Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  News  ጠቅላይ ኦዲተር በቢሊዮን የሚቆጠር ብር መመሪያ ባለመጠበቅ፣ በእላፊ ክፍያ፣ ከበጀት በላይ በመጠቀም … ግኝቱን ይፋ አደረገ
NewsTIPS 1

ጠቅላይ ኦዲተር በቢሊዮን የሚቆጠር ብር መመሪያ ባለመጠበቅ፣ በእላፊ ክፍያ፣ ከበጀት በላይ በመጠቀም … ግኝቱን ይፋ አደረገ

Ethioreview newsEthioreview news—June 18, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

በመንግስት ተቋማት ላይ በተካሄደ የኦዲት ምርመራ ከህግና መመሪያ ውጭ ክፍያ የፈጸሙ፣ በተቋማቸው ለማይገኙና ለተሰናበቱ ሰራተኞች ደመወዝ የሚከፍሉ፣ ከበጀታቸው በላይ እላፊ የተጠቀሙ፣ ያለ አማካሪ መሃንዲስ ማረጋገጫ ክፍያ የፈጸሙ፣ ለማን እንደሚከፍሉ የማያውቁ፣ እላፊ የከፈሉና የመሳሰሉትን ዝርዝር ጉዳዮች ያካተተ ሪፖርት ቀረበ፣ ተመላሽ እንዲሆን የተባለ ገንዘብ አስራ አንድ በመቶ ብቻ መመለሱ ተመልክቷል። የሪፖርቱ አቅራቢዎችና ምክር ቤቱ ጥፋት በፈጸሙት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥያቄ አቅርበዋል።

በዘጠና ሁለት መስሪያ ቤቶች ላይ በተደረገ የኦዲት ግኝት መሰረት ተመላሽ እንዲያደርጉ ተብሎ አስተያየት ከተሰጠበት 443 ሚሊየን 23 ሺህ 846 ብር ከ91 ሣንቲም፣ እንዲሁም 23 ሺህ 55 ዶላር ውስጥ የተመለሰው 48 ሚሊየን 217 ሺህ 965 ብር ከ67 ሣንቲም ብቻ መሆኑ ጠቅሰው የፌደራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት አድርገዋል።

ዋና ኦዲተር በተቋማቸው የተከናወኑ ሥራዎችን ሪፖርት ሲያቀርቡ እንዳሉት የተመለሰው ገንዘብ ሊመለስ ከሚገባው ውስጥ አስራ አንድ በመቶ ብቻ ነው። ይህም ከሚጠበቀው አንጻር እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ተመልክቷል።

በሪፖርቱ በባለበጀት መስሪያ ቤቶች በኩል ርምጃ እስከመውሰድ የሚደርስ መሻሻሎች መኖራቸውን ቢገለጽም ነገር ግን ተቀባይነት የሚያሳጣ የኦዲት ግኝት እና ብር ተመላሽ ያላደረጉ መስሪያ ቤቶች ላይ ምክር ቤቱ ርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ ቀርቧል።

More stories

አሜሪካ የጣለችው ማዕቀብ-ህግ የማይሆን፣ አስገዳጅነትን የማያካትት ” ቀ.ው” ነው

May 27, 2021

“ከኢትዮጵያዊነት ከፍታ እወርዳለሁ የሚለውን ማዕረጉን ገፈን …”

January 20, 2022

የአሳብ አንድነት – የአስደማሚው አድዋ ሙዚየም ኪነ ህንጻ ትውውቅ በአርክቴክቱ

February 10, 2024

ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ የ31 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

May 10, 2021

በዚሁ መሰረት ምክር በ2014 በጀት ዓመት በዋና ኦዲተር በኦዲት ግኝት መሰረት ብር ተመላሽ እንዲያደርጉ አስተያየት የተሰጠባቸውና ተመላሽ ያላደረጉ ተቋማት ላይ ተጠያቂነትን እንዲሰፍን ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

የበጀት አጠቃቀምን አስመልክቶ በሪፖርቱ እላፊ በጀት የበሉ

ተቋሙ ኦዲት ካደረጋቸው መስሪያ ቤቶች መካከል የተፈቀደላቸውን በጀት በስራ ላይ ያዋሉት ሂሳብ ሲነጻጸር ከበጀት በላይ ወጪ የተደረገበት ሆኖ ተገኝቷ። በርካታ ደግሞ ስራ ያልተሰራበት በጀት ተመዝግቦባቸዋል።

በ20 መ/ቤቶች በልዩ ልዩ የሂሳብ መደቦች በደንቡ መሰረት ሳያስፈቅዱ ለእያንዳንዱ የበጀት ኮድ ከተደለደለው በላይ ወጪ የሆነ ሂሳብ ከመደበኛው በጀት ብር 524. 7 ሚሊዮን ፣ ከውስጥ ገቢ 288.9 ሚሊዮን ፣ ከካፒታል በጀት 489.4 ሚሊዮን በድምሩ 1.3 ቢሊዮን ብር ተገኝቷል።

በኮድ ከተደለደለው በጀት በላይ ውጭ ያደረጉ ዋና ዋና መ/ቤቶችን ሪፖርቱ ዘርዝሮ አቅርቧል። በዚሁ ዝርዝር አብዛኞቹ ዩኒቨርስቲዎች እላፊ ሃብት መጠቀማቸው ተገልጿል

  • ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 322.5 ሚሊዮን
  • አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ተጠሪ ተቋማቱ 267.9 ሚሊዮን
  • ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 173.2 ሚሊዮን
  • ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 125.1 ሚሊዮን
  • የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 109.5 ሚሊዮን
  • ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ 91.3 ሚሊዮን
  • አምቦ ዩኒቨርሲቲ 83.3 ሚሊዮን
  • አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ 75.1 ሚሊዮን  ሲሆኑ ሁለት መስሪያ ቤቶች ደግሞ 9.7 ሚሊዮን ብር በጀት ስለመኖሩ ሳይረጋገጥና ሳይፈቀድ ክፍያ መፈጸማቸው ተመልክቷል።

ከደንብ ውጭ የተከፈለ ክፍያን በተመለከተ

ከደንብ እና መመሪያ ውጭ የተከፈለ ሃብትን አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት በ30 መ/ቤቶች ብር 16 ሚሊዮን 470 ሺህ ከደንብና መመሪያ ውጭ አላግባብ ክፍያ መፈጸሙ ይፋ ሆኗል። በዚሁ መሰረት ዋና ዋናዎቹ ተብለው የተጠቀሱት

  • ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 3 ሚሊዮን
  • የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት 2 ሚሊዮን 889 ሺህ
  • ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2 ሚሊዮን 42 ሺህ
  • መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ 1 ሚሊዮን 156 ሺህ 

በተቀጠሩበት መስሪያ ቤት የሌሉና ከስራ ገበታ ለተሰናበቱ ሰራተኞች የተከፈለ ደመወዝ

የኦዲት ግኝት ሪፖርቱ ይፋ ባደረገው ሌላ መረጃ ደግሞ በአስራ ስድስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ያገኛቸው ግኝቶች ናቸው። ስማቸውን ዘርዝሮ ሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው 485 ሺህ 183 ከ56 ሳንቲም ገንዘብ ባክኗል። የባከነውም መስሪያ ቤቶች በመስሪያ ቤት ለሌሉና ከስራ ለተሰናበቱ ሰራተኞች ያለማቋረጥ ደመወዝ ይከፍሉ እንደነበር በተገኘ ማስረጃ ነው።

በበልጫ አላግባብ የተከፈለ የመንግስት ሃብትን በተመለከተ

በ32 መ/ቤቶች እና በ9 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በተለያዩ የግንባታና ግዥዎች 4.9 ሚሊዮንና ለውሎ አበልና ሌሎች ክፍያዎች 57.6 ሚሊዮን በድምር 62.6 በብልጫ የተመዘገበ የኦዲት ግኝት መኖሩን ተቋሙ አመልክቷል።

የግዥ አዋጅ ደንብና መመሪያ ያልተከተሉ ግዥዎችን አስመልክቶ

በሰባ ሶስት መ/ቤቶች እና በ15 ቅ/ጽቤቶች ብር 2 ቢሊዮን 199 ሚሊዮን የመንግስት ግዥ አዋጅ ደንብ እና መመሪያን ሳይከተል ግዥ ተፈጽሟል። ይህ የተለመደና ሊታረም ያልቻለ አሰራር

  • በጨረታ መግዛት ሲገባው ያለጨረታ በቀጥታ የተፈጸመ ግዥ 1.8 ቢሊዮን ብር
  • መስፈርት ሳይሟላ በውስን ጨረታ የተገዛ 104.3 ሚሊዮን ብር
  • ግልጽ ጨረታ መውጣት ሲገባው በዋጋ ማወዳደሪያ የተፈጸመ 96.1 ሚሊዮን ብር
  • የዋጋ ማወዳደሪያ ሳይሰበሰብ በቀጥታ የተፈጸመ ግዥ 13.8 ሚሊዮን ብር 
  • ሌሎች የግዥ ሂደት ያልተከተሉ 134.6 ሚሊዮን ዋና ዋና ናቸው።

ዋና ዋና መስሪያ ቤቶች (ደንብና መመሪያ ሳይከተሉ ግዥ የፈጸሙ)

  • ገቢዎች ሚኒስቴር በዋናው መ/ቤትና በቅርንጫፍ ፅ/ቤት 1.4 ቢሊዮን
  • የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት 91 ሚሊዮን
  • የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 65.5 ሚሊዮን
  • የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 62.9 ሚሊዮን
  • የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ 57.1 ሚሊዮን
  • ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ 37.4 ሚሊዮን
  • የጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት 34 ሚሊዮን

በአማካሪ መሃንዲሳ ሳይረጋገጥ የተከፈለ ክፍያ

የግንባታ ክፍያ በአማካሪ መሃንዲስ ተረጋግጠው መከፈላቸውን ለማረጋገጥ በተደረገ ኦዲት በ2 መ/ቤቶች 170 ሚሊዮን  394 ሺህ በአማካሪ መሃንዲስ የክፍያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሳይቀርብ ክፍያ ተፈጽሞ ተገኝቷል። ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 169.7 ሚሊዮን ብር በአማካሪ መሃንዲስ ሳይረጋገጥ ክፍያ ፈጽሞ ተገኝቷል።

የተከፋይ ሂሳብ ፦

በአስራ አራት መ/ቤቶች 1.7 ቢሊዮን ብር በተከፋይ ሂሳብ ተይዞ ተገኝቷል። ይህ ገንዘብ ለማን እንደሚከፈል እንኳን ተለይቶ እንደማይታወቅ ሪፖርቱ ግኝቱን አስቀምጧል። የተከፋይ ሂሳብ ለባለመብት መለየት ካልቻሉ መስሪያ ቤቶች ፦

  • የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር 1.5 ቢሊዮን
  • የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 131.8 ሚሊዮን 
  • ማዕድን ሚኒስቴር 29.9 ሚሊዮን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ሪፖርቱ ከፋና አዲስ ዘመንና ቲክቫህ የተሰባሰበ ነው

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ግልፅ ደብዳቤ – ለተከበሩ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሬዚዳንት (ከደበበ እሸቱ)
የልብ ህመም በምን ምክንያት ይከሰታል? ችላ የማይባሉ ምልክቶች
Related posts
  • Related posts
  • More from author
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
News

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር

April 13, 2026
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2