Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  ECONOMY  ”የውጭ የምንዛሬ ቢሮዎች ሲከፈቱ ሕጋዊ ሥርዓት ያለውና ቀልጣፋ አገልግሎት ይኖራል” ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ
ECONOMY

”የውጭ የምንዛሬ ቢሮዎች ሲከፈቱ ሕጋዊ ሥርዓት ያለውና ቀልጣፋ አገልግሎት ይኖራል” ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ

Ethioreview newsEthioreview news—August 20, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የሚፈጥራቸው የግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ እና የጥቁር ገበያን ወደ ሕጋዊ ሥርዓት ለማምጣት የሚያግዝ መኾኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸ (ዶ.ር) ይገልጻሉ።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ሐምሌ 21/2016 ዓ.ም ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ማግስት ጀምሮ በሁሉም ባንኮች ተግባራዊ የምንዛሬ ለውጥ ተደርጓል።

ማሻሻያውን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ከዚህ በፊት ያልነበሩ በአዲስ የሚፈጠሩ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች የሚከፈቱ መኾናቸው ነው።  

ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ዳይሬክቲቭ መሠረት የምንዛሬ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ባንኮች እና ባንክ ያልኾኑ በአዲስ የሚቋቋሙ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ናቸው።

አዲስ የሚከፈቱት ተቋማት የምንዛሬ አገልግሎት ላይ ብቻ ተሰማርተው ይሠራሉ። ኾኖም ቢሮዎቹን ከፍቶ ለመንቀሳቀስ የተቀመጡ መስፈርቶችን ማሟላት እንደሚገባም የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ዳይሬክቲቭ ያስረዳል።

ከመስፈርቶች መካከል ቢሮውን ለመክፈት የሚቀርቡ አመልካቾች በሀገር ውስጥም ኾነ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የሌላ ሀገር ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሊኾኑ እንደሚገባ ይገልጻል።

ሌላው ደግሞ ቢያንስ 15 ሚሊዮን ብር ካፒታል እና በጊዜ ገደብ በዝግ የሚቀመጥ 30 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል። በተጨማሪም የሚከፈቱ ቢሮዎች የሚኖራቸው የደኅንነት ጉዳይንም ከመስፈርቶች ውስጥ እናገኛቸዋለን።

ቀልጣፋ አገልግሎትን ከመስጠት፣ የጥቁር ገበያን ከማስቀረት እና ኢትዮጵያ በቂ የምንዛሬ መጠን  እንድታገኝ ከማደረግ አንፃር አዲስ ይከፈታሉ የተባሉት የምንዛሬ ቢሮዎች የሚኖራቸውን ፋይዳ በተመለከተ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ቆስጠንጢኖስ በርኸ (ዶ.ር) ምን ይላሉ?

ሰዎች ከብዙ የዓለማችን ክፍሎች ሲመጡ ወይም ሲሄዱ ለተለያዩ አገልግሎቶች ምንዛሬን ሲፈልጉ በቀላሉ ማግኘት የሚችሉበት መንገድ መኖር እንዳለበት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸ ይገልጻሉ።  በተመሳሳይ ለጉብኝት እና ለተለያየ ዓላማ ወደ ሀገር የሚገቡ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች እና ዲያስፖራዎች በትላልቅ የገበያ ማዕከላት አካባቢ የምንዛሬ ችግር ሳይገጥማቸው በቅርብ የሚፈልጉትን ምንዛሬ ለማግኘት አማራጮች ቢኖሩ ቆይታን እና እርካታን ከመጨመር ባለፈ ምጣኔ ሃብታዊ ጠቀሜታም ይኖረዋል። 

እነዚህን እና ሌሎችንም ተግባራት ለማከናውን ታዲያ አዲስ ይከፈታሉ የተባሉ የምንዛሬ ቢሮዎች ተግባራዊ መኾን ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ዶክተር ቆስጠንጠኖስ በርኸ ጠቁመዋል።

እንደ ምጣኔ ሃብት ባለሙያው ገለጻ የምንዛሬ ቢሮዎች መከፈት ተቋማቱ በምንዛሬ ላይ ብቻ ስለሚሰማሩ የተለያዩ ሀገራትን ገንዘብ የማቅረብ ዕድልን ከማስፋት ባለፈ ሕጋዊ የምንዛሬ ተቋማት ሲከፈቱ በቀላሉ ሄዶ ለመመንዘር አመቺ ስለሚኾን የጥቁር ገበያን በማዳከም ለማጥፋትም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።

አሁን ላይ በጥቁር ገበያ እና በባንኮች መካከል ያለው የምንዛሬ መጠን የተቀራረበ በመኾኑ ጥቁር ገበያ ላይ የተሰማሩ አካላት ወደ ሕጋዊ አሠራር እንዲገቡ የሚያበረታታ እና ተቋማቱ ሲከፈቱ ደግሞ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥሩ መኾኑን ባለሙያው ተናግረዋል።

በአዲሱ የምንዛሬ አሠራር ማሻሻያ ባንኮች የሚኖራቸው የዶላር መጠን ከፍ ስለሚል የጥቁር ገበያ በራሱ ጊዜ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት እንዲመጣ እና እንዲጠፋ የሚያስገድድ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋልም ሲሉ አክለዋል።

የምጣኔ ሃብት ባለሙያው በአህጉራችን አፍሪካ ናይጄሪያ እና ኬንያ 30 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ከዳያስፖራ ቢያገኙም ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት 800 ሚሊዮን ዶላር ብቻ አግኝታለች በማለት የዓለም ባንክ መረጃን ዋቢ አድርገው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸ ተናግረዋል።

በጥቁር ገበያ ወደ ሀገራችን የሚገባውን የውጭ ሀገር ገንዘብ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት ማምጣት ከተቻለ ኢትዮጵያ ከ12 እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር በየዓመቱ ማግኘት እንደምትችል እና እዳዋን በጥቂት ዓመታት ውስጥ መመለስ እንደሚያስችላት አስረድተዋል።

ከባንኮች ተጨማሪ የምንዛሬ ቢሮዎች ሲከፈቱ እና ከዲያስፖራ የሚገኘው የውጭ ሀገር ገንዘብ በሕጋዊ መንገድ ሲመነዘር በቂ ዶላር ይገኛል።

የጥቁር ገበያ የተፈጠረበት ዋነኛ ምክንያት የምንዛሬ እጥረትን ተከትሎ በመኾኑ በባንኮች እና በሚከፈቱ ተቋማት የሚገኘው የምንዛሬ መጠን ከፍ ሲል ጥቁር ገበያ የማይጠፋበት ምክንያት አይኖርም ሲሉም ገልጸዋል።

አሚኮ

ECONOMY
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ተደራጅተው የመሬት ወረራ ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ ተያዙ
ኢሠማኮ ለግል ድርጅቶች ሠራተኞችም ማስተካከያ የሚደረግበት አቅጣጫ እንዲሰጥ ጥያቄ አቀረበ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
ECONOMY

ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

March 29, 2026
ECONOMY

“የስምምነቶች ሁሉ እናት” ህንድ እና የአውሮፓ ህብረትታሪካዊ የንግድ ስምምነት አደረጉ

January 27, 2026
ECONOMY

በኢትዮያ ከ21 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ በርላይ የጋዝ ክምችት ተገኘ

October 30, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2