Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  TIPS 1  ታምራት ቶላ – ኢትዮጵያዊያንን ፈወሰ!!  ኢትዮጵያ በልጇ ኮራች
TIPS 1

ታምራት ቶላ – ኢትዮጵያዊያንን ፈወሰ!!  ኢትዮጵያ በልጇ ኮራች

Ethioreview newsEthioreview news—August 10, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

አሁን የራቀው ደስታ ተመልሷል፣ የተከፋው ልብ ተጠግኗል፣ ያቺ ኀያል ሠንደቅ በዓለሙ ፊት ከፍ ብላለች፣ እንደ ወትሮው ሁሉ ከፊት ቀድማለች፣ የሚመጥናትን ቦታ ይዛለች፤  አሁን ሌሎቹን እያስከተለች በድል ታይታለች፣ የደከመው ጉልበት ተቀስቅሷል፣ ምን ነካው የተባለው ወኔ ተነስቷል፤ የተኛው አንበሳ ተቆጥቷል፡፡

ኢትዮጵያ በልጇ ኮርታለች፣ በልጇ ደስ ተሰኝታለች፣ በፓሪስ ሰማይ ሥር  ልጆቼን ምን ነካቸው፣ ወኔያቸውን ማን ወሰደባቸው፣ ጀግንነታቸውንስ ማን ነጠቃቸው እያለች የቆዘመችው፣ ምን ኾኑ እያለች የተከዘችው ኢትዮጵያ ጀግና ልጇ ሠንደቋን አስቀድሞ ሲገባ ተመልክታለች፤ ለክብሯ በጀግንነት ላቡን ሲያፈስስ አይታለችና ከቁዘማ ነቅታለች፣ ወደ ደስታም ተመልሳለች፡፡



የሠንደቃቸውን ከፍ ማለት፣ በጀግንነት ተነስቶ በድል መግባት የሚመኙ ኢትዮጵያውያን ከተከዙበት ተነስተዋል፤ በደስታ ተሞልተዋል፤ በደስታ ባሕር ውስጥ ገብተዋል፤ ስለ ምን ቢሉ አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ሠንደቃቸው ደምቃለች፣ ከፍ ብላለች፣ በድል ቀድማለችና፡፡ የራቀ ደስታ መላሽ፣ የተኛ አንበሳ ቀስቃሽ ልጅ አግኝተዋልና በደስታ ተሞልተዋል፡፡

ድል የለመደችው፣ በድል የኖረችው፣ በዓለም አደባባይ መቅደምን ታሪክ እና ባሕል ያደረገችው ኢትዮጵያ በ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ እንደቀድሞው ሁሉ ድል አላገኘችም፣ በምትታወቅበት ታሪክ አልደመቀችምና ኢትዮጵያውያን ተከፍተው ሰንብተዋል፤ ዘወትር ከፊት የምትገኘው ሠንደቃቸውን ፈልገዋል፤ አልሸነፍም የሚሉ እልኸኛ እና ሞገደኛ ልጆቻቸውን የት ገባችሁ? ምንስ ኾናችሁ? እያሉ ተጨንቀዋል፡፡  በዓለም አደባባይ አረንጓዴ ጎርፍን ሲያዩ የኖሩት፣ የድል ዜማ ማዜም የሚያውቁት ኢትዮጵያውያን ስለምን አይጭነቃቸው? ስለ ምንስ አይከፋቸው? ስለ ምንስ አያሳስባቸው? ለጀግና ከድል ውጭ ሌላ አይገባውምና፡፡

ዛሬ ግን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩዋ ሠንደቅ በፓሪስ ደምቃለች፡፡ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን የሰጡትን አደራ የተሸከመው፣ የኢትዮጵያውያንን ጭንቀት እና ጉጉት በልቡ የያዘው ታምራት ቶላ 42 ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጦ  ሠንደቋን ከሁሉ አስቀድሟልና፡፡

በፓሪስ ሰማይ ሥር እንደ ወትሮው በድል ያልደመቀችው ኢትዮጵያን ወደ ድል መልሷታል፡፡ በክብር ዙፋኗ ላይ አስቀምጧታል፡፡ አሁን ያለፉ ብስጭቶችን እና ሀዘኖቹን በደስታ ቀይሯቸዋል፡፡ ከምንጊዜውም ምርጡ አትሌት ቀኒነሳ በቀለ እና  ዴሬሳ ገለታ ጋር ሀገሩን የወከለው ታምራት ቶላ ለአዘነች ሀገር የደስታ በረከት ሰጥቷታል፡፡ ታምራት የፓሪስ ጎዳናዎችን በጀግንነት አቆራርጦ ኢትዮጵያን በዓለሙ ፊት ቀዳሚ አድርጓታል፡፡ አሁን ወሬዎች ሁሉ ስለ እርሱ እንዲኾኑ አድርጓል፤ አሁን ከጀግና ሀገር የመጣ፣ የጀግኖችን አደራ የተሸከመ፣ ጀግና መኾኑን አስመስክሯል፡፡

በሮም፣ በአቴንስ ፣ በቶኪዮ እና በሌሎች የዓለም ታላላቅ ከተሞች የደመቀችው ኢትዮጵያን ዛሬም በፓሪስ አድምቋታል፡፡ ከድሉ በኋላ የዓለም አትሌቲክስ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ “ ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ በኦሎምፒክ ታሪክ እጅግ አስቸጋሪ በኾነው የማራቶን ውድድር የኦሎምፒክ ክብረ ወሰንን ሰበረ” ብሏል፡፡

ታምራት ቶላ ከ24 ዓመታት ጥበቃ በኋላ የማራቶን ወርቅን ወደ ኢትዮጵያ አምጥቷል ይላል የዓለም አትሌቲክስ፡፡  በኦሎፒክ አዲስ ታሪክ ያስመዘገበው ኢትዮጵያዊው ጀግና 2፡06፡26 የገባበት ሰዓት ነው፡፡ ከፍታ እና ዝቅታ በበዛበት የፓሪስ ማራቶን የታላቅ ሀገር ታላቅ አደራ ይዞ የሮጠው ታምራት ቶላ አደራውን ከአዲስ ታሪክ ጋር ተወጥቷል፡፡

ቢቢሲ በዘገባው ኢትዮጵያዊው ታምራት ቶላ በ2008 ዓ.ም በኬኒያዊው አትሌት ሳሙኤል ዋንጂሩ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን መስበሩን አመላክቷል፡፡ እ.አ.አ. በ2022 የዓለም ሻምፒዮን የኾነው ታምራት ቶላ ወደ ማራቶን የገባው ከሁለት ሳምንት በፊት ኢትዮጵያዊው የቡድን አጋሩ ሲሳይ ለማ ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ነበር ይላል ቢቢሲ በዘገባው፡፡ ግማሽ ማራቶኑን ከሌሎቹ ተነጥሎ የሮጠው ታምራት ቶላ የአስደናቂ ድል ባለቤት ኾኗል፡፡

ሮይተርስ ደግሞ አዲስ ክብረ ወሰን በመጻፍ ያሸነፈው ታምራት ቶላ በፓሪስ ኦሎምፒክ ለሀገሩ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝቷል ብሏል፡፡  ሱፐር ስፖርትም ታምራት ቶላ ከኦሎምፒክ ክብረ ወሰን ጋር ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቱን ዘግቧል፡፡ 

ከድሉ በኋላ  የኢትዮጵያ መሪዎችን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን እየገለጹ ነው፡፡  ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ከድሉ በኋላ ደስታቸውን ሲገልጹ”ታምራት ቶላ ለሕዝባችን የሚገባውን ደስታ እና ኩራት አመጣህለት፤  የዛሬው ድል ልዩ ትርጉም አለው፤ ፈጣሪ ይባርክህ”  ብለዋል፡፡   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ደግሞ “በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ በማራቶን ውድድር ላይ ወርቅ በማግኘት ሠንደቅ አላማችንን በድጋሚ ከፍ አድርጓል” በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

ታምራት ያመጣው ድል ከሩጫ ባሻገር ነው፣ ይህ ድል ክብር፣ አደራ፣ ታሪክ ነውና፤ የራቀች ደስታን መልሰሀል፣ የቆየ ታሪክ አስቀጥለሀል፣ አዲስ ታሪክም ጽፈሀል እና ክብር ይገባሀል፡፡
Via (አሚኮ)

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
AliExpress is set to enter Ethiopia
ገዱን በዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ ትህነጎች በአቋም ተለያዩ” የወልቃይት ውለታ አለብን”
Related posts
  • Related posts
  • More from author
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 2025
TIPS 1

Almost a third of people in Gaza not eating for days, UN food programme warns

July 26, 2025
TIPS 1

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios

July 20, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2