Skip to content
  Saturday 16 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    የሠሜኑን ጦርነት ተከትሎ ወንጀሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ሥራ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን ተከትሎ እየተከናወነነው

    June 1, 2022

    በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

    February 1, 2021

    በተዓምር የተረፈች ህይወት ህያው ምስክርነት – ‘አትሙቺ ያላት ነፍስ

    December 14, 2021

    የአጥንት ህመም መነሻ መንስኤዎችና መፍትሄው

    August 20, 2024

    ሞዐ ተዋሕዶ ምንድን ነው? [ሞነግ] “ነጻ አውጪ ግምባር” ወይስ ?

    August 13, 2025
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE
VOE
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE
  TIPS 1  በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተሰማሩ የ49 ኤጀንሲ ባለቤቶች ታሰሩ
TIPS 1

በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተሰማሩ የ49 ኤጀንሲ ባለቤቶች ታሰሩ

Ethioreview newsEthioreview news—September 6, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail


የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት  – በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተሰማሩ የ49  ኤጀንሲዎች ባለቤቶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መረጃ እንዳስታወቀው፤ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን አስመልክቶ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ወንጀሉን በመፈፀም ላይ የሚገኙ አካላትንና የትስስር ሰንሰለታቸውን ለመለየት ሰፊ ጥናትና ክትትልና ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ጥናቱንና ክትትሉን መነሻ በማድረግ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በተከናወነው ስምሪት በድርጊቱ ሲሳተፉ ተደርሶባቸው የተጠረጠሩ የ49 ኤጀንሲዎች ባለቤቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

እንደ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መረጃ፤ መንግሥት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስቀረት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ስምምነቶችን በመፈራረም ዜጎች ጥቅማቸው ሳይጓደልና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ውጭ ለሥራ እንዲሰማሩ የሚያስችል ሕጋዊ አሠራር ዘርግቷል፡፡ ይህን የሥራ ስምሪት የሚመራ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከማቋቋም በተጨማሪ ሕጋዊ ስርዓትን የሚያሳልጥ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ በማድረግ፤  ከ1ሺ ሁለት መቶ ለሚበልጡ ኤጀንሲዎች ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ 

ይሁንና በሕጋዊነት ሽፋን በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ላይ የተሰማሩ ኤጀንሲዎች መኖራቸው በጥናት መረጋገጡን መረጃው ጠቁሟል፡፡ በዚህም ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር  ጋር በተያያዘ በተከናወነው ሰፊ ጥናት  ከነሐሴ 2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም ባሉት 11 ወራት ውስጥ ብቻ 15 ሺ ዜጎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ከሀገር መውጣታቸው ተረጋግጧል፡፡ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ ደላላዎች በዚህ የወንጀል ትስስር ውስጥ ተሳትፎ እንዳላቸው በጥናቱ የተለየ ሲሆን፤   በጥቅም ትሥሥር የሚሰጥ  የቱሪስትና የሥራ ቪዛ ለድርጊቱ እንደሚውል እንዲሁም በኤምባሲዎች የሚሠሩ ግለሰቦችን ጨምሮ  የተለያዩ አካላት እንደሚሳተፉበትም ተጠቁሟል፡፡

በሁሉም የወንጀሉ ተዋንያን ላይ ሕጋዊ ተጠያቂነትን ለማስፈን ስምሪት እየተከናወነ መሆኑም በመረጃው ተመላክቷል፡፡ በሌሎች ሀገራት የሚንቀሳቀሱ ሕገ-ወጥ ደላሎችንም ከውጭ አጋር አካላት ጋር በተመሠረተው ትብብር አማካኝነት ጭምር ተጠያቂ ለማድረግ እንደሚሠራ ተጠቁሟል፡፡

በሕገ-ወጥ መንገድ የሚከናወኑ የሥራ ስምሪቶች ኢትዮጵያዊያንን ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፤ ለሥነ-ልቦናዊ ጉዳት፤ ለአስገድዶ መደፈር እንዲሁም ለአካል ክፍሎች ስርቆትና ለሞት እየተዳረጉ ይገኛል ያለው መረጃው፤ ሕጋዊ ፈቃዳቸውን ሽፋን በማድረግ በሕገ-ወጥ መንገድ ዜጎች ከሀገር እንዲወጡ የሚደረገው የተቀናጀ የወንጀል ድርጊት ሀገሪቱ ማግኘት የሚገባትን 11 ሚሊዮን ዶላር ማሳጣቱን አመላክቷል፡፡

በመንግሥት መዋቅር የሚሠሩ አንዳንድ ግለሰቦች የጥቅም ትስስር በመፍጠር ለሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀሉ ተባባሪ እንደሚሆኑ ጥናቱን ዋቢ በማድረግ የገለጸው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መረጃ፤ ዜጎች በባሕር፣በየብስና በአየር ተጓጉዘው ወደ ውጭ ሀገራት ካቀኑ በኋላ በአንድ ማዕከል ተጠርንፈው  ከአሠሪዎች ጋር በሚደረግ ድርድር ለሽያጭ እየቀረቡ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

ይህ ከሞራልና ከሕግ ያፈነገጠ ድርጊት የሀገርን ገጽታና መልካም ስም ከማጉደፍ ባሻገር ያልፍልናል ብለው የሚሰደዱ ወጣቶችን እንዲሁም በልጆቻቸው ተስፋ በማድረግ ጥሪታቸውን እየሸጡና እየተበደሩ የሚልኩ ወላጆችን ለከፍተኛ ሰቆቃ እየዳረገ በመሆኑ በተከታታይ በሚከናወኑ ክትትሎች፣ ማጣራቶችና ስምሪቶች በአጥፊዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድም የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ መረጃ አረጋግጧል፡፡ በዚህ መሰሉ ዜጎችን የሚበድልና ሀገርን የሚጎዳ የወንጀል ድርጊት ውስጥ በመሳተፍ ላይ ያሉ አካላት ሁሉ ከብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎትና ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዕይታና ክትትል የተሰወሩ አለመሆናቸውን አውቀው ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በጥብቅ አሳስቧል፡፡

ከሕዝብ አይንና ጆሮ የተሰወረ ምንም ነገር ሊኖር አይችልም ያለው የብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት፤ መላው ኢትዮጵያዊያን ይህን መሰል ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን ለሚመለከታቸው የጸጥታና ደኅንነት አካላት በመጠቆም የድርሻቸውን እንዲወጡም ጠይቋል፡፡

በቀጣይ የሚወሰዱ ተከታታይ እርምጃዎችንም ለኅብረተሰቡ እንደሚያሳውቅ ጠቁሟል፡፡

መንግሥት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስቀረት  የተደራጀ፣ ፈጣን አገልግሎት የሚሰጥ፣ ጥቅምንና መብትን የሚያስከብር ሕጋዊ አሠራር የዘረጋ በመሆኑ ዜጎች በውጭ ሀገራት ለሥራ ስምሪት መጓዝ ሲፈልጉ በተመቻቸው ዕድል መጠቀም አንደሚገባቸው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኃን የላከው መረጃ አመልክቷል፡፡

NEWS
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ ትግበራ መስከረም 1 ሊጀምር ነው
Egypt Exploiting Somalia for Selfish Gains in Nile Dispute, Claims Minister
Related posts
  • Related posts
  • More from author
TIPS 1

WFP Country Director Says Ethiopia Registered Significant Economic Transformation by Focusing on Rural Dev’t, Poverty Reduction

July 28, 2025
TIPS 1

Almost a third of people in Gaza not eating for days, UN food programme warns

July 26, 2025
TIPS 1

Israeli spy chief visits US amid bid to move Palestinians out of Gaza – Axios

July 20, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2