Skip to content
  Sunday 17 May 2026
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • DESIGN
    • All
    • AFRICA
    • ART and CULTURE
    • BUSINESS
    • ECONOMY
    • EDITORIA
    • ENTERTAINMENT
    • ertips
    • Events
    • FEATURED
    • General
    • General
    • HOT
    • law
    • Media tips
    • News
    • News2
    • OPINION
    • POLITICS
    • Reaction
    • SOCIETY
    • SPORT
    • TIPS 1
    • TOP NEWS
    • VIDEO
    • WORLD
    • ማህደር
    • ያበደው

    ታላቁ ህዳሴ ግድብ በመገባደጃ ምዕራፍ ላይ

    April 1, 2023

    የአሊባባ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ለመጀመር የሚያስችል ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ

    August 22, 2024

    ዶናልድ ትራምፕ በቁጥጥር ሥር ውለው በቀረበባቸው ሰላሳ አራት ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ

    April 6, 2023

    የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሰነድ የሌላቸው የኤርትራዊ ስደተኞች መታሰራቸውን ኮነን፤ “ያለ ህጋዊ ማስረጃ የትኛው አገር መኖር ይቻላል?”

    June 4, 2023

    ቻይናዊው የፀሃይ ሪል ስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ ከ9 ግብረ አበሮቻቸው ጋር የውጭ አገር ብሮች በማተምና በጥቁር ገበያ ወንጀል ታስረው ፍ/ቤት ቀረቡ

    September 5, 2023
    Prev Next Showing 1 Of 1493
  • News
    • NEWS 2
  • AFRICA
    • WORLD
  • VIDEO
  • HOT
  • POLITICS
    • INTERVIEW
    • OPINION
    • SOCIETY
    • ENTERTAINMENT
    • ያበደው
    • SPORT
    • ማህደር
      • Travel
      • Social media
      • Stars
      • Technology
      • Tourism
      • Trends
    • Music
      • Movies
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  • Home demo times
  • VOE VIDEO
  • ENGLISH PAGE
  • Home Demo default 2
  • News
VOE - VOICES OF ETHIOPIA
  law  በኮበለሉት ዶ.ር ፍስሐ እሸቱና ባልደረቦቻቸው ላይ የተመሰረተው ተደራራቢ ክስ
law

በኮበለሉት ዶ.ር ፍስሐ እሸቱና ባልደረቦቻቸው ላይ የተመሰረተው ተደራራቢ ክስ

Ethioreview newsEthioreview news—October 15, 2024
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail

ቀደም ሲል በኢህአዴግ ዘመን የዩኒቲ ዩኒቨርስቲን ሸጠው ወደ አሜሪካ የሸሹት ዶክተር ፍስሃ እሸቱ በለውጡ ማግስት ወደ አገር ቤት የመመለስ እድል ካገኙ ዜጎች መካከል አንዱ ናቸው። የንግድ አሳብ በማመንጨት፣ አዲስ ፕሮጀክት በመጀመር ግን ባለመጨርሰ ወይም ገፍቶ ባለመሄድ የሚታወቁት እኚሁ ሰው አዲስ አበባ በገቡ በአጭር ቀን ውስጥ “ፐርፐዝ ብላክ” የሚባል ድርጅት ከፍተው የሚዲያ ቀልብ ስበው ነበር።

መጀመሪያ አሜሪካ እንደገቡ በስድስት ወር የወያኔን መንግስት ለመጣል የሚያችል የሽግግር መንግስት አቋቁማለሁ ብለው የዲያስፖራውን ወኔ ወዘወዙት። በወቅቱ ኢህአዴግ እንኳን ሊወድቅ ወዘወዝ ሊያደርገው የሚችል አንዳችም ነገር ባልነበረበት ወቅት እሸቱ ተነስተው በሸንጎ እንደሚያስወግዱት ሲናገሩ አጨብጫቢው ብዙ ነበር።

ቆም ብሎ መጠየቅ የማይችለውና የተሰጠውን በመጋት የሚታወቀው ዴያስፖራ አዳራሽ እየሞላ አጨበጨበ። እሸቱ ቀስ በቀስ ሞቅታቸው ለቀቃቸውና በዛው ጠፉ። ኢህአዴግ ውስጥ የተነሱ የውስጡ አርበኞች ለውጡን በየአቅጣጫው ኔት ወርክ መስርተው እውን ሲያደርጉት፣ እሸቱ “ብላክ ፐርፐዝ” የሚባል አስደንጋጭና አስገራሚ ስያሜ መርጠው አዲስ አበባ ከች አሉ።

ከዕርሻ ግብአት ጅመሮ በአስገራሚ ዋጋ የቤት ባለቤት የሚያድርግ አዋጅ ይዘው የተነሱት ዶክተር ፍስሃ መጀመሪያው ላይ አሳባቸውን የሚያደንቁ ጎረፉላቸው። በሚሊዮኖች ሰበሰቡ። ከጅምሩ ” መጀመር እንጂ መጨረስ መች ያውቁበታል” በሚል ስጋታቸውን የገለጹ ነበሩ። እያደር ይህ አሳብ ገዢ እየሆነ ሲመጣ በሚዲያ መዋከብና መሞገት የዕለት ተዕለት ስራቸው ሆነ።

More stories

ሿሿ – ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 25 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

May 20, 2023

አሸባሪ ቡድኑ በአማራና በአፋር የፈጸማቸውን ወንጀሎች የሚያጣራ ግብረ ኃይል ሥራውን ጀመረ

December 27, 2021

በአደገኛ ዕፅ ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች ከ2 ዓመት እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ

October 24, 2024

የሃጫሉ ገዳዮች የተባሉት ” ጥፋተኛ” ተባሉ

July 5, 2021

የብላክ ፐርፐዝ የማስታወቂያ አዋጅ ሚዲያውን ከማነቃነቅ አልፎ የተኛውን መንግስት ቀሰቀሰ። እሳቸውም አደባባይ እየወጡ በአንድ ሚሊዮን ብር የተንጣለለ ቤት እንደሚያስረክቡ መናገራቸውን ገፉበት። ነገሩ እየከረረ ሄዶ አንዳንድ ህጋዊ እርምጃዎች ሲወሰዱ ” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እርስዎን አምኜ ነው ወደ አገር ቤት የገባሁት ጩኸቱን ዝም አሰኙልኝ” ዓይነት ጥሪ አሰምተው፣ ሲነጋ እንደወትሮው አሜሪካ ተገኙ። እሳቸው በሌሉበት፣ ባልደረቦቻቸው ተያዘው ክስ ተመሰረተባቸው። ክሱ ይህን ይመስላል።

የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ የፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱን (ዶ/ር) ጨምሮ በ10 ግለሰቦችና ሁለት ድርጅቶች ላይ ክስ መስርቷል። ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹ
1ኛ የፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቦርድ አባልና ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሽቱ (ዶ/ር)፣
2ኛ የተቋሙ ም/ስራ አስፈጻሚ ኤርሚያስ ብርሃኑ (ዶ/ር)፣
3ኛ የተቋሙ ቺፍ  ኦፕሬሽን ኦፊሰር እና የቦርድ አባል ወ/ሮ ኤፍራታን ነጋሽን ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ግለሰቦች እንዲሁም ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ እና ኖትር ዲዛይን ሃ/የተ/የግ/ማህበር ናቸው፡፡

  • በአዲስ አበባ ከተማ መሃል ሜክሲኮ ላይ በ100 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ  ባለ 3 መኝታ ቤት መኖሪያ ቤት በ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚሸጥ መሆኑን በሚዲያ በማስተዋወቅ ሰዎች ቤት ለመግዛት ሲሄዱ “መጀመሪያ ገንዘቡን አስገቡና ውሉን ትመለከታላችሁ ” በማለት ከሌሎች ግብረዓበሮቻቸው ጋር በመሆን አሳሳች ቃላቶችን በመጠቀም፣
  • ሰዎች ገንዘቡን ካስገቡ በኋላ ደግሞ የአክሲዮን ግዢ ውል እንዲፈርሙ በማድረግ ምንም አይነት የግንባታ ቦታ ባልተረከቡበት ሁኔታ 2 ቢሊየን 234 ሚሊየን 200 ሺህ ብር በመሰብሰብ፣
  • ቤቱን ሰርተው ሳያስረክቡ በመቅረት
  • ግማሹን ገንዘብ ወደ ውጭ እንዲሸሽ በማድረግ፣
  • ኮሚሽን በመቀበልና በማታለል  ወንጀል ተጠርጥረው በአዲስ አበባ ፖሊስ በኩል በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ሲከናወን ነበር።

በዚህ መልኩ ፖሊስ ሲያከናውነው የቆየው የምርመራ ማጣሪያ ሥራ መጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ዐቃቤ ሕግ ተደራራቢ ዝርዝር ክሶችን በየደረጃቸው  አቅርቦባቸዋል።

ከቀረቡ ክሶች መካከል በአንደኛው ክስ ላይ ከ1ኛ – 9ኛ ባሉ ተከሳሾች ላይ እንደተመላከተው በኢፌዲሪ የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) እና (ለ) እንዲሁም  የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 32 (2) ላይ የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፍ የሚል ክስ ይገኝበታል።

እንደ አጠቃላይ በቀረበው ተደራራቢ ክስ ዝርዝር ችሎት ለቀረቡ 4 ተከሳሾች ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን የተከሳሾቹ ጠበቆች በደንበኞቻቸው ላይ የቀረበውን ክስ ዝርዝር ተመልክተው ዋስትና ላይ ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም ዋስትና ላይ የሚደረገውን የግራ ቀኝ ክርክር ለመከታተል ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ተዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ችሎት ያልቀረቡ ተከሳሾችን ፖሊስ በአድራሻቸው አፈላልጎ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ መስጠቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል። ፍስሕ እሸቱ (ዶ/ር) ኮብልለው አሜሪካ መግባታቸው ይታወሳል።

law
FacebookX TwitterPinterestLinkedInTumblrRedditVKWhatsAppEmail
ነጩ ወርቅ በወቅቱ እንዲሠበሠብ ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠየቀ
የአፍሪካ ሕብረት – ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላላት ተሳትፎ እውቅና ሰጠ
Related posts
  • Related posts
  • More from author
law

ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል የፈጸሙ 123 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሒሳብ ታገደ

September 20, 2025
law

እነ ቀሲስ በላይ በሙስና ወንጀል ሊፈርድባቸው እንደማይገባ ጠቅሰው ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ ሆነ

July 26, 2025
law

የአዲስ አበባ የከንቲባ ፅ.ቤት ፕሮቶኮልን ጨምሮ 12 ተከሳሾች በሌብነት ተከሰው ተፈረደባቸው

July 23, 2025
Load more
Read also
News

ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር?

April 26, 2026
WORLD

ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት

April 26, 2026
News

“ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ

April 26, 2026
WORLD

አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው

April 26, 2026
WORLD

የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች

April 26, 2026
WORLD

የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና?

April 26, 2026
Load more
Recent Posts
  • ፖሊስ “ቴዎድሮስ በሚስቱ ሚዲያ ለምን ቤቱ ቅጭ ብሎ መግለጫ አይሰጥም ነበር? April 26, 2026
  • ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ሂልቶን፤ ሶስት ቀን የተደበቀው “ትኩላ” ዝርዝር ሪፖርት April 26, 2026
  • “ኢሳያስ ከአሜሪካ ወዳጅነትን ይፈራሉ፤ ግንቡ ይፈርስባቸዋል” ቲቦር ናጊ April 26, 2026
  • አውሮፓ ህብረት የጋራ መከላከያ ለማቋቋም የስምምነት ረቂቅ ሊያዘጋጅ ነው April 26, 2026
  • የኢልሀን ኦማር የ30 ሚሊዮን ዶላር የሀብት መዝገብ እየተመረመረ ነው “የሂሳብ ስህተት ነው” ብላለች April 26, 2026
  • የፔትሮ-ዶላር ግርዶሽ! ወደ ዘመን ዩዋና? April 26, 2026
  • ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግል አምባሳደር April 13, 2026
  • Iran reneges on key point of ceasefire amid allegations of broken promises   April 8, 2026
  • Erdogan warns of ‘sabotage’ in Iran ceasefire during Trump call April 8, 2026
  • እዚህ ሀገር ያሉ የኤርዶኻን ወኪሎች እንዲያውም ቁርጣቸውን ቢያውቁ… April 8, 2026
  • የአውሮፓ ህብረት ሻዕቢያ ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም አሳሰበ – ኤርትራዊያን ተቃውሞ አሰሙ April 8, 2026
  • ትዕይንተ ሕዝብ ወይስ ትዕይነተ ውድቀት? – መልማዮቹና ለኪዎቻቸው ዒላማ ያደረጉት ምን እንደሆነ አየንበት! April 8, 2026
  • ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም በሰላማዊ ኒውክሊየር ኃይል መርሃ ግብር በጋራ ለመስራት ተስማሙ March 29, 2026
  • ምርጫ ለማጨናገፍ ሻዕቢያ ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ማንዋል “ምርጫ ማክሸፍ የህልውና ጉዳይ ነው” ይላል March 29, 2026
  • ስብሰቡን “ሸፍጥ ይመስላል” ያሉት ዶ.ር ሚኒሊክ ከመጪው ቅዳሜ የአመጽ ጥሪ ምድብ ውጪ ሆኑ፤ የፋኖ ጉዳይ አስፈርቷል March 28, 2026
Social networks
FacebookLikes
X TwitterFollowers
PinterestFollowers
InstagramFollowers
YoutubeSubscribers
VimeoSubscribers
    VOE - VOICES OF ETHIOPIA
    The VOICES OF ETHIOPIA/ VOE is free website provied news, information, opinions and analysis, from and to the public "በሰው ልጆች ዕልቂትና በብሄራዊ ጥቅም መነገድ ይቁም!"

    MENU

    NEWShomeMEDIAOPINIONtopnewswPOLITICSSOCIETYlawworldentertainmentECONOMYINTERVIEWeventsportOromiffafeaturedhotbusinessarchivetips
    © Copyright 2026,voicesofethiopia All Rights Reserved
    • CONTACT
    • law
    • INTERVIEW
    • ያበደው
    • ECONOMY
    • Home demo times
    • VOE VIDEO
    • ENGLISH PAGE
    • Home Demo default 2