Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  TIPS 1  መፈንቅለ ደራርቱ ቱሉ – በተቀነባበረ የሚድያ ዘመቻ
TIPS 1

መፈንቅለ ደራርቱ ቱሉ – በተቀነባበረ የሚድያ ዘመቻ

Ethioreview newsEthioreview news—August 5, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

“ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አትሌት ገዣኸኝ አበራ በፌዴሬሽኑ ውስጥ ከፍተኛ የአቅም እጥረት ችግር እንዳለ ጁላይ 17 በይፋ ሲናገር ግንባር ያደረገው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ነበር። ይህን ያለው ኦሊምፒክ ሊጀመር ቀናቶች ሲቀሩት ነው። ስለ ውድድር የሚያውቅ፣ ለአንድ ተወዳዳሪ ስነ ልቦና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ የሚረዳና ሮጦ ያሳለፈው ገዛሃኝ አበራ ስለ አቅም ማነስ ሲናገር እሱስ? ማራቶን ከመሮጡ ውጪ የት ሄዶ የገነባው አቅም ነው ያለው? የአቅሙ ጉዳይ ለጊዜው ይቁምና ለምንድን ነው ኦሊምፒክ ሲደርስ እየጠበቀ “የኢትዮጵያ ህዝብ ፍረድ” እያለ የሚጮኸው? ምንድን ነው ፍላጎቱ? ዕውነት የአቅም ችግር ካሳሰበው “እኔ አቅም የለኝም ብሎ መልቀቂያ በማስገባት ለምን ቀድሞ ምሳሌ አይሆንም? ነገሩ ሌላ ነው። ማን እንደሚጋልበው ይታወቃል”

ኦሊምፒክ፣ ዓለም ሻምፒዮናና ተመሳሳይ ታላላቅ ውድድሮች ሲቃረቡ ፍትጊያ አይጠፋም። ይህ ባህል ሆኖ የኖረው ሽኩቻ መነሻው “ተቆርቋሪነት የሚባል ታቤላ ያለው የሚደረብበት ነው። ሰሞኑን መልኩ ይቀያየር እንጂ የድራማው ሁሉ ማረፊያ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ከሃላፊነት የማስነሳት ወይም “መፈንቅለ ደራርቱ ቱሉ” ነው።

“አሁን ላይ የኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድር ላይ ናቸው። ጥፋት እንኳን ቢኖር ለአንድ ሳምንት መታገስ እንዴት ያቅታል? ሚዲያዎችስ እንዴት ይህን በሃላፊነት ስሜት አያስቡም” ሲሉ የገለጹልን ከግብግቡ ጀርባ ስላለው የተደራጀ አካሄድ መረጃ ያላቸው ወገኖች ናቸው።

ውድድር እየተጠበቀ፣ ህዝብ ወርቅና ብር በሚናፍቅበት ወቅት ሆን ተብሎ የንትርክ ዜና የሚያሰሙት ሁሉ ምህላቸው “የኢትዮጵያ ህዝብ ፍረድ” ነው። ህዝብ ምን አውቆ ይፍረድ? ማን ትክክለኛውን መረጃ ይስጠው? አንዳንድ ሚዲያዎች የአንድ ሰው አፍ እስኪመስሉ ድረስ አጀንዳ ሰፋሪዎች ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ የአንድ ወገን መረጃ ያለ አንዳች ማጣራት የሚያፈሱ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ የጉዳዩን ባለቤት ዘንግተው ያለ አንዳች ህጋዊ ማስረጃ “ወኪል ነን” የሚሉ ” ተበድለን” ሲሉ ለመከረኛ የላይክና የሼር ግብአት ሲባል መረጃው የሚያመጣው ጉዳትና ተዓማኒነት ሳይመዘኑ የሚረጩ ናቸው።

More stories

ከግብጽ ጉቦ ወስደዋል የተባሉት ሴናተር በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ፤ ኢትዮጵያ ላይ ዘምተውባት ነበር

July 17, 2024

ሶስት ለአማራ ህዝብ “የተቀቡ” መሪዎች – “የአማራ ደም በሊትር ስንት ነው”

July 23, 2024

ኢትዮጵያ በሶማሊያ እየተደገሰ ያለውን የትርምስ ድግስ እንደማትታገስ አስታወቀች

August 28, 2024

ሀኪሙን አትግደሉ!  (Whoever you are!)  የዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ መልዕክት

February 4, 2025

” እነማን፣ እንዴትና በምን መልኩ ተደራጅተው አትሌቶቹን በመረበሽና ውጤት ለማበላሸት እየሰሩ እንደሆነ ከውድድሩ በሁዋላ እንገልጸዋለን” የሚሉት ለጊዜው ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ ወገኖች፣ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነቷ ለማሰናበት የተጀመረው ዘመቻ ይሳካል ብለው እንደማያምኑም አመልክተዋል።

“ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገዣኸኝ አበራ በፌዴሬሽኑ ውስጥ ከፍተኛ የአቅም እጥረት ችግር እንዳለ ጁላይ 17 በይፋ ሲናገር ግንባር ያደረገው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ነበር። ይህን ያለው ኦሊምፒክ ሊጀመር ቀናቶች ሲቀሩት ነው። ስለ ውድድር የሚያውቅ፣ ለአንድ ተወዳዳሪ ስነ ልቦና ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ የሚረዳና ሮጦ ያሳለፈው ገዛሃኝ አበራ ስለ አቅም ማነስ ሲናገር እሱስ? ማራቶን ከመሮጡ ውጪ የት ሄዶ የገነባው አቅም ነው ያለው? የአቅሙ ጉዳይ ለጊዜው ይቁምና ለምንድን ነው ኦሊምፒክ ሲደርስ እየጠበቀ “የኢትዮጵያ ህዝብ ፍረድ” እያለ የሚጮኸው? ምንድን ነው ፍላጎቱ? ዕውነት የአቅም ችግር ካሳሰበው “እኔ አቅም የለኝም ብሎ መልቀቂያ በማስገባት ለምን ቀድሞ ምሳሌ አይሆንም? ነገሩ ሌላ ነው። ማን እንደሚጋልበው ይታወቃል” የሚሉት ወገኖች ገዛኸኝ አበራ ፓሪስ ደርሶም የሰጠው መረጃ ስህተት ስለመሆኑ ያነሳሉ።

” ከኢትዮጵያ ህዝብ የሞራል ካሳ እጠብቃለሁ ” ይላል ገዛኸኝ አበራ ከፓሪስ። አክሎም “ህብረተሰቡ በቃ ሊል ይገባል” ሲል ይጣራል። ገዛኸኝ አበራ በዚህ አያበቃም። ” ከሀገሬ ህዝብ ከፍተኛ የሞራል ካሳ እፈልጋለሁ ፣ የኔ የሞራል ካሳ ደግሞ ህዝቡን ከእውነት ጋር ቆሞ የደረሰብኝን የተቀነባበረ ተንኮል እንዲቃወምና ለአትሌቶቻችን ፍትህ እንዲሰጥ ሲያደረግ ነው” በሚል ህዝብ ፌዴሬሽኑ ላይ በተለይም ስሟን ጠቅሶ አስቀድሞ በብቃት ስም ሲያወግዛት የነበረችውን ደራቱን ” አውርዱ” ይላል።

ይህን ለማለት መነሻው ፓሪስ ሲደርስ ስታዲዮም መግቢያ ፈቃድ ስላልተሰጠው ነው። “ገዛኸኝ አበራ የፌዴሬሽኑ ምክትል ሆኖ ሳለ ይህ ሊሆን አይገባም። ክብረ ነክም ነው” በሚል ላቀረብነው ጥያቄ ከፓሪስ ያገኘነው ምላሽ ” የሚመጣበትን ቀን ሲቀያይር ስለነበር ሲስተሙ ራሱ ነው ስሙን ያነሳው። በሚቀጥለው ቀን ግን ተስተካክሎለታል። ደራርቱ ቱሉ ራሷ ነች የተቀበለችው። የጉዞ ሰሌዳውን በመቀያየሩ ሳቢያ የተፈጠረ ክፍተትን ህዝብ ዛንድ ወስዶ የዓላማ ማስፈጸሚያ ማድረግ ነውር ነው። ዓላማው አስቀድሞ እንደተባለው የመፈንቅለ ደራርቱ ጥሪ ነው”

” ከሀገሬ ህዝብ ከፍተኛ የሞራል ካሳ እፈልጋለሁ ፣ የኔ የሞራል ካሳ ደግሞ የህዝቡን ከእውነት ጋር ቆሞ የደረሰብኝን የተቀነባበረ ተንኮል እንዲቃወምና ለአትሌቶቻችን ፍትህ እንዲሰጥ ሲያደረግ ነው ”  ሲል ጥሪ ያሰማው ገዣኸኝ አበራ እነ መሰረት ደፋርና ቤተሰቦቿን በማሰባሰብ ደራቱ ቱሉ በዚህ መልኩ ነበር የተቀበለችው።

” አትሌቲክሳችን መጫወቻ መሆን የለበትም ህብረተሰቡም በቃ ሊል ይገባል ይሄ ነው የኔ ትክክለኛ ካሳ” ያለው ገዛኸኝ አበራ ቀደም ሲል ሲናገር የነበርውና ሌሎችም አሳቡን እንዲያጎለብቱት የተደረገው የመፈንቅለ ደራርቱ ጥሪ ከኦሊምፒክ መልስ ግልጥልጥ እንደሚል ጉዳዩን የሚከታተሉ እየጠቆሙ ነው።

ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ራሱን ሲያገል ምክትል የነበረቺው ደራርቱ ደጋግም አማላጅ መላኳን፣ ወንበሩን እንደማትረከብና ቦታው ለይሃሌ አግባብነት ያለው እንደሆነ ደጋግማ መግለጿን፣ ሃይሌን ጥይቆ ወይም ሁለቱንም አስቀምጦ ምላሻቸውን የሚያሰማ ቀና አሳቢ ሚዲያ ካለ እውነቱን መረዳት እንደሚቻል የጠቀሱት ክፍሎች፣ ሚዲያው ረግቶ እንዲያጤን መክረዋል። ስምና ዝናን ላይ በመንተራስ የሚረጩ መረጃዎች ውሎ ሲያድር ሌላም ጣጣ ሊያስከትሉ ስለሚችሉ እንዲታሰብበት አሳስበዋል።

የባህል እና ስፖርት ሚንስትር ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በወቅታዊ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሁነት ላይ ለትሪቡን ስፖርት የራድዮ ፕሮግራም በላኩት መልዕክት ” የአትሌቲክስ ውጤታማነታችን በአደገኛ ቀውስ ላይ ነው ” ማለታቸው ተሰምቷል። ስጋታቸው መልካምና የሚደገፍ ቢሆንም ይህ የታያቸው ፓሪስ ውድድር ሲጀመር ነው ወይ? “ድንቄም የስፖርት መሪ የሚያሰኝ” ሲሉ የወቀሷቸው እሳቸውንም የዚሁ የዘመቻው ተሰላፊ አድርገዋቸዋል።

ፕፕፕፕፕፕፕፕፕ

አምባሳደሩ በመልዕክታቸው ” የኦሎምፒክ ተሳትፎ ሆነ የአትሌቲክስ ውጤታማነታችን በአደገኛ ቀውስ እና የመንገዳገድ ጎዳና ላይ ነው ፣ ችግራችን ፈርጀ ብዙ ቢሆንም በግልፅ መነጋገር እና ተጠያቂነት ማረጋገጥ መቻል አለብን ” በመርህ ደረጃ የሚደገፍ ቢሆንም፣ ንግግራቸው ወቅቱን ያላገናዘበ ነው። “ገርሞናል” ሲሉ ሚኒስትሩ የዋሉበትን ሰፈር ገልጸው የተቹ “ግምገማም ቢሆን ከውድድሩ በሁዋላና አስቀድሞ እንጂ በውድድር ላይ የሚከናወን ባለመሆኑ ሚኒስትሩ እርማት ሊወስዱ ይገባል። አምባሳደርም አይመስሉም” ሲሉ የደቦው ዘመቻ አካል መሆናቸውን አመላክተዋል።

ከሁሉም በላይ የስፖርት ፌዴሬሽኖ ሉዓላዊ መሆናቸው እየታወቀ “መንግስት ይህን ተግባራዊ ለማድረግ በግልፅ ስራዎችን በመስራት ላይ ነው” ሲሉ መንግስት በቀጥታ ጣልቃ ለመግባት መዘጋጀቱን ማስታወቃቸው አስድንጋጭ ሆኗል። ንግግራቸው የመንግስት አቋም መሆኑ ቢያጠራጥርም ሚንስትር ዴኤታው ለራድዮ ጣቢያው ላኩት የተባለው መልዕክት በጥቅሉ ጥሬ መሆኑን እነዚሁ ወገኖች ተናግረዋል።

ተቺዎቹና አካሄዱን በመረጃ አግኝተነዋል የሚሉት ወገኖች እንደሚሉት የአገሪቱ ስፖርት በበርካታ ችግሮች የተተበተበ በመሆኑ መንግስት በተለይም እሳቸው ብዙ ስራ እንደሚጠብቀባቸው አይክዱም። ነገር ግን በደፈና ” ጀብደኛ ፣ አምባገነን ፣ ሴሬኛ እና ክፉ ሰዎች ስፖርታችንን በግል ንብረት ( እንደ አክስዮን ማህበር ) ጠፍረው ይዘው እያሰቃዩት ይገኛሉ ብሎ ወቅቱን ያልጠበቀ መረጃ መርጨት ፋይዳ የለውም።

ይህን መረጃ ቆጥበው የሰጡ ወገኖች እንዳሉት ደራርቱ ቱሉ ጥፋት ልትሰራና ልትሳሳት ትችላለች። ሰው በመሆኗ የመሳሳት መብትም አላት። ካበዛችውና ስህተቷ ከአቅም በላይ ከሆነ በየሚዲያው መጮህ ሳይሆን ሰክኖ መወያየት ግድ ነው። በውይይትና በመረጃ መግባባት ካልተቻለ በሰነድ አስደግፎ ከአንድም ሁለትና ሶስቴ ማሳሰቢያ መላክ፣ በስብሰባ ቃለ ጉቤዎች ላይ ልዩነትን ማስመዘገብ፣ ይህ የማይሆን ሲሆን ውድድር ሲደርስ ውጤቱ ለማጠልሸት በየሚዲያው ወሬ ከመርጨት አስቀድሞ በአደባባይ ማፍረጥረጥ አግባብ ያለው አካሄድ ነው። ኦሊምፒክ ኮሚቴንም ቢሆን በተመሳሳይ መክሰስ ሲቻል “መንግስት ጣልቅ ይግባ፣ መነግስት ጣልቅ ይገባል” በሚል የጅል አካሄድ መከተል እንደማይጠቅም እነዚሁ ወገኖች ገልጸዋል።

ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቀጥታ ደብዳቤ ለመጻፍ እንደተዘጋጁ የሚያወሱት እነዚ ወገኖች ለጊዜው ፓሪስ ላሉት የኢትዮጵያ አምባሳደሮች መልካም ውጤት ተመኝተዋል።

ዝግጅት ክፍላችን ይህንኑ ደብዳቤና መፈንቀለ ደራርቱ ቱሉን የሚመሩትን ወገኖች አካሄድና ቡድን ሙሉ በሙሉ የሚገልጽ ጽሁፍ ከውድድር ፋጻሜ በሁዋላ ይፋ እንደሚያደርግ ከወዲሁ ይገልጻል።

ማሳሰቢያ – አስተያየት ሰጪ ወገኖች በምርጫ፣ በአሰራር፣ በዝግጅት ወይም በአጠቃላይ ፌዴሬሽኑ እንዲሁም አመራሮቹ ችግር ወይም ግድፈት የላቸውም የሚል መከራከሪያ ያቀርቡም። ዓላማቸውም እሱ አይደለም። አሁን ከሚሰራጩት ስጋና ደም የተላበሱ የስልጣን ሽኩቻ አጀንዳ በላይ የሰከነና አገርን ሊጠቅም የሚችል ማሳሰቢያ ከአማራጭ መፍትሄ ጋር እንደሚያቀርቡ ጠቅሰዋል።

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
At least 32 killed in al-Shabab beach attack in Somalia’s capital Mogadishu
ሴት አትሌቶች በ800 ሜትር ፍጻሜ ደረሱ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 2025
TIPS 1

Almost a third of people in Gaza not eating for days, UN food programme warns

July 26, 2025
TIPS 1

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios

July 20, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2