮጵያ ለውጥ መምጣቱን ተከትሎ ሰንሰለቱ ተበጥሶላት ነበር። ጦርነትም፣ ሰላምም ባልነበረበት ሁኔታ ተዘግቶባት የነበረችው ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም አውርደው ብዙም… Read more: “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
    ቪኦኢ ዜና -በአውሮፓ ህብረት እና በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) መካከል ያለው ግንኙነት ጥርጣሬ ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወቅት፣ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድንገተኛ አደጋ ጊዜ… Read more: አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
    ቪኦኢ ዜና -በአሜሪካ ምክር ቤት አባል ኢልሀን ኦማር የሀብት መግለጫ ላይ ታይቶ የነበረውና ከፍተኛ ውዝግብ አስነስተው የነበረው የ30 ሚሊዮን ዶላር ሃብት “የሂሳብ ባለሙያዎች ስህተት” መሆኑን ጽህፈት… Read more: የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች
NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

Ethioreview news

A journalist

የአርሂቡ ሪል ስቴት ግንባታ ታገድ፤ በስራ ላይ እያሉ በሞቱት ሶስት ሰራተኞች ሳቢያ በህግ ሊጠየቅ ነው
የአገር መከላከያ በወገኖቹ የተከዳበት ቀን ” አይረሳም!” እንዳይደገም ትውልድ ሁሉ ያስበዋል!!
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 20260
Load more
Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 20260
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 20260
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 20260
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 20260
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 20260
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 20260
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedbusinesshotarchivetips
    © Copyright 2026, All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2
    • Home Demo news